2007

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 41

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.

ማውጫ
መግቢያ ............................................................................................................................ 2

ክፍል አንድ....................................................................................................................... 4

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ግቦች አፈጻጸም ..........................................................................4

በዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍ .................................................................................................... 4

ግብ 1፡-ተቋማዊ የሥራ ባህልን ማሳደግ .....................................................................................................4

በዕቅድ አፈጻጸም ምዕራፍ ................................................................................................... 4

ግብ 2. የሰው ኃይል ብቃትን ማሳደግ፣ ........................................................................................................5

ግብ 3. የኢኮቴ አጠቃቀምን ማሳደግ፣ ...........................................................................................................7

ግብ 4. የለውጥ ኮሙኒኬሽን ሥራን ማሳደግ ...............................................................................................8

ግብ 5. ተደራሽነትን ማሳደግ ...................................................................................................................... 12

ግብ 6.ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን ማሳደግ.............................................................................. 17

ግብ 7. የአገልግሎት ቅልጥፍናን ማሻሻል .................................................................................................. 20

ግብ 8. የአገልግሎት ጥራትን ማሳደግ ....................................................................................................... 25

ግብ 9. የፋይናንስና የንብረት አጠቃቀምን ማሻሻል.................................................................................... 25

ግብ 10. የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን ማሳደግ ...................................................................................... 32

ግብ 11 የተገልጋይን ዕርካታ ማሳደግ ........................................................................................................ 32

ክፍል ሁለት ................................................................................................................... 33

2 የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ............................................................................................................................ 33

ክፍል ሶስት..................................................................................................................... 35

የክትትልና ግምገማ ምዕራፍ ............................................................................................ 35

ማጠቃለያ ....................................................................................................................... 41

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 1


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት

መግቢያ
በፌዴራል ፍ/ቤቶች ደረጃ አዲስ የተዘረጋውን ሚዛናዊ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሥርዓት ተከትሎና
ከስትራቴጂክ ዕቅድተነስቶ የተዘጋጀው የተቋም ዓመታዊ ዕቅድ ከሁሉም ዕይታዎች (የተገልጋይ እርካታ
ማሳደግ፣ የውስጥ አሠራር ማሻሻል፣ የፋይናንስ/በጀት አጠቃቀም፣ መማማርና ዕድገት) የተወሰዱ አስራ
አንድ ግቦች እና ሰባት ፕሮጀክቶችን የያዘ ሲሆን በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ
ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በተገኙ ግብዓቶች መሰረት በመጋቢ ግቦች ላይ የተወሰኑ ማስተካከያዎች
ተደርገዋል፡፡ የዚህን ዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማ ለማድረግ በየደረጃው በሚገኙ ኃላፊዎች፣ ዳኞችና ድጋፍ
ሰጪ ሠራተኞችን አስተያየቶች በማሰባሰብ ተቀባይነት ያገኙ ማስተካከያዎች ተደርገዋል፡፡

በተቋሙ የዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍ የተቋሙን ዓመታዊ ዕቅድ ለሚመለከታቸው ክፍሎች በማስተዋወቅ
እስከ ፈጻሚዎች አውርዶ ለማቀድ የሚያስችሉ የኦረንቴሽንና የውይይት መድረኮች የተካሄዱ ሲሆን
ለዳኝነት ዘርፉ በተዘጋጀው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርድ እና በተቋሙ ዓመታዊ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ
ስምምነት ላይ ለመድረስ ተችሏል፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት በሁሉም ፍ/ቤቶች የሚገኙ የዳኝነት ዘርፎች
እና የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች ከተቋም ዓመታዊ ዕቅድ የሚመለከቱዋቸውን ግቦችና ፕሮጀክቶች
በመውሰድ የየራሳቸውን ዓመታዊ ዕቅድ ከማዘጋጀታቸውም ሌላ የችሎቶችን ዕቅድ እስከ ዳኞች እና የሥራ
ክፍሎችን ዕቅድ እስከ ፈጻሚ ግለሰቦች በማውረድ የተሟላም ባይሆን ዝርዝር ተግባራትን የያዙ ዓመታዊ
ዕቅዶች በየደረጃው ተዘጋጅተዋል፡፡

የተቋሙን የትግበራ ምዕራፍ አጠናክሮ በመቀጠል የዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማነትን ማሳደግ የሚያስችል
የክትትልና ግምገማ ሥርዓት ተዘርግቶ የተተገበረ ሲሆን የተቋሙ የበላይ አመራር፣ የችሎት/ምድብ ችሎት
አስተባባሪዎች፣ የችሎት ሰብሳቢዎችና የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍል ኃላፊዎች በየደረጃው ተገቢውን
ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ በማድረግ በዕቅድ የተያዙ ግብች እና ፕሮጀክቶች ለበጀት ዓመቱ
ከተቀመጠላቸው ዒላማ አኳያ እንዲከናወኑ ለማድረግ ያገዙ ጥረቶችን አድርገዋል፡፡ ከበጀት ዓመቱ
የመጀመሪያ ሩብ ዓመት(ነሐሴና መስከረም) የዳኞች የዕረፍት ጊዜ በመሆኑ እና ዕቅዶችን በየደረጃው
አውርዶ የማዘጋጀቱ ሥራ የተወሰነ ጊዜ በመውሰዱ በእነዚህ ወራት በፍ/ቤቶች ዕልባት ያገኙ መዛግብት
መጠን ከሌላው ጊዜ አኳያ ሲታይ ዝቅ ብሎ ታይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ለዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ
ውጤታማነት የሚያግዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማሟላት የተሻለ ጥረት የተደረገበት፣ በጥናት ላይ የቆየው
የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና ሥርዓት ወደ ትግበራ የተሻገረበትና በሥራ የደከሙ ዳኞች ተገቢውን ዕረፍት
አግኝተው በአዲስ ኃይል ወደ ሥራ እንዲመለሱ የተደረገበት ወቅት በመሆኑ የበጀት ዓመቱን የዳኝነት
አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል መሰረት የተጣለበት ነበር ለማለት ይቻላል፡፡

የዕቅድ አፈጻጸም ክትትልል፣ ድጋፍና ግምገማ ምዕራፍ በዕቅድ አፈጻጸም ሂደት ከዓመቱ ዕቅድ
እየተመነዘሩና ዳኞች ወርሃዊ፣ የአስተዳደር ክፍሎች ደግሞ ሳምንታዊ ዕቅድ እያዘጋጁ በዕቅዳቸው መሰረት
መፈጸምና የአፈጻጸም መረጃ መያዛቸውን፣ የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች የዕቅድ ዝግጅቶችንም ሆነ
የአፈጻጸም መረጃዎችን አግባብነት ተከታትለው ማስተካከያ ድጋፎችን ማድረጋቸውንና የአፈጻጸም ግምገማ
መድረኮችን በተገቢው ጊዜ ማካሄዳቸውን፣ በጋራ ግምገማ የተለዩ ክፍተቶች እና ከበላይ አመራር የሚሰጡ
ግብረመልሶች በአግባቡ መፈጻማቸውንና ከፍተቶች እንዲሞሉ መደረጋቸውን፣ እንዲሁም ወቅታዊ
የአፈጻጸም ሪፖርቶች ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸው አካላት መድረሳቸውን ማረጋገጥ ያስቻሉ ተግባራት

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 2


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ተከናውነዋል፡፡ በዚህ ምዕራፍ መከናወን የሚገባቸው እነዚህ የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ተግባራት
በሁሉም ፍ/ቤቶች በተሟላ ሁኔታ ተፈጽመዋል ለማለት ባይቻልም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አበረታች
የለውጥ ጅምሮች ነበሩ ለማለት የሚያስችሉ አፈጻጸሞች ታይተዋል፡፡ በተለይ በሁለተኛው መንፈቅ ዓመት
በየፍ/ቤቶች በተናጥል እና ሶስቱም ፍ/ቤቶች በጋራ ባካሄዱዱዋቸው የበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም
ግምገማዎች ለምዘና ሥርዓቱን ትግበራ እንቅፋት የፈጠሩ ችግሮች ተለይተው ከመውጣታቸውም ሌላ
በአመራር፣ በዳኛ፣ በድጋፍ ሰጪ ሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ፈጻሚዎች ዘንድ የነበሩ ጥንካሬ እና
ክፍተቶች/ድክመቶች በግልጽ እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ የመፍትሔ
አቅጣጫዎችንም በማመላከት በቀጣዩን በጀት ዓመት የምዘና ሥርዓቱን ትግበራ አጠናክሮ ለመቀጠል
ስምምነት ተደርጓል፡፡

የምዘና ምዕራፍን በተመለከተ የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በሁሉም ፍ/ቤቶች የተሟላ ምዘና ተካሂዷል
ማለት አይቻልም፡፡ በተወሰነ መልኩ የግቦች አፈጻጸም የሚገኙበትን ደረጃ መለየት ያስቻሉ መረጃዎችን
ለማግኘት ቢቻልም በየደረጃው ወርዶ በተዘጋጀው ዕቅድ መሰረት የዳኞችን፣ ችሎቶችንና ፍ/ቤቶች
እንዲሁም የደጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን፣ ቡድኖችን፣ የሥራ ክፍሎችንና ፍ/ቤቶችን አፈጻጸም በየደረጃው
ገምግሞ የተገኙ ውጤቶችን በመለየት የተቋሙን የመንፈቅ ዓመት አፈጻጸም የመመዘን ተግባር
አልተከናወነም፡፡ ለዚህም ዓይነተኛ ምክንያት ሆኖ የሚጠቀሰው አዲስ የተጀመረውን የምዘና ሥርዓቱን
ለመተግበር የሚያስችል አቅም በቀላሉ መፍጠር አለመቻልና የምዘና ሥርዓቱ የሚጠይቀውን ሂደት
ተከትሎ መተግበር የሚያስችል አመለካከት አለመዳበር ነው፡፡ የሁተኛውን መንፈቅ ዓመት ትግበራ
ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ተጠናክሮ የቀጠለ በመሆኑ የምዘና ሥርዓቱ ትግበራ የተሻለ ደረጃ ላይ
ከመድረሱም በላይ አፈጻጸምን በየደረጃው ለመመዘን የተጠናከረ ጥረት ተደርጓል፡፡

