Doc

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 17

መፍቀርያነ ግእዝ /ስለ ግእዝ እነማን አጠኑ/

መፍቀርያነ ግእዝ ስንል ስለ ግእዝ ያጠኑ፤


ጥናትና ምርምር ያደረጉ፤ ግእዝን የተማሩ የተመራመሩ
ያወቁ ያሳወቁ፤ የጻፉ ፣ ያጻፋ ለማለት ተፈልጎ ነው፡፡
የግእዝ ቋንቋን ከፊደላቱ ጀምሮ ቃላቱን
ሰዋሰውን /ዘርና ነባሩን፣ ግስና አገባቡን/፣ አንቀጹን
ቅኔውን እንዲሁም ሌሎች የግእዝ ዘርፎችን የውጭ
ሀገርና የሀገር ውስጥ ምሁራን የቋንቋ ሊቃውንት
ሌሎችም ከተሰማሩበትና ከዋና የሥራ መስካቸው
በመለየት ዘመናቸውን አሳልፈውበታል፤ ተራቅቀውበታልም፡፡
1 እነዚህንም ምሁራን በዘርፍ በዘርፍ ስንመለከታቸው
በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፤ የውጭ ሃገር ምሁራንና
የሃገር ውስጥ ሊቃውንትና ምሁራን በማለት፡፡
ሀ. ከውጭ ሀገር ምሁራን
፩. ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እና ከሱ ጋር ተከ ለው የመጡት
፫፻፲፰ቱ ሌዋውያን ካህናት/፱፻፹ ቅ.ል.ክ/፡ - እነዚህ
መምህራን ቀዳማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ከእስራኤል
ወደ ኢትዮጵያ ይዞ ሲመጣ አብረው የመጡ ሊቃውንት
ሲሆኑ የግእዝን ቋንቋ ተምረው ብሉይ ኪዳንን
ለመጀመሪያ ጊዜ ከእብራይስጥ ወደ ግእዝ የተረጎሙ
ናቸው፡፡ 2 እነዚህም ሊቃውንት መጻሕፍትን
በመተርጎማቸው በገድለ ቀውስጦስ ላይ ንጉሥ
ዘሩባቤል /ከባቢሎን ምርኮ በኋላ/ መጻሕፍተ ብሉያትን
ጽፈህ ላክልኝ ብሎ ለኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ልኮበታል፡፡
3
፪. አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን /በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን/ ፡-
አስቀድሞ መጠሪያ ስሙ ፍሬምናጦስ ነበር፡፡ ኋላ በሊቁ
ቅዱስ አትናቴዎስ ፓትርያርክ ዘእስክንድርያ አማካይነት
በ፫፻፴ ዓ.ም ‹‹ አባ ሰላማ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዘኵላ
ዘኢትዮጵያ ›› ተብሎ ተሹሞ መጣ፤ ኢትዮጵያውያኖችም
ከሳቴ ብርሃን የሚለውን ስም አወጡለት፤ ገና ጳጳስ
ሳይሆን ከወንድሙ ከአድስዮስ ጋር ወደ ኢትዮጵያ
እንደመጣ ከሊቀ ካህናቱ እንበረም /ኋላ ሕዝበ ቀድስ/
ዘንድ ሙራደ ቃል በምትባል ቦታ ግእዝን ተምሯል፡፡ 4
የሐዲስ ኪዳንን እና የሥርዐተ ቤተክርስቲያንን ጽሑፎች
እንደተረጎመም ይታመናል፡፡ 5
፫. ተሰዓቱ ቅዱሳን ፡- ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ቀድሞ
ፍሬምናጦስ በተማረባት ሙራደ ቃል በምታባል ቦታ
ግእዝን ተምረዋል፡፡ በዚህም መሠረትነት የግእዝን ቋንቋ
በመማር በማስተማር በመጻፍ በማጻፍ፣ መጻሕፍትን
በመተርጎምና በማስተርጎም ተሳትፈውበታል፡፡ 6
፬. ሊቀ ካህናት እንበረም (ኋላ ሕዝበ ቀድስ)// ፡- ከአብዩድ
እና ከሌሎች የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጋር በመሆን ከ፬፻፴፭-
፬፻፶ ዐ.ም ለ፲፭ ዓመታት ያህል በግእዝ ላይ ከፍተኛ
ጥናት አካሂዷል፤ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንን እና ወንድሙን
አድስዩስን ሙራደ ቃል በምትባል ቦታ ግእዝን
አስተምሯል፡፡
፭. አባ ካልኣይ ሰላማ (መተርጕም ሰላማ) /ከ፲፫፻፵፩-
፲፫፻፹/ ፡- ለአርባ ዓመታት ኢትዮጵያን በሊቀ ጵጵስና
የመራ ሲሆን ዜግነቱን ኢትዮጵያዊ ነው የሚሉም አሉ፡፡
ብዙ መጻሕፍትን ወደ ግእዝ ተርጕሟል ለአብነትም ሐዲስ
ኪዳንን ከዐረብኛ ወደ ግእዝ ተርጒሟል በተጨማሪም
ግብረ ሕማማትን፣ ገድለ አበከረዙን፣ ገድለ አዝቂር፣
ድርሳነ ገላውዴዎስ፣ ፊልክስዩስ፣ ገድለ ይስሐቅ፣ ገድለ
ዮስጦስ፣ ገድለ ኖብ/አባ ኖብ ድንግል/፣ ድርሳነ ያዕቆብ
ዘኢየሩሳሌም፣ ድርሳነ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ አስተርእዮቱ
ለእንባቆም፣ ለሃ ማርያም፣ መጸሐፈ ግንዘት ሲገኙበት
እርሱ እያስተባበረ ካጻፋቸው መጻሕፍትም መካከል
ቄርሎስና ፊሳልጎስ ይገኙበታል፡፡ 7
1. ትንሣኤ ግእዝ፣ ፳፻፪፣ ፪
2. መጽሐፈ ምሥጢር ፣ የልደት ምንባብ ፤ መጻሕፍተ
ሰሎሞን ወሢራክ መቅድም
3. አለቃ አስረስ የኔሰው፣ ትቤ አክሱም መኑ አንተ፣
፲፱፻፶፩፣ ፻፶፱ ፣ ገድለ ቀውስጦስ
4. አለቃ አስረስ የኔሰው፣ ፲፱፻፶፩፣ ፪፻፷፩
5. ሐመረ ጽድቅ፣ ፲፱፻፺፭፣ ፲፭
፮. እጨጌ እንባቆም /፲፬፻-፲፭፻፶፫/ : -በግእዝ ቋንቋ
መጻሕፍትን ጽፏል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትንም ወደ ግእዝ
መልሷል፡፡ ለአብነትም አንቀጸ አሚንን ራሱ ጽፏል፤
መጽሐፈ በርልአምን፥ መጽሐፈ ተልሚድን ከዐረብኛ ወደ
ግእዝ ተርጉሟል፤ አቡሻኽርን በመምሕር ሰሊክና
በእጨጌ አበሞ አማካይነት ተርጕሟል፡፡ 8
] የቋንቋውን ሥርዐተ ሰዋስው ለማጥናት እና የቋንቋውን የትመጣ
ለመመርመር የደከሙት ግን ከ፲፫ኛው ክፍለ ዘመን
ጀምሮ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህም ምሁራን
ተዋቂዎቹና ዋነኞቹ፡-
