CCC CCC CC

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ጠይም ያገሬ ልጅ

የማር ወለላ ነሽ ….. ማንም ያልቀመሰሽ

ያገሬ ልጅ ቆጆ … ጣፋጭ ነሽ ውድ ነሽ

ያበሻ ልጅና …. ባቅላባ አንድ ነው

መሃሉ ለስላሳ ….. ዳርዳሩ ጣፋጭ ነዉ

አንቺን የመሰለ ….. አላገኝም ዞሬ

ትኬቱን ቆርጨ ….. በቦይንግ በርሬ

እቃየን ሸክፌ …… ካልገባሁ አገሬ

እየጠመቅኩ አንቺን …… አለሁ እስከ ዛሬ

ጆሮየን ጨቁኜ ….. ከምክር ከወሬ

ጠይም እንጅ በዬ ….. ጫፌን ሁሉ አስሬ

ግን ምኑንም ሳልኖር ….. እረገፈ ፀጉሬ

ቀን ሲመሽ ….. ሲነጋ ፍቅርሽ እያየለ

አለ ልቤ አምጾ ….. ሌላ አላይ እንዳለ

ምን ቁጭ ያስብለኛል ….. ልሂድ ልንቅሳቅስ

ጠይሟን አግኝቼ …… የልቤ እስከሚደርስ

ሳር ቅጠሉ ሁሉ …… ነጭ በነጭ ሆኖብኝ

ትምጣ ያገሬ ልጅ …. ባለ ጡሩ ገላ ….. ብታጠይምልኝ

ተረት ተረት ስልሽ ….. በይኝ የመሰረት

ስልሽ ተረት ተረት …… በይኝ የላም በረት

ሙሉ አገር ባዶ ነዉ …… ጠይም ከሌለበት

ጠይም ጋር ሲሆኑ ….. ሰዓቱ እግር ያወጣል

ትንሽ ሠከን እንዲል ….. ቢታሰር ይሻላል

ፀባይ ከዉበት ጋር …. አጣምሮ ተቺሮሽ

ብዙ ሰው አስተኛሽ …. አሳመሽ በፍቅርሽ

ደማቅ አበባ ነሽ …. መዐዛሽ የሚያዉድ

አፍቃሪሽ ነኝ ሁሌም …. የኔ ፍቅር የኔ ዉድ

እይንሽ ላይ ሠይመሽ ….. የመዉደዱን ንጉስ


ባየሁሽ ቁጥር ….. መቅኔ ይላል ፍስስ

ቀለበት አደም - መጋቢት፣2002

You might also like