ማክያቬሊ.txt

You might also like

Download as txt, pdf, or txt
Download as txt, pdf, or txt
You are on page 1of 2

በፐብሊየስ ፦

ኒኮል ማክቬሊ በ 15 ኛው ክፍለ ዘመን ፤ በተለምዶ የአውሮፓ ህዳሴ ክፍለ ዘመን ተብሎ በሚታወቀው ዘመን የኖረ ፓለቲከኛ
ነው ።

አንዳንዶች ፦ ማክያቬሊ የፓለቲካውን አለም ሸፍጥ እና ተንኮል ቁልጭ አድርጎ ያወጣ እና ፖለቲካ ሞያ ሳይሆን ሸፍጥ እንደ
ሆነ ያሳየ ፤ እንደሚባለው ፦ ቀበሮ የሆነ ፤ ልዩ ፓለቲከኛ ነው ይሉታል ።

አንድ ፕሮፌሰር ደግሞ ይህን ያላዋቂዎች ብሂል ፦


የማካቬላዊ አረፋ መድፈቅ ብሎታል ፤ የሰነፎች አባዜ ።

ማቾዎች ፦ እኔ እኮ አንድ ጠርሙስ ውስኪ አያሰክረኝም ፥ በጣም ተወዳጅ ከመሆኔ የተነሳ ድንግልናዬን የጣልኩት ገና በ 13
አመቴ ነው ወይንም መሰል የጀብደኝነት ተረኮች በማብዛት እራሳቸውን እንደሚያዋድዱት ፤

አንዳንድ በፖለቲካ መጥቅያለው የሚሉ ሰዎችም ፤ በፖለቲካ አለም ፤ ማታለል ፣ ጠላቶችን ማጥፋት (ከፖለቲካው መድረክ)
፣ ሸፈጥ እና ሴረኝነት የፖለቲካ ብስለት ማሳያ ናችው ብለው በማውራት ( አረፋ በመድፈቅ) ፤ እራሳቸውን ሊህቅ
አድርገው ለማቅረብ የሚጥሩበትን አባዜ ማኪያቬሊያዊ አረፋ መድፈቅ ብሎታል።

በእርግጥ የማክያቬሊ ስም ፤ ከፖለቲካውም አለምም ውጭ፤ የአለምን ሀቅ ገሀድ ያወጣ ተብሎ በመወደስ የተለያዩ ሽቶዎች
ሳይቀር በማክያቬሊ ስም ተሰይመዋል ፥

ከዚያም በተጨማሪ ፥ ለምሳሌ አሁን በህይወት የሌለው ታዋቂው የራፕ ዘፋኝ ፤ ቱ ፓክ ሻኩር ሌላኛው የመድረክ ስሙ ፥
ማክያቬሊ ነው ።

ቱ ፓክ ፥ የማክያቬሊ አድንናቂ ከመሆኑ የተነሳ ፥ አንዳንዶች (ሞኞች እንበላቸው) ፦

በማክያቭሌያዊ ምክር ሞቻለው ብሎ አስወርቶ ፤ ጠላቶቹን አዘናግቶ ፤ በሁዋላ ተመልሶ ለመምጣት ስላሰበ ፥ ሞቷል ብሎ
አስወርቶ ሌላ አገር ተደብቆ እየኖረ ነው ፤ እና ቢ አይ ጂ ወይንም ክርስቶፈስ ዋላስ የሚባለው ተቀናቃኙ ራፐር ስለሞተ
ይመጣል ይላሉ ።

በሴረኝነት እንደዚህ ስሙ የገነነው ፤ ማኪያቬሊ ፦

1. ለዚህ በሴረኝነት ያገነነው ጹህፍ ጭብጥ ምንድ ነው ?


2. እውነት የፖለቲካው አለም ፥ የሸፍጥ አለም መሆን ግዴታ አለበት ወይንስ ይህ አባባል ወይንም አስተሳሰብ ፤ ድንግልናዬን
ያጣልኩት በ 13 አመቴ ነው የሚሉት አይነት አረፋ ነው ?
3. ይህ አባባል አረፋ ብቻ ከሆነ ፤ ምን አይነት አገራዊ ችግር ሊፈጥር ይችላል ?