በዚህ ሪፖርት ሶስት ክፍሎች የተካተቱ ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል በዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍ ከተቋማዊ
እስከ ግለሰብ የዘለቀውን የዕቅድ ዝግጀት ሂደት እና በአፈጻጸም/ትግበራ ምዕራፍ የግቦችን አፈጻጸም
እንዲያሳይ ተደርጓል፡፡ ሁለተኛው ክፍል ለበጀት ዓመቱ የተያዙ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም የሚያሳይ ሲሆን
ሶስተኛው ክፍል በክትትልና ግምገማ ምዕራፍ ዕቅዱን ለማሳካት በዕቅድ ዝግጅት እና በትግበራ ሂደት
የተደረጉ ክትትልና ድጋፎች በማሳየት በግምገማ የተለዩ ጥንካሬና ድክመቶችን፣ በአፈጻጸም ያጋጠሙ
ችግሮችንና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን፣ በዕቅድ ተይዘው በተለያዩ ምክንያቶች ያልተከናወኑ
ተግባራትን እንዲሁም የቀጣዩን በጀት ዓመት አፈጻጸም ውጠየታማነት ለማጎልበት የተቋሙ የበላይ
አመራር ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገው ጉዳዮችን አመላክቷል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 3


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ክፍል አንድ

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ግቦች አፈጻጸም

በዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍ

ግብ 1፡-ተቋማዊ የሥራ ባህልን ማሳደግ (አፈጻጸሙ 95.5% ደርሷል)


1.1 የምዘና ሥርዓቱን የተከተለ ዕቅድ አዘገጃጀትን ለማጠናከር በተያዘው ዕቅድ፡-
 የተዘጋጀውን የተቋሙን ዓመታዊ ዕቅድና የዳኝነት ዘርፉን የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርድ
ለሚመለከታቸው ክፍሎች ለማስተዋወቅ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የፌዴራል ፍ/ቤት ዳኞች፣ የፍርድ
አፈጻጸምና የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤትን ጨምሮ የሁሉም ፍ/ቤት የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ኃላፊዎች
በተሳተፉበት የጋራ መድረክ እና በየፍ/ቤቶች በተናጥል በተካሄደ ውይይት ግንዛቤ ለማስጨበጥ
የሚያስችል ኦረንቴሽን ተሰጥቷል፣
 ከተሳታፊዎች በተገኙ አስተያየቶች መሰረት የዳበረው የተቋም ዓመታዊ ዕቅድ እና የዳኞች
የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርድ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፣
 የፍ/ቤቱ ማህበረሰብ የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች በመጋራትና ከተዘጋጀው የተቋሙ ዓመታዊ
ዕቅድ ችሎቶችና የድጋፈ ሰጪ ክፍሎች የሚመለከቱዋቸውን ግቦችና ፕሮጀክቶች ወስደው ዓመታዊ
ዕቅድ እንዲያዘጋጁ በማድረግ ከሚመለከቱዋቸው የበላይ ኃላፊዎች ጋር የአፈጻጸም ስምምነት ውል
ተፈራርመዋል፣
 በየደረጃው የሚገኙ ዳኞች ከችሎቶች፣ የድጋፍ ሰጪ ሥራ ከፍል ፈጻሚዎች ደግሞ ከሥራ
ክፍሎች/ቡድኖች መጋቢ ግቦችን በመውሰድ የየራሳቸውን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጁ ሲሆን በዕቅድ
ዝግጅቱ ሂደት በሚመለከታቸው አካላት ተገቢው ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል፣
 በየደረጃው የተዘጋጁ ዕቅዶች በሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃግብር የሰፈሩ ድንጋጌዎችን፣ የመልካም
አስተዳደርና ሥነ ምግባር መርሆችን፣ የኪራይ ሰብሳቢነት መከላከያ ስልቶችን ያካተቱ መሆናቸውን
ለማረጋገጥ ያስቻሉ ክትትሎች፣ ድጋፎችና ግምገማዎችን በማድረግ ክፍተቶችን ለመሙላት ያስቻሉ
ጥረቶች ተደርገዋል፣
 ዕቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ የሚስችሉ ግብዓቶችን ለማሟላት ካለፉት ዓመታት የተሻሉ ጥረቶች
የተደረጉ ሲሆን ችሎቶችም ሆነ የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች በግብዓት አቅርቦት በኩል የነበሩባቸው
ችግሮች የተሻሻሉ መሆናቸውን መገንዘብ ተችሏል፣

በዕቅድ አፈጻጸም ምዕራፍ


1.2 በአፈጻጸም ምዕራፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል፡-

የፍ/ቤቶች ማህበረሰብ የተቋሙን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶችና ግቦች በአግባቡ
ተረድቶና ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚችልበትን አመለካከትና ብቃት አጎልብቶ በየደረጃው ያዘጋጃቸውን
ዕቅዶች እንዲፈጸም ለማድረግ፡-
 የለውጥ አመለካከት እና የመፈጸም ብቃት የሚያጎለብቱ የተለያዩ የስልጠና እና የውይይት መድረኮች
መዘጋጀታቸውን፣
 ተቋማዊ ይዘት ያላቸው የለውጥ ኮሚኒኬሽን ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 4


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 ተደራሽነትን ማጎልበት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን፣


 የዳኝነት ጥራት፣ ቅልጥፍና፣ ነጻነት፣ ገለልተኝነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት መርሆችን ትግበራ
ማሻሻል ያስቻሉ ጅምሮች መኖራቸውን፣
 በተሟላ መልኩ ባይሆንም የአፈጻጸም ክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማና ምዘና ሥርዓት ትግበራ ተጀምሮ
በመጠናከር ላይ መሆኑን
 በአጠቃላይ በዕቅድ የተያዙ ግቦችና ፕሮጀክቶችን መፈጸም የሚያስችሉ ጥረቶች መደረጋቸውን
መረዳት ተችሏል፣

በዚህም በተቋም ደረጃ በዕቅድ የተያዙ ግቦችን/መጋቢ ግቦችን ለማሳካት የሚከተሉት ዝርዝር ተግባራት
ተከናውነዋል፡፡

ግብ 2. የሰው ኃይል ብቃትን ማሳደግ (አፈጻጸሙ 74.5% ደርሷል)


2.1 በፍላጎት ጥናትና በዕቅድ ላይ የተመሰረቱ የስልጠና አካሄዶችን ለማጠናከር ታቅዶ፡-

 በፌዴራል ጠቅላይ፣ ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት፣ በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት
እና ሸሪዓ ፍርድ ቤት የሚገኙ ዳኞች፣ የሲቪል ሰርቪስ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን የመፈጸም አቅም፣
የአመለካከት፣ የዕውቀትና ክህሎት ስልጠና ፍላጎቶችና ክፍተቶች መለየት ያስቻለ ጥናት ተካሂዶ
የተቋሙ የበጀት ዓመት የሥልጠና ዕቅድ ተዘጋጅቷል፣
 በስልጠና ዕቅዱ የተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮች የሴቶችን የመሪነትና የመፈጸም አቅም ለማጎልበት፣
የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃግብር ድንጋጌዎችን ግንዛቤ ለማዳበር፣ የመልካም
አስተዳደርና የሥነ መግባር መርሆችን የዕለት ተዕለት ተግባር ለማድረግ፣ ለባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ልዩ
ትኩረት ሰጥቶ ለማስተናገድ፣ በአጠቃላይ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ የለውጥ
አተገባበሮችን ለማጠናከር የሚያስችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስቻለ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ
ተደርጓል፣
 በዚህ ዕቅድ መሰረት 14 የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮችን ለማሰልጠን ከኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
እና በሾፌር መካኒክነት ለማሰልጠን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምርታማነት ማሻሻያ ማዕከል ጋር
ስምምነት ተደርጓል፣
 በሲቪል ሰርቪስ ሕጎች ላይ የሠራተኞችን ግንዛቤ ለማዳበር የሲቪል ሰርቪስ ባለሙያዎችን በሥነ
ምግባር መርሆች ላይ ተገቢው ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማድረግ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና
ኮሚሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ የተለያዩ የስልጠና መድረኮች ተዘጋጅተዋል፣
 በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ አተገባበር ዙሪያ ተገቢው ግንዛቤ እንዲጨበጥ በመመሪያው
አዘጋጅ ኮሚቴ አማካኝት ለተለያዩ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ክፍሎች (ለምሳሌ ተከላካይ ጠበቆች፣ የህግ
ጥናትና ድጋፍ ባለሙያዎች ወዘተ…) ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፣
 የዩንቨርስቲ መምህራንን በመጋበዝ የሕግ ጥናት እና የፕሮጀክት ዝግጅት ጉዳዮችን የሚመለከቱ
ስልጠናዎችን ለመስጠት ያስቻሉ መድረኮች የተዘጋጁ ሲሆን በአጠቃላይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ
በተዘጋጁ ከ15 በላይ በሆኑ ስልጠናዎችና የተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ 1‚910 ተሳታፊዎችን
ማስተናገድ ተችሏል፡፡
 የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የትምህርትና ስልጠና አፈጻጸም መመሪያም ተዘጋጅቷል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 5


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

2.2 የለውጥ አመለካከትና የመፈጸም አቅምን ለማጎልበት የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ለማካሄድ


በተያዘው ዕቅድ፡-

 የመንግሥት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን አስመልክቶ ለዳኞችና ለፍትህ አካላት በተዘጋጀው ሁለት


