Concept Note - Final

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 8

የአካል ጉዳተኞች ሁሉን አቀፍ የተቀናጀ ህክምና እና የማህበራዊ ተሃድሶ አገልግሎት አመራርና

አስተዳደርን ለመወሰን የተደረገ ጥናት አጭር ሪፖርት

ነሃሴ፣ 2010
የጥናቱ መነሻ

በሃገራችን የሚገኙትን አካል ጉዳተኞች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አገራዊ፣

አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ህግጋት ወጥተው ስራ ላይ የዋሉና በርካታ የማህበራዊና

ኢኮኖሚያዊ ፕሮግራሞች ያሉ ቢሆንም የአካል ጉዳተኞችን ልዩ ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ

የአገልግሎት መስጫ ተሃድሶ ማዕከላት በበቂ ሁኔታ ባለመደረጀታቸው ፣ በአካላዊ ተሃድሶ

ማዕከላት የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት የሚችሉ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ማፍራት

ባለመቻሉ፣ በርካታ አካል ጉዳተኛ ዜጎች በገጠሩ የአገራችን ክፍል መኖራቸውን ታሳቢ ያደረገ

የአካላዊም ሆነ የማህበራዊ ተሃድሶ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል አደረጃጀትና

አስራር ባለመዘርጋቱ ምክንያት አካል ጉዳተኞች ያሉባቸው ችግሮች ተቃለውላቸው

እንደሌሎች አቻዎቻቸው በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊነታቸውና

ተጠቃሚነታቸው ሙሉ በሙሉ አለመረጋገጡን መነሻ በማድረግ ከላይ የተጠቀሱትን

ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ከወቅታዊ የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ

አደረጃጀትና አስራር እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው

ሁለቱ መስሪያቤቶች በጋራ በመሆን የተሃድሶ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል አጭር

የጥናት ሪፖርት እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡ በዚህም መሰረት ከሰራተኛና መህበራዊ ጉዳይ

ሚኒስቴር ሁለት ባለሞያዎች እና ከ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አራት ባለሞያዎች በአንድ ላይ

በመሆን የአገልግሎት አሰጣጡን፣ አሰራሩንና አደረጃጀቱን እንዲሁም የሌሎች ሃገራትን

ተሞክሮዎች በመፈተሽ የተዘጋጀ ለበላይ አመራር ለውሳኔ የሚያግዝ አጭር ሪፖርት

እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
መግቢያ

በሀገራችን በህዝብ ቁጥር መጨመር፣ በድህነት፣ በአደጋ፣ በበሽታና በግጭቶች


ከእርጅናእንዲሁም ከፍ ካለው በሃገራችን ያለ ተጋላጭነት ጋር ተያይዞ የተሃድሶ ህክምና
የሚያስፈልጋቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር በየአመቱ እያሻቀበ ይገኛል። በዚህም
የተነሳ የተሃድሶ ህክምና አገልግሎትን በማዘመንና ሁሉን አቀፍ በማድረግ እየጨመረ ካለው
ፍላጎት ጋር ማጣጣም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

እ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም በዓለም የጤና ድርጅት እና በዓለም ባንክ የወጣው ዓለም አቀፍ የአካል

ጉዳተኞች ሪፖርት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ 15 ሚሊዮን የሚገመቱ ህጻናት፣ ወጣቶች እና

አዋቂዎች የአካል ጉዳተኞች እንደሚገኙ ተመላክቷል። ከነዚህም የአካል ጉዳተኞች መካከል

አብዛኛዎቹ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶች በማይገኝበት ገጠራማ ስፍራዎች የሚኖሩ ሲሆን

95 % በድህነት ውስጥ ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። ስለዚህ የተደራጀና ጥራቱን የጠበቀ

እንዲሁም በዘመኑ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የተሃድሶ አገልግሎትን ማስፋፋት አስፈላጊ ነዉ።

የተሃድሶ ህክምና ማለት የአንድ አካል ጉዳተኛን እንቅስቃሴ ወይም ተሳትፎ ሊቀንሱና

ሊወስኑ የሚችሉ ማንኛውም አይነት ተግዳሮቶችን በማስወገድና በተቻለ አቅም በመቀነስ

የአካል ጉዳተኛዉን የኑሮ ደረጃ ከፍ በማድረግ የተቻለዉን ያህል አካላዊ፣ አዕምሯዊና

ማህበራዊ ተሳትፎ እንዲኖረው የማስቻል አገልግሎት ነው።

በተጨማሪም መንግስት የአካል ጉዳተኞችን ሁሉን አቀፍ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት

ለማሳደግና ለማረጋገጥ ዓለም አቅፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምነት ኮንቬንን

