CCC CCC

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የጊዜ ዕድሜ

የዛሬ ልጅ ነገ … ሆኖ ትናንት አያት

ቅድም ወደኋላ … መጭውን ወደፊት

ድህረ-ግብር ታሪክ … አሁን ያለንበት

መቁጠሩን ካልሆነ … አልቻልን ጊዜን ማርጋት

ዓመት ተለክቶ … ወራት ተሰይሞ

አስልተን ሠዓታት … ቀን አልበቃ ብሎ

መሬት እየዞረ … ፀሀይ ወጥቶ ገብቶ

ብዙ ነገር ፍርሷል … ጊዜ ብቻ ቆሞ

ብዙ ነገር ሞቷአል … ጊዜ ብቻ ኖሮ

አያል ነገር ወልዷል … ጊዜን አስመስክሮ

በፀደይ በክረምት … በመከር በበጋ

ሳምንት ተከታትሎ … ወራትን ፍለጋ

ተሢያት ሲተካ … የጡዋትን ቦታ

ጊዜ ያስጉዘናል … በንጋት በማታ

አምና ከርሞ ብለን …ዘመኑን ቀይረን

ተዋልደም ሞተን … ሽህ አመቱን አከበርን

የአመቶች አብራክ … ዘላለም ቀፍቃፊው

ዘንድሮን አምና አድርጎ … በአዲስ ሊቀይረው

አስራ ሁለት ወር ፈጅቶ … ጷጉሜ ብቻ ቀረው

የዛሬ ልጅ ነገ … ሆኖ ትናንት አያት

ቅድም ወደኋላ … መጭውን ወደፊት

ድህረ ግብር ታሪክ … አሁን ያለንበት

መቁጠሩን ካልሆነ … አልቻልን ጊዜን ማርጋት


መልካም አዲስ አመት!

ቀለበት አደም - ዋሽንግተን ዲሲ - ጷጉሜ፣ 2002

You might also like