ዙር ስልጠና የፌዴራል ዳኞችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ኃላፊዎች ተካፍለዋል፡፡
ስልጠናውን በማስተባበሩም ሂደት ተሳትፎ ተደርጓል፣
 የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ለመካከለኛ አመራሮች ባዘጋጀው የመንግሥት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች
በሁለት ዙር ስልጠና ላይ ሁሉም የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፣
 ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር የፌዴራል ዳኞች በዓለም አቀፍ ሂውማንቴሪያን
ህግ አስፈላጊነትና በአፈጻጸም ሂደት በሚያጋጥሙ ተግደሮቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና እንዲገኙ
ተደርጓል፣
 የለውጥ ሥራዎችን በተለይም የምዘና ሥርዓቱን በአግባቡ ለመተግበር፣ የዳኝነት ሥርዓቱን ቀልጣፋ፣
ጥራት ያለው፣ ውጤታማ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ የሚያደርግ አቅም ለመገንባት፣ የብሔራዊ የሰብዓዊ
መብት ድርጊት መርሃግብር ድንጋጌዎችን ተገንዝቦ ለመፈጸም፣ የመልካም አስተዳደርና የሥነ ምግባር
መርሆችን አስርጾ የሥራ አካል እንዲሆኑ ለማድረግ፣ በመረጃ ነጻነት ሕግ መሰረት የሕብረተሰቡን
መረጃ የማግኘት መብት ለማስከበር፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል የሙስና ምንጮችን ለመቀነሽና
በአጠቃላይ የህብረተሰቡን ፍላጎት ያገናዘበና የተገልጋይን እርካታና አመኔታ የሚጨምሩ አመለካከትና
አቅም ለመገንባት የሚያስችሉና የስልጠና እና የውይይት መድረኮች ተዘጋጅተዋል፣
 የፌዴራል ፍ/ቤት ዳኞችን አቅምና አመለካከት ለማጎልበት በፍትህ ማሰልጠኛ ማዕከል የተዘጋጁና
እያንዳንዳቸው አንድ ወር የፈጁ አምስት ዙር የስልጠና መድረኮች ተዘጋጅተዋል፣
 በተቋሙ በተዘጋጀው የፍትህ ሰራዊት ግንባታ አፈጻጸም መመሪያ ሰነድ ላይ የፌዴራል ዳኞችን፣
መካከለኛ አመራሮችንና ድጋፍ ሰጪ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞችን ግንዛቤ ለማዳበር ያለሙና
በመመሪያው አዘጋጆች አማካኝት በየፍ/ቤቶች የተካሄዱ ከስምንት ዙር ያላነሱ የስልጠና መድረኮች
ተዘጋጅተዋል፣
 በየደረጃው የሚገኙ ዳኞች፣ የሲቪል ሰርቪስ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ባለ ብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን
ለማስተናገድ ወይም ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ
ክፍሎችን (የሴቶች፣ የሕጻናት፣ አረጋዊያን፣ የአካልና የአዕምሮ ጉዳተኞች ወዘተ...) መብቶች
ለማስከበር ማከናወን በሚገባቸው ተግባራት ላይ ተገቢውን ግንዛቤ ለመጨበጥ ያስችሉ የተለያዩ
የስልጠናና የውይይት መድረኮች ተዘጋጅተዋል፣
 የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት 93 ዳኞችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በተቋም ከተዘጋጀው መድረክ
በተጨማሪ በኢትዩጵያ ሥራ አመራር ኢንስትቲዩት በተዘጋጀ መድረክ በለውጥ ሰራዊት ግንባታ ላይ
ያተኮረና የማስፈጸም አቅም ክህሎት በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል፣
 በመንግሥት ፖሊሲዎችና መርሐግብሮች፣ በሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት፣ በፍትሕና ልማት ሠራዊት
ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና በሁሉም ደረጃ ለሚገኙት የሸሪያ ጠ/ፍ/ቤት ሠራተኞች አራት ቀን
የወሰደ ስልጠና ተሰጥቷል፣
 አራት የሸሪዓ ድጋፍ ሰጭ ሠራኞች በኢትዮጵያ ስራ-አመራር ኢንስቲትዩት አማካኝነት በፋይናንሺል
አካውንቲንግ የአስር ቀን ሥልጠና ወስደዋል፣
 በሥርዓተ ጾታና ወጣቶች ጉዳይ ዙሪያ የወጣቶች /ጉዳይ ፖሊስ፣ የወጣቶች የእድገት ፓኬጅና
የወጣቶች ጉዳይ ማካተቻ ማኑዋል/ በተመለከተ ከፌ/ፍ/ቤቶች ለተውጣጡ 91 ወጣት ሠራተኞች
/ሴት 67 ወንድ 24 / ግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና/ትምህርት ተሰጥቷል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 6


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 የሴት ሠራተኞችን አቅም በሥልጠናና ትምህርት ማጐልበትን አስመልክቶ ከተለያዩ የግል ኮሌጆት
በተገኘ ድጋፍ ሁለት ሴት ሠራተኞች ነጻ ሁለት ደግሞ 5ዐ በመቶ ቅናሽ የትምህርት እድል
አግኝተዋል፡፡
 ሥርዓተ ጾታን በየሥራ ዘርፉ ማካተትና የሥርዓተ ጾታ መረጃን አስመልክቶ ከፌደራል ፍ/ቤቶች እና
ከፌ/ጠ/ ሸሪዓ ፍ/ቤት ለተውጣጡ 24 ሴት 32 ወንድ በጠቅላላው ለ56 የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና
ባለሙያዎች የአንድ ቀን ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
 የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጐለበት እንዲቻል በተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ዘዴ ላይ ለ33 ሴቶች
ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
 ራስ አገዝ የሴቶች ድርጅት ከሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተደረገው የባለሙያና
የቁሳቁስ ድጋፍ ለ22 ሴት የጽዳት ሠራተኞች መሠረታዊ የንግድ ክህሎት በሚል ርእስ የ5 ቀን
ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
 ዓለም አቀፍ የጸረ ጾታዊ ጥቃትና የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን ከፌደራል ፍ/ቤቶችና ከፌ/ጠ/ሸሪዓ ፍ/ቤት
ከተውጣጡ 200 ሠራተኞችና /115 ሴት 85 ወንድ/ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተያያዥ በሆኑ
ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና በመስጠትና ሰፋ ያለ ውይይት በማድግ ቀኑ ተከብሯል፡፡
 የፌ/ፍ/ቤቶች ወጣት ሠራተኞች በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማዳበር ይቻል ዘንድ
በአቻ-ለአቻ ውይይትና በሥነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ለ5ዐ/ 33 ሴት 17ወንድ/ ወጣቶች የአንድ ቀን
ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
 ለዳታ ቤዝ ባለሙያዎች ከአዲሱ መረጃ ስርዓት ጋር ተስማምተው ለመስራት እንዲችሉ በሶስት ዙር
የተከፈለ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፣
 በፌዴራል እና በክልል ፍርድ ቤቶች በህጻናት ችሎቶች ላይ ለሚሰሩ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች
የረጅም ጊዜ በዘርፉ ላይ እውቀትና ክህሎት የሚያስጨብጥ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ የዲፕሎማ
ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል፣ ስልጠናውን ለመስጠት በተዘጋጁት
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ወርክ ትምህርት ክፍል የቀረቡ የብቃት ምዘና ፈተናዎች ተሰጥተዋል፡፡
 ለኦዲዮቪዥዋል ሁለት ባለሙያዎች ከሙያቸው በተያያዘ ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት ግምት ውስጥ
ያስገባ የሦስት ወር ሥልጠና በቪዲዮ ቀረፃ እና በቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ በፎቶ አነሳስ እና በፎቶ ኤዲቲንግ
ሥልጠና ወስደዋል፣
 በአዲስ ቅጥር ፍ/ቤቱን ለተቀላቀሉ 101 ባለሙያዎችና ሠራተኞች በተቋሙ ሥራ ባህልና የለውጥ
እንቅስቃሴዎች ላይ ያተኮሩ የማስተዋወቂያ ስልጠናዎች ተዘጋጅተዋል፣
 በተሰጡ ስልጠናዎች የተገኘውን የመፈጸም አቅም ዕድገትና የአመለካት ለውጥ መኖሩን ማረጋገጥ
የሚያስችሉ ግምገማዎች በየሥራ ክፍሎች እንዲከሄዱ ተደርጓል፣

ግብ 3. የኢኮቴ አጠቃቀምን ማሳደግ (አፈጻጸሙ 97.5% ደርሷል)

3.1 በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ አሠራሮችን ለማሳደግ ፡-


 በኢንፎርሜሽን ኮሙኑኬሽን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም እየጎለበተ እንዲሄድ ለማድረግ በዳታቤዝ
ወጥነት ያለዉ የመረጃ አግባብነት እና አጠቃቀም ላይ ያተኮረና ብዛታቸዉ 155 ለሚሆኑ
ሬጅስትራሮች፤ ፋይል ከፋቾች፣ የዳታቤዝ ኦፕሬተሮች ስልጠና ተሰጥቷል፤
 የፍርድ ቤቱን ሰራተኞች በልዩ ልዩ የኮምፒውተር አጠቃቀም ለማሰልጠን በተያዘው እቅድ መሰረት
በሲ.ሲ.ኤም ኤስ፤ ዳታ ቤዝ ፤ፋይል መክፈት ላይ በሚታዩ ችግሮች በመዝገብ እስካኒግ ስልጠና
ተሰጥቷል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 7


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 አማካሪ ድርጅቶች በመቅጠር በኔትወርኪንግ እና ተዛማጅ የስልጠና ርዕሶች ላይ ለ40 የኢንፎርሜሽን


ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን ስልጠና ተሰጥቷል
 በችሎቶችና ሥራ ክፍሎች የሚሰጡ የዳኝነት አገልግሎቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ
እንዲሆን ለማድረግ ለ 16 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም
ስልጠና ተሰጥቷል፣
 ከመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተገኘ የስልጠና እድል መሰረት 20 የኢኮቴ
ባለሙያዎች በልዩ ልዩ ሙያዎች ለአንድ ወር ያህል ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

3.2 በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን የመጠቀም አቅምን የሚያጎለብቱ አቅርቦቶችን ለማሳደግ ታቅዶ፡-