የሚሉትን ጥያቂዎች ፤ በማንሳት እና ግላዊ እይታን በማስቀመጥ ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሰደደን አንድ ፖለቲካዊ አባዜን
በማብጠልጠል ይህንንም አባዜ ከመላካም አስተዳደር ችግር ጋር በማያያዝ ፤ ምናልባት ፦ የኢትዮጵያን የመልካም አስተዳደር
ችግር ከምንጩ ለመጠቆም ይሞከራል ፦

1. የታዋቂው የማክቬሊ ስራ ዋና ጭብጥ ፦

ማክያቬሊ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው የተለያዩ መጽሀፎችን ጽፏል ፤ ከእነዚህ የተለያዩ መጽሀፍት ታዋቂ ያደረገው «ልዑል»
የሚለው እና በአንዷ የጣልያን ግዛት አዲስ ወደ ስልጣን የመጣን አልጋ ወራሽ ፤ እንዴት አድርጎ አገሩን ማደርጀት ፣ ጠላቶቹን
ማሸነፍ እና የቀድሞ የታላቋን ሮማ ክብር ማስመለስ እንዳለበት ፤ የመከረበት እና ለዚህ አዲስ ልዑል በእጅ መንሻነት
የቀረበው መጽሀፍ ነው ።

ማኪያቬሊ እርሱ በነበረብት ዘመን አገሩ ጣሊያን ፤ ከዚያ ታላቅ ሮማዊ ክብሯ ተዋርዳ የምትገኝበት ዘመን አንገብግቦት እንዲህ
ያለበት ነው ፤

ያሁኗ ጣሊያን ከእብራዊያን በላይ ተበዝብዛለች ፥ ከፋርሶች በላይ ተረግጣለች ፥ ከአቴናዊያን በላይ ተበትናለች ፥ መሪ
አታለች ፥ ስረአት የለም ፥ ተቀጥቅጣለች ፥ ተበዝብዛለች ፥ ተቀዳዳለች ፥ መጥፎ ሚባለውን ገጠመኝ ሁሉ ተግታለች ፦

ይህ ሁሉ ግን ፤ ይላል ማኪያቬሊ በአጋጣሚ እና በእድል የደረሰብን ሳይሆን የአመራር ጥበብ ስለጠፋብን ነው

እድል ፤ አለ ማኪያቬሊ ፦ እንደ ቆንጆ ሴት ናት


ሀብታም ፤ ደፋር እና ወጣት (ጡንቸኛ እና ደፋር) ትወዳለች
እድል ነው ብለህ አጉል መነኩሴ ብትሆን ቆንጆዋ ሴት (እድል) ወደ አንተ ሳይሆን ፤ ደፋር ወደ ሆነው ፤ ወደ ጡንቸኛው
ወጣት ትሄዳለች

እንደዚሁም ጣሊያንም ይሄ ሁሉ ውድቀት የደረሰባት መሪዎቿ አጉል ፤ መልካም እንሆናለን ብለው

ቤተመንግስቱን ለመኳንንት የስልጣን ፍትጊያ ከፍተው ስለተውት ነው ።

አንድ ረባሽን መኳንንት መቅጣት ፤ በኋላ አገር አቀፍ ብጥብጥ እና የእርስ በእርስ ጦርነት የሚያስቀር ከሆነ መልካም
ተግባር ነው ፤

በአጭሩ በአገር አስተዳደር ውስጥ ፤ ስነምግባር ትርጉም የለውም ፤ ዋናው እና ትልቁ ጥያቄ እርምጃው የአገርን አንድነት እና
ብልጽግና ያስጠብቃል ወይንስ አያስጠብቅም ነው

አንድ መሪ ፤ ለአገር ይጠቅማል ወይንስ አይጠቅምም ነው እንጂ ልክ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነገር ሊያሳስበው አይገባም
ነው እሚለው ።

