Islamic Sci

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 23

ጃቢር ኢብኑ ሀያን

ጃቢር ኢብኑ ሀያን የመካከለኛው ዘመን የኬሚስት ሊቁ ጀብር የሚባል ሲሆን “የኬሚስትሪ አባት” በመባል
በስፋት ይታወቃል።

ሙሉ ስሙ አቡ ሙሣ ጃቢር ኢብኑ ሀያን የሆነው ጃቢር አልፎ አልፎ አል ሀራኒ እና አል ሱፊ በሚባሉ


ስሞችም ይጠራል። ጃቢር አባቱ የመድሃኒት ቀማሚ (አጣር) ናቸው። ትክክለኛ የተወለደበትን ቀን ለማወቅ
ተጨማሪ ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም እንደ አጠቃላይ ግን ጃቢር በ776 አካባቢ ኩፋ ውስጥ ህክምናን እና
ኬሚስትሪን ያዘወትር እንደነበር በታሪክ አጥኚዎች መካከል ስምምነት አለ።

ጃቢር በኢማም ጃዕፈር አስ ሣዲቅ እና የኦማያድ ሠርወ መንግስት ልዑል በሆነው ኻሊድ ኢብኑ የዚድ ሥር
ሆኖ ነው ትምህርቱን የተከታተለው። ህክምናን የተማረው ገና በልጅነቱ በባርማኪ ወዚር ቤት ሆኖ በአባሲድ
አገዛዝ ኸሊፋ ሃሩን አር ረሺድ ዘመን ነበር። ለባርማኪስ መውደቅ የተወሰነ ሚና የነበረው ሲሆን በወቅቱም
ምድር ቤት ውስጥ ታስሮ ነበር። ጃቢር የሞተው እ.ኤ.አ. በ803 ነው።

ማክስ ሜየርሃፍ (Max Mayerhaff) እንዳለውም በአውሮፓ የኬሚስትሪ እድገት በቀጥታ መመለሻው ጃቢር ኢብኑ ሀያን ነው
ብሏል።

ጃቢር በኬሚስትሪ ዘርፍ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው። ወደ ዘመናዊው ኬሚስትሪ ለማደግ መሠረት የሆነውን
ተግባር ተኮር (experimental investigation) የኬሚስትሪ ምርምርን ለዓለም ያሣወቀው እርሱ ነበር።
እጅግ የታወቀው ላቦራቶሪው ፍርስራሹ ለዘመናት የቆየ ቢሆንም ነገር ግን ጃቢር እውቅናን የተጎናፀፈው
በመቶ ትላልቅ ድርሰቶቹ ምክኒያት ነበር። ከነኚህም መካከል ሀያ ሁለቱ ከኬሚስትሪ ጋር የተያያዙ ናቸው።

ለኬሚስትሪ መሠረት ከሆኑትና የሱ አስተዋፅኦ ከታከለባቸው ነገሮች መካከል የኬሚስትሪን ሣይንሣዊ


ዘዴዎች በላቀ መልኩ ማሣደግ ሲሆን ማድረቅ (ክሪስታላይዜሽን)፣ ማጣራት (ዲስቲሌችን)፣ ማጠጠር
(ካልሲኔሽን)፣ ማቅለጥ (ሰብሊሜሽን)፣ ማትነን (ኢቫፖሬሽን)፣ እና የተለያዩ ለዚሁ ምርምር የሚያግዙ
ቁሣቁሦችን ያጠቃልላል። ያልጠሩ ሀሳቦች ተንሰራፍተው በሚገኙበት በዚያ ዘመን ኬሚስትሪ እንደ አንድ
የሣይንስ ዘርፍ ሆኖ በዐረቦች ዘንድ በእጅጉ ተደራጅቶ ነበር። ኬሚስትሪ የሚለው ቃል የመጣውም “አል-
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
ኪሚያ” ከሚለው የዐረብኛ ቃል ነው። ይህም በሙስሊም ተመራማሪዎች በሰፊው ጥናት ተደርጎበት
ተሻሽሏል።

የጃቢር ተግባር ተኮር ምርምር ከፍተኛ ስኬት የነበሩት የተለያዩ ማዕድናትን እና ሌሎችን አሲዶችን ማግኘቱ
ላይ ነበር። እነኚህም ለመጀመሪያ ጊዜ በርሱ አለምቢክ (አለንቢቅ/alembic) የማጣሪያ መሣሪያ ውስጥ
የተዘጋጁ ነበሩ። ለኬሚስትሪ መሠረታዊ ባህሪ በርካታ አስተዋፅኦዎችን ከማድረጉም በላይ አዳዲስ ውህዶችን
(compounds) እና የኬሚካል አሠራር ዘዴዎችን እንዲሁም በርካታ ተግባር ተኮር የሆኑ ኬሚካላዊ
ሂደቶችን (applied chemical processes) አጎልብቷል። በዚህም ሰፊ ሥራው የተነሣ በተግባር ተኮር
ሣይንስ ዘረፍ መሪና ሞዴል ተጠቃሽ ለመሆን ችሏል። በዚሁ ዘርፍ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል የተለያዩ
ብረታ ብረቶች ስለሚዘጋጁበት ሁኔታ፣ የሽቦ (steel) አሠራር፣ የልብስ አነካከር፣ የቆዳ አዘገጃጀት፣ ውሃ
የማያስገቡ ልብሦችን ስለ መቀባት፣ በመስታወት ሥራ ማንጋኒዝ ዳይ ኦክሣይድን መጠቀም፣ ዝገትን
መከላከል፣ በወርቅ መሙላት፣ ቀለማትን መለየት፣ ቅባቶች እና የመሣሰሉት ይጠቀሳሉ። በዚህ ረጅምና እልህ
አስጨራሽ የተግባር ምርምር ወቅት ወርቅን ለማሟሟት የሚያስችል አኳራጂያ ማግኘት ችሏል። አለምቢክ
የሱ ትልቅ ፈጠራ ሲሆን ይህም የማጣራትን ሥራ ቀላልና ስልታዊ በሆነ መልኩ እንዲሆን አድርጎታል። ጃቢር
ከዚህም በላይ በተግባር ምርምሮችና በትክክለኛነታቸው (experimentation and accuracy) ላይ
ትልቅ ትኩረት የመስጠትን መሠረት ጥሏል።

ጃቢር ከባህሪያቸው በመነሣት ንጥረ ነገሮችን (substances) በሦስት የተለያዩ አይነቶች ይከፍላቸዋል።
የመጀመሪያው ሰፒሪት/መንፈስ ማለትም በሚሞቁበት ጊዜ የሚተኑት ሲሆኑ እነኚህም ካምፎር፣ አርሰኒክና
አሞኒየም ክሎራይድን የመሣሰሉትን ይይዛል። ሁለተኛው ብረት ነኬ ሲሆን ይህም ወርቅን፣ ብርን፣ መዳብን፣
ሊድ እና ብረትን ያጠቃልላል። በሦስተኛው ምድብ ውስጥ ደግሞ ወደ ዱቄትነት/ብናኝነት የሚለወጡ
ነገሮችን አስቀምጧል። ይህም ክፍፍል ኋላ ላይ ነገሮችን ብረት ነኬ (metals)፣ ብረት ነኬ ያልሆኑ (non-
metals) እና በቀላሉ የሚተኑ (volatile) ተብለው ለተከፈሉበት ሁኔታ መሠረትን ጥሏል።

ጃቢር ምንም እንኳ በኬሚስትነቱ ቢታወቅም እንደ አልኬሚያ ባለሙያ ግን ምናባዊ የተከበሩ ማእድናት
አዘጋጃጀት ለይ ትኩረት አድርጎ የተንቀሣቀሠ አይመስልም። ባይሆን ትልቁን ጉልበቱንና ጊዜውን የጨረሠው
መሠረታዊ የሆኑ ኬሚካለዊ አሠራሮች አንዴት እንደሚያድጉና በኬሚካል ፅግበራ (chemical
reactions) ዙሪያ ነበር። በዚህም የኬሚስትሪ ሣይንስ ከአልኬሚ ምናባዊ እንቆቅልሽ ጎልብቶ ይወጣ ዘንድ
ረድቷል። በኬሚካላዊ ፅግበራ በርካታ የተለያዩ ውጤቶች ሊገኙ እንደሚችሉ አፅንኦት ሠጥቷል። በዚህም
የተነሣ የኮንስታንት ፕሮፖርሽን ህግ (the law of constant proportions) የማግኘቱ መንገድ ቀላል
ሊሆን ችሏል።
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
በጃቢር የፅሁፍ ክምችት ውስጥ በርካታ የመፅሃፍ ቅጂዎች ተካተዋል። ከኬሚስትሪ በተጨማሪ ለህክምና እና
ለሥነ ከዋክብት ጥናትም የጃቢር አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው። በኬሚስትሪ ዙሪያ ከሚጠቀሱ መፅሃፎች መካከል
“ኪታብ አል-ኪሚያ” እና “ኪታብ አስ-ሰቢኢን” ይጠቀሳሉ። መፅሃፎቹም ወደ ላቲን እና በርካታ የአውሮፓ
ቋንቋዎች ተተርጉመዋል። እነኚህም ትርጉሞች በአውሮፓ ውስጥ ለክፍለ ዘመናት ገነው የቆዩ ሲሆን
ዘመናዊዉ ኬሚስትሪ መከሠትም አቢይ ምክኒያት ነበሩ። ጃቢር ይጠቀምባቸው የነበሩና የዛሬው
የአውሮፓውያኑ ቋንቋዎች የሚጠቀሙባቸው አልካሊ (alkali) እና የመሣሠሉት በርካታ ከምርምሩ ጋር
የተያያዙ ቃላት የሳይንስ መዝገበ ቃላት ክፍል ሊሆኑ ችለዋል። ከመፅሃፎቹ ታርመው ለህትመት የበቁት
የተወሰኑት ብቻ ሲሆኑ በርከት ያሉትና በዐረቢኛ ቋንቋ የተፃፉት ግን ዛሬም ድረስ ትኩረት ተነፍጎአቸው
ሣይታተሙ ተቀምጠዋል።