 የቴክኖሎጂ አቅርቦቶችን ለማሟላት በተደረጉ ጥረቶች ነባር መዝገቦች ዲጂታይዝ ለማድረግ
የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተከናውነዋል፣ ለስራው የሚያስፈልጉ እቃዎቸ ለምሳሌ
እስካነር እና እስቶሬጅ ሰርቨር ግዢ ለማከናወን ሰፔስፊኬሽን ተዘጋጅቶና የቴክኒካል ግምገማ ተሰርቶ
የእስካነር ግዢ ተጠናቋል፤
 የተሻሻለው ዳታቤዝ ሲሲኤምኤስ 2.5 በ 30 ኮምፒተሮች እንዲጫን ተደርጓል፣ ከየክፍሉ ለሚጠየቁ
የድጋፍ ስራዎች ጥያቄዎች በ 35 ኮምፒተሮች፣ በ15 ፕሪንተሮች እና በ5 እስካነሮች ቀላል እና ከባድ
የጥገና እና የድጋፍ ስራዎች ተሰርቷል፤
 ለተለያዩ ክፍሎች እና ክልሎች የተጠየቁትን ከ10 ያላነሱ የሰፐስፊኬሽን ጥያቄዎች በማስናገድ
ሰፔስፊኬሽኖች ተዘጋጅተዉ ተልከዋል፤ ተገዝተው ለቀረቡት የተለያዩ ዓይነት እቃዎች በተጠየቀው
መስፈርት መቅረባቸዉ የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል፣
 በዚህ መሰረት ለልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ክልሎችን ጨምሮ የኮምፒውተር እቃዎች
ለሲሲቲቪና ቪዲዬ ኮንፈረንስ ካሜራ ስፔስፊኬሽንና ቴክኒካል ግምገማ ተደርጓል፣
 ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 11 ሰርቨሮች የኮንፊገሬሽን ስራ ተከናውኗል፣
 የኢኮቴ አጠቃቀምን ለማጎልበት የሚያስችል ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እስካን እየተደረጉ ያሉ
ፋይሎች በአግባቡ እና በትክክል ሰርቨር ላይ መቀመጣቸው የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል፣
 ከክልሎች ለቀረቡ የእሰፐስፊኬሽን እና መሰል የድጋፍ ጥያቄዎች በኢ-ሜልና በስልክ የመደገፍ
ስራዎች ተሰርቷል፤
 ወደ ዳታቤዝ የሚገቡ መረጃዎች ጥራታቸው እና ወቅታዊነታቸው በመከታል በመ/ቤቱ የበላይ
ሃላፊዎች የሚፈለጉ ወቅታዊ ሪፖርቶች በየወሩ ተዘጋጅተዋል፣

ግብ 4. የለውጥ ኮሙኒኬሽን ሥራን ማሳደግ(አፈጻጸሙ 87.7% ደርሷል)

4.1 የለውጥ ኮሚኒኬሽን ሥራዎችን በማጠናከር ተቋማዊ ገጽታን ለመገንባት፡-

 የተለያዩ መገናኛ ብዙሐንን (ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ብሮሽር፣ ጋዜጣዊ መግለጫ
ወዘተ…) በመጠቀም የሰብዓዊ መብት የደርጊት መርሃግብር ድንጋጌዎችን አፈጻጸም ጨምሮ
የፌዴራል ፍ/ቤቶችን የዕቅድ አፈጻጸም ለሕዝብ በማስተዋወቅ የተቋሙን ገጽታ የሚገነቡ የተለያዩ
መልዕክቶች እንዲተላለፉ ተደርጓል፣
 ተቋሙ ያዘጋጃቸውን የተለያዩ የውይይትና የስልጠና መድረኮች የመንግሥት የኤሌክትሮኒክስና
የህትመት ሚዲያ ጋዜጠኞች ተገኝተው እንዲዘግቡ በማድረግ የዜናና የዘገባ ሽፋን አንዲሰጡ
ተደርጓል፤

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 8


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 አገር አቀፍ የፍትህ አካላት የበላይ አመራሮች የተሳተፉበትን የአቅም ግንባታ ስልጠና የኢትዮጵያ
ቴሌቪዥን፣ አ.አ መገናኛ ብዙኃን ቴሌቪዥንና ሬዲዮ፣ ኦሮሚያ ቴሌቪዥን፣ ኢትዮጵያ ኘሬስ
(አማርኛ፣ እንግሊዘኛና አረብኛ) ዛሚ፣ ሸገር፣ ሬዲዮ ፋና ተገኝተው በመዘገብ ለሕዝብ እንዲያስተላልፉ
ተደርጓል፣
 የዳኝነት ነፃነት፣ ተጠያቂነት፣ ግልፅነት በኢትዮጽያ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ፅሁፍ ለኢትዮጵያ ኘሬስ
ድርጅት በመላክ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
 አገር አቀፍ ነፃ የህግ ድጋፍ ቅንጅት ለመመስረት በተዘጋጀ መድረክ የአትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣
የኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት ዛሚ እና ሸገር ተገኝተው እንዲዘግቡ ተደርጓል፣
 የፌ/ጠ/ፍ/ቤት እና የፌ/ጠ/ሸሪዓ ፍ/ቤት ዳኞችና ሠራተኞች ለሕዳሴ ግድብ ማጠናከሪያ የሚሆን
ለሁለተኛ ዙር የቦንድ ግዥ ለመፈፀም በተካሄደ ስብሰባ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ የአዲስ አበባ መገናኛ
ብዙኃን /ሬዲዮ/ የኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት/ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዛሚ ኤፍ ኤም ተገኝተው
እንዲዘግቡ ተደርጓል፣
 አገር ዓቀፍ የሕፃናት የፍትህ አስተዳደር ያለበትን ሁኔታ በሚያሳይ አገር ዓቀፍ ጥናት ላይ ለመነጋገር
በተዘጋጀ የምክክር መድረክ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ የኦሮሚያ ቴሌቪዥን፣ የአ.አበባ ቴሌቪዥንና
ሬዲዮ፣ ኢትዮጵያ ኘሬስ /ሄራልድዘመን/ ፋና፣ ዛሚ፣ ሸገር ተገኝተው ዘግበዋል፣
 የፌዴራል ፍ/ቤቶች የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት የፀደቀበትን 2ዐኛ ዓመት ለማክበር በተዘጋጀ መድረክ
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ ኦሮሚያ ቴሌቪዥን፣ የአ.አበባ ኤፍ ኤም ሬዲዮ፣ዜና አገልግሎት ፣
የኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት ተገኝተው እንዲዘግቡ ተደርጓል፣
 የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2 ለተከላካይ ጠበቆችና ሰሌሎች የፌ/ፍ/ቤቶች የሕግ
ባለሙያዎች በተሰጠ ሥልጠና ላይ የተገኘው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎ ሆኖ ዘገባው ግን በኢትዮጵያ
ቴሌቪዥን፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ ኤፍ ኤም 97.1 እና በአ.አ ኤፍ ኤም ሬዲዮ እንዲሁም በፋና
ተላልፏል፣
 የፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት እና የሕፃናት ፍትህ ኘሮጀክት የ2ዐዐ6 ዓ.ም. የሥራ
አፈፃፀም በሸገር ሬዲዮ ጣቢያ ከአድማጮች ጋር በመገናኘት የ4 ሰዓት ሽፋን እንዲሰጣቸው ተደርጓል፣
 የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት የተቋሙ የአይሲቲ አጠቃቀም በተመለከተ ሁለቴ የዜና ዘገባ
እንዲሰራ ተደርጎ በቴዤቪዥንና በሬዲዮ ተላልፋል፤
 የ2ዐዐ7 የኢኮቴ፣ የሕፃናት ፍትህ ኘሮጀክት የፍርድ አፈፃፀም እና የተከላካይ ጠበቆች የሥራ
አፈፃፀምና ዋና ዋና ተግባራት እንዲሁም ያመጣቸው ለውጦች በተመለከተ በኢትዮጵያ ሬዲዮ በኩል፣
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ዋና ተግባርና ወቅታዊ የሥራ አፈፃፀም በሸገር ሬዲዮ ጣቢያ
በሁለት ዘገባ ሽፋን ተሰጥቶታል፣
 የተቋም ገፅታ ግንባታ ሥራ ለማከናወን በአጀንዳ እና በካላንደር መልክ የሚተላለፉ መልክዕክቶች
ዓይነተኛ መሳሪያዎች በመሆናቸው የ2007 አጀንዳና ካሌንደሩ ለማዘጋጀት የሚሰፍሩ መረጃዎች፣
መልዕክቶች፣ ፎቶግራፎችና ጠቃሚ አድራሻዎች የማሰባሰብና የማደራጀት ሥራ ቢከናወንም በግዥ
ሂደት መጓተት ምክንያት ሥራው ባለመጠናቀቁ የተሰባሰቡ መረጃዎች ወደ 2008 በጀት ዓመት
እንዲሸጋገሩ ተደርጓል፣
 ችሎት ቁጥር 3 መፅሔት ባለ 70 ገፅ መፅሄት ሚያዚያ 2007 ታትሞ ለባለድርሻ አካላት፣ ለክልል
የፍትህ አካላት፣ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ለፍ/ቤቱ ተገልጋዮች፣ በአጠቃላይ ከ 320 በላይ
ለሚሆኑ መንግታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ለፍ/ቤቱ ማህበረሰብ እንዲሰራጭ
ተደርጓል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 9


