Professional Documents
Culture Documents
Recomendation For Shewa
Recomendation For Shewa
Recomendation For Shewa
ግ/ማህበር
የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካዎች የጥጥ ጥራትን ከመጠበቅ አንጻር ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ አስፈላጊው
ጥንቃቄ ተደርጎ መመረት እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን የሀገራችን ጥጥ መዳመጫ ፋብሪካዎች ምርት
አያያዝና አሰራር ስርዓት ሲታይ ለምርቱ ጥራት የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆኑ ነው፡፡ በአብዛኞቹ ጥጥ
መዳመጫ ፋብሪካዎች ጎልተው ከሚታዩ ችግሮች ውስጥ ወቅቱን ጠብቆ አለመዳመጥና ለረጅም ጊዜ
ማቆየት፣ በቂ የማከማቻ መጋዘን ባለመኖሩ ለዝናብና አቧራ ተጋላጭ መሆኑ፣ አስፈላጊ ማሽነሪዎች
ተሟልተው አለመገኘት፣ ዘመናዊ የአመራረት ሂደት አለመከተል እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ይህ ሂደትን
የጥጥ ጥራትን የሚቀንስ በመሆኑ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎችን ገዥ ከማሳጣቱ በተጨማሪ አገሪቱ
ከዘርፉ ልታገኝ በምትችለው የውጭ ምንዛሬ ገቢ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡
የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ጥራት ያለው ምርት ለገበያ አቅርበው ተወዳዳሪ መሆን ካልቻሉ የጥጥ
መዳመጫ ፋብሪካዎች የገበያ ድርሻም አብሮ የሚቀንስ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ አጠቃላይ እሴት
ሰንሰለቱን ውጤታማ ከማድረግ አንጻር ዘመናዊ የአመራረት ሂደት የሚከተልና አስፈላጊው መሰረተ
ልማት የተሟላለት የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ ሊኖር ይገባል፡፡ በመሆኑም የሀገራችን የጥጥ መዳመጫ
ፋብሪካዎች ከመሰረተ ልማትና አመራረት ሂደት አንጻር ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለመረዳት
በ 16(አስራ ስድስት ) ፋብሪካውች የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ለመዳመጫ ፋብሪካ ባለ ሀብቶች እና
ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡
የጥናቱ ዋነኛ ዓላማ እያንዳንዱ ፋብሪካ ካለው የመሰረተ ልማትና አመራረት ሂደት በመነሳት
ደረጃውን በኮከብ መለየትና በቀጣይ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች መፍትሄ መጠቆም ነው፡፡
ስለሆነም ከአንድ ኮከብ (ዝቅተኛ ደረጃ ) እስከ አምስት ኮከብ (በጣም ጥሩ ደረጃ ) ደረጃዎች
በመስጠት የእያንዳንዱን ፋብሪካ ወቅታዊ ሁኔታ ለማመላከት ተሞክሯል፡፡ አንድ ኮከብ ደረጃ ውስጥ
ለመግባት በተቀመጡ መስፈርቶች ሲመዘን አማካይ ውጤቱ 50 በመቶ መምጣት ያለበት ሲሆን
አምስት ኮከብ ለመግባት ደግሞ አማካይ ውጤቱ ከ 90 በመቶ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
የሸዋ ጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ ጥናቱ ከተካሄደባቸው ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ከላይ
በተቀመጠው የኮከብ ደረጃ መሰረት የፋብሪካው አማካይ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ
ሊሆን ባለመቻሉ ከደረጃ በታች በሚል ተይዟል፡፡ ፋብሪካው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንዲወድቅ ካደረጉ
ምክንያቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ናቸው፡፡
ፋብሪካው በአሁኑ የጥጥ ማስቀመጫ መጋዘን ያስገነባ ቢሆንም በተያዘው የምርት ዘመን
በስፋት ሊመጣ የሚችል በቂ የማከማቻ ቦታ ማዘጋጀት
ጥጥን ከዝናብና እርጥበት ሊከላከል የሚችል በቂ መሸፈኛ እና የሲሚንቶ ወለል /ርብራብ
ማዘጋጀት
የጥገና ፕሮግራም ማዘጋጀት ( maintenance plan for daily, weekly, monthly
and yearly activities)
በቂ መለዋወጫ መያዝ
የማሽኖች ተሽከርካሪ አካላትን (ፑሊዎች ) መሸፈን እንዲሁም ለሰራተኞች ደህንነት
አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ
የስራ ቦታ ጽዳት አጠባበቅን ማሻሻል
የፋብሪካውን የጥጥ ብናኝ ማስወገጃ መስመር እና ፋን ማስተካከል
በመዳመጫ ደረጃ ሊኖሩ የሚገባቸው የርዝመት መለኪያ፣ንጣት ደረጃ (grading charts)
የእርጥበት መጠን መለኪያ፣አነስተኛ ሚዛን አለመኖር
ጥጥ በጣም ደረቅ በሚሆንበት ወቅት ውሃ ለመርጨት የሚያስችል (moisturizer)
አለመኖር
ከጥጥ ጋር የተቀላቀሉ በዕድ ነገሮችን ቀጣይነት ባለው መልኩ የመለየት ስራ በመስራት
ዘርፉን ለማሻሻል ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በሌላ በኩል በመካከለኛ ጊዜ መፈታት ያለባቸውን ቴክኖሎጂ የማዘመንና መሰረተ ልማት የሟሟላት
ስራዎች ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ለማከናወን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እና ፕሮፖዛል እንድታዘጋጁ
እየገለጽን ለመነሻ የሚሆኑ ዝርዝር የመፍትሄ ሀሳቦችን ከዚህ ደብዳቤ ጋር - ገጽ አባሪ አድርገንላችኋል፡፡