ሚቲኩ

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 2

ቀን 13/07/2018

ለአቶ/ ምትኩ ካሳ ፦የብሄራዊ አደጋ እና ስጋት ቅነሳ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር

ለአቶ/ ደበበ ዘውዱ ፦የብሄራዊ አደጋ እና ስጋት ቅነሳ አመራር የመገናኛ ዳይሬክተር

ለአቶ/ ማለዳ ናደው ፦ የፌድራል ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባብሪያ ጽ/ቤት የመረጃ ኦፊሰር
ጉዳዩ ፦ በሓዋሳ እና አካባቢዋ ተፈናቅለው በችግር ዉስጥ ለሚገኙ ለወላይታ ተወላጆች ድጋፍ እንዲደርግ ስለመጠየቅ

እንደሚታወቀው በቅርቡ በሲዳማ ዞን በሓዋሳ እና አካባቢዋ በወላይታ ብሄር ላይ ያነጣጠረ ጭካኔ


የተሞላበት በኢትዮጵያ ታሪክ ያልነበረ የዘር ጭፍጨፋ መካሄዱ ይታወቃል። በዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ በአሰቃቂ
ሁኔታ ማለትም በእሳት በማቃጠል እና ፍጹም አረመኒያዊ በሆነ አኳሃን በዱላ ተቀጥቅጠው ተገድለዋል እንዲሁም
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤት ንብረታቸው ወድሞባቸው ጥለው ተሰድደዋል። በአሁን ወቅት አብዛኞቹ በየት/ቤቶች እና
በአብያተ ክርስቲያናት ተጠልለው ይገኛሉ።

ይህ በእንዲህ እናዳለ ጌዲኦ እና ጉጂ በተቀሰቀስው ግጭት ምክኒያት በርክታ ዜጎቻችን ችግር ላይ እንዳሉ አይዘነጋም።
ለነዚህ ከአለም አቀፍ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እና በጎ አድራጎት ተቋማት ወደ $ 118,000,000 ዶላር ያክል
እንደሚያስፍልግ መስሪያ ቤቱ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህም ተጎጂዎቸን በዘላቂነት ለማቋቋም እንዲሁም ምግብ ፤
ንጹህ የመጠጥ ዉሃ ፤ ንጽህና መጠብቂያ እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማሟላት እንደሆነ ተገልጿል።

በተመሳሳይ በሲዳማ ዞን ጉዳት የደረሰባቸዉ የወላይታ ተፈናቃዮች ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ናቸዉና ከላይ የተጠቀሱትን
ግልጋሎቶቸን የብሄራዊ አደጋ እና ስጋት ቅነሳ ስራ አመራር መስሪያ ቤት ለእነዚህም ተጎጂዎች እንዲያቀርብ እንዲሁም
ተገቢውን እርዳታ እና ድጋፉን እንዲስጥ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋልን።

ከሰላምታ ጋር !

@holozy⎽1896

Chozeh HaMedinah

Shenne minnin shempoyikka hayqenna !

ግልባጭ፦ ለዕርዳታ ሰጪ ተቋማት

-United Nations Children’s Fund (UNICEF) -World Health Organization (who)

-World Food Programme (WFP) -World vision

-MSF-Spain -People In Need

- International Resource Committee (IRC) -Save The Children

- ERC -CARE

You might also like