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 የመፅሔቱ የፅሁፍ ይዘት ጥራት ብስለትና ክብደት በተመለከተ የአንባቢው ግብረመልስ የሚሻ ቢሆንም
መፅሔቱ ሌሎች የመንግስት ተቋማት ከሚያሳትሟቸው ዓመታዊ ህትመቶች አንፃር ሲገመገም
ደረጃውን የጠበቀ ነው ማለት ይቻላል፣
 በመሰለ መልቲ ሚዲያ በሚዘጋጀው ሽግግር መፅሄት ጋር በመተባበር (ስፖንሰር በማድረግ)
የፍርድቤቱን የእድገትና ትራንስፎረምሽን ዕቅድ አፈፃፀም፡ ስለዳኞች የስራ ሸክምና ከባድ ሃላፊነት
በተመለከተ በመፅሄቱ 12 ገጥ ላይ ሽፋን አግኝቷል፡፡ መፅሄቱ በተለይ በአስፈፃሚ ተቋማት ሰፊ
ስርጭት ያለው ስለሆነ የዳኝነት አካሉ የስራ ሸክም ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ በኩል
የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፣
 በበጀት ዓመቱ ስድስት ብሮሸሮችን ለማሳተም ታቅዶ ስድስቱንም ብሮሸሮች ማዘጋጀትና ማሰራጨት
የተቻለ ሲሆን የሁለት ተጨማሪ ብሮሸሮች ዝግጅት በሂደት ላይ ይገኛል፣
 ቡክሌት ማዘጋጀት በበጀት ዓመቱ ዕቅድ የተካተተ ባይሆንም በበርካታ ፎቶግራፎች የተደገፉ አንድ
የአማረኛ እና አንድ የእንግሊዘኛ ቡክሌቶች ተዘጋጅተው ለህትመት በቅተዋል፡፡
 የህጻናት የህግ ከለላ ማዕከል አገልግሎቶችን የሚያሳይና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የሚሰጥ በራሪ ጽሁፍ
በ5,000 ኮፒ ለህትመት በማብቃት እንዲሰራጭ ተደርጓል፣
 የህጻናት ፍትህ አስተዳደሩን በሐገር አቀፍ ደረጃ ለማሻሻል የሚደረጉት ዓመታዊ የምክክር መድረኮች
ውጤት የሆነውና ሁሉም ክልል ግብዓት ሰጥቶበት በጋራ የጸደቀው በዳኝነት ስርአት ውስጥ ለሕፃናት
ምቹ እና ወጥ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት የሚያግዝ መለኪያ/መመሪያ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ
ለዳኝነት አካሉ ባለሙያዎች ተደራሽ እንዲሆን በ3,000 ኮፒ ታትሞ ተሰራጭቷል፣
 የፕሮጀክት ጽ/ቤቱን ዋና ዋና ተግባራት እና ሌሎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሁፎችን የያዘ ዓመታዊ
መጽሄት ዝግጅት ተጠናቅቆ በ 2000 ኮፒ ተሠራጭቷል፣
 የፌዴራል ፍ/ቤቶች የ2007 ዕቅድ እና የዳኝነትን አገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ ለማስተዋወቅ
በተዘጋጀ የምክክር መድረክ የኢትዮጵያ ቴሌቪዢን ፣ አ.አ መገናኛ ብዙኃን / ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ/
ሬዲዮ ፋና፣ ዛሚ፣ ሸገር ኢትዮጵያ ኘሬስ/ አዲስ ዘመን፣ ሄራልድና በሪሳ ተገኝተው በመዘገብ ሕዝብ
እንዲያውቅ አድርገዋል፣
 የፌ/ፍ/ቤቶች በኢኮቴ አጠቃቀም ያስመዘገቡት ለውጥ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዜናና
የኘሮግራም ሥራ ለመስራት የሁለት ቀናት ቀረፃ ሥራና ቃለ- መጠይቅ ተደርጓል፡፡ ሰፋ ያለ ዜና
ተሰርቶ ተሰራጭቷል፣
 የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ገለልተኛነት ዋና ተግባርና ወቅታዊ የሥራ አፈፃፀም እንዲሁም
የ2007 የዕጩ ዳኞች ምልመላ ለማካሄድ የወጣው የተወዳዳሪዎች የምዝገባ ስርዓት በተመለከተ በሸገር
ሬዲዮ ጣቢያ በተደጋጋሚ የዜናና የዘገባ ሽፋን እንዲሰጠው ተደርጓል.
 በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥ የሰባት ወርና የዘጠኝ ወር አፈፃፀም የተመለከተ ዘገባ
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፡ በሬደዮ ፋና፤ በሸገርና በዛሚ የኤፍኤም ሬድዮ ጣቢያዎች ተላልፏል፣
 የፌ/ፍ/ቤቶች የ10 ወር የስራ አፈፃፀምና የዳኝነት አካሉ የአይሲቲ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም
በተደራሽነት፤ በቅልጥፍናና የተገልጋዮችን ወጪ ከመቀነስ ጊዜ ከመቆጠብ ያሰገኛቸው ለውጦች
በተመለከተ በአዲስ አበባ ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ተላልፏል፣
 ስለ ሐሰት ምስክርነት፣ ስለይግባኝ፣ ስለችሎት መድፈር፣ ስለ ዳኝነት ሥልጣን በተመለከተ የሕግ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ በአዲስ ዘመን ጋዜጣና በአዲስ አበባ መገናኛ
ብዙኃን በዳኞች መግለጫ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 10


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 የተቋሙ ዳኞችና የሲቪል ሠራተኞች ከጥር 29 እስከ የካቲት 1/2007 የህዳሴ ግድብ ጉብኝት
በማድረግ ስራው ያለበትን ደረጃ ለማየት እንዲችሉ ተደርጓ፣
 የፌደራልና የክልሎች የፍትህ አካላት አስተባበሪ ባዘጋጀውና ከመጋቢት 9 እስከ 13/2007 በመቀሌ
ከተማ በተካሄደው የምክክር ጉባኤ የሚዲያና የዶክሜንቴሽን እንዲሁም ፕሮግራሙን የማስተባበር ስራ
ተከናውኗል፡፡
 የተለያዩ የህፃናት የህግ የማህበራዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮችን በመለየትትና የህፃናትን የህግ ከለላ ማዕከል
የሚሰጠውን ድጋፍ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ በሚሆን መልኩ በአጫጭር የቪዲዮ ኪሊፖችን
በማዘጋጀት የህፃናት ጉዳዮች በሚታዩባቸው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የባለጉዳይ መጠበቂያዎች
ቦታዎች ላይ እንዲታዩ ለማድረግ ተችሏል፡፡
 የፍርድ ቤቱን የአሰራር ስርዓት የሚያስገነዝቡ፣ የፍትህ ተደራሽነትን የሚያጎለብቱ፣ በፍ/ቤቶች
የሚሰጡ ባለብዙ ዘርፍ አገልግሎቶችን የሚያስተዋውቁ፣ የፍ/ቤቱን ማህበረሰብ የለውጥ አመለካከት
የሚያጎለብቱና የመፈጸም አቅምን የሚጨምሩ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ከ3ዐ በላይ የግልና
የመንግሥት ሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞችና ከ2ዐ በላይ የፌዴራል ተቋማት የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች
የተሳተፉበት የጉብኝት ኘሮግራም በማዘጋጀት የሚዲያ ተቋማት እንዲዘግቡት ተደርጓል፣

4.2 አሳታፊነትን ማጎልበት የሚያስችሉ አሠራሮችን ለማሳደግ ታቅዶ


የፍ/ቤቶች ተጠቃሚ ሕብረተሰብ በፍ/ቤቶች አሠራር፣ አደረጃጀትም ሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት
የታዘባቸውንና የሰብዓዊ መብት አጠባበቅን ጨምሮ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ያላቸውን አስተያየቶች
የሚገልጽበት ሥርዓት ተዘርግቷል፣

 ከሚያዝያ 2ዐ-26/2ዐዐ7 «ፍትህ ለሁለንተናዊ ዕድገት» በሚል መሪ ቃል በተከበረው


አምስተኛው የፍትህ ሳምንት የፌዴራል ፍ/ቤቶችም ዝግጅታቸው በማቅረብ የፍ/ቤቱን
የአምስት ዓመት (2003-2007) የስራ አፈፃፀምን ጨምሮ በረካታ መልእክቶች ማስተላለፍ
ተችሏል፣
 ለአንድ ሳምንት ክፍት ሆኖ በቆየው በዚህ የፍትህ ኤግዚብሽን ሳምንት ፍ/ቤቶችን
የሚመለከቱና የተለያዩ መልዕክቶችን የሚያስተላፉ 90 ፎቶግራፎች፣ የ1997- 2001 እና
የ2003-2007 የፍ/ቤቶች አፈጻጸም በንጽጽር የሚያሳዩ ሰንጠረዦችና ግራፎች፣ የፌዴራል
ዳኞች ቁጥር በየዓመቱ ያሳየውን ዕድገት የሚያመላቱ ቻርቶች፣ የፌዴራል ፍ/ቤቶችን የተለያዩ
ሥራ ዘርፎች የአምስት ዓመት አፈጻጸም ንጽጽር የሚያሳዩ ሰንጠረዦች፣ የፌዴራል ፍ/ቤቶች ዳኞችን
እና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን ብዛት፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የጾታ ተዋጽዖ የሚያሳይ በአኃዝ
የተደገፈ የንፅፅር ሠንጠረዥ እና ኢለሊቲጌሽንና ቪዲዮኮንፍርንስን ጨምሮ የተለያዩ
የዳኝነት
አገልግሎት የሚሰጥባቸው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶች በስዕላዊ መግለጫ
ለዕይታ በቅተዋል፣
 በዚህም 992 ነጻ የጥሪ ማዕከል በመጠቀም በአማካይ በቀን ከ 500 በላይ ጥሪዎችን በማስተናገድ ላይ
ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ 125,000 በላይ ጥሪዎችን አስተናግዶ መረጃዎችን በመስጠትና በመቀበል
የተለያዩ የማሻሻያ አስተያየቶችን ለማግኘት ተችሏል፣
 የፍ/ቤቶች ማህበረሰብ በስልጠና ያዳበራቸውን የሥነ ምግባርና የመልካም አስተዳደር መርሆች የዕለት
ተዕለት የሥራ ባህል እንዲያደርጉዋቸው የአስተያየት መስጫ ሳጥኖች እና ደብተሮች ተዘጋጅተው

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 11


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

የፍ/ቤቱን ሠራተኞች፣ ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካት አስተያየት በማሰባሰብ የእርምት እርምጃዎችን