፯. ኢዮብ ሉዶልፍ :- ዜግነቱ ጀርመናዊ ሲሆን «
የመጀመሪያውን» የግእዝ ሰዋስው ያሳተመው በአባ
ጎርጎርዮስ ርዳታ እ.ኤ.አ በ፲፮፻፷፩ ዐ.ም ሲሆን በ፲፮፻፺
ዐ.ም ደግሞ የአማርኛ ሰዋስውን በአጭሩ ጽፎ አሳትሟል፡፡
በአንዳንዶች ዘንድ የመጀመሪያው የግእዝ ሰዋስው በሮም
አውሮፓ/ጳ/ ተሰራ ተብሎ የሚታመነው በ፲፮፻፴፰ ዐ.ም
የተሰራው የጂ . ወመር ሥራ ሲሆን ግእዝን በተመለከተ
መጻሕፍትን ለማሳተም ግን በ፲፭፻፲፫ዐ.ም የታተመው
የፑተን / የፑትከን/ መጽሐፍ ቀዳማዊ መሆኑ ይታወሳል፡፡
እንዲሁም በ፲፭፻፶፪ ዐ.ም የታተመው የግእዝ ሰዋስው
መልክዕ ገላጭ የማሪያነስ ቪቶሪ / ቪክቶሪየስ / ነው፡፡
ከፑተን እና
ከማሪያነስ ቪቶሪ ግን የዐረብኛ እና የእብራይስጥ ቋንቋ
እውቀቱን የተጠቀመበት የኢዮብ ሉዶልፍ ሥራ የተሻለ
ነበር፡፡
፰. ኦውገስት ዲልማን /፲፰፻፳፫-፲፰፻፺፬/ ፡- ዜግነቱ
ጀርመናዊ ሲሆን የግእዝ ሰዋስውን በ፲፰፻፶፭ ዐ.ም፤
የግእዝ መዝገበ ቃላትንም በ፲፰፻፶፭ ዐ.ም በላቲን/
ያለፉትን መዛግብት በመጠቀም ያዘጋጀው ሥራ በግእዝ
የተሰማሩ ሊቃውንትንና ደቀመዛሙርትን በመርዳት
የሚያኽለው የለም፡፡ ብዙዎችን ይጥቀም እንጂ ዲልማን
የግእዝን የአነባበብ ሥርዐት ለማስቀመጥ ያደረገው ጥረት
ስኬታማ ነበር ለማለት እንደማይቻል ኹሉ የግእዝን
ቀዳማይ አንቀጽ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለማስረዳት
የተጠቀመበት የንዑስ አንቀጽ ትርጕም ግን እንደ ድክመት
ሊታይ የሚችል ነው፡፡
ለጀማሪ የግእዝ ተማሪዎች ሊረዱ የሚችሉ መጻሕፍትን
ከሠሩት ከፕሪቶሪየስ እና ቼል ጀምሮ ኮንቲሮሲኒ ፣
ሊትማን፣ ሊኦኔል ቤንደር (ስለ ግእዝ ፊደላት)፣ ሚትወች
(ስለ ሥርዐተ ንባብ) እና የተሻለ የግእዝ መዝገበ ቃላት
እስካዘጋጀው ወልፍ ሌስሎው ድረስ በግእዝ ቋንቋ ላይ
የተደረጉ ምርምሮች አበረታች ነበሩ፡፡ 9
ለ. ከሀገር ውስጥ ሊቃውንትና ምሁራን
፩. ሊቁ ቅ/ያሬድ /፭፻፭- /፡- ለግእዝ ቋንቋ እድገት ከፍተኛ
አስተዋጽኦ ያደረገ አባት ነው፡፡ ካደረጋቸው አስተዋጽዖ
መካከልም ፭ቱን የዜማ መጻሕፍት /ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣
ምዕራፍ፣ መዋስዕት፣ ዝማሬ/ እና አንቀጸ ብርሃንን በግእዝ
ቋንቋ በ፫ት ዓይነት የዜማ ስልት ማለትም በግእዝ
በዕዝልና በአራራይ ደርሷል፡፡ እንደሁም በሰሜን ተራሮች
ከራስ ዳሽን አጠገብ በሚገኘው በደብረ ሃሌ ሉያ ተራራ
ላይ፣ … እንዲሁም በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች
መንፈሳዊ ትምህርትን በግእዝ አስተምሯል፡፡
፪. ሊቁ ቅ/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ) /
፲፫፻፶፯-፲፬፻፲፯/ ፡- ከ፵ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን
የጻፈና የወርቃማ ዘመን ወርቅ ደራሲ እስከመባል የደረሰ
ሲሆን መጻሕፍቶቹን ሁሉ በግእዝ ቋንቋ በመጻፍ ለግእዝ
ቋንቋ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ በተለይም ዕንዚራ
ስብሐት በተባለው መጽሐፉ በሁሉም የግእዝ ፊደላት
6. መ/ር ዘርአዳዊት አድሐና (የቃል ትምህርት)
7. ዶ/ር ሥርግው ኃብለ ሥላሴ ቅጽ ፊ ፵፱
8. ሐመረ ጽድቅ፣ ፲፱፻፺፭፣ ፲፭
9. ትንሣኤ ግእዝ፣፳፻፪፣ ፪
(በ፪፻፪ቱም ፊደላት) እመቤታችንን በግጥም አመስግኗታል፤
በግእዝ ሥነ ጽሑፍ በኩልም ብራን ካሌዎን ለተባለ
ካቶሊካዊ በመጽሐፈ ምሥጢር «በተጠየቅ ልጠይቅ»
አካሄድ ግሩም በሆነ የግእዝ ሥነ-ጽሑፍ አጻጻፍ
መልሶለታል፡፡
፫ . ከነገሥታት ወገንም አጼ አብርሃ ወአጽብሐ ግእዝን
ብሔራዊ ቋንቋ በማድረግ፤ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ /፲፬፻፳፮-
፲፬፻፷ ዐ.ም/፡- የተለያዩ መጻሕፍትን በግእዝ ቋንቋ
በመጻፍና ሌሎችም እንዲጽፉ፤ መጻሕፍትን እንዲተረጕሙ
በማድረግ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡
፬. አእጋረ ፀሐይ ተክለሃይማኖት ፡- የፊደላት ቅርጽን
በየገዳማቱ እየጻፈ እንዳይጠፉ ያደረገ ታላቅ አባት ነው፡፡
2
፭. እነ ዮሐንስ ገብላዊ /፲፬፻፳፯-፲፬፻፷ ዓ/ም/ : -ቅኔን
ከነቤት መምቻውና ከነምሥጢሩ አስፋፍቶ በማስተማር/
፮. ሠምራ አብ ፡ - ዘአምላኪየ፣ ዋይዜማ፣ ዘይእዜ፣ ግእዝና
እዝል ክብር ይእቲ እንዲሁም ግእዝና እዝል ዕጣን ሞገር
የተሰኙትን ቅኔያት በመድረስ፤
፯. ድድቅ ወልደማርያም ፡- በ፲፭፻፳፪ ዐ.ም ግራኝ መሐመድ
በኢትዮጵያ በተነሣ ጊዜ ቅኔን አገባብን እና ዕርባ ቅምርን
ይዞ ለትውልድ በማሰተላለፉ፤
፰. ድድቅ ፯ኛ ፡- የቅኔ ጉባኤን በማስፋፋት ሰባት ዓይነት
የአግባብ አዋጅና አገባብ፣ ሰባት ዓይነት የዕርባ ቅምር
አዋጅና ዕርባ ቅምር በማስተማር፤
፱. ሊቁ ክፍለ ዮሐንስ፡- በግእዝ ቅኔያት ላይ እጅግ
በመራቀቅ፣
፲. አለቃ ገብረ ሃና ፡- በግእዝ ቅኔያት ላይ እጅግ
በመራቀቅ፣ የተክሌን አቋቋም በግእዝ ቋንቋ በመድረስ፤
፲፩. መ/ር አክሊሉ ፡- የቅኔ ዜማ ልክን በደንብ መስመር
በማስያዝ
፲፪. ወላዴ ሊቃውንት መልአከ ምሕረት ጥበቡ ታዬ፡-
ከመምህራቸው ከመ/ር አክሊሉ የተማሩትን ለብዙ
