Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

መመሪያ፣ አዋጅና ደንብ ቢጣረስ የትኛው ተፈጻሚ እንደሚሆን ያውቃሉ?

*************************************

መመርያ፣ አዋጅና ደንብ ቢጣረስ የትኛው ተፈጻሚ ይሆናል? በአዋጅና ደንብ መሰረት የተፈጸመን የስራ ውል የሚጥስ
መመሪያ በውል ሰጪ ተግባራዊ ቢደረግ ተፈጻሚ ይሆናል ወይ? የሚል ጥያቄ በጠየቃችሁን መሰረት
ከሚመለከተውን የህግ ባለሙያ ማብራርያ ይዘንላችሁ ቀርበናል ተከታተሉን፡፡

በኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የፌዴራል ህጎች ተፈጻሚነት መከታተያ ዐቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ወርቁ ሐቤቤ እንደገለጹት
በኢትዮጵያ የህግ ስርዓት ውስጥ የህጎች ቅደም ተከተል እንዳለውና በቅደም ተከተሉም መሰረት የኢፌዴሪ ህገ-
መንግስት የአገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ እንደሆነ የገለጹልን ሲሆን ከዚያ ቀጥሎ በተዋረድ አዋጅ፣ ደንብ እና
መመርያ እንደ ቅደም ተከተላቸው የተቀመጡ የህግ ማዕቀፎች ናቸው ብለዋል፡፡ ህገ-መንግስት የመንግስትና የሀገሪቱ
የጋራ ቃልኪዳን ሰነድ ነው ያሉት ዐቃቤ ህጉ፡፡

አዋጅ ደግሞ ህገ-መንግስቱን ሳይጣረስ በህግ አውጪ አካል (በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) የሚወጣ ሲሆን ደንብ
በአንድ አዋጅ ውስጥ የተዘረዘሩ ተግባራትን ለማስፈጸም የሚረዳ በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 77(13) መሰረት
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወጣ ህግ ነው ብለዋል፡፡

ሌላው መመሪያ ሲሆን በአንድ ደንብ ውስጥ ለተዘረዘሩት ተግባራት ማስፈጸሚያ የሚሆን በህግ አስፈጻሚ አካላት
የሚወጣ የህግ አይነት እንደሆነ የገለጹት አቶ ወርቁ ደንብም ይሁን መመሪያ አስቻይ ህጉን በሚቃረን መልኩ የወጣ
እንደሆነ ግን ተፈጻሚነት የሚኖረው አስቻይ ህጉ ብቻ ይሆናል ብለዋል፡፡ ሌላው አንድ መመሪያ አዋጅና ደንብን
በሚጣረስ መልኩ ከወጣ ተፈጻሚ የሚሆነው አዋጅ እና ያንን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ይሆናል፡፡
ምክንያቱም መመሪያ የወጣው ደንብን ለማስፈጸም ስለሆነ ደንብን በሚጣረስ መልኩ የወጣ መመሪያ ዋጋ
እንደሌለውም ጭምር ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዋጅና ደንብ መሰረት የተፈጸመን የስራ ውል የሚጥስ መመሪያ በውል ሰጪ ተግባራዊ ቢደረግ
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 15 መሰረት አንድ የስራ ውል ሊሻሻል የሚችልባቸውን ምክንያቶች
አቶ ወረወቁ ሐቤቤ ሲገልጹ፡-

ሀ/ በህብረት ስምምነት

ለ/ አዋጅ መሰረት በሚወጡ የስራ ደንቦች እና

ሐ/ ሁለቱ ወገኖች በጽሁፍ በሚያደርጉት ስምምነት ብቻ ነው በማለት አስቀምጦታል በመሆኑም በአዋጅና ደንብ
መሰረት የተፈጸመን የስራ ውል የሚጥስ መመሪያ በውል ሰጪ ተግባራዊ ተደረገ ማለት መመሪያው ደንብን ወይንም
አስቻይ ህጉን በሚቃረን መልኩ ወጣ ማለት በመሆኑ መመሪያው የሚጸና አይሆንም ስለዚህ ውሉ የጸና ይሆናል
ማለት ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ውድ ተከታታዮቻችን ለዛሬ አበቃን ሌሎች መሰል ጥያቄዎች ካሏችሁ በአስተያየት መስቻ ሳጥን ውስጥ ብትልኩልን
መልሰን ለናንተው የምናደርስ መሆኑን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን፡፡

You might also like