በመቀበልና ሰኔ 4 ቀን 2002 ዓ.ም በተወካዮች ምክር በማጽደቅ የአገሪቱ ህግ አካል

እንዲሆንና ስራ ላይ እንዲውል በወሰነው መሰረት በኮንቬንሽኑ አንቅጽ 25 ለተዋዋይ

መንግስታት ከጤና ጋር ተያያዥነት ያለውን ተሃድሶ ጨምሮ አካል ጉዳተኞች ጾታ ተኮር

በሆኑ የጤና አግልግሎቶች የመጠቀም እድል ያላቸው መሆኑን የተደነገገ ሲሆን ይህም

የሚፈጸመው በአገራችን ባሉ የጤና ተቋማት መሆን ይኖርበታል፡፡


የተሃድሶ ህክምና አገልግሎትን በጤና ጥበቃ ሚንስቴር መዋቅር ውስጥ ማቀፍ
ያስፈለገበት መነሻዎች
የተሃድሶ ህክምና አገልግሎት ዓላማ አካል ጉዳተኞች በህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ

እንቅስቃሴ ውስጥ እንደ ሌሎች አቻዎቻቸው ሙሉ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማደረግ መሆኑ

ይታወቃል። በተጨማሪም አብዛኛውን ጊዜ የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍ አገልግሎት

ፍላጎት የሚኖረው ከከፍተኛ አደጋና ከባድ ቀዶ ህክምና በመቀጠል ስለሆነ ህክምናው

መሰጠት ያለበት የተለያዩ የማህበራዊና የህክምና ባለሙያዎች እንደ ቡድን ተቀናጅተው

ሲሆን አገልግሎቱ ላስፈለገው ተገልጋይ የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍ እንዲሁም ሌሎች

ተያያዥ የሆኑ የተሃድሶ ህክምና አገልግሎቶችን በጋራ ተመካክሮ በመወሰን መሆን

ይኖርበታል።

ይህንንም በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር በቂና የተሟላ የህክምና አገልግሎት፣ ማህበራዊ

ድጋፍ፣ የፊዚዮቴራፒ ህክምና፣ የተለያዩ የአካል ድጋፍና ሰው ሰራሽ አካላት አቅርቦት፣ የስነ

ልቦናና የምክክር አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 7.5 ሚሊዮን ሰዎች የተለያዩ የአካል ድጋፍ፣ ሰው

ሰራሽ አካልና ሌሎች ደጋፊ መሳሪያዎችን የሚፈልጉ ሲሆን ከነዚህም 5% ብቻ አገልግሎቱን

እያገኙ መሆናቸውን የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ቀደም ተብሎ እንደተጠቀሰውም

በተለያዩ ምክንያቶች ፍላጎቱ በየጊዜዉ እየጨመረ ስለሆነ የአካል ጉዳተኝነትን ለመከላከል

ፈጣንና ጊዜውን የጠበቀ ህክምና፣ የፊዚዮቴራፒና የተሃድሶ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት

በቂ የሰው ኃይልና አደረጃጀት ያስፈልጋል።


አሁን ባሉት የተሃድሶ ማዕከላት እየተሰጡ ያሉት የተሃድሶ ህክምና እና መልሶ ማቋቋም

አግልግሎት ከተገልጋዮች ፍላጎት ጋር ያልተጣጣመ ከመሆኑም በተጨማሪ ወደፊት

የአገልግሎት ጥራታቸውንና ተደራሽነታቸውን አስጠብቀው የመቀጠል እጣ ፈንታቸውም

የሚያስተማምን ሁኔታ ላይ አይደሉም።

በመሆኑም የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስቀጠል፣ ለማሻሻል፣ ተደራሽነቱን ለማስፋትና

ለማጎልበት፤ እንዲሁም በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት፤ አስፈላጊ ትብብሮችን

ለመዘርጋት፤ የረቀቀ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ አሰራርን ለማዘመን አዳዲስ አሰራሮችን

በመዘርጋት የአደረጃጀቱን ማሻሻልና እና የመዋቅር ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል።

ከዚህም በመነሳት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ክልሎች ያሉትን የተሃድሶ

ማዕከላት በጤና ጥበቃ ሚንስቴርና በተዋረድ ባሉ ተቋማት ስር እንዲተዳደሩ ማድረግ

አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህ ዕውን ሲሆንም የአካል ጉዳትን ለመከላከል፣ የተሻሻለ

የህክምናና የተሃድሶ አገልግሎት ለመስጠት የሚችሉ ምርታማና የተደራጁ የተሃድሶ ህክምና

አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በማቋቋም ተገቢዉን የአካል ድጋፍ፣ ሰው ሰራሽ አካልና