ሊቃውንት በማስተማር፡፡ የቅኔውን ትምህርት ሲያስፋፉ
አብሮም የግእዝ ቋንቋ እንዲስፋፋ አስተዋጽዖ
አድረገዋል፡፡ 3
] ለግእዝ ሰዋሰው መጠበቅ፣ ለሥነ ጽሑፍ ዕድገቱ መዳበር
በዋናነት ተጠቀሽ የሚሆኑት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በቃልም
ይሁን በመጽሐፍ ለቋንቋው ሥርዐተ ሰዋሰው እና ዕሤታት
መጠበቅ በሀገር መዓዛዎቹ በሊቃውንቷ እና በጉባኤ ቤቶቿ
በተለይም በቅኔ ጉባኤ ቤት ውስጥ ዓይናማ/ሊቅ/ የሆኑ
መምህራን ያደረጉትና እያደረጉ ያሉት አስተዋጽኦ እና
ተጋድሎ ሕያውና ታላቅ ነው፡፡
ከዚህም መካከል ከላይ የጠቀስናቸው ሲገኙበት
በመጽሐፍ ዝግጅት ደግሞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉት
መካከል ዋና ዋናዎቹ፡-
ከቀደምቶቹ፡-
፩. አባ ተክለማርያም ወልደ ሰማሃራይ
8. ሐመረ ጽድቅ፣ ፲፱፻፺፭፣ ፲፭
9. ትንሣኤ ግእዝ፣፳፻፪፣ ፪
3. መ/ር ገ/ሕይወት ፈንታሁን፣ ሥርዐተ ትምህርተ ቅኔ
ዘግእዝ፣ ፳፻፩
፪. አባ ያዕቆብ ገብረ ኢየሱስ
፫. አለቃ ታየ
፬. አለቃ ክፍለ ጊዮርጊስ /፲፰፻፲፯-፲፱፻/ ፡- «መጽሐፈ
ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ» የሚለውን
መጽሐፍ ረቂቁን በማዘጋጀት፤
፭. አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ /፲፰፻፷፬-፲፱፻፴፮/ ፡-
«መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ»
የሚለውን መጽሐፍ ለመጽሐፍ ሕትመት እንዲሆን
በማዘጋጀት፣ በተጨማሪም መዝገበ ፊደል ሴማውያት፣
አበገደ ፊደልና፣ ፊደላዋርያ» በሚባሉ መጻሕፍቶቻቸው፤
፮. አለቃ ደስታ ተክለወልድ /፲፰፻፺፫-፲፱፻፸፯/ ፡-
«መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
የሚለውን መጽሐፍ በማሳተም»፣ እንዲሁም «ረብሐ ስም
ወአንቀጽ» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፯. አለቃ አስረስ የኔሰው፡- የግዕዝና የአቡሻኽር ሊቅ
ሲሆኑ «ትቤ አክሱም መኑ አንተ» እንዲሁም «የካም
መታሰቢያ» በሚባሉ መጽሐፍቶቻቸው፡፡
፰. ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ መስቀል ፡- «መጽሐፈ ቅኔ»
በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፱. መልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬ ፡- «ዝክረ ሊቃውንት
ክፍል ፩ እና ፪» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፲. መምህር ይኄይስ ወርቄ ፡- «ንባብ ወትርጓሜ ዘቅኔያት
አዕማደ ምሥጢራት» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
ከቅርቦቹ፡-
፩/ ዜና ማርቆስ እንዳለው፡- «የግዕዝ ቋንቋ መግቢያ፣
ጥንታዊ ግእዝ በዘመናዊ አቀራረብ፣ ቅኔ ለወጣቶች፣ እና
ግዕዝ ቋንቋ ላራተኛ ክፍል» በሚባሉ መጻሕፍቶቻቸው፡፡
፪. መ/ር ያሬድ ፈንታ ፡- «ፍኖተ ግእዝ» በሚል
መጽሐፋቸው
፫. መሪጌታ ልሳነ ወርቅ ገብረ ጊዮርጊስ ፡- «ጥንታዊ
ሥርዐተ ማኅሌት ዘአቡነ ያሬድ ሊቅ» በሚል
መጽሐፋቸው፡፡
፬. ዶ/ር ኢሳይያስ ዓለሜ እንግዳ ፡- «የግእዝና የዐረብኛ
ቃላት ተዛምዶ /ግንኙነት/» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፭. አፈወርቅ ዘውዴ ፡- «ሀገረ መጻሕፍት» በሚል
መጽሐፋቸው
፮. መ/ር ዘርአዳዊት አጽሐና፡ - «መርኆ ሰዋስው ዘልሳነ
ግእዝ» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፯. ሊቁ መልአከ አርያም ይትባረክ መርሻ ፡- «የግእዝ
አገባብና የቅኔ መንገዶች» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፰. ሊቃ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው ፡ - «መጽሐፈ ሰዋሰው
ወግስ መርኆ መጻሕፍት» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፱. ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፡- «ኢትዮጵያና
ኢትዮጵያዊነት /ክፍል ፩-፫/» እንዲሁም «ኢትዮጵያ
የዓለሙ መፋረጃ» በሚባሉ መጻሕፍቶቻቸው፡፡
፲. አባ ተክለ ሀይማኖት «ቀላል የግእዝ ቋንቋ መማሪያ»
በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፲፩. ክንፈ ርግብ አታለል
፲፪. ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን ፡- «ሕያው ልሳን»
እንዲሁም «ትንሣኤ» በሚባሉ መጻሕፍቶቻቸው
፲፫. መ/ር ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም ፡- «በቀላሉ የግእዝ
ቋንቋ መማሪያ» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፲፬. መ/ር ፍሰሐጽዮን ካሣ ፡- «መርኆ አዳም ወግዕዝ»
በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፲፭ . መ/ር ታምር ገብረመስቀል ፡ - «የግእዝ ቋንቋ ፈደላት
