Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 8

እኛ ማን ነን፤ ከየትስ መጣን?

የእኛነት ስብዕና እንዴት ይገነባል?

3 ቱ የስብዕናችን መሰረቶች ኢድ፣ ኢጎና ሱፐር ኤጎ… ሲግመን

ፍሩድ እንደተነተነው

ውድ አንባቢያን ስለ ሰው ልጆች ስብዕና ወይም ባህሪ የተለያየ

አመለካከት ሊኖራችሁ ይችላል፡፡ የሰዎችም ዋነኛ የማንነት

መገለጫ ባህሪያቸው ወይም ስብዕናቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡

ራስን ማወቅ ማለት ማንነትን ማወቅ ማለት ነው፡፡ ማንነትን

ማወቅ ደግሞ ስብዕናንን ወይም ባህሪን ማየት ነው፡፡ በዚህ

ክፍልም ስለሰዎች ስብዕና አገነባብ አይነቶችና የባህሪ

ዝንፈቶች እናያለ፡፡ ከዚያም የራሳችንን ሰብዕና ተግባር በማወቅ

እንዴት እንደምናሻሽል እንረዳልን፡፡

ለመሆኑ ባህሪያችን እንዴትና ከምን ከምን የሚገነባ

ይመስልዎታል?

ባህሪን መቀየር ይቻላል? መቀየር ከተቻለስ እንዴት?

የአንዱ ባህሪ ከሌላው ባህሪ በምን የሚለይ ይመስሎታል?

እንሰሳትን ከሰው የሚለያቸው ባህሪይ ምን ምን ነው?

ማንነትን ባለማወቅ ብዙ እንጐዳለን፡፡ በዚህ የተነሳም

ማጣጣም ያለብንን ደስታ እናጣዋለን፡፡ ናፋቂውንና መልካሙን

ትዳር ብንፈልገውም እንደፈለግነው አንኖርበትም፡፡ ባልንጀሮች

ማፍራት እንፈልጋለን፤ እንደተፈለገው ግን አይሳካም፡፡ በኑሯችን

ስኬታማ ለመሆን እንተልማለን፤ ውጤቱ ግን ባመዛኙ ግቡን

አይመታም፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ እቅዱ ከወረቀት የማያልፍ

በመሆኑ የህልም እንጀራ ሆኖ ያርፈዋል፡፡ እናም “እነማን ነኝ?”

ለሚለው ጥያቄ መልስ ካላገኘንለት ለችግሮቻችን ችግር

ፈጣሪ መሆን እንጀምራለን፡፡


ሰዎች ምንም ለመሆን ምንም አያስፈልጋቸውም፡፡ ስኬታማ

ለመሆን፣ ደስተኛ ለመሆን፣ ሰዎች የደረሱበት ለመድረስ፣

በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን፣ ሰዎች የማያከብሩን ሰዋች

እንድንሆን፣ ጥሩ ባል ወይም ሚስት ለመሆን፣ ቱጃር ወይም

ባለፀጋ ለመሆን፣ ካስፈለገም ጨረቃ ላይ ለመውጣት፡፡ አንድ

ነገር ግን በእርግጠኝነት ያስፈልጋቸዋል፤ “እኔ ማን ነኝ?”

የሚለውን ጥያቄ መመለስ፡፡ ማጋነን አይደለም፤ የስነ-ልቦና

ሊቃውንት የሚስማሙበት ሃቅና ሃቅ ነው፡፡ እናማ ሁላችንም

“እኔ ማን ነኝ?” የሚለው ጥያቄ ከህሊናችን ሳናወጣ ራሳችንን

እንፈትሽበት፡፡ 3 ቱ የማንነታችን መሰረቶች ኢድ፣ ኢጎና ሱፐር -

ኢጎ ይባላሉ፡፡ እንደሚከተለው አንድ በአንድ እናያቸዋለን፡፡

የኢድ ባህሪያት

የመጀመሪያው (ዓመት ዕድሜ)