በሱ የፅሁፍ ክምችት ውስጥ ሁሉም የሱ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ስለመካተታቸው ጥያቄ ያለ ሲሆን


ክምችቶቹም የሱ ስብስቦች ብቻ ናቸው ወይንስ ኋላ ላይ የመጡ ተከታዮቹ ትንታኔ ተካቶባቸዋል የሚል
ጥያቄም አለ። እንደ ሣርቶን (Sarton) አባባል ከሆነ የሱ ሥራዎች ስለመሆናቸው ልናረጋግጥ የምንችለው
ሁሉም መፅሃፎቹ የታረሙና የታተሙ እንደሆነ ብቻ ነው። በፅሁፉ ውስጥ የተካተተው ሃይማኖታዊ
አመለካከቱና የፍልስፍና ጭብጡ ምንም እንኳ ትችት የገጠመው ቢሆንም ስለ ትክክለኛታቸው የሚነሣው
ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ሊካድ የማይችል ሀቅ ቢኖር ጃቢር በዋናነት ለሃይማኖቱ ሳይሆን ለኬሚስትሪ ሣይንስ
ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተ መሆኑን ነው።

በርካታ ግኝቶቹ ለምሣሌ አሲድ ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘቱ በተለይ ናይትሪክ፣ ሃይድሮ ክሎሪክ፣ ሲትሪክ፣ እና
ታርታሪክ አሲድ እና ስልታዊ ሙከራዎቹ እጅግ የተዋጣላቸው ነበሩ። ይህም በመሆኑ ነው ይህ ሰው
የዘመናዊው ኬሚስትሪ አባት (father of modern chemistry) ተብሎ ሊታይ የቻለው። ማክስ
ሜየርሃፍ (Max Mayerhaff) እንዳለውም በአውሮፓ የኬሚስትሪ እድገት በቀጥታ መመለሻው ጃቢር
ኢብኑ ሀያን ነው ብሏል።

ኢብኑ ነፊስ (1213-1288 እ.ኤ.አ)


1
4875

Share on Facebook
ጃቢር ኢብኑ ሀያን

ዐላእ አድ-ዲን አቡ አል ሀሠን ዓሊ ኢብኑ አቢ አል ሀዝም አል ቀርሺ አል ደመሽቂ አልሚስሪ ይባላል፡፡


የተወለደው እ.ኤ.አ በ607 በደማስቆ ከተማ ነው፡፡ ትምህርቱንም የተማረው በኑረዲን አዝ-ዘንኪ
በተመሠረተው የህክምና ኮሌጅ ሆስፒታል ነው፡፡ በህክምናው ትምህርት ዙሪያ መምህሩ የነበረው ሙሀዘብ
አድ ዲን አብዱል ረሂም ሲሆን ከህክምናው ትምህርት ሌላ ኢብኑ ነፊስ የህግ ትምህርትን፣ የሥነ-ፅሁፍንና
ሥነ-መለኮትን ትምህርት ተከታትሏል፡፡

በፊቅሂ እውቀትም በሻፊዒይ መዝሀብ እውቀቱ የበቃ (ኤክስፐርት) ሲሆን የታወቀ ሃኪምም ነበር፡፡

በህክምናና በህግ እውቀት ከፍተኛ ትምህርት ካገኘ በኋላ ወደ ካይሮ በመጓዝ በታዋቂው ናስሪ ሆስፒታል
በዋና ሥራ አስኪያጅነት የተሾመ ሲሆን እዚያም ሣለ ለታዋቂው የቀዶ ጥገና ባለሙያ ኢብኑ አል ቁፍ አል
መሲሂን ጨምሮ ለበርካታ የህክምና ጠበብቶች ሥልጠና ሠጥቷል። ከዚህም ሌላ በካይሮ በሚገኘው
መንሱሪያ ትምህርት ቤት ግልጋሎት ሠጥቷል፡፡ የሞተውም እ.ኤ.አ በ678 ሲሆን የግል ቤቱን፣ ቤተ-
መፅሃፍቱንና ክሊኒኩን ለመንሱሪያ ሆስፒታል በስጦታነት አበርክቷል፡፡
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
የኢብኑ አን-ነፊስ ዋነኛ አስተዋፅኦዎቹ በህክምና ዙሪያ ያተኮሩ ናቸው፡፡ አቀራረቦቹም በቀደሙት ሥራዎች
ላይ ዝርዝር አስተያየቶች መፃፍን፣ እነሱን በጥልቀት መመርመርንና የራሱን ወጥ የሆኑ አስተዋፅኦዎች
መጨመርን ያካትታሉ፡፡ ጉልህ ተፅእኖ ከነበራቸው ትላልቅ ወጥ ሥራዎቹ መካከል ከሦስት ምእተ አመታት
በኋላ በዘመናዊው ሣይንስ እንደገና የተደረሠበት የደም ዝውውርን ማግኘቱ ይጠቀሳል፡፡ ሣንባ ውስጥ
የሚገኙትን ነገሮች በትክክል ለመግለፅ የመጀመሪያው ሰው ሲሆን ስለ ብሮንካይ ምንነት፣ በሰው ልጅ የደም
ቱቦዎችና በአየርና በደም መካከል ስለሚከሠተው አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር አስፍሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
ልብ ላይ የሚገኘውን የኮሮናሪ አርተሪን (ልብ ላይ የሚገኝ የደም ሥር) ጥቅም በመግለፅ የልብ ጡንቻዎችን
የሚመግብበትን ሁኔታ ተንትኗል፡፡

አሽ-ሻሚላ ፊ አጥ-ጢብ የሚባለው ባለ ብዙ ጥራዝ መፅሃፉ ሦስት መቶ ክፍሎችን ሊይዝ የሚችል


እንሣክሎፒዲያ ተደርጎ የተቀረፀ ሲሆን በመሞቱ ምክኒያት ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡ የእጅ ፅሁፎቹ ግን ዛሬም
ድረስ በደማስቆ ይገኛሉ፡፡ በአይን ህክምና ዙሪያ የተፃፈው መፅሃፉ ወጥ የሆነ የራሱ አስተዋፅኦው ሲሆን
ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ነገር ግን እጅግ ሊታወቅ የቻለው መፅሃፉ ሙጃዝ አልቃኑን የሚባለው ሲሆን በሱ ዙሪያ
በርካታ ማብራሪዎችም ተፅፈዋል፡፡ ከሱ ማብራሪያዎች መካከል አንዱ በሂፖክራተስ መፅሃፍ ላይ የጻፈው
ነው፡፡ የኢብኑ ሲናን ቃኑን አስመልክቶ ዛሬም ድረስ ያሉ በርካታ ጥራዞችን ፅፏል፡፡ እንደዚሁም በሁነይን
ኢብኑ ኢስሃቅ መፅሃፍ ላይም ማብራሪያ ፅፏል፡፡ ሌላው ታዋቂውና የሱ ወጥ ጥንቅር አስተዋፅኦ የሆነው
መፅሃፍ ምግብ በጤና ላይ ስለሚያሣድረው ተፅእኖ የሚዳስሰው ኪታብ አልሙኽታር ፊ አል
አግዚያ የሚባለው ነው፡፡

የኢብኑ አን-ነፊስ ሥራዎች በያኔውን ዘመን የነበረውን እውቀት በእጅጉ ከመዋሃዳቸውም


በላይ አበልፅገውታልም፡፡ ከዚህም ባለፈ መልኩ በምሥራቁም ሆነ በምእራቡ ዓለም በነበረው በያኔው
የህክምና ሣይንስ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ሆኖም ከመፅሃፎቹ መካከል አንደኛው ብቻ ነው ወደ
ላቲን የተተረጎመው፡፡ በመሆኑም ከፊል ሥራዎቹ ለአውሮፓ ሣይታወቁ ለረጅም ዘመናት ኖረዋል፡፡
ጃቢር ኢብኑ ሀያን

አሕመድ ዲዳት (1918-2005 ዓ.ል)

ይህ ታላቅ ሰው በልጅነታቸው በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማሯቸው የግድ አስፈላጊ ከሆኑ


ትምህርቶች በስተቀር ብዙ ትምህርት አላገኙም። ደህና ከሚባል ትምህርት ቤት ገብተውም በምቹ ድባቧና
በሰፊው ግቢዋ ዉስጥ አልተንሸራሸሩም። እንደነዚያ ነገሮች ሁሉ ገር እንደሆኑላቸውና ጠዋት ማታ
ቦርሣቸውን ተሸክመው ወደ ትምህርት ቤት እንደሚመላለሱት ልጆችም በተረጋጋ ሁኔታ አላደጉም።
ቤተሰባቸውን ባጋጠማቸው ከባድ ድህነት ምክንያት ገና በልጅነታቸው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ እና ወደ
ሥራው ዓለም ለመግባት የተገደዱ ናቸው።

ሁሉም ልጆች በዚያ የልጅነት ዕድሜ ከጎናቸው ሊያጧት የማይፈልጉትንና የሚወደውን ምግብ
የምታዘጋጅለት፣ የምታጫውት፣ በደስታም ሆነ በሐዘን ወቅት ከጎን የምትሆን እናት ከአጠገባቸው ባለመኖሯ
ምክንያት በዉስጣቸው አስከፊ እና ትልቅ የብቸኝነት ስሜት ተሰምቷቸው አድገዋል… አሕመድ። አባታቸው
የቤተሰቡን የዕለት ወጭ ለመሸፈንና የአባትነት ኃለፊነታቸውን ለመወጣት ሌት ተቀን ይታትሩ ነበር።