የተናጠል አገባብና ሥርዓተ አጻጻፍ መዝገበ ቃላት /፩ኛ/»
በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፲፮. ዶ/ር ለይኩን ብርሃኑ፡- «የግዕዝ መማሪያ» በሚል
መጽሐፋቸው
፲፯. መሪጌታ አፈወርቅ
፲፰. የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ሰንበት ት/ቤት ፡- «ፍሬ ግእዝ» በሚል መጽሐፋቸው፡፡
፲፱. መ/ር ደሴ ቀለብ /ማኅበረ ቅዱሳን/ ፡- «ትንሣኤ
ግእዝ» በሚል መጽሐፋቸው ይታወቃሉ፡፡
]ምንም እንኳን በመጽሐፍ መልኩ ባያሳትሙም በሽት መልክ /
Handout/ እያዘጋጁ በአሁኑ ጊዜ ለግእዝ እድገት
ከፍተኛ አስተዋጽዖ ካደረጉትና እያደረጉ ከሚገኙት
መካከል፡-
፩. መ/ር ረዘነ ኪዳነ ፡- የከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ
የግእዝ ቋንቋ መምህር፡፡
፪. ዲ/ን ዶ/ር ሲሳይ ደመቀ ፡- ግእዝን በጎንደር ለሚገኙ ፫ት
የግቢ ጉባኤያት፣ ለሰንበት ት/ቤቶች በማስተማር፤ ግእዝን
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንደ ጋራ የትምህርት መስክ /
common course/ በማስተማር ላይ ያሉ፡፡
፫. መ/ር እንባቆም፡- በደ/ብርሃን ለሚገኙ የግቢ
ጉባኤያት የግእዝ መምህር
፬. ሊቀ ጠበብት ይባቤ ፡- በፍኖተ ሰላም ከተማ በግላቸው
ኰሌጅ ውስጥ ግእዝን እንደ አንድ ቋንቋ እያስተማሩ
የሚገኙ፡፡
፭. ዲ/ን መንግሥቱ ሐጋዚ ፡- በማይጨው ለሚገኙ
ተማሪዎችና በአካባቢው ለሚገኙ ምዕመናን ግእዝን
በማስተማር ላይ ያለ፡፡
፮. የልሳነ ግእዝ ወዳጆች ማኅበር ፡- በአ/አበባ ለሚገኘው
የማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማዕከል፣ በሐመር
መጽሔት እና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች እንዲሁም
በአንዳንድ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ግእዝን በማስተማር
ላይ ያሉ፡፡
፯. የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኰሌጅ የግእዝ ዲፕሎማ
ተማሪዎች፡- በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ግእዝን በቋንቋ
ደረጃ ለብቻው በዲፕሎማ እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች
ሲሆኑ ለወደፊቱ ግእዝን በማሳደግ ተስፋ የተጠላባቸውም
ናቸው፡፡
፰. ፕ/ር ባዬ ይማም፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ
ጊዜ የቀንየሥነ ልሳን ጥናት /Philology/ እንዲጀመር
ያደረጉ፡፡
፱. አኵስም፣ ጎንደርና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፡- ግእዝ ቋንቋ
እንደ አንድ የትምህርት መስክ/Department/ በመክፈት
ትምህርቱ እንዲስፋፋ እያደረጉ ያሉ ናቸው፡፡
ግእዝ የማን ቋንቋ ነው /አይቴ ብሔሩ ለግእዝ?/
ግእዝ ቋንቋ ኢትዮጵያዊ ቋንቋችን ነው፡፡ በራሱ
ዜጎች አማካኝነት በራሱ ፊደል የተቀመረ ኢትዮጵያዊ
ቋንቋ ነው፡፡ ግእዝ የማን ቋንቋ/የማን ወገን/ ነው ብለን
ስንጠይቅ በስድስት ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
እነርሱም፡-
፩. የእግዚአብሔር፣ የመላእክትና የአዳም ቋንቋ ነው
የሚሉ
ባጠቃላይ እነዚህ ሊቃውንት ከማስረጃነት ከማያቀርቡት
መካከል፡-
W የእግዚአብሔር ቋንቋ ለማለታቸው ንግበር ሰብዓ በአርያነ
ወበአምሳሊነ ዘፍ.፩ በሚለው ላይ ንግበር የሚለው ቃል
የግእዝ ግስ ርባታ ሣልሳይ አንቀጽ መሆኑ፤
W የመላእክት ቋንቋ ለማለታቸው «ንቁም በባህላዌነ እስከ
ንረክቦ ለአምላክነ» በሚለው ላይ ንቁም የሚለው ቃል
የግእዝ ግስ ርባታ ሣልሳይ አንቀጽ መሆኑ፤
W የአዳም ቋንቋ ለማለታቸውም አዳም ከተሰጠው ኃብታት
መካከል አንዱ የግእዝ ቋንቋ ነው በግእዝ ቋንቋም
ይጸልይበት ነበር፡፡ አዳም ጥፋትን ባጠፋ ጊዜ ግን
ከተነሳው ጸጋ መካከል አንዱ የግእዝ ቋንቋን ነው በአቤል
ፋንታ ለተወለደው ለሴት እግዚአብሔር ፊደላትን ገለጸለት
የሴት ልጅ ሔኖስም በቃሉ አጠናቸው ሆኖም ግን የአዳም
ልጆች ጸጋ ዕውቀትን ስለተነሣቸው ረሱት፡፡ ዳግመኛም
ለአዳም ፯ኛ ትውልድ ለሔኖክ እግዚአብሔር በጸፍጸፈ
ሰማይ/በሰማይ ጣርያ/ ፊደላትን አሳየው ሔኖክም ብልህ
ነበርና በሸክላ ጻፈው፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልም
በቀደምትነት የመጀመሪያ የሆነውን መጽሐፈ ሔኖክን
በ፬ሺህ፲፬ ቅ.ል.ክ ጻፈበት ይኸም እስከ ቅድመ ስናዖር
ድረስ ቆየ፡፡ ከዚህም በኋላ የዓለም ቋንቋ ለ፸ዓይነት
ቋንቋዎች ተደበላለቀ በኖኅ ጊዜም ኖኅ ለ፫ቱ ልጆቹ
ለሴም ለካምና ለያፌት ቦታንና ቋንቋን አወረሰ፡፡
Ä ይህንንም ሐሳብ ከሚደግፉት ምሁራን መካከል፡-
R አለቃ አስረስ የኔሰው «የኢትዮጵያ ፊደሎች የአዳምና
የመላእክት መነጋገሪያ ነበሩ» ብለዋል፡፡
R አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ «ግእዝ የመጀመሪያ የሰው ልጀ
ቋንቋ ነው የተሰጠውም ከእግዘአብሔር ነው፡» ይላሉ፡፡
ለዚህም፡-
‹‹ከንጉሡም ከእግዜር ከባለቤቷ
