New Microsoft Word Document

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

ተሀድሶ(Reformation )

ክፍል አንድ

Abel kasa from wolkite

የፕሮተስታንት እምነት የሚያራምዱ አህዛብ፤ መናፍቃን እና በክርስቶስ የባህሪ ልጅነት ልጁ


ያደረገን የክርስቶስ ቤተሰቦች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች አምላካችን
መዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በወደደ እና በፈቀደ ለዛሬ የሚሆን የመማሪያ ሀሳብ
አንስተን እንወያይ አምላካችን መዳህኒያለም የማስተዋል ጥበብ ያድለን።

አምስቱ የፕሮተስታንት እምነት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚለዩባቸው ዋና ዋና


ክፍሎች

1,sola scriptura(scripture alone);የ66ቱ መፅሀፍት ብቻ

2,sola fide (faith alone ) እምነት ብቻ

3,sola gratia(Grace alone) ፀጋ ብቻ

4,solus (christus) ክርስቶስብቻ

5,soli Deo Glaria(Glory to God alone) ክብር ለእግዚአብሄር ብቻ

1,sola scriptura(scripture alone);የ66ቱ መፅሀፍት ብቻ


(1)ይሁ 1:14 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ፡እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ በኃጢአተኛ ስለ ሀጢያት ስራቸው
ሁሉ አመፀኞች እና ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ
ከአእላፋት ቅዱሳን ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ፡፡

እንግዲህ በስልሳ ስደስቱ መፅሐፍ ቅዱስ የሄኖክ የትንቢት መፅሐፍ የለም ታዲያ እንዴ ይታያል ይህ ጥቅስ በአህዛብ
ዘንድ?????

(2) ዮሐ 21:25 እየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢፃፍ ለተፃፋት መፅሐፍት አለም ራሱ
ባልበቃቸው ይመስለኛል፡፡

አለ ወንጌላዊ ዮሐንስ

(3) ዮሐ 20:30 እየሱስም በዚህ መፅሀፍ ያልተፃፉ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀመዝሙራን ፊት አደረገ፡፡


እንግዲህ ይህም ማለት በመፅሐፍ ቅዱስ መሠረት ሌላ ብዙ ታምራትን ያደረገ ጌታችን አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ
እንዴት በስልሳ ስድስቱ ብቻ ሊገደብ ይችላል??? አለማወቅ ሀጢያት አይደለም የሚያቅ ይመልስልኝ ስላልገባኝ
ይሆናል፡፡ የገባው ክርስቲያን አሜን ይበል አህዛብ ለኔ መልስ ስጡ

(4) ራዕ 22:19 ማንም በዚህ በትንቢት መፅሐፍ ከተፃፉት ቃላቶች አንዳች ቢያጎድል በዚህ መፅሐፍት ከተፃፉት
ከህይወት ዛፍ እና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር እድሉን ያጎድልበታል፡፡

ኧረ እናስተውል በዚህ በትንቢት መፅሀፍት ነው ያለው ስጀምር መፅሐፍ ቅዱስ የትንቢት መፅሐፍ ብቻ አይደለም
ሲቀጥል በ ይሁ 1:14 ላይ የተገለፀው የሄኖክ የትንቢት መፅሀፍት የት አለ??????? መልስ ከአህዛብ ወንድሞቼ

(5) ሰይጣን ከይት መጣ?እንዴትስ ሳተ?

(6)መላዕክ መቼ ተፈጠሩ?
ዘፍ 4:17 የቃዮል ሚስት ፀነሰች ልጅም አገኘች ስሙንም ሄኖህን አለችው ለመሆኑ ቃየል
እንዴት አገባ እንዴትስ ሚስቱን አገኘ?ማለትም በዛን ዘመን የነበሩት አዳም:ሄዋን:
ቃዮል ብቻ ነበሩ ታዲያ ከየት አገኛት??
(7)ማቴ 27:9 የእስራኤል ልጆች የተስማሙበትን ሰላሳ ወንበር ለእንግዶች መቀመጫ
ለሸክላ ሰሪው ሰው መሬት ገዝተው ሰቱበት ምድርም የደም መሬት ተባለ ይህንንም
ኤርሚያስ የተናገረው ትንቢት ተፈፀመ አለ።ታዲያ ይሄ ትንቢት በማን ተነግሮ ማቲዮስ
ፃፈው ይህ ቃል በተረፈ ኤርሚያስ የትንቢት መፀሃፍ ላይ ነው።
 የእግዜአብሄር መንፈስ ያለበት መፅሀፍ ሁሉ ለትምህርት እና ለተግሳፅ ጠቅማል
ያለው ብርሀነ አለም ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲወስ ሰዎች

2,sola fide (faith alone ) እምነት ብቻ


ያዕ 2:14 ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ስራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅማል እምነትስ ሊያድን
ይችላልን??