ታሪካቸውን የምናወሳላቸው አሕመድ ዲዳት፣ ምንም እንኳ በርካታ ችግሮች የተጋረጡባቸው ቢሆንም
በልጅነታቸው ከትምህርት ባልንጀሮቻቸው መካከል እጅግ ጎበዝ እና ቀዳሚ፣ ብልህ ልጅ ነበሩ። ዕድሜያቸው
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
አሥራ ስድስት ዓመት ሲሆን እርሣቸውንና ቤተሰባቸውን የከበበውን የድህነት ማቅ ለመግፈፍ ሲሉ
በራሣቸው ሥራ ጀመሩ። ሱቅ ዉስጥ ሰዎች ዘንድ ተቀጥረው ሻጭ ሆኑ።

ዛሬ ላይ ሆነን ከተወለዱና ወደዚህች ምድር ከመጡ ድፍን መቶ ዓመት ሊሞላቸው አንድ ዓመት ብቻ
የቀራቸውንና በሕይወት ካለፉ ደግሞ 12 ዓመት የሆናቸው ታላቁን የኢስላም ፈርጥ አሕመድ ዲዳትን
ስናስብ ትክክለኛውን የእስልምናን ጥሪና አስተምህሮ ለማድረስ የተጉ ጎበዝ ፈረሠኛ ብቻ ሆነው አይደሉም
የምናገኛቸው። በምላስም ሆነ በብዕራቸው እስልምናን ከምዕራባውያን ጥቃትና የሥም ማጥፋት ዘመቻ
በመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱ የሙስሊም ዓለማቀፍ ስብእናዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን

እንረዳለን።

ዲዳት የጽሑፍም የመድረክም አንበሳ ናቸው። መድረክ አያያዛቸው፣ ሞገሳቸውና የንግግራቸው ሁኔታ ሁሉ
ሀሳብን ይሰርቃል፣ ልብን ይገዛል። መድረክ ላይ የትኛውም ርቱዕ ተናጋሪ አይረታቸውም። በንግግራቸውና
በክርክራቸውም የገጠሟቸውን ብዙዎችን መሳቂያ መሳለቂያ አድርገዋል። አንዲት ቃል የተናገሩ እንደሆን ያች
ቃል በዓለም ዙሪያ አሉ በተባሉ ጳጳሶች ጉያ በመግባት ታሸብራቸዋለች፣ ዕረፍትም ትነሳቸዋለች።

በርግጥም አሕመድ ዲዳት ለየት እና ወጣ ያሉ ዳዒ ናቸው። በደዕዋ ሥራ ላይ የሚያህላቸው ማንም የለም።


በዚህ ዘርፍ ከሀያ አንደኛው ክፍለዘመን ጋር ሊሄድ በሚችል መልኩ ተክነው ወጥተዋል።

አሕመድ ሑሴን ቃሲም ዲዳት የተወለዱት በ1918 ዓ.ል በህንድ ሱራት ነው። አባታቸው ሑሴን ቃሲም
ዲዳት በደቡብ አፍሪካ ዉስጥ በልብስ ሰፊነት ይሠሩ ነበር።

አሕመድ ዲዳት በ1927 ዓ.ል አባታቸው ወደሚገኙበት ። በወቅቱ የዘጠኝ ዓመት ዕድሜ ታዳጊ ነበሩ።
ህንድን ከለቀቁ በኋላ እናታቸው ሞተች። አላህ ይዘንላት። አሕመድ እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ
ትምህርታቸውን ቀጠሉ። ከዚያ በኋላ ድህነት አላፈናፍን አላቸው። የትምህርት ክፍያቸውን እንኳን መክፈል
እስኪሳናቸው ሲደርሱ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ።
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
አባታቸው ልጃቸው ያቋረጠውን ትምህርቱን ይቀጥል ዘንድ ከብዙ ነጋዴዎች ጋር ቢነጋገሩም ምንም መፍትሄ
ሊያገኙ አልቻሉም። ስለዚህም ሌላ አማራጭ መፈለግ ያዙ።

አሕመድ ዲዳት በተለያዩ ሙያዎች ላይ በመሥራት ዕድላቸውን ሞክረዋል። በብዙ የንግድ ቦታዎች ላይ
ሠርተዋል። ከዚያም ቤተሰባቸው የሚኖርበትን ደርባን ከተማን በመልቀቅ ከአንድ የተከበረ ሙስሊም ሱቅ
ዉስጥ ለመሥራት ከደርባን ሀያ አምስት ማይል ርቀው ተጓዙ። እዚያም ተቀጥረው ሻጭ ሆነው ቆዩ።
ቀጥሎም ትላልቅ መኪናዎችን ከሚያመርት አንድ ፋብሪካ ዉስጥ ሹፌር ሆነው ተቀጠሩ። ቀጥሎም የገቢና
ወጭ ምርቶች መዝጋቢ ሆነው ሠሩ። ከዚያም የፋብሪካው ኃላፊ ሆኑ።

በ1936 በናታል ደቡባዊ ዳርቻ በቢሮ ዕቃዎች ሻጭነት ተቀጥረው በመሥራት ላይ እያሉ በክርስቲያኖች
ሴሚናር ላይ ሙስሊሞችን ወደ ክርስትና ለመለወጥ የተሰማሩ የተወሰኑ ሚሽነሪዎችን አገኙ። ሰዎቹ
የእስልምና ሃይማኖት መልዕክተኛ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እስልምናን ያስፋፉት በሰይፍ ኃይል እንደሆነም
ይናገሩ ነበር። የዚህ ዓይነቱ ውንጀላ ሸይኽ አሕመድ ዲዳትን ይበልጥ እንዲነሳሱና ወደሃይማኖት ንፅፅር
ጥናት እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

ስለኢስላም ማጥናት የጀመሩትም ሚስተር ፋየርፋክስ የሚባል ወደ እስልምና የገባ ሰው በሚሰጠው


ትምህርት ላይ በመገኘት ነበር። ትምህርቱ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች እየጨመሩ በመምጣታቸው ፋየርፋክስ
ክፍለጊዜውን በማራዘም ስለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና እስልምናን ለክርስቲያኖች እንዴት መስበክ
እንደሚቻልም በተጨማሪ አስተማራቸው። በጊዜ ሂደት ፋይርፋክስ ማስተማሩን ሲያቆም ስለመጽሐፍ ቅዱስ
የተሻለ ዕውቀት የነበራቸው አሕመድ ዲዳት በቦታው ተተክተው ለሶስት ዓመታት ያህል አስተማሩ። ዲዳት
መደበኛ በሆነ መልኩ እንደሙስሊም ምሁራን ጊዜ ወስደው ኪታቦችን አልተማሩም።
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
ሸይኽ አሕመድ ዲዳት በ1937 ዓ.ል ደግሞ ሐዋእ ገንገት የምትባል እንስት አገቡና አንዲት ሴት እና ሁለት
ወንድ ልጆችን ከሷ አገኙ።

በ1949 ዓ.ል ወደ ፓኪስታን በመጓዝ በአንድ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ዉስጥ ለሦስት ዓመታት ያህል
አገልግለዋል።

በ1996 ዓ.ል እዚያ ከሚገኙ ትላልቅ ጳጳሶች ጋር የተሳካ ክርክር አድርገው ከአውስትራሊያ ሲመለሱ
አንገታቸው ሥር ባገኛቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ሙሉ በሙሉ ፓራላይዝድ በመሆን ለዘጠኝ ዓመታት
ያህል ፍራሽ ላይ ወድቀው ቆዩ።

በታመሙበት ጊዜ ሁሉ ከተለያዩ የዐረብ ሀገራት መንግሥታት እና መሪዎቻቸው ትልቅ እንክብካቤ


ይደረግላቸው ነበር። ስለሆነም በተሻለ ሁኔታ እንዲታከሙና በዘርፉ በተካኑ ሐኪሞች እንዲታዩ ተብሎ
ከደቡብ አፍሪካ ወደ ሪያድ ሆስፒታል ተዛወሩ።

አሕመድ ዲዳት በመጨረሻም ወደማይቀረው ሞት እና ወደ አላህ ጉርብትና የሄዱት በ2005 ዓ.ል በሰማኒያ
ሰባት ዓመት ዕድሜአቸው በእጅጉ የሚወዱትን የአላህን (ሱ.ወ) ቃል ቁርኣንን በማዳመጥ ላይ እያሉ ነበር።

ለአሕመድ ዲዳት የተቸሩ የአላህ ጥበቃዎችን እንክብካቤዎች

በአሕመድ ዲዳት ሕይወት ዉስጥ ያልተጠበቁ የአላህ ጥበቃዎችና እንክብካቤዎች ታይተዋል። አላህ (ሱ.ወ.)
ነገሮችን አስተካክሎላቸዋል፣ ሰበቦችንም አሟልቶላቸዋል። የመጀመሪያው – ለንባብ ያላቸው ጉጉት እጅግ
ከፍተኛ መሆኑ ነው። በብቸኝነታቸው ጊዜያት ሁሉ መጽሐፎች መልካም ወዳጆቻቸው ነበሩ። በዚህም
የመጽሐፎች ጥብቅ ጓደኛ ሆነው ኖሩ። መጽሐፍ፣ መጽሄት ይሁን ጋዜጣ አሊያም ሌላ ነገር በእጃቸው
የገባውን ሁሉ በጥልቅ የመረዳት ስሜት ሳያነቡ አያልፉም ነበር። በቤተመጽሐፋቸው ዉስጥ ያላነበቧቸው
አንድም መጽሐፍ የለም። ከዚህም ጎን ለጎን አላህ ጥልቅ የመረዳት ተሰጥኦ እና የመጠቀ እይታን፣ አንደበተ
ርቱእነትን፣ በነገሮች ስኬትና ድልን፣ ትግልና ብርታትን አላህ ለግሷቸዋል።
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
ለማንበብ ያላቸው ከፍተኛ ጉጉት ከባበድ መሠናክሎች ሁሉ እንዲገሩላቸው እገዛ አድርጎላቸዋል። ከእስልምና
መከላከል እና ጠበቃው መሆን ትልቁ ዓላማቸውና ጭንቀታቸው ነበር። እስልምና የሚነካውን ሰው ሁሉ
ባገኙበት በተለያዩ ጉዳዩች ላይ ይከራከሩ ነበር። በዚህም በአዕምሮ ምጥቀትም ሆነ በክርክር ችሎታ ዘወትር
ይረቷቸው ነበር። ከዚህም ባለፈ ከፍተኛ የሆነ የቋንቋ ንግግር ችሎታ ነበራቸው።