ስለተሰጠች እቴጌነቷ
እንዲህ ብታይዋት ደሃ መስላችሁ
ባለጸጋ ናት ግእዝ ቋንቋችሁ፡፡›› ብለዋል፡፡
R ክንፈ ርግብ አታለል «ግእዝ ማለት አንደኛ መጀመሪያ ማለት
ነው» በማለት ከቃሉ ፍቺ በመነሳት የቋንቋውን አዳማዊነት
አስረግጠዋል፡፡ ለዚህም ሁለት የውጭ ሀገር ምሁራንን
ጠቅሰዋል፡፡ «... ይህን መሠረት በማድረግ ሲዲ
ጳውሎስና መአልም ዮሐንስ የተባሉ ሁለት ጀርመናውያን
ሊቃውንት ልሳነ ግእዝ የአዳም ቋንቋ ነው ብለውታል፡፡»
ይላሉ፡፡
R ዶ/ር ኢሳይያስ ዓለሜ እንግዳዊ ቀደም ሲል «ግእዝ
ከእግዚአብሔር ስለመውረዱ አብደልመጅድ አቢድን
የተባለ ዐረብ በካይሮ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋ
መምህር በዳነአል- ሐበሻ -ውእል- ዐረብ፤ በሐበሻና
በዐረቦች መካከል በሚል መጽሐፉ ግእዝ ከሰማይ የወረደ
ቋንቋ በማለት ጽፏል» ብለው ገልጸዋል፡፡
፪. የካም ቋንቋ የሚሉ፡-
ግእዝን የደቡብ ሴማዊ ልሳን ሳይሆን በዐረብ
ምድር የመጀመሪያዎቹ የአፍሪካውያን ወይም
የኩሻውያን /የካም/ ቋንቋ ነው የሚሉ ናቸው ከነዚህም
መካከል፡-
® ኤቢ ዶጐፖልስኪ /A.B Dogopolsky/ እና ኢጎር
ዲያክኖፍት /Igor Diaknoft/ - ከሶቭየት ምሁራን፡፡
® ቸክ አንታ ዲዮፕ /Cheek Anta Diop /
® አቤንጃ
® ሺናይዳር
® አለቃ አስረስ የኔሰው
® መሪጌታ ልሳነ ወርቅ ገብረ ጊዮርጊስ
® ኃይሉ ኃብቱ
® አየለ በከሪ ወዘተ ናቸው
በተለይም ከላይ ካየናቸው ምሁራን መካከል
የግእዝና የአቡሻክር ሊቅ የሆኑት አለቃ አስረስ የኔሰው
«ግዕዝን ካም ወደ አፍሪካ ይዞት የመጣ ኖኅ በሕይወቱ
ዓለምን ለ፫ት ልጆቹ ለሴም ለካም ለያፌት ባካፈለ ጊዜ
ስለ ዓለም መከፋፈል ነው፡፡» ኩፋ.፱፣ ኦ.ዘፍ.፪ ሲሉ፤
መሪጌታ ልሳነወርቅም «እኛ የኢትዮጵያውያን ሕዝብ
ከግዕዝ ቋንቋችን በላይ እሊህ ሕጸጽ የሌለባቸው የተሟሉ
፳፮ ፊደሎችን
የወረስናቸው ከአባታችን ካም በ፪ሺሕ ፯፻፯ ዓመተ ዓለም
ሲሆን፤ የሴም ዘር የሆኑ ሕዝብ የወረሱት አበገደ ብሎ
እስከ ተ ያሉትን ፳፪ቱን ፊደሎች ስለሆነ ከዚያ ዘሩን
እያበዙ መጻሕፍታቸውን ይጽፋሉ፡፡» ብለዋል፡፡
፫. የሴም ቋንቋ የሚሉ
£ ሲዲ ጳውሎስ
£ ኤ መርቶኒን እና ሊኦኔል ቤንደር ከኢትዮጵያ የወጣ
ቋንቋ ነው የሚል አቋምም አላቸው፡፡
£ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
£ ፕ/ሮ ጌታቸው ኃይሌ፡- የግእዝ ተናጋሪዎች እነማን
እንደነበሩ ግን አላውቅም የሚሉ ከላይ ካየናቸውም
መካከል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የግእዝን፣ የሱርስትን፣
የዐረብን እና የዕብራይስጥ ቋንቋን ሴማዊ የሚሉ ናቸው፡፡
] በአንጻሩ ካም ወይም ሴም የሚለውን ቃል
ከቋንቋ ጋር በማገናኘት የተጠቀመበት የጀርመን
መልእክተኛ ጆህን ሉድዊግስፍ /Johunn Lvowiskapf/
ነው፡፡ ካርል ፍሬድሪክ ሌፐሲየስ /Karl Friedrich
Lepsius/ ደግሞ ካምም ሴማዊም አይደለም የሚለው
ከግብጻውያን ቋንቋ ጥናት በመነሣት ከቋንቋ ሰዋሰው
ውስጥ የጾታ ሥርዓትን በማየት ነው፡፡
፬. የግእዝ ቋንቋ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር በማነጻጸር
አስተያየት ከሰጡት መካከል
ደራሲ ማሞ ውድነህ ቋንቋውን ጥንታውያት ከሆኑት የግሪክና
የላቲን ቋንቋዎች ጋር በማነጻጸር እንዲህ ይላሉ፡፡
ጥንታዊው የግእዝ ቋንቋ እጅግ የተጣራ በመሆኑ
ለግሪክና ለላቲን ቋንቋ ተወዳዳሪ ለመሆን ይቃጣዋል፡፡
ይበሉ አንጂ በቀሪው ጽሑፋቸው ስለ ቋንቋው ጥንታዊነት
በሰፊው አትተዋል፡፡
አባ ተከስተ ገ/መድኅን የግእዝን ቋንቋ ከሀገር ውስጥ
ቋንቋዎች ጋር በማነጻጸር በግንባር ቀደምትነት በማሰለፍ
እንዲህ ይላሉ «አማርኛም ሆነ ትግርኛ እንዲሁም ሌሎች
የአሁኑ ቋንቋዎቻችን ረጅም እድሜ እንደሌላቸው ግልጽ
ነው፡፡ ... ኢትዮጵያ ከሠለጠኑ የድሮ ሕዝብ ውስጥ
የሚያስቁጥራት አንደኛው ሀብቷ ... ጥንታዊው ቋንቋዋ
ግእዝ ነው» ይላሉ፡፡
፭. ከተናጋሪዎች ሕዝቦች/ጎሳዎች/ ጋር በማያያዝ
አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል፡-
n አባ ገ/ኢየሱስ ኃይሉ ግእዝ ግእዛውያን አግአዝያን ወደ
ብሔረ አግአዚ የተሻገሩበት የመጡበትም ሐበሻት የተባሉ
አንድ የዓረብ ዘር ሰሐርታን ከተባለ ከባሕር ጠረፍ የሚገኝ
ከየመን አውራጃ ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው
ነበር፡፡ ...ከተባለው ዘመን ፊት ግእዝ ወደ ኢትዮጵያ ደረሰ
ለአገሩ የሚሆን ቋንቋ ይዘውም ገቡ፡፡ መምጣታቸው ሳባ
ከሚባል ደቡባዊ ዐረብ አውራጃ ነው የመጡትንም ቋንቋ
እንደ ባሕርያዊ አካሄድ ከአገሩ ቋንቋ ጋር በትንሽ
ተስማምቶ ተቀላቅሎ ግእዝን ወለደ፡፡
፮. አፍሮ እስያዊ ነው የሚሉ
በአሁኑ ሰዓት ያለው የሥነ ልሳን ጥናት /
Philology/ ከሐረገ ዘር(የካም፣ የሴም) ከማለት ይልቅ
መልክዐ ምድራዊ በመኾኑ የካም የሴም ቋንቋ መባሉ
ቀርቶ በአጠቃላይ በአፍሮ እስያነት ውስጥ ነው መድቦ
የሚየየው ይህንንም ሐሳብ ከሚደግፉት መካከል፡-
t ፕ/ር ባየ ይማም
t ዮሴፍ ግሪን በርግ /Joseph Green berg/
t መ/ር ደሴ ቀለብ
]]] ማጠቃለያ ፡- የዚህ ጽሑፍ አዘጋጆችም ባጭሩ ግእዝ ኢትዮጵያዊው ቋንቋችን