አዎ እምነት ያለስራ ስራ ያለእምነት ምንም አይደል ወገኖቼ ሆይ እምነት በስራ ስራም በእምነት ሊደጋገፉ ግድ ነው
ቅዱስ ቃሉም ይህን ይላል።እምነት ብቻውን በፍጹም ሊያድን አይችልም

ያዕ 2:19 እግዜአብሄር አንድ እንደሆነ አንተ ታምናለህ መልካም ታደርጋለህ ደግሞ አጋንትም ያምናሉ ስራቸው
ግን አያድናቸውም ይንቀጠቀጡማል።

ያዕ 2:20 አንተ ከንቱ ሰው እምነት ከስራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን??
ማቴ 7:21_28 በሰማያት ያለውን ያባቴን ፈቃድ የሚያደርጋ እንጅ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ
ሰማያት የሚገባ አያደለም

በዛን ቀን ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህስ አጋንንት አላስዉታንም በስምህ ብዙ ታምር


አልሰራንም ይሉኛል የዛን ጊዜም ከቶ አላውቃቸውም እናንተ አመፀኞች ከእኔ እራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ

ማቴ 7:13_20 በጠባብም ደጅ ግቡ ወደ ደግሞ የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገድ ነው


ትልቅም ነው ወደ እረሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ወደ ህይወት የሚወስድው ደጅ
የጠበበ መንገድ የቀና ነውና የሚያገኛትም ጥቂቶች ናቸው።የቀረውን መፅሀፍ ቅዱስ ላይ
አንብቡት
ማቴ 7:20 ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ

3,sola gratia(Grace alone) ፀጋ ብቻ


ኤፌ 2:8 ፀጋው በእምነት አድኟችኋል እና ማንም በስራው አይደለም ብዙዎች ያህን የመፅሃፍ ጥቅስ ባለማገናዘብ
ተረድተው ተስተውበታል የአህዛብ አስተምህሮ አበክሮ የሚያዘወትረው በሀዲስ ኪዳን ትምህርት ላይ ብቻ ነው
ስለሆነም ስለ ሶስት ነገር ህግን ይሽራሉ።

1፣ህገ_ልቦና ከአዳም_ሙሴ

2፡ህገ_ኦሪት ከሙሴ_ሄዋንስ መጥምቁ

3፡ጌታችን ከሞተበት_ምፅአት

ይህም ቃል በሉቃስ ወንጌት በግልፅ ጠቀምጦ እናገኘዋለን

የሉቃ 24:44 እነርሱም ከእናንተ ጋር ስለሆኑ በሙሴ ህግ እና በነባያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተፃፈው ሁሉ


ያፈፀም ዘንድ ይገባል ብሎ የነገራችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።

በሙሴ_ማለት ኦሪት አምስቱ የኦሪት መፅሀፍ ናቸው በትንቢት ማለቱ 16ቱ ይትንቢት መፅሀፍት ናቸው እና
መዝሙራት የተባሉት እነ ሲራክ እነ ዳዊት እነ ሰሎሞን ወዘተ ናቸው።

ማቴ 5:17 እኔ ህግ እና ነብያትን ልሽር የመታሁ አይምሰላችሁ ልፈፅም እንጅ ለመሻር አልመታሁም እውነት
እውነት እላችኋለሁ ሰማይ እና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም ሁሉ እስኪያልፍ ድረስ

ቀሪዎችን በሌላ ክፍን እንመለከታለን

የአምላካችን የመዳህኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ሰላም እና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን የድንግል ማሪያም
ተራዳይነቷ እና አማላጅነቷ አያለየን የቅዱሳን በረከታቸው በእኛ ላይ ይደር አሜን!!!!!

You might also like