ሌላው አላህ ያሳካላቸው ነገር ደግሞ ። “ኢዝሃሩል ሐቅ /እውነትን መግለጽ” የተሠኘውን


የረሕመቱላህ አልሂንዲን መጽሐፍ ማግኘታቸው ነበር። ይህም የሆነው በአንድ ወቅት የሚነበብ ነገር ፍለጋ
በአንድ መጋዘን ዉስጥ የተከማቹ መጽሐፎችን ሲያገላብጡ ነበር። ይህን ጥንታዊ የሆነ መጽሐፍ
በማግኘታቸው እጅጉን ተገረሙ፣ ማመንም አቃታቸው። መጽሐፉ የታተመው በ1915 ዓ.ል ሲሆን
መጽሐፉን አንስተው በእንግሊዝኛ ፊደል የተፃፈውን ርዕሱን ማየት ጀመሩ። “HAKK IZARUL” ይላል።
ሆኖም ግን የዚህን ቃል ትርጉም ማወቅ አልቻሉም። ምክንያቱም ዐረብኛ ቃል ነውና። ሆኖምግን ዝቅ ሲሉ
የእንግሊዝኛ ትርጉሙን ተመለከቱ “TRUTH REVEALED” ይላል።

ረሕመቱላህ ይህንን መጽሐፍ ያዘጋጁት ለክርስቲያኖች መልስ እንዲሆናቸው ነበር። በዋናነትም በመበረዝና
መከለስ፣ በሥላሴ ምንነት፣ በቁርኣን እውነትነትና በነቢይነት ዙሪያ አምስት ጥናቶች የተካተቱበት ነበር።
በወቅቱ የክርስትና ሚሽነሪዎች በሙስሊም ህንዶች መካከል ገብተው በሰፊው ይንቀሳቀሱ ነበር።

አሕመድ ዲዳት ሃይማኖታዊ ንጽጽር ጉዳዮች በሚገባ ካነበቡና በጥልቀት ከተረዱ በኋላ በማስረጃዎች እና
መረጃዎች በእጅጉ ታጥቀው በአዳራሽ ዉስጥ ትምህርት መስጠት ጀመሩ። ትምህርቱንም የሚሠጡት በጉዳዩ
ዙሪያ በቂ ዕውቀት ላላቸውና ለሌሎችም ወገኖች ነበር። ትምህርታቸው እጅግ ሳቢ እና ፋይዳውም የጎላ
ነበር። የአዳራሹን ኪራይም ሆነ የተለያዩ ወጭዎችንም የሚችሉት ራሣቸው ነበሩ።

ይህ ወጣት ተናጋሪ የከተማውን ህዝብ ለመሳብና ትኩረት ለማግኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም። ስለ መጽሐፍ


ቅዱስ ያለው ዕውቀት እና መረጃ፣ በቁርኣን እና በመልዕክተኛው ላይ ያለው ጠንካራ እምነት እጅግ አስደናቂ
ነበር።

ከዕለታት በአንዱ ቀን በደርባን ንግግራቸውና ትምህርታቸው ላይ የነበሩ የጆሃንስበርግ ሰዎች ወደርሣቸው


በመምጣት የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) መውሊድ ምክንያት በማድረግ ንግግር እንዲያደርጉላቸውና ትምህርት
እንዲሠጧቸው ጋበዟቸው። ትንሽ ካመነቱ በኋላ ሀሳቡን ሳይቀበሏቸው ቀሩ። ለዚህም ምክንያት ነበራቸው።
ዲዳት ከዝቅተኛ ገቢ የማኅበረሰብ ክፍል ዉስጥ የሚመደቡ ናቸው። የጉዞ ወጭያቸውን እንኳን ለመሸፈን
አቅም የላቸውም። ሆኖምግን ሰዎቹ የመሄጃውንም ሆነ የመልስ ጉዞውን ወጭ ለመሸፈን ቃል ገቡላቸው።
በዚህም ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን ለመሄድ ዕድል አገኙ። በጆሃንስበርግ አዳራሽም እጅግ አነጋጋሪና
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
አስደማሚ የሆነ ንግግራቸውን አደረጉ። ሆኖምግን መልዕክታቸው በንግግርነቱ ብቻ የተወሰነ አልነበረም።
በዉስጣቸው ትልቅ የራስ መተማመን ስሜት ተተከለ። በዚህም የተነሳ በደዕዋው ዘርፍ በሠፊው ለመሥራት
አሰቡ። በእንዴትነቱ ዙሪያም አዳዲስ ሀሳቦችን በማከል ስለትግበራው ብዙ አሠላሠሉ።

አሕመድ ዲዳት የደዕዋ ትምህርት መስጠቱን በጆሃንስበርግ ቢጀምሩ ትልቅ አቀባበል ሊኖረው እንደሚችል
አሰቡና በ1958 ዓ.ል በደርባን ከተማ አዳራሽ የደዕዋ ትምህርታቸውን መስጠት ጀመሩ። እዚያ የሚገኘውን
ትልቁን መስጂድም ለደዕዋ ሥራው ማዕከል አደረጉት። እጅግ ጠንካራ እንቅስቃሴዎች በማድረጋቸውም
ሰዎች በብዛት እስልምናን መቀበል ጀመሩ። አሕመድ ዲዳት በእውነት መንገድ ላይ አንዳችም ነገር አይፈሩም
ነበር። በፓኪስታን ያሉበት ድረስ ሄደው ሦስት ቄሶችን በመከራከር አጣብቂኝ ዉስጥ ሲያስገቧቸው
ከርሣቸው የሚወጡ ቃላቶች በሙሉ በጀግንነትና በወኔ የተሞሉ ነበሩ።

የመድረክ ላይ አንበሳ

ልጃቸው ዩሱፍ ዲዳት አባታቸውን “የመድረክ አንበሳ’ ሲሉ ይገልጿቸዋል። በርግጥም ሸይኽ አሕመድ ዲዳት
በዋናነት በክርክር ስልታቸውና በማራኪ የመድረክ አቀራረባቸው ነው የሚታወቁት። ከዚህም በተጨማሪ
የተዋጣለት ፀሐፊም ናቸው። ከሀያ በላይ መጽሐፎችን የፃፉ ሲሆን በርካታ በራሪ ወረቀቶችንም አዘጋጅተው
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቅጂዎች በዓለም ዙሪያ ተበትነዋል። እነኚህ የህትመት ዉጤቶችም ብዙዎቹ ወደ

ሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉመው ተሠራጭተዋል።

ልጃቸው ዩሱፍ ዲዳት የቀድሞው የደቡብ አፍረካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት
በ1994 ዓ.ል ሳውዲ ዐረቢያን ሲጎበኙ ያሉትን ያስታውሳሉ። ማንዴላ እንዳሉት በሄዱበት ሁሉ ሰዎች
በተለይም ወጣቶች ስለታላቁ የሙስሊም ምሁር ስለ ዲዳት ሁኔታ ይጠይቋቸዋል። ለቴሌቭዥን ቃለምልልስ
ሲቀርቡም የጋዜጠኛው ቀዳሚ ጥያቄ ደቡብ አፍሪካ የሚገኙት ሸይኽ ዲዳት እንዴት ናቸው የሚል ነው።

ሸይኽ አሕመድ ዲዳት በዓለማቀፍ ደረጃ ከታዋቂ ሰዎች ጋር ያደረጓቸው በርካታ ክርክሮችን አድርገዋል።
ጎልተው ከሚጠቀሱት መካከል፡-
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
1. ከጆን ጊልኽረስት ጋር ያደረጉት ክርክር – ጊልኽረስት ከቤኖኒ ደቡብ አፍሪካ ሲሆን በሃይማኖቱ
ክርስቲያን የሆነ ጠበቃ ነው። በ1975 ዓ.ል በኢየሱስ ክርስቶስ ስቅላት ዙሪያ ከዲዳት ጋር ክርክር
አድርገዋል።
2. ከጆሽ ማክዶዌል ጋር ያደረጉት ክርክር – አሕመድ ዲዳት በዓለማቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ
ያደረጉትና ሰፊ እውቅናም ያስገኘላቸው ክርክር ሲሆን በኦገስት 1981 በደርባን ደቡብ አፍሪካ
ነበር ያደረጉት። ጆሽ ማክዶዌል ታዋቂ የክርስቲያን ሰባኪ ነው።