ጥንታዊ ነው፡፡በራሱ ዜጎች አማካይኝነት በራሱ ፊደል
የተቀመረም ነው፡፡ አፍሪካዊ የኢትዮጵያ ልሳንም ነው
ይላሉ፡፡

ያት ወምድር ማለት ነው፡፡


ጉ ማለት ለአስካለ ሕይወት ሐረጉ ማለት ነው፡፡
ጊ ማለት ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጋ ማለት ጋሜል ግሩም እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጌ ማለት ጽጌ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ግ ማለት ሐጋጌ ሕግ ማለት ነው፡፡
ጐ ማለት ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ማለት ነው፡፡
ጕ ማለት ስንጓጕ እምኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጒ ማለት ጒንደ ሐረገወይን ወልድ ማለት ነው፡፡
ጓ ማለት ዕጓለ እመሕያው ማለት ነው፡፡
ጔ ማለት ዝንጓጔ መስቀል ማለት ነው፡፡
ጕ ማለት ስንጓጕ እምኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጠ ማለት ጠቢብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጡ ማለት ውስጡ ለሰብእ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጢ ማለት መያጢሆሙ ለኃጥአን ማለት ነው፡፡
ጣ ማለት የውጣ እንተ አሐቲ ሕርመታ ማለትነው፡፡
ጤ ማለት ጤት ጠቢብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጥ ማለት ስሉጥ ወርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጦ ማለት ሦጦ ለመንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ ማለት ነው፡፡
ጰ ማለት ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጥድቅ ማለት ነው፡፡
ጱ ማለት ኮጱ መዓዛ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ጲ ማለት ሠራጲሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ጳ ማለት ጳጳስ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ጴ ማለት አክራጴ ኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጵ ማለት ጵርስፎራ ማለት ነው፡፡
ጶ ማለት ጶሊስ ማለት ነው፡፡
ጸ ማለት ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፀ ማለት ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጹ ማለት ገጹ ለአብ ማለት ነው፡፡
ፁ ማለት ዮም ሠረፁ ጽጌ በረከት ማለት ነው፡፡
ጺ ማለት ሐዋጺ ነፍሰ ትሑታን ማለት ነው፡፡
ፂ ማለት መላፂ ዘክልኤ አፉሁ ማለት ነው፡፡
ጻ ማለት ጻዴ ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፃ ማለት ፋፃ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ጼ ማለት አዕቃጼ ሰኮና ማለት ነው፡፡
ፄ ማለት ሕፄሁ ለዳዊት ማለት ነው፡፡
ጽ ማለት ጽንሁ ተስፋሁ ማለት ነው፡፡
ፅ ማለት ዕፅ አብርሃም ዘሰፀረ ለምስዋዕ ማለት ነው፡፡
ጾ ማለት ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ ማለትነው፡፡
ፆ ማለት ማዕፆ አፉሆሙ ለጻድቃን ማለት ነው፡፡
ፈ ማለት ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ፉ ማለት ምዕራፉ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ፊ ማለት ፊደለ ወንጌል ዘአባ ኀነፊ ማለት ነው፡፡
ፋ ማለት አልፋ ወኦ ማለት ነው፡፡
ፌ ማለት ኀዳፌ ነፍሳት ማለት ነው፡፡
ፍ ማለት ፍኖት ለኀበ አቡሁ ማለት ነው፡፡
ፎ ማለት ፎራ ኅብስተ ቍርባን ማለት ነው፡፡
ፐ ማለት ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፑ ማለት ኖፑ አስካለ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ፒ ማለት ፒላሳሁ ማለት ነው፡፡
ፓ ማለት ፓንዋማንጦን ማለት ነው፡፡
ፔ ማለት ፔ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፕ ማለት ሮፕ ጽኑዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፖ ማለት በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ
ወበደኃሪ የኀልፎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
የፊደላትን ትርጉም በአግባቡ ከተረዳን በዝተዋል ይቀነሱ
የሚሉትን ሰዎች ማስረዳት ከመቻላችንም በላይ ፊደላትን
ያለቦታቸው ከመጠቀም እንቆጠባለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር!
*
ወራዙት አፍቀሩ ልሳነ ግእዝ ይትማህሩ
ወጣቶች የግእዝን ቋንቈ ይማሩ ዘንድ ወደዱ።
*
ምንጭ: መምህር ሄኖክ ፈንቴ
የብሉያትና የቅኔ መምህር

ግእዝ ሕያው ልሳን


እነሆ ትርጉማቸው ...
ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡
ሐ ማለት ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ማለት ነው፡፡
ኀ ማለት ኀብአ ርእሶ ማለት ነው፡፡
ሁ ማለት ኪያሁ ተወከሉ ማለት ነው፡፡
ሑ ማለት ሰብሑ ለሥመ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኁ ማለት እኁዝ አቅርንቲሁ ማለት ነው፡፡
ሂ ማለት አስተይዎ ብሂዐ ማለት ነው፡፡
ሒ ማለት መንጽሒ ማለት ነው፡፡
ኂ ማለት ዘልማዱ ኂሩት ማለት ነው፡፡
ሃ ማለት ሃሌ ሉያ ማለት ነው፡፡
ሓ ማለት መፍቀሬ ንስሓ ማለት ነው፡፡
ኃ ማለት ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሄ ማለት በኵለሄ ሀሎ ማለት ነው፡፡
ሔ ማለት ሔት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኄ ማለት ኄር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ህ ማለት ህልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሕ ማለት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኅ ማለት ኅብስት ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ሆ ማለት ኦሆ ይቤ ወመጽአ ማለት ነው፡፡
ሖ ማለት ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኆ ማለት ኆኅተ ገነት ወልድ ማለት ነው፡፡
ኈ ማለት ኈለቈ አዕፅምትየ ማለት ነው፡፡
ኋ ማለት ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ኌ ማለት ይኌልቍ አሥዕርተ ማለት ነው፡፡
ኊ ማለት በኊበኊ ሥጋ አዳም ማለት ነው፡፡
ኍ ማለት ዑጽፍት ወኍብርት ማለት ነው፡፡
ለ ማለት ለብሰ ሥጋ ዚአነ ማለት ነው፡፡
ሉ ማለት ሣህሉ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሊ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ላ ማለት ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሌ ማለት መቅለሌ ዕጹብ ማለት ነው፡፡
ል ማለት መስቀል ዘወልደ አብ ማለት ነው፡፡
ሎ ማለት ዘሀሎ እምቅድም ማለት ነው፡፡
መ ማለት መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሙ ማለት ሙፃአ ሕግ ማለት ነው፡፡
ሚ ማለት ዓለመ ኀታሚ ማለት ነው፡፡
ማ ማለት ፌማ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሜ ማለት ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ም ማለት አምላከ ሰላም ማለት ነው፡፡
ሞ ማለት ሞተ በሥጋ ማለት ነው፡፡
ሰ ማለት ሰብአ ኮነ ከማነ ማለት ነው፡፡
ሠ ማለት ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ማለት ነው፡፡
ሱ ማለት ፋሲልያሱ ማለት ነው፡፡
ሡ ማለት መንበረ ንግሡ ማለት ነው፡፡
ሲ ማለት ዘይሴሲ ለኲሉ ዘሥጋ ማለት ነው፡፡
ሢ ማለት ሢመተ መላእክት ማለት ነው፡፡
ሳ ማለት ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሣ ማለት ሣህል ወርትዕ ማለት ነው፡፡
ሴ ማለት ለባሴ ሥጋ ማለት ነው፡፡
ሤ ማለት ሤሞሙ ለካህናት ማለት ነው፡፡
ስ ማለት ልብስ ለዕሩቃን ማለት ነው፡፡
ሥ ማለት ንጉሥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሶ ማለት መርሶ ለአሕማር ማለት ነው፡፡
ሦ ማለት አንገሦ ለአዳም ማለት ነው፡፡
ረ ማለት ረግዓ ሰማይ ወምድር በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ሩ ማለት በኵሩ ለአብ ማለት ነው፡፡
ሪ ማለት ዘይሰሪ አበሳ ማለት ነው፡፡
ራ ማለት ጌራ መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ሬ ማለት ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ር ማለት ርግብ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሮ ማለት ፈጠሮ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቀ ማለት ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ወውእቱ ቃል ኀበ
እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቁ ማለት ጽድቁ ለኃጥእ ማለት ነው፡፡
ቂ ማለት ፈራቂሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቃ ማለት ቃልየ አጽምዕ ማለት ነው፡፡
ቄ ማለት ሰዋቄ ኃጥአን ማለት ነው፡፡
ቅ ማለት ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቆ ማለት ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቈ ማለት ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ማለት ነው፡፡
ቊ ማለት ቊርባነ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ቍ ማለት ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ ማለት ነው፡፡
ቌ ማለት ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ ማለት
ነው፡፡
በ ማለት በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ማለት ነው፡፡
ቡ ማለት ጥበቡ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቢ ማለት ረቢ ነአምን ብከ ማለት ነው፡፡
ባ ማለት ባዕድ እምአምአማልክተ ሐሰት ማለት ነው፡፡
ቤ ማለት ቤት ባዕል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ብ ማለት ብርሃነ ቅዱሳን ፍጹማን ማለት ነው፡፡
ቦ ማለት አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ ማለት ነው፡፡
ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት
ድንግል ማለት ነው፡፡
ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡
ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው፡፡
ነ ማለት ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ማለት ነው፡፡
ኑ ማለት ዛኅኑ ለባሕር ማለት ነው፡፡
ኒ ማለት ኰናኒ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ና ማለት መና እስራኤል ማለት ነው፡፡
ኔ ማለት ወጣኔ ኵሉ ማለት ነው፡፡
ን ማለት መኰንን እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኖ ማለት ኖላዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
አ ማለት አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዐ ማለት ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኮቴቱ ማለት
ነው፡፡
ኡ ማለት ሙጻኡ ለቃል ማለት ነው፡፡
ዑ ማለት ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኢ ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው፡፡
ዒ ማለት ለሊሁ ሠዋዒ ወለሊሁ ተሠዋዒ ማለት ነው፡፡
ኣ ማለት ኣሌፍ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ
ማለት ነው፡፡
ዓ ማለት ዓይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ ማለት ነው፡፡
ኤ ማለት አምጻኤ ዓለማት ማለት ነው፡፡
ዔ ማለት ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
እ ማለት እግዚአብሔር እግዚእ ማለት ነው፡፡
ዕ ማለት ብፁዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኦ ማለት እግዚኦ ማለት ነው፡፡
ዖ ማለት ሞዖ ለሞት ወተንሥአ ማለት ነው፡፡
ከ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኩ ማለት ዐርኩ ለመርዓዊ ማለት ነው፡፡
ኪ ማለት ኪያሁ ንሰብክ ማለት ነው፡፡
ካ ማለት ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኬ ማለት ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው ማለት
ነው፡፡
ክ ማለት ክብሮሙ ለመላእክት ማለት ነው፡፡
ኮ ማለት ዘረዳእኮ ለአብርሃም ማለት ነው፡፡
ኳ ማለት ኳሄላ አይሁድ ወልድ ማለት ነው፡፡
ኰ ማለት ኰናኔ ዓለም ማለት ነው፡፡
ኵ ማለት ኵርጓኔ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ኲ ማለት ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስሳ ምዕት ሐራ
በምዕር ማለት ነው፡፡
ኴ ማለት ወይኴንን እምባሕር እስከ ባሕር ማለት ነው፡፡
ወ ማለት ወረደ እምሰማያት ማለት ነው፡፡
ዉ ማለት ጼዉ ለምድር ማለት ነው፡፡
ዊ ማለት ናዝራዊ ሐዊ ማለት ነው፡፡
ዋ ማለት ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዌ ማለት ዜናዌ ትፍሥሕት ማለት ነው፡፡
ው ማለት ሥግው ቃል ማለት ነው፡፡
ዎ ማለት ቤዘዎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ዘ ማለት ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዙ ማለት ምርጒዙ ለሐንካሳ ማለት ነው፡፡
ዚ ማለት ናዛዚ ማለት ነው፡፡
ዛ ማለት ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዜ ማለት አኃዜ ዓለም በእራኁ ማለት ነው፡፡
ዝ ማለት ሐዋዝ ሕገ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዞ ማለት አግአዞ ለአዳም ማለት ነው፡፡