ሌሎች ደጋፊ መሳሪያዎችን ለተጠቃሚ ማቅረብ እንደሚቻል ታምኖበታል፡፡

ይህ ሁሉን አቀፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ዘይቤ አሁን ያለውን የአካል ጉዳተኝነት ጫና ብቻ

ሳይሆን የወደ ፊት ጫናንም ለማቅለል የሚረዳ ዕቅድ በመተግበር የአካል ጉዳትን

ለመከላከልና ከአደጋ በኋላ የተሟላ ጤንነትን ለመመለስ ይረዳል።

የተሃድሶ ማዕከላት በጤና ጥበቃ ሚንስቴር እና በተዋረድ ባሉ ተቋማት ስር እንዲተዳደሩ

ማድረግ ያለው ፋይዳ፡-


1. የአገልግሎት አሰጣጥ

ማዕከላቱ በጤና ተቋማት ስር እንዲተዳደሩ በማድረግ ለእያንዳንዱ አገልግሎት ፈላጊ ሁሉን


አቀፍ የተሃድሶ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ደረጃ ማዋቀር አገልግሎቱን ምሉዕ
የሚያደርገው ሲሆን የአገልግሎት ዘርፎቹ የሚከተሉት ይሆናሉ፦

ሀ. የህክምና አገልግሎት፦ ከድንገተኛ አደጋ በኋላ ቀልጣፋህክምና መስጠት፣ የተሃድሶ


ህክምና አስፈላጊነት ምርመራ ማድረግ፣ አስፈላጊዉን የአካል ድጋፍ፣ ሰው ሰራሽ አካልና
ሌሎች ደጋፊ መሳሪያዎችን ማዘዝና በአሰጣጥና ስልጠናቸው ዙሪያ ክትትልና ግምገማ
ማድረግ፡፡

ለ. የፊዚዮቴራፒ / የኦኩፔሽናል ቴራፒ፦ የአካል ተሃድሶ ህክምና ማለትም በፊዚዮቴራፒና


ኦኩፔሽናል ቴራፒ ባለሙያ የሚሰጥ ህክምና ሲሆን አካል ጉዳተኛ ወይም የአደጋ ተጎጂ
አካላዊ ብቃት ለአካል ድጋፍ ወይም ለሰው ሰራሽ አካል ብቁ እንዲሆን የሚያደርግ ህክምና
መስጠት፣ ከደጋፉ ጋር የማለማመድ ስልጠናና አካል ድጋፉን/ ሰው ሰራሽ አካሉን በመጠቀም
ጉዳቱን በመቋቋም አካል ጉዳተኛ ወደ ምርታማ ኑሮ እንዲመለስ ማድረግ፡፡

ሐ. ሰው ሰራሽ አካል፣ የአካል ድጋፍና የእንቅስቃሴ ደጋፊ መሳሪያዎችን ማምረትና


ማቅረብ

ይህንን አገልግሎት ለመስጠት ባለሙያዎች አስፈላጊ የህክምና ዕውቀት፣ የቴክኒክ ሙያ


ክህሎት ኖሮኣቸው በተቀናጀ አኳኋን የሰው ሰራሽ አካላት፣ አካል ድጋፍና የእንቅስቃሴ ደጋፊ
መሳሪያዎችን በበቂ ሁኔታ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በማምረት የተሟላ አገልግሎት መስጠት
ነው፡፡

2. ትምህርት፣ ስልጠና፣ ጥናትና ምርምር

ለጤና አገልግሎትና ለተሃድሶ ህክምና የሚያስፈልገው ሃብት ሀገራችንን ጨምሮ በአብዛኛው


ታዳጊ ሀገሮች በጣም ውስን ናቸው። በሀገራችን ውስጥ በተሃድሶ ህክምና የሰለጠን የሰው
ኃይል በበቂ ሁኔታ አለመኖርና ያሉትም በተሟላ ሁኔታ ስራው ላይ አለመሆናቸው
አገልግሎቱ የተሟላ እንዳይሆን አድርጎታል ተብሎ ይታሰባል።
የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ባሁኑ ጊዜ ያለውን አለም አቀፍ ትብብርና ድጋፍ በመጠቀም አሁን
ከሚሰጠዉ አገልግሎት በተጨማሪ የቴክኒክና ሙያ፣ የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ
ትምህርቶችን ወደሚሰጥ የትምህርትና ስልጠና ተቋም በማሳደግ አሁን በዘርፉ ያለውን
የሰለጠነ የሰዉ ኃይል እጥረት ለማሟላት ከታወቁ ሀገር በቀልና ዓለማቀፍ ባለሙያዎች ጋር
የመስራት አቅም እንዳለው ይታወቃል።

ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ባለሞያዎችን ለማፍራት ስለጠና መሰጠት ያለበት በዋናነት