3. ከአኒስ ሾሮሽ ጋር ያደረጉት ክርክር – አሕመድ ዲዳት ከፍልስጤማዊው አኒስ ሾሮሽ ጋር


በተደጋጋሚ ክርክር አድርገዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በሴፕተምበር 8ቀን 1977 ዓ.ል
በበርሚንግሃም ክርክር አደረጉ። ክርክሩንም ያደረጉት በቁርኣንና መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ
ቃልነት ዙሪያ ነበር። በ1980ዎቹ ዉስጥ ደግሞ ዲዳት እና ሾሮስ ለሁለት ጊዜ ያህል ክርክር
አድርገዋል። የመጀመሪያውን ክርክር ያደረጉት በ1985 ዓ.ል በለንደን ሮያል አልበርት አዳራሽ
ሲሆን የክርክሩ ርዕስ የነበረውም “የሱስ አምላክ ነውን?” የሚል ነበር። ሁለተኛው ክርክር ደግሞ
በተሻለ ቅንጅትና ደማቅ ዝግጅት በኦገስት 7 ቀን 1988 ዓ.ል በበርሚንግሃም የተካሄደው ሲሆን
ከቁርኣንና ከመጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል የትኛው ነው? በሚል ርዕስ ሥር ነበር።
4. ከጂሚ ሰዋጋርት ጋር ያደረጉት ክርክር – አሕመድ ዲዳት በኖቨምበር 1986 ዓ.ል ከክርስቲያን
የቴሌቭዝን ሰባኪው ጂሚ ስዋጋርት ጋር ክርክር አድርገዋል።
5. ሌሎች ተጠቃሽ ክርክሮች – ሸይኽ አሕመድ ዲዳት በኦክቶበር 1991 ዓ.ል ወደ ስካንዴኔቭያን
አገራት በመጓዝ ሶስት ክርክሮችንና በርካታ ንግግሮች አድርገዋል። ሁለቱ ክርክሮች የተደረጉት
በተከታታይ ምሽቶች በስቶክሆልም ስዊድን ከፓስተር ስታንሊ ጆበርግ ጋር ነበር። የመጀመሪያው
ክርክር የተደረገው “መጽሐፍ ቅዱስ እውነት የአምላክ ቃል ነውን?” በሚል ርዕስ ሥር ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ “እውን ኢየሱስ አምላክ ነውን?” የሚል ነበር።
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
ዲዳት እና ጳጳሱ

የሮማው የካቶሊክ ጳጳስ ጆን ፖል በሙስሊሞች ጋር የጋራ ግንዛቤ መፍጠር፣ መከባበርና መነጋገር እንዲኖር
ጥሪ ካደረጉ በኋላ በ1984 ዓ.ል ዲዳት በቫቲካን አደባባይ ለህዝብ ክፍት በሆነ መልኩ ከጳጳሱ ጋር
ለመከራከር ሀሳብ አቀረቡ። ሆኖምግን ጳጳሱ ሀሳቡን አልተቀበሉም። የጳጳሱ ቢሮ መልስ ሊሠጣቸው
ባለመቻሉም በጥር ወር 1985 ዓ.ል አሕመድ ዲዳት ብፁዕነታቸው ከሙስሊሞች ጋር ድርድር ይደረግ
የሚል የድብብቆሽ ጨዋታ ይዘዋል የሚል አርዕስት የያዘ በራሪ ወረቀት አሠራጩ።

መጽሐፎቻቸው እና ንግግሮቻቸው

አሕመድ ዲዳት ከደርዘን በላይ የሆኑና በብዛት የተሠራጩ አነስተኛ መጠን ያላቸው መጽሐፎችን አዘጋጅተው
አሳትመዋል። ዲዳት የሠጧቸው ትምህርቶችና ያደረጓቸው ንግግሮችም በዋናነት የሚያተኩሩት በኢስላም
ክርስቲያን ሃይማኖት ንጽጽር ዙሪያ ነው። መጽሐፎቻቸውም የተዘጋጁት በመድረክ ላይ ያቀረቧቸውን
ትምህርቶችና ንግግሮች መሠረት አድርገው ነው። ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል-

 Is the Bible God’s Word? – መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነውን?


 What the Bible says about Muhammad – መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነብዩ ሙሐመድ
ምን ይላል?
 Crucifixion or Cruci-Fiction? – እውነተኛ ስቅላት ወይስ ልቦለድ
 Muhammad: The Natural Successor to Christ – ሙሐመድ ትክክለኛው
የክርስቶስ ወራሽ
 Christ in Islam – ክርስቶስ በኢስላም
 Muhammad the Greatest – ሙሐመድ የታላቆች ታላቅ
 Al-Qur’an the Miracle of Miracles – ቁርኣን የተዓምራት ሁሉ ተዓምር

ዲዳት አራት አነስተኛ እውቅ መጽሐፎቻቸውን በአንድ ላይ በመጠረዝ ያሳተሙ ሲሆን 10,000 ኮፒ
የሚሆኑ መጽሐፎችን “The Choice” በሚል ስያሜ ነበር የታተሙት። የመጀመሪያው መጽሐፋቸው
በአፕሪል 1993 ዓ.ል የታተመው Islam and Christianity የተሠኘው ነው። ይህ መጽሐፍ በ1990ዎቹ
ዉስጥ ከፍተኛ እውቅናን የተጎናፀፈ ነበር። በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ በርካታ ሚሽነሪዎችም በነፃ ታድሏል።
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
መጽሐፉን በርካታ ማተሚያ ቤቶች በተደጋጋሚ ያሳተሙት ሲሆን በሁለት ዓመት ዉስጥ ብቻ 250ሺህ

ያህል ኮፒ በመካከለኛው ምሥራቅ ሊታተም ችሏል።

ቀጥሎ ደግሞ ሁለተኛው ጥራዝ “The Choice” ስድስት አነስተኛ መጽሐፎችን በማካተት ታተመ። ዲዳት
በዐብደላህ ዩሱፍ ዐሊ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው የቅዱስ ቁርኣን በሰፊው እንዲተዋወቅና
እንዲሠራጭ እገዛ አድርገዋል። በንግግራቸውም ዉስጥ በተደጋጋሚ ይጠቅሱት ነበር።

ዘመናት በሰዎቻቸው ይዘከራሉ

አሕመድ ዲዳት አላህ ይዘንላቸውና በደዕዋው ዘርፍ ለሙስሊሞች አዲስ መንገድ ያሳዩ ታላቅ ሰው ነበሩ።
ሕይወታቸውን በሙሉ በእስልምና እና በቁርኣን ላይ አንፀው ኖረዋል። በአላህ እና በመልዕክተኛው ማመን
ብቻውን በቂ እንዳልሆነና መልዕክታቸውን ትክክለኛው ጥሪ ካልደረሣቸው ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች መካከል
በማሠራጨትና በማስተማር ስለዚህች ዓለምም ሆነ ስለመጨረሻው ዓለም እንዲሁም ለዘመናት ስለ
እስልምና እና ቁርኣን የተሳሳተ ግንዛቤ የያዙ ሰዎችን አመለካከት አደገኛነት በማስተማር የሚገባቸውን ሐቅ

ለነርሱ መስጠት እንደሚገባ በልቦናቸው ዉስጥ የሰረፀ አቋም ሆኗል።


ጃቢር ኢብኑ ሀያን
በርግጥም ማንኛውም ስለ እስልምና የሚያሳስበው ሙስሊም ሁሉ እኚህ አንጋፋ ሸይኽ ከእስልምና
ለመከላከል ሲሉ በቁርጠኝነት እና በፅናት ትላልቅ ቄሶችን ሲሞግቱ ሲያይ ዐይኑ በእንባ የሚሞላ ስለመሆኑ
አያጠራጥርም። ዲዳት ቄሶቹ ንግግራቸውን እስኪጨርሱ ተራቸውን ሲጠብቁ የተመለከታቸው ሁሉ
በፊታቸው ላይ አንድም ዓይነት ጥርጣሬ፣ መረበሽም እና ወደኋላ የማለት ስሜት አያይም። ፍጹም በሆነ
መልኩ እርጋታ ይነበብባቸዋል። ነጭ ፂማቸው፣ ሞገሳቸውና ሳቢ ፈገግታቸው ሕይወታቸውን በሙሉ
ተለይቷቸው አያውቅም። ባጠረ ጸጉራቸው ላይ የተደፋችውና በመጠኑ ወደ ግንባራቸው ወጣ ያለችው ትንሿ
ኮፊያቸው ከብዙዎች ህሊና የምትጠፋ አይደለችም። በቂ እና አሳማኝ የሆነ መረጃ ታጥቀው ከነሞገሳቸው
በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ ይቀመጣሉ። ጉያቸው በሰሉ ቀስቶች የተሞላ ነው። ግዳያቸውን ለመጣል በዝምታና
በተረጋጋ መንፈስ ተራቸውን የሚጠባበቁ ይመስላሉ። …

ምናልባት በተደጋጋሚ ሲወያዩና ሲከራከሩ በምታዩዋቸው ጊዜ ቁርኣንን አንስተው ከፍ ባለ ድምጽ “ይህ


ከአላህ ዘንድ ነው!” የሚሉበት ሁኔታ አይረሣችሁም። የአላህ ቃል ከፍ ብሎ ለዘላለሙ ይኖር ዘንድ
በርግጥም ብዙ ጥረዋል።

በእንግሊዝኛ ቋንቋ በጻፏቸው መጽሐፎችና ባሰሟቸው ዲስኩሮችና ክርክሮች ዓለማቀፍ ዝናን ያተረፉት
ሸይኽ አሕመድ ዲዳት በ1986 ዓ.ል ሃምሳ ዓመት ሙሉ እስልምናን ለማገልገል ስላበረከቱት አስተዋጽኦ
የንጉስ ፈሀድን ዓለማቀፍ ሽልማት አግኝተዋል።

አላህ አሕመድ ዲዳትን ይዘንላቸው። ከሰፊው የእዝነት ጀነቱም ያስገባቸው። ስለ ኢስላም ላደረጉት አስተዋጽኦ
ሁሉ መልካሙን ይመንዳቸው።