ይህ ስሜታዊ ሀይላችን ሲሆን አብሮንም የተወለደ ነው

በህፃንነታችንም ለህይወታችን መቀጠል የሚያስፈልገን

ነገሮች እንድናሟላ ይረዳናል

የኢድ ሀይል የሚመራው ደስታን በተመረኮዘ መልኩ ነው

ይህ የባህሪያችን ክፍል በየትኛውም ጊዜ ውስጥ ደስ

የሚለውን ነገር መከወን የሚፈለግ ነው፤

ኢድ የደስተኝነት ስሜቱን ለማሟላት ሲፈለግ ነባራዊውን

ሁኔታ አያገናዝብም

የኢድ ባህሪያችን ነባራዊውን እውነታ ማገናዘብና

የሌሎችን ፍላጎት የማክበር አይነት አመለካከት የለውም

ይህ ባህሪ የህፃናት መገለጫ ባህሪያቸው መሆኑ

ይታወቃል

ህፃናት ሲራቡ ወዲያው መብላት ይፈልጋሉ፣ ስለዚህም


ያለቅሳሉ

ሲበርዳቸው፣ ሳይመቻቸውና ሲቆረቁራቸው፣ ሲያማቸው፣

በጣም ሲሞቃቸው፣ ትኩረት ሲፈልጉ… የኢድ ባህሪያቸው

ፍላጎቱ እስኪሟላ ድረስ ይወተውታል፡፡

ኢድ ባህሪያቸው የራሱ ፍላጐት ይሳካለት እንጅ ለሊት ሆነ

ምሽት፣ ወላጆቻቸው እንቅልፍ ላይ ሆኑ አልሆኑ፣ እየተዝናኑ

ነው፣ እየበሉ ነው፣ እየታጠቡ ነው፣ እየሰሩ ነው፤ ብሎ

ማገናዝብና መዘግየት /ማሳለፍ/ የለም፡፡

የኢድ ባህሪያቸው አንዳች ነገር ከፈለገ ፈለገ ነው፤

ከዚህ ፍላጎት የሚበልጥ አይኖርም

እንደሚታወቀው የኢድ ፍላጎታችን በወላጆቻችን በኩል

እንደሚኖረው ተፈፃሚነት ሁለት አይነት ሂደት ሊኖረው

ይችላል፡፡

1. ቤተሰቦቻችን ፍላጎታችንን ከሚገባው በላይ የሚፈፅሙልን

ከሆነ፡- የበዛ አፈፃፀም ወይም ደግሞ “over

indulgence”

በጡት ማጥባት ሂደት (Oral Stage) የበዛ አፈፃፀም ካለ

በልጁ የወደፊት ባህሪ ላይ ብስለት አለመኖርን፣ ጥገኝነት፣

እንደ እናት ክብካቤ መፈለግን፣ የመታቀፍ /መጠጋጋት/

ፍላጎትን፣ ከፍተኛ የቅርርቦሽ ባህሪን፣ ሆደ ባሻነትን /ገራ

ገርነትን ሰው ማመንን፣ ግልፅነትን፣……. መልካምና ብሩህ

ተስፋ መመኘትን፣ ሩህሩህነትንና ለጋስነትን…. የዚያኑ ያህል

ከሌሎች መጠበቅን ያሰርፃል፡፡ እንዲሁም ለውሳኔ አሠጣጥ

የሌሎችን አስተያየት በእጅጉ መንተራስ

2. ቤተሰቦቻችን ፍላጎታችንን ከሚገባው በታች የሚፈፅሙልን

ከሆነ ደግሞ የመነጫነጭንና ተስፋ ቢሰነትን ወይም


ደግሞ “frustration” ውስጥ መገባትን ያስከትላል፡፡

ይህም ደግሞ በተራው ስሜትን በውስጡ አምቆ ለጊዜው

ግን ተመሳስሎ ማለፍን ይጋብዛል

ውስጣዊ ጭንቀትን፣ ጥላቻን፣ ለህይወት ጨለምተኛ

አመለካከትን፣ ሰዎችን በጥሩ መልኩ አለማየትን፣ ጨካኝነትን፣

ገለልተኝነትን፣ ከሰው ጋር ተቀራርቦ ለመግባባት መፍራትን/

ግልፅነት ማጣትን፣ ሰው ለማመንን፣ ሲበዛ ራስ ወዳድነትን፣

የመለየት ስጋትን፣ የፀረ-ፍቅር (ant seductive)

ባህሪያትን….

የኢጎ ባህሪ

(3-4 ዓመት ዕድሜ)

ይህ ባሀሪ በእውነታ ወይም ምክንያታዊነት ላይ ወይም

ከተጨባጩ ሁኔታ አንፃር ነገሮችን የሚመለከት ነው፡፡

ህፃኑ የበለጠ ከሌላው ዓለም ጋር መስተጋብሮች

መፍጠር ይጀምራል

ይህ ባህሪያችን መዳበር የሚጀምረው በተግብ የአኗኗር

እውነታዎችና መመሪያዎች ላይ ነው (Reality

Principles)

