Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

ጎመንን በስጋ

ተራሮች ሲያጌጡ ….. በአደይ አበባ

አመቱ ሲታደስ ….. መስከረም ሲጠባ

ዘፈኑም ሲሆን …… ወለባ ወሸባ

ምሽቱም ሲደምቅ ….. በችቦ በላምባ

ፀሎት ተያዘለት …… ሆድም እንዳይባባ

ተባል ጎመን ዉጣ …… ደግሞ ስጋ ግባ

ስጋ በነብስ ሲያዝ …… መግባቱን ቢረሣ

ፀላዩ ወግኔ …… አንጀቱ ቢሣሣ

ሆዱ ሲጠይቀው ….. ሲርበው ሲከሣ

ጌታውን ለመነ …… ፀሎቱ እንዲረሣ

የነሣውን ጎመን …… መልሶ እንዲሰጠው

የደረቀ አንጀቱን …… ደግሞ እንዲያርሰው

ፈጣሪን ነገረ ….. በጾመ በመኃላ

ፀሎቱ እንደሚሆን …… ከእንግዲህ በኋላ

ጎመን በጤና እንጅ …… እንደማይሆን ሌላ

በተራበ ምላስ ….. ጎመን እስኪመጣ ….. ነገር እየበላ

አለ

ከእንግዲህስ ወዲያ ማን ስጋን ያምናላ

ቀለበት አደም - መስከረም - 2003

You might also like