ኢማም አን-ነወዊ
0
5267

Share on Facebook

Tweet on Twitter



ጃቢር ኢብኑ ሀያን

የዘር ሀረጋቸውና ዕድገታቸው

አቡ ዘከሪያ ሙሕይዲን ኢብኑ ሸረፍ አን-ነወዊ ይባላሉ። የተወለዱት በሶሪያ ከሐውራን መንደር አንዷ
በሆነችው በነዋ ነው። ጊዜውም በ631 ዓ.ሂ ሲሆን ከደጋግ ወላጆች ነው የተወለዱት። ዕድሜአቸው አሥር
ዓመት ገደማ ሲሆን ቁርኣንን በቃላቸው ማጥናት እና ፊቅሂን በአንዳንድ ዑለማኦች እጅ መማር ጀመሩ።
በ649 ዓ.ሂ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ብለው ከአባታቸው ጋር በመሆን ደማስቆ ወደሚገኘው የሐዲሥ
ማዕከል አቀኑ። እዚያም የረዋሒያ መድረሳን ተቀላቀሉ። መድረሳው ከታላቁ የኡመዉያ መስጂድ ጋር ተያይዞ
የተሠራ ነበር። በ651 ዓ.ሂ ከአባታቸው ጋር በመሆን ሐጅ አደረጉ። ከዚያም ወደ ዲመሽቅ (ደማስቆ)
ተመለሱ። እዚያም ሆነው ሙሉ ሀሳባቸውንና ፊታቸውን ወደ ዑለማኦች ማዕድ በማዞር ዕውቀት መቅሰም
ጀመሩ።

የኢማም ነወዊ ሥነምግባር እና ባህሪያቸው


ጃቢር ኢብኑ ሀያን
ኢማም ነወዊ ሞገስ ያላቸው ሰው ነበሩ። ሲስቁ እምብዛም አይታዩም። ከጨዋታና ላግጣም የራቁ ናቸው።
የቱን ያህል መራራ ቢሆንም እውነትን ከመናገር ወደኋላ ባለማለት አቋማቸው ይታወቃሉ። በአላህ ጉዳይም
የየትኛውንም ወቃሽ ወቀሳን አይፈሩም። ለዓለማዊነት ከማደር እጅግ የራቁ በአላህ ፍራቻም የሚታወቁ
የታላቅ ስብእና ባለቤት ናቸው። ስለርሣቸው የፃፉ ሁሉ በርግጥም ከዚህች ዓለም እጅግ ቁጥብ እና የተብቃቁ
ስለመሆናቸው መስክረዋል።

ኢማም ነው ለአላህ ያላቸው ፍራቻ በእጅጉ ይለያል። ለመሪዎችና አስተዳዳሪዎች መልካም ምክራቸውን
ያቀብላሉ። በጥሩ ያዛሉ፣ ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ። ለኢማም አንነወዊ አላህ ይዘንላቸው – በሀያ አራት
ሰዓታት ዉስጥ አንድ ጊዙ ብቻ ማለትም ከዒሻ በኋላ ነበር የሚመገቡት። ከማንም ምንም ፈልገው
አያውቁም። ብዙን ጊዜ ለመሪዎች እና ለሚኒስቴሮቻቸው ይጽፉ፤ ለህዝቡም ሆነ ለሀገራቸው በሚጠቅም
ነገር ላይ ያመላክቱና ይመክሩ ነበር።

የዕውቀት ሕይወታቸው

ዲመሽቅ ከደረሱ በኋላ ያለው የዕውቀት ሕይወታቸው ሶስት የተለያየ ክፍል ነበረው።

የመጀመሪያው – ገና በልጅነትና በወጣትነት ሕይወታቸው ዕውቀት ፍለጋ መጣር እና ለማግኘት የተጉበት


ነው።

ሁለተኛው – ዕውቀታቸውን የበለጠ ለማስፋት፣ በጥልቀትም ለማወቅ የጣሩበት ነው። በዚህም የተለያዩ
ዕውቀቶችን ፍለጋ አብዝተው ደክመዋል። በየቀኑ በተለያዩ ሸይኾች ላይ አሥራ ሁለት ያህል ትምህርቶችን
ይማሩ ነበር።

ሦስተኛው – ዕውቀትን መጠቀም፣ ማስተማርና ማሠራጨት። ይህንን የጀመሩት በ660 ዓ.ሂ ገና በሰላሳ
ዓመታቸው ነበር። አላህም (ሱ.ወ) ጊዜያቸውን ባርኮላቸዋል። በርግጥም ረድቷቸዋል። ጊዜያቸውን እጅግ
የሚገራርሙና የማይታመኑ ትላልቅ የሆኑ መጽሐፍት በመፃፍ ተጠቅመውበታል። በመጽሐፍቶቻቸው ዉስጥ
የሚጠቀሙት ገለፃ የለሰለሰና ገር፣ ማስረጃቸው ግልጽ፣ እይታቸው የተብራራ ነበር። ድርሰቶቻቸው
ዘመናትን ተሻግረው ዛሬም ድረስ በያንዳንዱ ሙስሊም ቤት ዉስጥ ይገኛሉ።

ኢማም አንነወዊ – በቀንም ይሁን በሌሊት አንድም የሚያባክኑት ጊዜ አልነበራቸውም። ሙሉ ጊዜያቸውን


በዕውቀት ጉዳዮች ላይ ያውሉታል። መንገድ ሲሄዱም ሆነ ሲመለሱ በማንበብ እና ትምህርቶቻቸውን
በማጥናት የተጠመዱ ነበሩ። በዚህ መልኩ ዕውቀትን ሲገበዩ ለስድስተ ዓመታት ዘለቁ። ከዚያም ወደ
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
መፃህፍት ዝግጅትና ለሙስሊሞችና ለመሪዎቻቸው ምክሮቻቸውን ወደማካፈል ፊታቸውን አዞሩ።
ራሣቸውንም በእምነት ለማጠንከር በብርቱ ይታገሉ ነበር። ረቂቅ የሆኑ የፈቅሂ ዕውቀቶችን በማስተንተን
ከዑለማኦች መንገድ ላለመውጣት ይመራመሩ ነበር። በቀልብ ሥራዎች ዙሪያም የራሣቸውን ሁኔታ
ይገምግሙ፤ ቀልባቸውንም ከመጥፎ ነገር ለማንፃት ይጥሩ ነበር። ኢማሙ በጣም ትናንሽ በሆኑ ነገሮች ላይ
ጭምር ራሣቸውን ይገመግሙ ነበር። በዕውቀታቸውና በዕውቀት ፍለጋ ስልታቸው የማይደክሙ ነበሩ።
የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሦችንም በአግባቡ ያውቃሉ። ዓይነቶቻቸውንም ሁሉ እንዲሁ።
ትክክለኛውንና ያልሆነውን፣ ውድቅ የሆነውንና እና ተቀባይነት ያለውን የሌለውን ይለያሉ። ትርጉሙን እና
መልዕክቱንም ይገነዘባሉ።

ኢማም ነወወዊ ጊዜያቸውን በሙሉ በዕውቀትና በትግበራው ላይ ያዋሉ ታላቅ ዓሊም ናቸው። ከፊሉን
ድርሰት ያዘጋጁበታል፣ ከፊሉን ይማሩበታል፣ ከፊሉን ደግሞ ይሰግዱበታል፣ ሌላውን ቁርኣን ለማንበብ፣
በጥሩ ነገር ለማዘዝና ከመጥፎ ለመከልከል ይጠቀሙበታል።

በቃል በማጥናት ሁኔታቸው (በሒፍዛቸው) ሲበዛ ፈጣን ናቸው። በአጭር ጊዜ ዉስጥ በርካታ መጽሐፎችን
ሐፍዘዋል። በዚህም የኡስታዛቸውን አቢ ኢብራሂም ኢስሓቅ ኢብኑ አሕመድ አልመግሪቢን ዉዴታና
አድናቆት ማትረፍ ችለዋል። በትምህርት ማዕዳቸውም ላይ የየዕለቱን ትምህርት መልሰው ለታዳሚዎች
እንዲያስተምሩ አድርገዋቸው ነበር። ከዚያም በአል-አሽረፊያ የሐዲሥ ማዕከል እና በሌሎችም ተምረዋል።

ተማሪያቸው የነበረው ዐላአዲን ኢብኑ አልዐጣር ስለ ትምህርት አቀሳሰማቸው ኢማም ነወዊ የነገሩትን ሲናገር
– በየቀኑ በተለያዩ ሸይኾች እጅ አሥራ ሁለት ትምህርቶችን ከነማብራሪያውና ትክክለኛ መልዕክቱ ይማሩ
ነበር። በአል-ወሲጥ ዙሪያ ሁለት ትምህርት፣ በሙሀዘብ አንድ ትምህርት፣ በአል-ጀምዕ በይነ ሶሒሐይን ዙሪያ
አንድ ትምህርት፣ በሶሒሕ ሙስሊም ዙሪያ አምስት ትምህርት፣ በለምዕ ኢብኑ ጀኒይ ነሕው ዙሪያ አንድ
ትምህርት፣ በኢብኑ ሰኪት ኢስጢላሕ አልመንጢቅ የቋንቋ ትምህርት ዙሪያ አንድ ትምህርት፣ በሶርፍ ዙሪያ
አንድ ትምህርት፣ በኡሱል አልፊቅህ ዙሪያ አንድ ትምህርት፣ በአስማእ ሪጃል ዙሪያ አንድ ትምህርት፣
በኡሱለዲን ዙሪያ አንድ ትምህርት፣ የሚማሩ ሲሆን ከነኚህ ትምህርቶች ጋር የተያያዘውን ሁሉ
ከነማብራሪያው፣ ጥያቄ ከሚያስነሳው ጉዳይና ከቋንቋ አንጻር እና ከመሳሰሉት ሁሉ አስፈላጊውን ነገር ይፅፉ
ነበር።