የ ማለት የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ ማለት ነው፡፡
ዩ ማለት ዕበዩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዪ ማለት መስተሥርዪ ማለት ነው፡፡
ያ ማለት አንተ ኬንያሁ ማለት ነው፡፡
ዬ ማለት ዐሣዬ ሕይወት ማለት ነው፡፡
ይ ማለት ሲሳይ ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ዮ ማለት ዮድ የማነ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ደ ማለት ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ ወሥጋነ ምስለ
መለኮቱ ማለት ነው፡፡
ዱ ማለት ፈዋሴ ዱያን ማለት ነው፡፡
ዲ ማለት ቃለ ዐዋዲ ማለት ነው፡፡
ዳ ማለት ዳሌጥ ድልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዴ ማለት ዐማዴ ሰማይ ወምድር ማለት ነው፡፡
ድ ማለት ወልድ ዋሕድ ማለት ነው፡፡
ዶ ማለት ፈነወ ዋሕዶ ወተሰብአ ማለት ነው፡፡
ገ ማለት ገባሬ ሰማ
ተውሳክ ማለት ጭማሪ፤ የጎደለውን ማስተካከያ ማለት ነው፡፡
✔ዕለታት የራሳቸው ተውሳክ አላቸው፡፡
✔በዓላትና አጽዋማትም የየራሳቸው ተውሳክ አላቸው፡፡
☞የዕለታት ተውሳክ፦
❖ የእሁድ ተውሳክ 7 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ በዓለ መጥቅዕ እሁድ የዋለ እንደው ከእሁድ ማግስት እስከ ፆመ ነነዌ
ያለው ቀን 127 ይሆናል፡፡ 127 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 7 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የእሁድ ተውሳክ 7 ነው
ማለት ነው፡፡
❖የሰኞ ተውሳክ 6 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ በዓለ መጥቅዕ ሰኞ የዋለ እንደው ከሰኞ ማግስት እስከ ፆመ ነነዌ ያለው
ቀን 126 ይሆናል፡፡ 126 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 6 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሰኞ ተውሳክ 6 ነው ማለት
ነው፡፡
❖የማክሰኞ ተውሳክ 5 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ በዓለ መጥቅዕ ማክሰኞ የዋለ እንደው ከማክሰኞ ማግስት እስከ
ፆመ ነነዌ ያለው ቀን 125 ይሆናል፡፡ 125 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 5 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የማክሰኞ
ተውሳክ 5 ነው ማለት ነው፡፡
❖የረዕቡ ተውሳክ 4 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ በዓለ መጥቅዕ ረዕቡ የዋለ እንደው ከረዕቡ ማግስት እስከ ፆመ ነነዌ
ያለው ቀን 124 ይሆናል፡፡ 124 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 4 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የረዕቡ ተውሳክ 4 ነው
ማለት ነው፡፡
❖የሐሙስ ተውሳክ 3 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ በዓለ መጥቅዕ ሐሙስ የዋለ እንደው ከሐሙስ ማግስት እስከ ፆመ
ነነዌ ያለው ቀን 123 ይሆናል፡፡ 123 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 3 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሐሙስ ተውሳክ
3 ነው ማለት ነው፡፡
❖የዓርብ ተውሳክ 2 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ በዓለ መጥቅዕ ዓርብ የዋለ እንደው ከዓርብ ማግስት እስከ ፆመ ነነዌ
ያለው ቀን 122 ይሆናል፡፡ 122 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 2 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የዓርብ ተውሳክ 2 ነው
ማለት ነው፡፡
❖የቅዳሜ ተውሳክ 8 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ በዓለ መጥቅዕ ቅዳሜ የዋለ እንደው ከቅዳሜ ማግስት እስከ ፆመ
ነነዌ ያለው ቀን 128 ይሆናል፡፡ 128 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 8 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የቅዳሜ ተውሳክ 8
ነው ማለት ነው፡፡

ማስታወሻ፡ መጥቅዕ ማለት ነጋሪት ወይም ደወል ማለት ሲሆን መባጃ ሐመርን ለማግኘት ይጠቅማል፡፡ መባጃ
ሐመር ደግሞ በዓለትንና አፅዋማትን ለማግኘት እንጠቀምበታለን፡፡ ዝርዝሩን በሚቀጥለው ጊዜ እናየዋለን፡፡

☞ የአጽዋማትና በዓላት ተውሳክ፦


❖ ፆመ ነነዌ ተውሳክ የለውም፡፡ መባጃ ሐመርን እንደ ተውሳክ ይጠቀማል፡፡
❖የዐቢይ ፆም ተውሳክ 14 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ዐቢይ ፆም ያለው ቀን 14 ነው፡፡
14 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 14 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የዐቢይ ፆም ተውሳክ 14 ነው ማለት ነው፡፡
❖የደብረ ዘይት ተውሳክ 11 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ደብረ ዘይት ያለው ቀን 41 ነው፡፡
41 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 11 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የደብረ ዘይት ተውሳክ 11 ነው ማለት ነው፡፡
❖የሆሳዕና ተውሳክ 2 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ሆሳዕና ያለው ቀን 62 ነው፡፡ 62 ን ለ 30
ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 2 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሆሳዕና ተውሳክ 2 ነው ማለት ነው፡፡
❖የስቅለት ተውሳክ 7 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ስቅለት ያለው ቀን 67 ነው፡፡ 67 ን ለ 30
ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው ይሆናል፡፡ ስለዚህ የስቅለት ተውሳክ 7 ነው ማለት ነው፡፡
❖የትንሳኤ ተውሳክ 9 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ትንሳኤ ያለው ቀን 69 ነው፡፡ 69 ን ለ 30
ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 9 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የትንሳኤ ተውሳክ 9 ነው ማለት ነው፡፡
❖የርክበ ክህናት ተውሳክ 3 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ርክበ ካህናት ያለው ቀን 93 ነው፡፡
93 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 3 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የርክበ ካህናት ተውሳክ 3 ነው ማለት ነው፡፡
❖የዕርገት ተውሳክ 18 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ዕርገት ያለው ቀን 108 ነው፡፡ 108 ን ለ
30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 18 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የዕርገት ተውሳክ 18 ነው ማለት ነው፡፡
❖የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ጰራቅሊጦስ ያለው ቀን 118 ነው፡፡
118 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 28 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28 ነው ማለት ነው፡፡
❖የፆመ ሐዋርያት ተውሳክ 29 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ፆመ ሐዋርያት ያለው ቀን 119
ነው፡፡ 119 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 29 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የፆመ ሐዋርያት ተውሳክ 29 ነው ማለት
ነው፡፡
❖የፆመ ድኅነት ተውሳክ 1 ነው፡፡ ከየት መጣ ቢሉ፡፡ ከፆመ ነነዌ ማግስት እስከ ፆመ ድኅነት ያለው ቀን 121 ነው፡፡
121 ን ለ 30 ስንገድፈው/ስናካፍለው ቀሪው 1 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የፆመ ድኅነት ተውሳክ 1 ነው ማለት ነው፡፡

You might also like

  • Research (2015)
    Research (2015)
    Document5 pages
    Research (2015)
    Dessalegn Tadiwos
    No ratings yet
  • Ew
    Ew
    Document1 page
    Ew
    Dessalegn Tadiwos
    No ratings yet
  • 500
    500
    Document4 pages
    500
    Dessalegn Tadiwos
    No ratings yet
  • Number
    Number
    Document29 pages
    Number
    Dessalegn Tadiwos
    No ratings yet
  • Hateta
    Hateta
    Document54 pages
    Hateta
    Dessalegn Tadiwos
    No ratings yet
  • ለመስቀል
    ለመስቀል
    Document54 pages
    ለመስቀል
    Dessalegn Tadiwos
    100% (2)