የኤጎ ባህሪ የሌሎች ሰዎችም ፍላጎትና አምሮት

እንዳላቸው የሚያምን የራስን ራስ ወዳድነት እና ስሜታዊ

ባህሪ ብቻ ማስተናገድ ጎጅ መሆኑ ማገናዘብ ይጀምራል፡፡

የኤጎ ባህሪም የሌሎችን ሰዎች ፍላጎት በባማከለ መልኩ

የግለሰቡን የኢድ /ስሜታዊ/ ፍላጎት ማርካት ላይ

ያተኩራል፡፡

ስንወለድ የአዕምሯዊ ሀይላች መሉ በሙሉ ኢድ ላይ ብቻ

የነበረ ሲሆን አሁን ግን የተወሰነው ወደ ኤጎ ይከፈላል፡፡


ስንወለድ ጀምሮ የሚኖረን ኢነርጅ ወጥነት ያለው

በመሆኑ (Closed System) ኢድ ላይ የነበረው መሉ

ኢነርጅ ወደ ኤጎ ሲከፈል ኢድ የተወሰነ ኢነርጅ ብቻ

ይቀረዋል፡፡

በመሆኑም ኢድ ቶሎ ለመርካት የሚያደርገውን አፈፃፀም

ወዲያውና ቶሎ ከመሆን ይልቅ መዘግየትን መልመድ

ይጀምራል፡፡

ኢድ በእርካታ መርህ (pleasure principle) ላይ

ሲመሰረት ኤጎ ደግሞ በአግባባዊ አፈፃፀም (Reality

print ciple) ላይ ይመሰረታል፡፡

ኤጎ የኢድን ፍላጎት የሚደመስስ ሳይሆን ለጊዜው ግን

እርካታው አንድ ዘገይ ይፈልጋል፡፡

የመጀመሪያ ስራው ምን እንደሚያስደስተው ማወቅ ሲሆን

ሁለተኛው ስራው ያንን ነገር ለማግኘት ስትራቴጂን

መፍጠር ነው፡፡

የኤጎ ባህሪ አርቆ ማስተዋልን፣ ችግር መፍትትን /መፍትሄ

መሻትን/፣ የማተግበር ሲሆን የበሳልነትና የአርቆ

ማስተወልነት መቀመጫ በመባልም ይጠራል፡፡

ስዕላዊ ማስረጃ፡- ፈረሰና ጋላቢው /ፈረሱ ኢድ ሲሆን

ጋላቢው ደግሞ በኤጎ ይመሰላል/

ስዕላዊ ትርጉም፡- ፈረሱ በስሜት፤ ጋላቢው ደግሞ በስሜት

ተቆጣጣሪው ኢጎ ይመስላል፡፡ ጋላቢው ፈረሱን

የሚቆጣጠረውና የሚመራው በልጓሙ አማካኝነት ነው፡፡ ነገር

ግን ጋላቢው ፈረሱን ተቀጣጥሮ መጋለብ ባይችል ግለሰቡ

የሚሄደው እንደ ፈረሱ ፍላጎት ሳይሆ አንደፈረሱ ፍላጎት ነውና

ለአደጋም ሊጋለጥ ይችላል፡፡ እኛም ስሜታችንን በሚገባ


ተቆጣጥረን ካልተጠቀምንበት ስሜታችን እንደፈለገው ሊነዳንና

ሊጎዳን ይችላል ማለት ነው፡፡

ሱፐር-ኢጎ (4 ኛ ዓመት)፡-

የማህበረሰቡ /የወላጆቹና የሌሎች ሰዎች/ መግባቢያና

መተዳዳሪያ የአኗኗር /የባህል/ ህግና ደንብን ፍፁማዊነትን

በተላበሰ መልኩ ማክበር ላይ ያተኩራል፡፡

ይህ ባህሪም አንድን ነገር ከማህበረሰቡ አተያይ አንፃር

የግለሰቡን ፍላጎት አግባብነት ያለው /የሌለው/ በማለት

የሚፈርጅ ነው፡፡

ሁለቱ የሱፐር-ኢጎ መገለጫዎች፤

1. በመጀመሪያ የማህበረሰቡን ባህል ፍፁማዊነትን /

ከተጨማባጭ እውነታ ይልቅ/ እንዲፈፀም ማድረግ እና

በዚህ የጨዋነት /ባህል አክቦሪነት/ የተነሳም ግለሰቡን

ማድነቅ፣ ማሞገስና መመረቅ ግን ያጠቃልላል፡፡

2. የፀፀት ስሜትን በማሳደር ግለሰቡ በሰዎች ዘንድ /በባህል