ከርሣቸውም እጅ በርካታ ዑለማኦች ተምረዋል። ዕውቀታቸውም በተለያዩ አገራት ተበትኗል፣ ስለ እስልምና


ጥያቄዎች መልስ የሠጡባቸው ትምህርቶችም በሰፊው ተሠራጭተዋል። በድርሠቶቻቸውም በበርካታ
ሙስሊም አገራት የሚገኙ ሙስሊሞች ተጠቃሚ ሆነዋል። መጽሐፍቶቻቸው ዛሬም ድረስ ዓለም ላይ እጅግ
ተፈላጊዎች ናቸው።
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
የኢማም አንነወዊ ሸይኾች

ኢማም ነወዊ በአባ አልፈረጅ ዐብዱረሕማን ኢብኑ አቢ ዑመር እና በዋና ሸይኻቸው ሙሐመድ ኢብኑ
አሕመድ አልመቅዲሲ እጅ ተምረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከአባ ኢስማዒል ኢብን አቢ አስሓቅ ኢብራሂም
ኢብኑ አቢ አልዩስር፣ ከአባል ዐባስ አሕመድ ኢብኑ ዐብዱ ዳኢም፣ ከአቡልበቃእ ኻሊድ አንናቡሊሲ ፣ ከአባ
ሙሐመድ ዐብዱልዐዚዝ ኢብኑ ዐብደላህ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልሙሕሲን አልአንሷሪይ፣ ከዲያእ ኢብኑ
ቲማም አልሒሲ፣ ከአልሓፊዝ አባልፈድል ሙሐመድ ኢብኑ ሙሐመድ አልበክሪይ፣ ከአባልፈዳኢል
ዐብዱልከሪም ኢብኑ ዐብዱሶመድ (የዳመስቆ ኸጢብ)፣ ከአባ ሙሐመድ ዐብዱረሕማን ኢብኑ ሳሊም ኢብኑ
የሕያ አልአብናሪ፣ ከአባ ዘከሪያ የሕያ ኢብኑ አልፈትሕ አሲራፊ አልሐራኒ፣ ከአባ ኢስሐቅ ኢብራሂም ኢብኑ
ዐሊ ኢብኑ አሕመድ ኢብኑ ፋዲል አልዋሲጢ እና ከሌሎችም እጅ ተምረዋል።

ኢማም ነወዊ ለዕውቀት ያበረከቱት አስተዋጽኦ

በፊቅሂ ዙሪያ

ኢብኑ አልዐጣር እንዲህ ይላል – “ነወዊ የሻፊዒ መዝሀብ ጥልቅ አዋቂ ናቸው። መርሆቹን፣ መሠረቶቹን እና
ቅርንጫፎቹን ሁሉ አሳምረው ያውቃሉ። እንዲሁም ስለ ሶሓቦች እና ታቢዒዮች መዝሀብም፣ ሙስሊም
ዑለማኦች ስለተለያዩባቸውና ስለተስማሙባቸው ነጥቦች፣ ይበልጥ ዕውቅና ስላገኘውና ስለተተወው እይታ
ሁሉ ያውቃሉ። በዚህ ሁሉ አቋማቸው ቀደምት ደጋግ ሙስሊሞችን መንገድ ይከተሉ ነበር።›

በሐዲሥ ዙሪያ

አንድ ዘመን በመጣ ቁጥር በዚያ ዘመን ዉስጥ አላህ የሐዲሥ ሰዎችን ያስነሳል። እነርሱም በሐዲሥ ዕውቀት
ዙሪያ በማብራራት፣ አዲስ አቅጣጫ በማሳየትም ሆነ በማረም በኩል ሌላ አብዮት ያስነሳሉ። በመካከለኛው
ዘመን ከተነሱ ትላልቅ ስብእናዎች መካከል ኢብኑ ሶላሕ፣ ኢማም ነወዊ፣ አልሚዚይ እንዲሁም ኢማም ዘሀቢ
ይጠቀሳሉ። ኢማም ነወዊ ከነርሱ ባላቸው የጠለቀ ዕውቀት ይለያሉ። በፊቅሂም ሆነ በሐዲሥ ዕውቀት
እርሣቸውን የሚስተካከል አልነበረም ማለት ይቻላል።[1]

ኢብኑ አልዐጣር እንደዘገቡት ኢማም ነወዊ ቡኻሪና ሙስሊምን፣ የአቢ ዳዉድን፣ የቲርሚዚን እና የነሳኢን
የሒዲሥ ጥንቅሮችን፣ የኢማም ማሊክን አልሙወጦእ፣ የሻፊዒን እና የኢማም አሕመድን ሙስነድ፣
የዳሪሚን፣ የአቢ ዐዋናን፣ የአቢ የዕላ አልመውሱሊን፣ የኢብኑ ማጀህ ሱነንን፣ የዳር ቁጥኒን፣ የበይሀቂን፣
የበገዊ ሸርሑ ሱናን እና የተፍሲር ኪታባቸውን መዓሊሙ ተንዚልን፣ የዙበይር ኢብኑ በካር አልአንሳብን፣
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
የነባቲያ አልኹጠብን፣ የአልቁሸይሪ ሪሳላን፣ የኢብኑ ሱንኒን ዐመል አልየውም ወልለይላን፣ የአልኸጢብን
ኣዳቡ ሳሚዕ ወርራዊን እና ሌሎችንም በርካቶችን ተምረዋል። እነኚህ ሁሉ በሸይኹ የእጅ ጽሑፍ የተጠቀሱ
ናቸው።

ኢማም ነወዊ እና የሐዲሥ ዕውቀታቸው

ኢማም ነወዊ እንደ በርካታ ሙሐዲሶች ጥረታቸውን በሐዲሱ ዘገባ ሰንሰለት (ሰነድ) ዙሪያ ብቻ ትኩረት
አያደርጉም ነበር። የሐዲሡን መልዕክት ለማወቅ ትልቅ ጥረት ያደርጉ ነበር። ይህንኑ በሶሒሕ ሙስሊም
ማብራሪያቸው መቅድም ላይ ጠቅሰውታል። ከዚያም ወደዕውቀታዊ ጭብጡ ያተኩራሉ። ከርሣቸውም
በርካታ ሰዎች ተምረዋል። አቡልፈትሕ፣ አልሚዚይ እና ኢብኑል ዐጣር ጥቂቶቹ ናቸው።

ኢማም ነወዊ እና የቋንቋ ትምህርት

አንድ ሰው ቁርኣንንም ሆነ ሐዲሥን መረዳትና ትርጉማቸውንም ሊገነዘብ የሚችለው፣ የቀደሙትንም ሆነ


ኋላ ላይ የመጡትን የዕውቀት ሰዎች አባባል በአግባቡ የሚገነዘበው የዐረቢኛ ቋንቋን ጠንቅቆ ሲያውቅ ነው።
ይህም ነሕው እና ሶርፉን ያጠቃልላል (ስለ ዐረብኛ ቋንቋ ሰዋስዎና ህግጋት ጥናት)። የቃላትንም ትርጓሜ
ሊያውቅ ግድ ይላል። ይህ የኢማም ነወዊ አቋም ሲሆን ሌሎችንም የሚመክሩበት ጉዳይ ነው። ተህዚብ
አልአስማእ ወል-ሉጋት በተሠኘውና የቋንቋ አስፈላጊነት ላይ አተኩረው ባዘጋጁት መጽሐፋቸው መቅድም ላይ
እንዲህ ብለዋል – “አስፈላጊ ስለመሆኑ ብዙ ማብራራት አያስፈልግም። ሁሉም ዑለሞች
ተስማምተውበታልና። እንዲያውም ሙፍቲ፣ ኢማምም ሆነ ቃዲ የሆነ ሰው ማወቁ መስፈርት ነው።
መማሩም የወል ግዴታ ነው። ከፊሉ ካልተማረ ግዴታነቱ ከሌላው ላይ አይወድቅም።”[2]

ሌሎች ሁለቱ የነወዊ መጽሐፎች “ተሕሪር አት-ተንቢህ” እና “ተህዚብ አልአስማእ ወልሉጋት” ኢማም ነወዊ
በቋንቋ ዕውቀት ዙሪያ በዘመናቸው አቻ እንዳልነበራቸው የሚያመላክቱ ናቸው።

ኢማም ነወዊ በሕክምና ሥራ ለመሠማራት ስለመሞከራቸው

ኢማም ነወዊ እንዲህ ይላሉ – “በሕክምና ሥራ ለመሠማራት በዉስጤ አስቤ ነበር። ለዚህም ሲባል የኢብኑ
ሲናን ‘አልቃኑን’ መጽሐፍ ገዛሁኝ። በዚሁ ዙሪያ ለመሥራትም ቆርጬና አቋም ይዤ ተነሳሁኝ። ሆኖምግን
ልቤ ላይ ተጋረደ። ለበርካታ ቀናትም ምንም ሳልሠራ ቆየሁኝ። ጉዳዩን መልሼ አሰብኩበት። እንዴት ነው ይህን
ነገር ላስብ የቻልኩት አልኩኝ። ስለህክምና አብዝቼ ማሰቤ እንደሆነ አላህም ሰበቡን አሳወቀኝ። ወዲያውኑ
ጃቢር ኢብኑ ሀያን
የገዛሁትን የኢብኑ ሲናን መጽሐፍ አውጥቼ ሸጥኩኝ። ከህክምና ጋር የተያያዙ ነገሮችንም ከቤቴ አስወጣሁኝ።
ቀልቤ እንደገና ሲበራ ታወቀኝ። መጀመሪያ ወደነበርኩበት ሁኔታ ተመለስኩኝ።”[3]