ለመውሰድ ያስቻሉ መረጃዎችን ለማግኘት ተችሏል፣
 እንዲሁም የጥቆማ መዝገቦች ተዘጋጅተው ከውስጥ እና ከውጭ ተገልጋዮች በየዕለቱ የሚቀረቡ
ጥቆማዎች በመስተናገድ ላይ ይገኛሉ፡፡
 በብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የደርጊት መርሃግብር አፈጻጸም በመሪነትና በተባባሪነት የተወሰዱ
ኃላፊነቶችን አፈጻጸም ለማጠናከር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ተችሏል፣
 በዚህም የ2007 በብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የደርጊት መርሃግብር ዕቅድ እና የበጀመት ዓመቱን
አፈጻጸም የሚገልጽ ሪፖርት ተዘጋጅቶ ለፍትህ ሚ/ር ጸልኳል፣ ሌሎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው
አካላትም (ባህል ሚ/ር/፣ ሲቪል ሰርቪስ ሚ/ር፣ ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር ወዘተ…) የጠየቁዋቸው
የአፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲደርሳቸው ተደርጓል፣ በጋራ መድረኮችም በመገኘት ተሳትፎ ተደርጓል፣

4.3 የመረጃ ነጻነት ሕጉን ትግበራ በማጠናከር የመረጃ ጠያቂዎችን ፍለጎት ለማሟላት በተያዘው
ዕቅድ፡-
 በመረጃ ነጻነት ሕግ እንዳይገለጹ ከተፈረጁት በስተቀር በየፍ/ቤቶች ችሎቶችና ሥራ ክፍሎች የተያዙ
መረጃዎች በሚመለከተው ክፍል አማካኝነት ተሰባስበውና በአግባቡ ተደራጅተው ባለፉት በበጀት ዓመቱ
46 የሚዲያ ተቋማትና 526 መረጃ ፈላጊ ዜጎችና ተቋማት ተስተናግደዋል፣
 የመገናኛ ብዙኃን ለፍ/ቤቱ ተገቢው ቦታና ሽፋን እንዲሰጡና በዕቅዳቸው እንዲያካትቱት ለማድረግ
ከኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ ከኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት፣ ከሸገር እና ከዛሚ ጋር ስምምነት ተፈጥሯል፣
ፍ/ቤቶችን የሚያከናውኑዋቸው ተግባራትና ትኩረት የሚሹ የሥራ ዘርፎችን በተመለከተ ለየተቋማቱ
ለዘጋቢ ጋዜጠኞች ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
 በዚሁ መሠረት በተለይ የኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ የኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት እና ሸገር ኤፍ ኤም ወደ ሥራ
ገብተው ሽፋን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
 በፍ/ቤቱ ድረ-ገፅ ባለው ጥቂት የሰው ኃይል ቢያንስ በወር አንድ ዜና መረጃዎችን ለመጫን ታቅዶ
በበጀት ዓመቱ ፍ/ቤቱን የሚመለከት ዘጠኝ ዜናዎች እንዲጫኑ ተደርጓል፡፡
 የ132 ሰዓት የቪዲዮ ቀረፃ እና የፎቶግራፍ ማንሳት ሥራ ተከናውኗል፡፡ ከዚህ ውስጥ 680 ፎቶ
ግራፎች ተመርጠው በፎቶ ዜና መልክ ታጥበው የተቋሙ ማህበረሰብ እንዲመለከታቸው ተደርጓል፡፡
ስድስት የሚሆኑ ፎቶግራፎችም በድረ-ገፅ ላይ ተጭነዋል፡፡
 ከለጋሽ ድርጅቶች በሚገኘው ድጋፍ ከችሎት ሚዲያ ፕሮግራም ጋር በተገባው ውል መሰረት
ለማህበረሰቡ በህጻናት ጉዳይ ላይ ግንዛቤ ሊያስጨብጡ የሚችሉ የቴሌቪዥን ድራማዎች እየተሰራጩ
የሚገኙ ሲሆን 6 ያህል የሚዲያ ፕሮግራም ለማስተላለፍ ተችሏል፣
 ስለችሎት አጋዥ ማህበራዊ ሳይንስ ክፍል አገልግሎት የሚያሳዩ ባነሮች በየምድብ ችሎቶቹ
ለህብረተሰቡ መረጃ መስጠት በሚያስችል መልኩ እንዲቀመጥ ተደርጓል፣

ግብ 5. ተደራሽነትን ማሳደግ (አፈጻጸሙ 91.1% ደርሷል)


5.1 በኢኮቴ ተጠቅሞ የዳኝነት አገልግሎቱን ተደራሽነት ለማጎልበት በተያዘውን ዕቅድ፡-

 በበጀት ዓመቱ 1200 መዝገቦችን በኢፋይሊንግ ስርዓት ለመክፈት ታቅዶ 1‚508 መዝገቦችን በመክፈት
አፈጻጸሙ 125.6% ደርሷል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 12


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 በቪዲዮ ኮንፍረንስ አማካኝነት በሁሉም ፍ/ቤቶች 3‚100 የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ1‚518፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ በ 4‚886 መዝገቦች
ላይ አገልግሎቱን መስጠት በመቻሉ አፈጻጸምን 206.5% ለማድረስ ተችሏል፣
 የቪዲዮ ኮንፍረንስ ማዕከላት ለማስፋፋት በተደረገ ጥረት በቤኒሻንጉል ጠቅላይ ፍ/ቤት አሶሳ ከተማ እና
በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቦንጋ ከተማ እንዲሁም በፌዴራል ከፍተኛፍ/ቤት
አራዳ ምድብ ችሎት የቪዲዮ ኮንፈረንስ ማዕከል በመክፈት አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል፣
 የቪዲዮኮንፍረንስ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን በመከታተልና በመገምገም ለሥርዓቱ እንቅፋት
የሚፈጥሩ የቴክኒክ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ ተደርጓል፣
 በአጠቃላይ በጠቅላይ እና በከፍተኛ ፍ/ቤት የሚሰጠውን የቪዲዬ ኮንፍርንስ አገልግሎት በማጠናከር
አገልግሎቱ የሚሰጡባቸውን ቦታዎች 32 ለማድረስ ተችሏል፣

5.2 የተዘዋዋሪ ችሎቶችን ለማጠናከር ታቅዶ ፡-

 ተዘዋዋሪ ችሎቶችን በማስፋፋትና በማጠናከር ዳኞች ተገልጋዮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች እየተገኙ


የዳኝነት አገልግሎት እንዲሰጡ በተደረጉ ጥረቶች አፋር፣ አሶሳ፣ ጋምቤላና የደቡብ ክልሎችን የሸፈነ
የዳኝነት አገልግሎት ተሰጥቷል፣
 በደቡብ ክልል በሃዋሳ፣ በአርባምንጭ፣ በሚዛን፣ በቦንጋ፣ በቡታጅራ ወዘተ… የተዘዋዋሪ ችሎት
አገልግሎቶች ተሰጥተዋል፣
 በችሎቶች አፈጻጸም የሚከሰቱ ችግሮችን በመለየት ችሎቶችን ማበራከትና አገልግሎቶችን ማስፋፋት
የሚያስችሉ መፍትሄዎችን የማመላከት ተግባራት ተከናውነዋል፣

5.3 በጉዳዮች አይነትና ይዘት የተከፋፈሉ የችሎት አደረጃጀቶችን ለማጠናከር የተያዘው ዕቅድ፡-

 የህዝብ አሰፋፈርና ብዛት መሰረት በማድረግ ምድብ ችሎቶችንና ችሎቶችን ለማስፋፋትና ለማጠናከር
በተደረጉ ጥረቶች ከ 2006 በጀት ዓመት መጨረሻ ጀምሮ በከፍተኛ ፍ/ቤት ደረጃ በአራዳ ክፍለ ከተማ
ሶስት ችሎቶችን የያዘ አንድ ምድብ ችሎት፣ በልደታ ሶስት የወንጀል ችሎቶችን የያዘ አንድ ምድብ
ችሎት እና የተለዩ ጉዳዮች የሚስተናገዱባቸው አምስት የፍትሐብሔር ችሎቶች (Specialized
Bench) እንዲከፈቱ ተደርጓል፡፡
 በፌ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ድሬድዋን ጨምሮ አስራ አንድ ምድብ ችሎቶች የተደራጁ ሲሆን
ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ አዲስ አበባ በአሥሩም ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ምድብ ችሎቶች 23
ተጨማሪ የወጀንልና የፈትሐብሔር ችሎቶች ተከፍተዋል፡፡
 በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም የተሰሩ የተጠቂ ህጻናት ጉዳዮች የሚታይባቸው 4
ምድብ ችሎቶች የሲሲቲቪ ካሜራዎች ከግዜ ብዛት እና በአጠቃቀም ጉድለት የአገልግሎት ጥራት
ደረጃቸው የቀነሰ በመሆኑና ከቀላል እስከ ከፍተኛ ጥገናና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ፤ ቀደም
ሲል ስራውን ከሰራም ድርጅት ጋር የእድሳት ውል በመግባት ጥገና ተካሂዷል፣
 ችሎቶችን በጉዳዩ ዓይነት በማደራጀት አማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓትን ለመተግበር የተቋቋሙ
የማስማሚያ ጽ/ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ችሎቶች በጉዳዮች ዓይነት ለምሳሌ በፍትሐብሔር ችሎቶች
ስር የቤተሰብ ችሎት፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ችሎት ወዘተ… ተደራጅተው አገልግሎት በመስጠት
ላይ ይገኛሉ፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 13


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 በእነዚህ ችሎቶች አፈጻጸም የሚከሰቱ የአደረጃጀት፣ የአሠራር ሥርዓትና የመፈጸም አቅም ችግሮቹን
ተከታትሎ ለመፍታትና ውጤታማነታቸውን ለማሳደግ እንዲቻል ዕቅዶች በየደረጃው አሳታፊ በሆነ
መልኩ እንዲዘጋጁ ከመደረጋቸውም በላይ ከዓመታዊ ዕቅድ የተመነዘሩ ወቅታዊ ዕቅዶች ተለይተው
እየተፈጸሙ የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል፣

5.4 አማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓትን ለማስፋፋትና ለማጠናከር የተያዘው ዕቅድ፡-

 በፌዴራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍ/ቤት የግልግል ዳኝነት አገልግሎት የሚሰጡ የማስማሚያ ጽ/ቤቶች
ተደራጅተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፣ በዚህም የፍ/ቤቶች ጫና በመቀነስ ረገድ ብዙ
የሚቀር ቢሆንም ተከራካሪዎች ጉዳያቸውን በስምምነት ለመፍታት የሚችሉባቸው ምቹ ሁኔታዎችን
ተፈጠርዋል፣
 በአማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓት የሚሳተፉ የህግ ባለሙያዎች (ረዳት ዳኞች) ተመድበው
አመለካከትና የመፈጸም አቅም የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን በመውሰድ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ
ይገኛሉ፣
 በጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘረጋውን ተከራካሪዎችን የማስማማት ሥርዓት አፈጻጸም በመከታተል፣
በመደገፍና በመገምገም ክፍተቶችን እየለዩ ማስተካከያዎችን ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት
በመከናወን ላይ ይገኛሉ፣
 የሥርዓቱን ውጤታማነት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለማጎልበት የሚያስችሉ ድጋፎች በመደረግ ላይ
ሲሆኑ በየፍ/ቤቶች ለተደራጁ ጽ/ቤቶች የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች በመሟላት ላይ ናቸው፤
 የሥርዓቱን አፈጻጸምና ጥቅሞች ለሕብረተሰቡ ማስተዋወቅና ተደራሽ የሆነ ፍትህ የማግኘት መብት
ተጠቃሚነቱን አጎልብቱ የፍ/ቤቶች ጫና እንዲቀንስ ለማድረግ የሚያስችሉ የማስተዋወቅ ሥራዎች
በተፈለገው ፍጥነትና መጠን ባይፈጸሙም የተወሰኑ ጅምሮች ታይተዋል፣

5.5 የተከላካይ ጠበቆችን አደረጃጀትና አሠራር ለማጠናከር በተያዘው ዕቅድ፡-

በከባድ ወንጀል ለተከሰሱና ተከላካይ ጠበቃ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ነጻ


የተከላካይ ጠበቃ አገልግሎት እና የሙያ ምክር ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል የአሠራርን አጠናክሮ
በመቀጠል፡-

 በ 2‚6ዐዐ መዛግበት ለተከሰሱ 3‚15ዐ ተጠርጣሪዎች የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ በ 7‚201
መዛግብት ለተከሰሱ 9‚585 ተጠርጣሪዎች የጥብቅና አገልግሎት በመሰጠቱ አፈጻጸሙን 243%
ለማድረስ ተችሏል፣
 ለ 9‚600 ተገልጋዮች የምክር አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለ 8‚078 ተገልጋዮች የምክር አገልግሎት
በመስጠትና ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ 72% ደርሷል፣
 ፈጻሚዎች የተጠቀሙባቸውን መረጃዎች በጥራት በመያዝ ለሌሎች እንዲያስተላልፉ በዕቅድ ከተያዙ
378 መዛግብት 117 ጠብቆ ማስተላለፍ በመቻሉ አፈጻጸሚን 33.3% ደርሷል፣
 የተከላካይ ጠበቆችን አቅም የሚገነቡ ሁለት ስልጠናዎችን ለመስጠት ቢታቀድም አንድ ስልጠና ብቻ
በመሰጠቱ አፈጻጸሙ 50% ደርሷል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 14


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 የተከላካይ ጥብቅናን የግልጽነትና ተጠያቂነት አሰራር ከማሳደግ አንፃር የ 50 ተገልጋዮችን አስተያየት


እና 25 ቅሬታዎች ማስተናገድ ከመቻሉም ሌላ በተገኙ አስተያየቶች መሰረት ማስተካከያዎችን
ማድረግ የሚያስችሉ ጥረቶች ተጀምረዋል፣
 የተከላካይ ጽ/ቤቶችን በሁሉም ፍ/ቤቶች ማደራጀት ባይቻልም በሥራ ላይ ያለው ጽ/ቤት የሁሉንም
ፍ/ቤት ችሎቶች መሸፈን ያስቻለ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፣

5.6 የአስተርጓሚ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ታቅዶ

 አስተርጓሚ ለሚያስፈልጋቸው ተከራካሪዎችና ምስክሮች አስተርጓሚ ለመመደብ የሚያስችለውን


ሥርዓት በማጠናከር ለ 647 ተከራካሪዎችና ምስክሮች የትርጉም አገልግሎቶች ተሰጥቷል፣
 የትርጉም አገልግሎት የሚሰጡ የቋንቋ ባለሙያዎችን አቅም የሚያጎለብቱ ስልጠናዎች ተዘጋጅተዋል፣
 የባለሙያዎችን አፈጻጸም ተከታትሎ በመደገፍና በመገምገም ክፍተቶች ተለይተው እንዲሞሉ
ተደርገዋል፣
 በአጠቃላይ የውጭ ሀገር እና የአገር ውስጥ ቋንቋ ለማይችሉ ተገልጋዮች የትርጉም አገልግሎት
ለመስጠት ከተያዘው እቅድ 70% ማከናወን ተችሏል፣

5.7 ባለ ብዙ ዘርፍ ጉዳዬች (አካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች፣ ህፃናት፣ አርብቶ አደሮች፣


አረጋውያን፣አቅመ ደካሞች ወ.ዘ.ተ…) የሚስተናገዱባቸውን አሠራሮች ለማጠናከር
በተያዘው ዕቅድ፡-
 አዲስ በሚገነቡ ሕንጻዎች ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካሞቸ አመች የሆኑ የችሎት
ቢሮ አደረጃጀቶች እንዲኖሩ፣ ከሌሎች በተሻለ ሁኔታ ተቀብሎ በማስተናገድ ቅድሚያ አግኝተው
የፍ/ቤቶችን አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፣
 የፍ/ቤቶች ተገልጋይ የሆኑ አነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ቅድሚያና አክብሮት አግኝተው
በመስተናገዳቸውም የሬጅስትራር እና የችሎት አገልግሎቶችን ጨምሮ በተለያዩ ሥራ ክፍሎች
በተሰጡ አገልግሎቶች መርካታቸውን ገልጸዋል፣
 ለጥቃት የተጋለጡና የህግ ከለላ የሚያስፈልጋቸው ሴቶችና ሕጻናትን ለመደገፍ የተዘረጋው
የቅብብሎሽ ሥርዓት አጠናክሮ የሚሰጠውን የህግ፣ የማህበራዊና ስነልቦናዊ ድጋፍ ለማሳደግ
በየግላቸው የህግ ድጋፍ ከሚሰጡ አካላት ጋር የጋራ ውይይት መድረኮች ተዘጋጅተዋል፣
 በቅብብሎሽ ስርዓቱ በፍትሕ ስርዓት ውስጥ ለሚያልፉ ህፃናት የሚሰጠውን አገልግሎት አሁን ካሉት
ሶስት ማዕከላት በተጨማሪ በክልሎችም (በአማራ፣ በኦሮምያ፣ በደቡብ ) ለማስፋፋትና ነባር
ማዕከላትን አቅም ለማሳደግ በተያዘውን ዕቅድ መሰረት ጥናቶች ተካሂደው ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን
ማድረግ ተጀምሯ፣
 ከዚህ ጋር በተያያዘ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንቶች፣ ተከላካይ
ጠበቆች ቢሮ፣ ፍትህ ቢሮ፣ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያሉ የነጻ የህግ ድጋፍ መስጫ ማዕከላት
ተወካዮች፣ ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ነጻ የህግ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም
ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ብሔራዊ ነፃ የህግ ድጋፍ ቅንጅት ለማቋቋም ተችሏል፣
 ለህጻናት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመው የቅብብብሎሽ ሥርዓቱን ውጤታማነት፣
ያሉበትን የጥራት ደረጃና የሚታዩበትን የአፈጻጸም ክፍተቶች ለይቶ ማስተካከያዎችን በማድረግ
ተደራሽነቱን አጠናክሮ ለመቀጠል መወሰድ የሚገባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች መለየት የሚያስችል

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 15


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ውጤት ተኮር የዳሰሳ ጥናት ተካሂዷል፣ አስፈላጊ የሆኑ የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ሥራዎችም
ተሰርተዋል፣
 በህጻናት የሕግ ከለላ ማዕከል አማካኝነት ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ በርካታ ህጻናት የህግ፣
የማህበራዊና ስነልቦናዊ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ በተቻለ መጠን አማራጭ የግጭት መፍቻ
ሥርዓትን ተጠቅመው ጉዳያቸውን እንዲጨርሱ ተደርጓል፡፡
 በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር የሚገኙ የአራት ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች የህጻናት ጥበቃና
ማቆያ ክፍሎችን በማደራጀት የቁሳቁስ ግዢው ተጠናቆ ክፍሎቹን በፓርቲሽን የመለየት ስራ
ተጠናቅቋል፣
 በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚገኘው የችሎት አጋዥና አገናኝ የማህበራዊ ሳይንስ ክፍል አሰራር
ለህጻናት ምቹ እንዲሆን የሚያደርጉ ድጋፎችን በማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች ተለይተው የግዢ
ሂደቱ ተፈጽሟል፣
 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በህጻናት ፍትህ አስተዳደር ዙሪያ ያለውን ሚና እና ያሉትን ክፍተቶች
የሚያሳይ ጥናት ተጠናቆ በጥናቱ ግኝቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች መሰረት በቀጣይነት መወሰድ
በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ ያተኮሩ ተግባራት ተከናውነዋል፣
 በፌደራል ፍርድ ቤቶች (ድሬዳዋን ጨምሮ) የሚሰሩ ሬጅስትራሮች፣ የዳታ ቤዝ ሰራተኞችና ፋይል
ከፋቾች በአጠቃላይ 112 ተሳታፊዎች የተካፈሉበትና በህጻናት የተሟላ መረጃ አያያዝ ስርአት ላይ
ያተኮረ የውይይት መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን በዚህ የውይይት ከመረጃ ቋት የማሻሻያ ስራ በተጨማሪ
የዘርፉ ባለሙያዎች በመረጃ ቋቱ በሚገቡ መረጃዎች ምሉዕነትና ጥራት ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው
ተደርጓል፣
 ከአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር በፌደራል ፍርድ
ቤቶች ለሚሰሩ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ከሱስ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮችን
ማሳወቅ ያስቻለ የ2 ቀን ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው 24 ባለሙያዎች (8 ሴቶች) ተሳታፊ
ሆነዋል፣
 ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ከህጻናት ጉዳይ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ካላቸው የክልልና
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣ ከዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ መምህራንና ተማሪዎችን ለተውጣጡ እና
101 ለሚሆኑ ባለሙያዎች በፍትህ ስርዓት ስለሚያልፉ ሕፃናት፣ በሴቶች ላይ ስለሚፈፀሙ የቤት
ውስጥ ጥቃቶች ተፈጻሚ ስለሚሆኑ የሕግ ማዕቀፎች እና ስለምርመራ አካሄድ፣ በወንጀል ለተሳተፉ
ሕፃናት ተፈጻሚ ስለሚሆኑ የወንጀል ሕግ ስነስርዓት እና ከሕፃናት ሕግ ከለላ ማዕከል ጋር በቅርበት
እና በተጠናከረ መልኩ አብሮ መስራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ሁለት ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና
ተሰጥቷል፣
 በአጠቃላይ በ 2007 በጀት ዓመት ለ 687 የፍትህ ስርዓቱ ባለሙያዎች በህጻናት ፍትህ አስተዳደርና
ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት 275 ሴቶችን ማሳተፍ
ያስቻሉ በርካታ በስልጠናዎች ተሰጥተዋል፣ በፍትህ ስርአት ለሚያልፉ ሕጻናት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ
ለመስጠት በተቋቋመው የቅብብሎሽ ስርዓት ላይ ያተኮሩ በርካታ የውይይት መድረኮችም
ተዘጋጅተዋል፣
 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች የጥያቄና መልስ ውድድር፣ ዕለቱን አስመልክቶ
አስተማሪ ብሮሸሮችን በማዘጋጀትና የስነ ጽሑፍ ዝግጅት በማቅረብ አስተማሪና አሳታፊ በሆነ መልኩ
ተከብሯል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 16