ምንም እንኳን በማኪያቬሊ ሀሳብ ውስጥ ፤ ዋናው የአገር ደህነነት ነው የሚለው ሀሳብ ትልቅ እውነታ ቢኖረውም ፥

አንድ መሪ ግን በአገር ደህንነት ስም ዜጎችን እንዲገድል፤ እንዲያሰቃይ ፤ እንዲያስር እና ተቀናቃኞቹን እንዲያጠፋ


ስለሚያበረታታ

ወራዳ ምክር ቢባል አይበዛበትም ።

ነገር ግን ፤ በብዙ ይዘቱ መጽሀፉ መንግስት ህዝብን ማገልገል እንዳለበት ፤ መኳንንት ህዝብን እንዳይጨቁኑ ከለላ መሆን
እንዳለበት ፤ መንግስት ህዝብን አሰልጥኖ ጭቆናን እምቢ ማለት ማስተማር እንዳለበት ብዙ ይወተውታል

ትልቁ የማኪያቬሊ ችግር ፤ ቤተመንግስት ውስጥ ብዙ የስልጣን እና ህዝብ የመበዝበዝ አባዜ ያለባቸው መኳንንቶች ስለሚበዙ
፤ አገር እንድትረጋጋ እነዚህን የስልጣንን ተቀናቃኞች ማስወገድ ወይንም ስረአት ማስያዝ ትክክል ነው ብሎ ፤ ስነምግባር
ቢጓደልም አገር ከቆመች ችግር የለውም ብሎ ማስተማሩ ነው ። ያም ብቻ ሳይሆን ስነምግባር ላይ ካተኮርን እንደ ሮም
እንወድቅ እና እድል ይህን አደረገብን እንላለን ይላል ።

ያም ቢሆን ግን አዲስ ነገር አይደለም ፤ ተመሳሳይ አስተሳሰቦች ከማኪአቬሊ በፊት በብዙ ስርው መንግስታት ሲራመዱ
እንደነበር ታሪክ ያሳያል ፦

የእኛን አገሩን እንኳን ብንወስድ ፤ በዘመነ መሳፍንት ፤ በጎንድር ቤተመንግስት ፤ የስልጣንን የበላይነትን ለመጨበጥ ብዙ ሴራ
ይጎነጎን የነበረው ፤ ከዘመነ መሳፍንት በኋላም ፤ በቴውድሮስ ፤ በዩሀንስ ፤ በተክለሀይማኖት እና በምንሊክ መካከል የነበረው
የበላይነት ፉክክር በባህሪው ማኬያቬላዊ እንደሆነ ግልጽ ነው ፤ እነርሱ ግን ይህን ያደረጉት የማክያቬሊን መጽሀፍ አንብበው
ሳሆን በወቅቱ የአለም የፖለቲካ እውቀት ልክ ያ ስለነበር ነው ፤ ጠላትህን አሸንፈው ወይንም ደልለው ፤ የሚል የዜሮ ድምር
ፖለቲካ እንጂ ሰቶ መቀበልን መሰረት ያደረገ ዘመናዊ ዴሞክራሲያዊ ፖለቲካ በአለም አቀፍ ድረጃ አልዳበረም ነበር ።

የእኛ አገሩ ዘመነ መሳፍንት ስያሜውን ያገኝብትን የመጽሀፍ ቅድሱ ዘመነ መሳፍንት ብንመለከት ተመሳሳይ ማክያቬሊያዊ
አስተሳሰቦች እና ታሪካዊ ድርጊቶች ገነው እናያለን ፤ ከዚያም በላይ ብዙ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል ነገር መደጋገም ይሆናል
እንጂ ።

ለአገር ክብር በሚል ሰበብ ሴረኞችን በሴራ ማጥፋት ትልቁ ችግሩ ፤ ሴራ ሴራን እንዲወልድ ሲያደርግ እና የማያቆም የሴራ
ኡደት ሲፈጥር ፤ ሰዎች ያለህግ ማእቀፍ ተቀናቃኝቸውን የአገር ፣ የመስመር ጠላት ብለው በመፈረጅ ዜጎችን እንዲያሳድዱ
በመፍቀድ ፤ የዜሮ ድምር ፖለቲካ አገርን እንዲያምስ ያደርጋል ።

ማኪያቬሊ አላስተዋለም እንጂ ያደነቀው ሴዣር ቦርጂያ ቤተሰብ እራሱ በዚሁ ለአገር አንድነት እና ክብር ተብለው በተጎነጎኑ
ሴራዎች ማእበል ተበልተዋል ።

ይልቁንም የማክያቬሊ አስተሳሰብ በጣሊያን ፖለቲካ ውስጥ ሴረኝነትን

You might also like