31 Bemitik Silemigebu Ekawoch

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 6

በምትክነት ስለሚገቡ Eቃዎች

የወጣ ዝርዝር የAፈፃፀም መመሪያ

የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን


ነሐሴ 2001 ዓ.ም.
Aዲስ Aበባ
በምትክነት ስለሚገቡ Eቃዎች የወጣ
ዝርዝር የAፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 31/2001

ለAገር ውስጥ ፍጆታ ተብሎ የገባ Eቃ ተመልሶ ከAገር የሚወጣበትንና በምትኩ


ተመሣሣይ Eቃ የሚገባበትን ስርዓት በመመሪያ መደንገግ በማስፈለጉ፣

በምትክነት በሚገባ Eቃ ላይ ሊወሰድ የሚገባውን የጥንቃቄ Eርምጃ፣ ስለፈቃድ


Aሰጣጡና ስለቁጥጥር Aፈፃፀም ወጥ በሆነ Aግባብ Aሠራሩን መግለጽ በማስፈለጉ፣

የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በAዋጅ ቁጥር 622/2001 Aንቀጽ 58(2)


በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን ዝርዝር የAፈፃፀም መመሪያ Aውጥቷል፡፡

1. Aጭር ርEስ
ይህ መመሪያ “በምትክነት ስለሚገቡ Eቃዎች የወጣ ዝርዝር የAፈፃፀም መመሪያ
ቁጥር 31/2001” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ
ለዚህ መመሪያ Aፈፃፀም ሲባል፡-
1) “Eቃ” ማለት ወደ Aገር ከገባ በኋላ፣ በስህተት፣ በብልሽት፣ ለታለመለት ዓላማ
ሊውል የማይችል በመሆኑ ወይም ያልተሟላ በመሆኑ ተመልሶ Eንዲወጣ
ጥያቄ የቀረበበትና በባለሥልጣኑ ፈቃድ የተሰጠው Eቃ ሲሆን በምትኩ የሚገባ
ተመሣሣይ Eቃን ይጨምራል፡፡
2) “Eቃን መልቀቅ” ማለት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያለ Eቃ ለተገለፀለት ዓላማ
Eንዲውል በባለስልጣኑ የሚለቀቅበት ስርዓት ነው፡፡
3) “በስህተት የመጣ Eቃ” ማለት ወደ Aገር የገባው Eቃ በዲክላራሲዮን ላይ
ከተመዘገበው Eቃ ጋር በመጠን፣ በጥራትና መሰል መመዘኛዎች የተለየ ሆኖ
የተገኘና Aስመጪው የማይፈልገውና መልሶ የሚልከው ነው፡፡

1
4) “ያልተሟላ Eቃ” ማለት ወደ Aገር የገባው Eቃ ለባለሥልጣኑ መግለጫ
ከቀረበበት Eቃ በቁጥር፣ በመጠን፣ በክብደት፣ Eና በመሳሰሉት ምክንያቶች
የጐደለ ወይም ያነሰ Eቃ ነው፡፡
5) “ተመሣሣይ Eቃ” ማለት ወደ Aገር Eንዲገባ ለባለሥልጣኑ መግለጫ ከቀረበበት
Eቃ ጋር በስያሜው፣ በAካላዊ ባህሪው፣ በጥራቱ፣ በተፈላጊነቱ፣ በንግድ
ምልክቱ Eና በስሪቱ Aንድ ዓይነት የሆነና በምትክነት የመጣ ወይም የሚመጣ
Eቃ ነው፡፡
6) “Aስመጪ” ማለት Eቃን ወደ Aገር ውስጥ የሚያስገባ ማንኛውም ሰው ነው፡፡
7) “ላኪ” ማለት Aገር ውስጥ ላለ Aስመጪ ከውጭ Aገር Eቃ የሚልክ ወይም
የሚያቀርብ ሰው ነው፡፡
8) “ዋራንቲ ሰርተፊኬት” ማለት ማንኛውም ላኪ ለEቃ ተቀባይ ወይም
ለAስመጪው ስለላከው Eቃ የሚሰጠው ዋስትና የተገለፀበት ሰነድ ነው፡፡
9) “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ነው፡፡
10)“ባለሥልጣን” ማለት የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ነው፡፡
11)“Aዋጅ” ማለት የጉምሩክ Aዋጅ ቁጥር 622/2001 ነው፡፡

3. የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ ለAገር ውስጥ ፍጆታ ሲባል ወደ Aገር የገባ Eቃ በጉምሩክ ቁጥጥር
ስር Eያለ ባለስልጣኑ በሚሰጠው ፈቃድ ከAገር ወጥቶ በምትኩ በሚገባ ተመሳሳይ
Eቃ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

4. ማመልከቻ ስለማቅረብ
ማንኛውም Aስመጪ ለAገር ውስጥ ፍጆታ ሲባል ያስገባው Eቃ፡-
ሀ/ ስህተት ያለበት፣
ለ/ የተበላሸ፣
ሐ/ ለታለመለት ዓላማ መዋል የማይችል፣
መ/ ያልተሟላ መሆኑን፣ ወይም
ሠ/ በሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶች፣