ወይም በሃይማኖቱ/ በኩል ተቀባይነት የሌለው /አስነዋሪ/

ነገሮች ሲፈፅም አዕምሯዊ ቅጣትን የሚያስከትል ነው

በመሆኑም፡-

በፀፀት ስሜት ይቀጣል /በተለይም ወሲባዊና ሃይለኝነትን/

ራስን ለሌላው ፍላጎት ማስገዛትን፤ ለሌሎች ሲሉ መኖርን፣

ራስን ለሌሎች ሲሉ መጉዳትን

ግለሰቡ ፍፁም መሆን አጥብቆ እንደፈለገው ያደርገዋል፡፡

ግለሰቡ ራሱም ሆኑ ሌሎች ፍፁም እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡

ስህተት መስራት /አለማወቅ/ ያሳፍረዋል፡፡

ስለ ራስ ደካማ ጎን /ስህተትን/ ማመንና ግልፅነት

ያሳፍረዋል፡፡
የሱፐር-ኢጐ ባህሪ “ህሊና ፈራጅ” (Conscience)

የሚል ስያሜ አለው፡፡ ብቻ ነበር፤

ከነባራዊው ህይወት አስገዳጅነት አንፃር አገናዛቢው ኢጎ

(Rational) መበልፀግ ጀመረ፤

ከማህበራዊ የአኗኗር ግዴታ አንፃፀር ሱፐር-ኢጎ (Moral)

ባህሪ መበልፀግ ጀመረ፤

የግለሰቡን ፍላጎታዊ እርካታ ለማስፈፀም የሚፈልገው

ኢድ፤ ፍላጎትን ከሌሎች ፍላጐት፣ ከራስ ጥቅምና ጉዳት

የአንፃር አመዛዝኖ ፍላጎቱን /በኤጎ በኩል/ ማስፈፀምና

ከማህበረሰቡ ማዕቀብ አንፃር /ሱፐር-ኢጎ/ ነገሮችን

ማየትንና መወሰንን ይጠይቃል፡፡

ኢጎ የኢድና የሱፐር-ኢጎን ፍላጎት ከግለሰቡ ሴፍቲ /

ደህንነትና የወደፊት ጥቅም/ አንፃር በመቃኘት

የማስታረቅና የመወሰን ስራን ይሰራል፡፡

ውስን የሆነው ሜንታል ኢነርጅ በሶስቱ ስብዕናዎች በኩል

ተከፋፍሎ ከግለሰቡ ጋር የሚበለፅግ ሲሆን አንዳንዴም

መጠኑ በሶስቱ ላይ ሊቀያየር ይችላል፡፡

ኤጎ የኢድን ፍላጎት ከተጨባጩ የህይወት እውነት፣

ከማህበረሰቡ ደንብና ባህል አንፃር አመዛዛኝ ውሳኔን

በሚያደረግበት ወይም የሀይል ሚዛኑ በአንዱ በኩል ካየለ

ወይም ሚዛናዊ ካልሆነ አዕምሯዊ ግጭት ይፈጠራል፡፡

አዕምሯዊ ሃይል = የኢድ ኃይል+ የኤጎ ኃይል+ የሱፐር ኢጎ

ኃይል

100% ኢነርጅ = X%+Y%+Z%

የኢድ ኢነርጅ እጅግ ከፍተኛ ከሆነ የግለሰቡ ህይወት በኤጎ

ከመመራት ይልቅ በስሜታዊነትና በራስ ወዳድት ላይና


የራስን ፍላጎትና ስሜትን ብቻ በማርካት ላይ ያተኩራል፡፡

የሱፐር ኢጎ ኢነርጅ በጣም ከፍተኛ ከሆነ የግለሰቡ

ህይወት በጠበቀ የጨዋነት ደንብ፣ በይሉኝታ፣ በሌሎች

ላይ የፈራጅነት ባህሪ፣ ከሌላው ዓለም ጋር ያለው

መስተጋብሮሽ የተገደበና የማይታጠፍ አመለካከትን

ይከተላል፡፡

ይሉኝታን በእጅጉ የሚከተል ይሆናል፡፡

አዕምሯዊ ግጭትም የአንደኛው የስብዕና ኃይል ፍላጎት

ከሌላው አንዱ ወይም ከሁለቱ ፍላጎቶች ጋር

አለመጣጣምን ተከትሎ ሲፈፀም ነው፡፡

ለመሆኑ የኢድ ባህሪያችንን እንዴት ወደ ኢጎ በመቀየር የሰከነ

ስነልቦናዊ ባህሪ ባለቤት መሆን እንችላለን?

You might also like