ምናልባት ያ ኢማሙን ያገኛቸው የቀልብ ጨለማ በሕክምና ዙሪያ እንዳይጽፉ አግዷቸው ይሆናል። ስለ
ሕክምናም ነገሮች እንዲከብዱ አድርጎባቸው ይሆናል። ኢማም ነወዊ ወደ ሕክምና ትምህርት ሊያዘነብሉ
የቻሉት ምናልባት “ከሐላል እና ከሐራም ዕውቀት ቀጥሎ ከሕክምና ትምህርት በላይ ምርጥ የሆነ ትምህርት
አላውቅም” ያሉትን የኢማማቸውን የኢማም አሽ-ሻፊዒን አባባል ተከትለው ሊሆን ይችላል።[4]

ኢማም ነወዊ የሠሩባቸው ኃላፊነቶች

ኢማም ነወዊ የኢብኑ ኸልካን ምክትል በመሆን በኢቅባሊያ መድረሳ እስከ 669 ዓ.ሂ መጨረሻ ድረስ
ሠርተዋል።[5] እንዲሁም በአል-ፈለኪያ እና ሩክኒያ መድረሳዎችም ምክትል ሆነው አገልግለዋል።[6]

ኢማም ነወዊ ከ665-676 ዓ.ሂ ባለው ጊዜ ዉስጥ የአል-አሽረፊያን ሐዲሥ ማዕከል በዋና ኃላፊነት
መርተዋል። በወቅቱ ይህ ማዕከል በሐዲሥ ትምህርት በሻም ምድር እጅግ ይታወቅ ነበር። እዚያ የገባ ሰው
ሙሉ ጊዜውን ዕውቀት በመቅሰም ላይ ነው የሚያሳልፈው። በተለይ የሐዲሥ ዕውቀትን። “የሐዲሥ ማዕከሉ
ሸይኽ” የተባለ ሰው በዕውቀት ደረጃ ከፍተኛውን ማዕረግ እንደተጎናፀፈ ነው የሚቆጠረው። ከኢማም ነወዊ
በፊት የማዕከሉ ኃላፊ የነበሩት ተቂየዲን ኢብኑ ሶላሕ እና ሺሃቡዲን አቡ ሻማህ አልመቅዲሲ ነበሩ።

ታጅ አስ-ሱብኪ እንዲህ ይላል “አባቴ እንዲህ አሉኝ .. ከኢማም ነወዊ እና ኢብኑ ሶላሕ በላይ ሓፊዝ እና
አላህን ፈሪ የሆነ ከአል-አሽረፊያ የሐዲሥ ማዕከል አንድም ሰው አልገባም።”[7]

የኢማም ነወዊ ድርሠቶች

ኢማም ነወዊ በዚህች ምድር ላይ የኖሩት ለ46 ዓመታት ብቻ ነበር። ይህ ከመሆኑ ጋር ትተው ያለፉት
የድርሰት ክምችት ለዕድሜያቸው ቢካፈል በየቀኑ ሁለት ቀለል ያሉ መጽሐፍትን የመፃፍ ያህል ነው።[8] ወደ
ዕውቀቱ ዓለም የገቡት በ18 ዓመታቸው መሆኑን ስናስተውል ደግሞ በርግጥም አላህ ዕድሜያቸውን
እንደባረከላቸውና እርሣቸውም የቱን ያህል ብርቱ ጥረት ያደርጉ እንደነበር እንረዳለን።

እጅግ ከሚታወቁ ድርሰቶቻቸው መካከል


ጃቢር ኢብኑ ሀያን
 ሸርሑ ሙስሊም ፡- የኢማም ሙስሊምን መጽሐፍ መሠረት ያደረገ ዳጎስ ያለ ማብራሪያ ሲሆን
የዘገባ ሰንሰለቶችን፣ ስለ ቋንቋዊ ትርጓሜዎች፣ ስለ ሐዲሡ አጠቃላይ ትርጉሞች፣ ከየሐዲሡ
ስለሚገኙ ጠቃሚ ትምህርቶች፣ የየሐዲሡ ጥንካሬና ድክመት ዙሪያ ስለተባሉ ጉዳዮች እና ስለ
ሌሎችም ጠቃሚ ሀሳቦች በዝርዝር ይዳስሳል።
 ረውዳ ወይም ረውደቱ ጣሊቢን – በኢማም ሻፊዒ መዝሀብ ዙሪያ ወሳኝና ትላልቅ ከሚባሉ
መጽሐፎች መካከል አንዱ ነው። ነወዊ ይህን መጽሐፍ ያዘጋጁት “ሸርሕ አል-ከቢር” የተሠኘውን
የኢማም ራፊዒን መጽሐፍ አሳጥረው ነው። መጽሐፉ ብዙ ሙገሳ ተችሮታል።
 አልሚንሃጅ – በብዛት ተሠራጭተው ከሚገኙ የኢማም ነወዊ መጽሐፎች መካከል አንዱ ነው።
የራፊዒን “ሙሐረር” የተሠኘውን መጽሐፍ አሳጥረው ያቀረቡት ነው። መጽሐፉ ታርሟል።
የተለያዩ አማራጮችም አሉት።
 ሪያዱ ሷሊሒን – የሐዲሥና የምክር መጽሐፍ ነው። ልዩ የሚያደርገው እንደዚህ መጽሐፍ
እምነት የተጣለበትና በዓለም ላይ የተሠራጨ መጽሐፍ አለመኖሩ ነው። ታላቁ ዓሊም ሙሐመድ
ኢብኑ ዐሊ አስ-ሲዲቂ አሽሻፊዒ “ደሊሉል ፋሊሒን ሊጠሪቅ ሪያዱ ሷሊሒን” በሚል ሥያሜ
ለመጽሐፉ ማብራሪያ ሠርተውለታል። ሪያዱ ሷሊሒን ሌሎች ማብራሪያዎችም በተለያዩ ዑለሞች
ተዘጋጅቶለታል።
 አልአዝካር – በዚህ መጽሐፍ አንድ ሙስሊም የቀንና የሌሊት ሥራዎች ተዳሰውበታል።
የየአጋጣሚዎች ዚክሮች (ዉዳሴዎች)ንና ድንጋጌዎቻቸውን ይዟል።

ሌሎች መጽሐፎች

አት-ቲብያን፣ ተሕሪር አት-ተንቢህ፣ አልኢዳሕ ፊልመናሲክ፣ አልኢርሻድ፣ አት-ተቅሪብ፣ አል-አርበዒን አን-


ነወዊያ፣ ቡስታን አል-ዓሪፊን፣ መናቂብ አሽ-ሻፊዒ፣ ሙኽተሶር አሰድ አልጋባ፣ አልፈታዋ፣ አደብ አልሙፍቲ
ወልሙስተፍቲ፣ ሙኽተሶር ኣዳብ አልኢስቲስቃእ፣ ሩኡስ አልመሳኢል፣ ቱሕፈት ጡላብ አልፈዷኢል፣ አት-
ተርኺስ ፊልኢክራም ወልቂያም፣ መስአለቱ ተኽሚስ አልገናኢም፣ ሙኽተሶት አት-ተዝኒብ፣ መስአለቱ ኒየቱል
ኢግቲራፍ፣ ደቃኢቅ አልሚንሃጅ፣ ረውዳ፣ አት-ተቅሪብ ወት-ተይሲር ይገኙበታል።

ህልፈታቸው

ኢማም ነወዊ የሞቱት በ676 ዓ.ሂ ወደ ነዋ ከተመለሱ በኋላ ነበር። ከዚያ ቀደም ብሎ ለወቅፍ የተሠጡና
የተዋሷቸውን መጽሐፎችን ለየባለቤቶቻቸው መልሰዋል። የሸይኾቻቸውን መቃብሮች ጎብኝተውም
አልቅሰዋል። እንዲሁም በሕይወት ያሉትን ወዳጆቻቸውን ጎብኝተው ተሰናብተዋልም። አባታቸውንም
‫‪ጃቢር ኢብኑ ሀያን‬‬
‫‪እንዲሁም በይት አልመቅዲስ (ኢየሩሳሌምን) እና አልኸሊልን (ቤተልሄምን) ጎብኝተዋል። ከዚያም ወደ ነዋ‬‬
‫‪ተመለሱ። እዚያም ታመሙ። በረጀብ 24 ቀን እዚያው ሞቱ።‬‬

‫‪አላህ ኢማም ነወዊን በሰፊ እዝነቱ ዉስጥ ያስገባቸው። ለኢስላምና ለሙስሊሞች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሁሉ‬‬
‫‪በመልካም ይመንዳቸው።‬‬

‫‪55‬ص النووي اإلمام ‪:‬الدقر الغني عبد ]‪[1‬‬

‫‪، 1/ 3‬واللغات األسماء تهذيب ‪:‬النووي ]‪[2‬‬

‫‪ 4/1470‬والتذكرة ‪6- 7،‬ص ‪،‬الحديث ألفية شرح المغيث فتح ‪:‬السخاوي ]‪[3‬‬

‫‪273‬ص الشافعي اإلمام ‪:‬الدقر الغني عبد ‪[4] :‬‬

‫‪ 13/ 279‬والنهاية البداية ‪:‬كثير ابن ]‪[5‬‬

‫‪ 13/ 279‬والنهاية البداية ‪:‬كثير ابن ]‪[6‬‬

‫‪، 6/ 36‬م‪ 1990‬بيروت – العلمية الكتب دار ‪،‬المدارس تاريخ في الدارس ‪:‬القادر عبد ‪،‬النعيمي ]‪[7‬‬

‫‪[8] አንዱ መጽሐፍ የአርባ ገጽ ያህል‬‬

You might also like