2
መኖራቸውን ከተረዳ Eቃው በባለስልጣኑ ከመለቀቁ በፊት ወደ መጣበት Aገር
Eንዲመለስና በምትኩ ተመሣሣይ Eቃ ለማስገባት Eንዲፈቀድለት Eቃው ለገባበት
የባለሥልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጽሑፍ ማመልከት ይኖርበታል፡፡

5. ከማመልከቻ ጋር ተያይዘው ስለሚቀርቡ ሰነዶች


Aስመጪው በዚህ መመሪያ Aንቀጽ 4 መሠረት ጥያቄ ሲያቀርብ የሚከተሉትን
ሰነዶች ከማመልከቻው ጋር ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
1) ወደ Aገር የገባው Eቃ የተመዘገበበትን የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ኮፒ፣
2) ቀደም ሲል ከዲክለራሲዮኑ ጋር በAባሪነት ለባለሥልጣኑ የቀረቡ ሰነዶች በመሉ
ኮፒ፣
3) ላኪው ስለ Eቃው የሰጠው ዋራንቲ ሰርተፊኬት ከዋናው ጋር የተመሣከረ
ኮፒ፣
4) Aስመጪው በዋራንቲ ሰርተፊኬቱ ላይ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ከAገር
Eንዲወጣ Eና በምትክ ተመሣሣይ Eቃ Eንዲላክለት ለላኪው ጥያቄ
ያቀረበበትን ኮፒ፣ Eና
5) ላኪው Eቃው Eንዲመለስለትና ተመሣሣይ Eቃ Eንደሚልክ የገለፀበትን ደብዳቤ
ከዋናው ጋር የተመሳከረ ኮፒ፡፡

6. ውሣኔ ስለመስጠት
የባለሥልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ Aስኪያጅ በዚህ መመሪያ መሠረት
የሚቀርብለትን ጥያቄ በመመርመር በAምስት የስራ ቀናት ውስጥ ውሣኔ ይሰጣል፡፡

7. ስለ ቀረጥና ታክስ ክፍያ


1) በዚህ መመሪያ መሠረት በምትክነት ለሚገባ Eቃ ቀረጥና ታክስ
Aይከፈልበትም፡፡
2) የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም በምትክነት የመጣው Eቃ
ቀደም ሲል በስህተት ገብቶ ከነበረው Eቃ ጋር በዋጋ፣ በመጠን Eና ከመሰል
መመዘኛዎች Aንፃር ከAምስት በመቶ (5%) ያልበለጠ ልዩነት ያለው ከሆነና

3
Aስቀድሞ ለEቃው ከተከፈለው ቀረጥና ታክስ በተጨማሪ የሚያስከፍል ሆኖ
ከተገኘ ተጨማሪ ቀረጥና ታክስ ይከፍላል፡፡
3) የተገኘው ልዩነት ከAምስት በመቶ (5%) የበለጠ Eንደሆነ በጉምሩክ ሥራ ላይ
የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በAስተዳደራዊ ውሣኔ ለመጨረስ በወጣው መመሪያ
መሠረት ይስተናገዳል፡፡

8. Aስቀድሞ የገባን Eቃ ስለመላክ


1. በዚህ መመሪያ ድንጋጌዎች መሠረት ወደ Aገር Eንዲገባ የተጠየቀው ምትክ
Eቃ በስህተት የመጣው Eቃ ተመልሶ ከAገር ለመውጣቱ ከIትዮጵያ
መውጫ ከሆነው የመጨረሻ ጣቢያ ከሚገኝ የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ማስረጃ
ካልቀረበ በቀር ወደ Aገር ሊገባ Aይችልም፡፡
2. በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ 1 መሠረት ከAገር Eንዲወጣ የሚላከው Eቃ
በAጃቢ መሆን ይኖርበታል፡፡

9. ተመልሶ ለሚላከው Eቃ ስለሚከፈል ክፍያ


ወደ Aገር የገባው Eቃ በዚህ መመሪያ Aንቀጽ 8 መሠረት ተመልሶ ከAገር
Eንዲወጣ ሲፈቀድ በAዋጁ Aንቀጽ 57 (1) መሠረት የቀረጥና ታክሱን 5 በመቶ
ይከፈልበታል፡፡

10. ክልከላ
1) በዚህ መመሪያ Aንቀጽ 7 (2) የተደነገገው Eንደተጠበቀ ሆኖ በምትክነት ወደ
Aገር የሚገባ Eቃ ወደ መጣበት Aገር Eነዲላክ ከተደረገው Eቃ ጋር ተመሳሳይ
ካልሆነ በቀር ወደ Aገር ማስገባትም ሆነ Eንዲገባ መፍቀድ የተከለከለ ነው፡፡
2) ባለሥልጣኑ በምትክነት የገባው Eቃ ተመሣሣይ ያልሆነ Eንደሆነ በAዋጁ
Aግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች መሠረት ተገቢውን Eርምጃ ይወስዳል፡፡

11. የተሻሩ መመሪያዎችና ሰርኩላሮች


ይህንን መመሪያ የሚቃረኑ መመሪያዎች፣ ሰርኩላሮች Eና የAሠራር ስርዓቶች
በሙሉ በዚህ መመሪያ ተሽረዋል፡፡

4
12. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተፈርሞ ከወጣበት Eለት ጀምሮ
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

Aዲስ Aበባ_________ ቀን 2001 ዓ.ም.

መላኩ ፈንታ
የIትዮጵያ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
ዋና ዳይሬክተር

You might also like