በሚከተሉት ሶስት የሙያ ዘርፎች ሲሆኑ እነሱም፦

I. የቴራፒ ባለሙያዎች፦ በዚህ ዘርፍ የፊዚዮቴራፒ ሀኪሞችና ባለሙያዎች፣


የኦኩፔሽናል ቴራፒ ባላሙያዎች፣ የስፒችና ላንጉጅ ባለሙያዎችና ሌሎችን ለስራው
አስፈላጊ የሆኑትን የሚያጠቃልል ሲሆን፤
II. ኦርቶፔዲክ ቴክኖሎጂስትና ቴክኒሽያን፤
III. የኦርቶፔዲክና ሪኮንስትራክቲቭ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ናቸው፡፡

የአገልግሎቱን ሽፋን፣ ተደራሽነትና ጥራት ለማሻሻል በዘርፉ የሚካሄዱ ጥናቶችና


ምርምሮች ደግሞ ለሚንስቴር መስሪያቤቱና ለሚመለከታቸው አካላት በአካል ጉዳትን
መከላከልና ህክምናና ቅንጅት፣ ለጤና ሴክተር ትራንስፎርሜሽን፣ የመሰረተ ልማትን
ጨምሮ ሌሎች የዕድገት ዘርፎች ዕቅድ በግብዓትነት የሚያገለግል ይሆናል።
3. የሰው ሰራሽ አካል፤ የአካል ድጋፍና ደጋፊ መሳሪያዎችን ማምረትና አቅርቦት

የሰው ሰራሽ አካል፤ አካል ድጋፍና ደጋፊ መሳሪያዎችን ለአካል ጉዳተኖች አስፈላጊ ናችው፡፡ እንደአለም ጤና ድርጅት
ሪፖርት በጠቅላላው የሃገሪቱ 5 ፐርሰንት ሚሆነው ህዝብ የሰው ሰራሽ አካል፤ አካል ድጋፍና ደጋፊ መሳሪያዎችን
ይፈልጋል፡፡ይህም ፍላጎት የተሸከርካሪ አደጋዎችና የግጭቶች መበራከት ጋር ተያይዞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱ
ይታመናል፡፡

የአካል ጉዳተኝነትን ከመባባስ ለመከላከል ፤ ተገቢውን ህክምና ለመስጠት ብሎም ተተቂዎችን ጤናማና ምርታማ
ለማድረግ የተሃድሶ ህክምና ማዕከላት ከንድፍ እስከ ምርትና አቅርቦት በሚመለከቱት መሰረት መቃኘት አለባቸው

1. ጥራትና ምቾትን መሰረት በማድረግ አሁን የሚሰራበትን ልማዳዊ አሰራር ማዘመን መቻል፤
2. የአግልሎት ቅልጥፍናን ማዕከል በማድረግ የሚጠቅበትን ጫና ለመቋቋም የሚችል የግለሰቡን/ቧን
የሰውነት ሁኔታና የጉዳት አይነት ያገናዘበ ንድፍ መተግበር መቻል፤
3. ወጪን/ በሰው ሃይልና በ ግብኣት/ ለማመጣጠን የሚያስችሉ የአሰራር እና የአመራረት ሂደቶችን
በመተግበር የተገልጋዮችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡
4. በዘርፉ በሚካሔዱ ምርምር ውጤቶችንና በሌሎች ዘርፎች የተገኙ ልምዶችን /ተሞክሮዎችን/ ተቀብሎ
በማስረፅ በየጊዜው አሰራርንና አመራረትን እንዲሁም የምርት ውጤቶችን ማሻሻል

አደረጃጀትና መዋቅር

1. የተሃድሶ ህክምና ስራዎችን በማስተባበር የሚመራና የሚያስተዳደር የልዕቀት ማዕከል ያስፈልጋል፡፡


2. በየክልሎቹ የሚገኙ የተሃድሶ ማዕከላት ተጠናክረው ከሆስፒታሎች ጋር በመቀናጀት አገልግሎቱን እየሰጡ
ለዘርፉ የሚያስፈልገውን የመካከለኛ ባለሞያዎችን ስልጠና የሚሰጡ ይሆናሉ፡፡
3. የተሃድሶ ህክምና አገልግሎትን ለማስፋፋትና ተደራሽ ለማድረግ ደረጃ በደረጃ በሃገሪቱ ውስጥ ባሉ
አጠቃላይ ሆስፒታሎች ውስጥ የተሃድሶ ህክምና መስጫ ክንፍ ሆነው ራሳቸውን ችለው ይቋቋማሉ፡፡
ይህም አደረጃጀትና መዋቅር ውጤታማ እንዲሆን የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ዝርዝር
ጥናት ሊጠና ይገባዋል፡፡

You might also like