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 ከሥርዓተ ጾታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አስተማሪ ብሮሸሮች አዘጋጅቶ ለማሠራጨት በተያዘው ዕቅድ


በ 500 ቅጅ የተሰራጩ የተለያዩ ብሮሽሮች ተዘጋጅተው ዕቅዱን 100% መፈጸም ተችሏል፣
 የኢትዮጵያ የሴቶች ማሕበራት ቅንጅት የጾታዊ ጥቃት ሁኔታና የፍትህ ሥርዓቱ እና የተለያዩ
የፖሊስ ማእቀፎች ለሴቶች እና ሕጻናት ጥቃቶች ያለውን ምላሽ ለመዳሰስ ባዘጋጀው የውይይት
መድረክ ላይ ከፌ/ፍ/ቤቶች የተውጣጡ 35 የሚሆኑ ልዩ ልዩ ባለሙያዎች ተካፋይ እንዲሆኑና
ያላቸውን ልምድ እንዲያካፍሉ ተደርጓል፡፡

5.8 የሰበር ውሳኔዎችንና ሌሎች የህትመት ውጤቶችን ዝግጅትና ሥርጨት ለማሻሻል በተያዘው
ዕቅድ፡-
 የሠበር ውሣኔዎችን የያዙ ሕትመቶች በጥራት እንዲዘጋጁና በበቂ ቅጅ ታትመው የተገልጋዮችን
ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ እንዲሰራጩ ለማድረግ የቅጽ 14፣ 15 እና 16 ህትመትና ስርጭት
የተጠናቀቀ ሲሆን ቅጽ 17 ለማሳተም የሚያስችሉ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ Soft copy በፌ/ጠ/ፍ/ቤት
ድረ ገጽ ተጭኖ ለሕዝብ እንዲደርስ ተደርጓል፣
 ከዚህ በፊት ለህትመት ያልበቁና እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸውን
የሰበር ችሎት ውሳኔዎች በማሰባሰብና ተገቢውን ጭብጥ በመለየት ለሕትመት የሚበቁበትን ሁኔታ
የማመቻቸት ተግበር ተከናውኗል፣ ፣
 ቀደም ሲል የታተሙ ቅጽ 6-13 የሰበር ውሳኔዎችን ድጋሚ ሕትመት ለመስራት የሚያስችሉ
ዝግጅቶች ተጠናቅቀዋል፣
 በቅፅ መልክ የተዘጋጁ የሰበር ውሳኔዎችን ማውጫ ሰንጠረዥ በማሻሻል በተቋሙ ድረ-ገፅ
ተጭነዋል፣
 የፌዴራልና የክልል አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን አሰባስቦ ለተጠቃሚው ለማድረስ በተደረገ
ጥረት የተለያዩ ክልሎች አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን አሰባስቦ ለዳኞች ማሰራጨት ተችሏል፣
 የፌዴራል ፈ/ቤቶችን ቤተመጻሕፍት ለተጠቃሚዎች ምቹ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ
ተግባራትን በማከናወን የተቋሙን ቤተ-መጽሐፍት ለማጠናከር ብዛታቸው 288 የሆነ 108 ዓይነት
መጻህፍት በብር 38‚534.50 ተገዝተው አገልግሎት ላይ ወለዋል፣

በአጠቃላይ የጥናትና ሕግ ድጋፍ አገልግሎቶችን በማጠናከር የሰበር ውሳኔዎችን የያዙ ቅጾችን ማሳተምን
ጨምሮ የሕግ ጥናቶችን ለማካሄድና የተለያዩ የሕግ ጆርናሎችን አዘጋጅቶ ለማውጣት የሚደረጉ ጥረቶች
ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡

ግብ 6.ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን ማሳደግ (አፈጻጸሙ 85.62% ደርሷል)

6.1 በግልጽ ችሎቶች የመሰየም ልምድን ለማዳበር በተያዘው ዕቅድ ፡-


 የቢሮ አደረጃጀቶችን በማሻሻል በግልጽ ችሎት የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረቶች
በመደረግ ላይ ሲሆኑ በተወሰነ ደረጃ ለውጥ ማምጣት ተችሏል፣ የቢሮ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ
ማስወገድ ግን አልተቻለም፣
 የግልጽ ችሎት አሠራሮችን ለማጠናከር የሚያግዙ ክትትልና ድጋፎች የተደረጉ ሲሆን በዳኞች ወርሃዊ
የአፈጻጸም ግምገማ ወቅት በግልጽ ችሎት ለመሰየም እንቅፋት ለሚሆኑ ችግሮች የመፍትሄ
አቅጣጫዎች ተጠቁመዋል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 17


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

6.2 የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎችን የአሠራር ግልጽነት ለማጎልበት በተያዘው ዕቅድ፡-

 የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች ለዳኝነት ዘርፉ የሚያደርጉትን የድጋፍ አገልግሎት በተሟላ መልኩ
ለመስጠት የሚያስችል የአሠራር ግልጽነት እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚረዱ ክትትልና ድጋፎች
የተደረጉ ሲሆን አፈጻጸማቸውን እየገመገሙ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል አሠራር መተግበር
እየተለመደ መጥቷል፣
 በዚህም እያንዳንዱ የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍል የሳምንት ዕቅድ አፈጻጸሙን በመገምገም ጠንካራ
አፈጻጸሞችን ማበረታታትና ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችሉ አሠራሮችን በማጠናክ ለይ ይገኛል፣
 ወርሃዊ የግምገማ ሪፖርቶችን ማዘጋጀትና ለሚመለከታቸው ክፍሎች አድርሶ በመረጃ ምንጭነት
እንዲያገለግሉ የማድረጉ ሥራም ተጠናክሮ ቀጥሏል፣

6.3 የተጠያቂነት ሥርዓትን ለማጠናከር በተያዘው ዕቅድ፡-

 በዳኝነት ዘርፉ የሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታዎች በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በኩል በመስተናገድ
ላይ ሲሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎችን በተመለከተ የሚቀርቡት በሥነ ምግባር ክፍል እና
በዲስፕሊን ኮሚቴ አማካኝነት በመስተናገድ ላይ ይገኛሉ፣
 በዚህም ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩና የመልክም አስተዳደርና የሥነ ምግባር መርሆች እንዲተገበሩ
በማድረግ የፍ/ቤት ተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ በአፈጻጸም ለሚከሰቱ ችግሮች የሚቀርቡ
አቤቱታዎችና ቅሬታዎች የሚስተናገዱበት ሥርዓት ተዘርግቶ በመተግበር ላይ ይገኛል፣
 በበጀት ዓመቱ በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤቱ በኩል ዳኞችን የሚመለከቱ 72 የዲሲፕሊን
አቤቱታዎች የቀረቡ ሲሆን በፍርድ ምርመራ ተጣርተው ለጉባዔው ከቀረቡ 21 የዲሲፕሊን
ቅሬታዎች ውስጥ 15 ቱ በዲሲፕሊን የማያስጠይቁ በመሆናቸው ተዘግተዋል፣
 በ 6 ዳኞች ከቀረቡ አቤቱታዎች 3ቱ ዳኞች የጽሁፍ መልስ እንዲሠጡ፣ 1 ዳኛ ጉባዔው ፊት
ቀርበው የቀረበባቸውን ቅሬታ እንዲያስተባብሉ፣ 2 ዳኞች ከስራቸው ታግደው ለጉባዔው የጽሁፍ
መልስ እንዲሠጡና በአካል ቀርበውም እንዲያስረዱ ተደርጓል፣
 ጉባዔው በ 6 የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ከዳኞች የተሠጡ መልሶችን መርምሮ፤ 2 ዳኞች የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ፣ 1 ዳኛ የቃል ማስጠንቀቂያ፣ 1 ዳኛ የቀረበባቸውን ቅሬታ በአግባቡ አስተባብለዋል
በሚል ነጻ እንዲሆኑ የወሠነ ሲሆን፤ 1 ዳኛ የዲሲፕሊን ጥፋት መፈጸማቸውን በማረጋገጥ ውሳኔ
ለመስጠት እንዲቻል ዳኛው በአካል ተገኝተው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፣
 በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸው የተረጋገጠ ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች
በህገመንግስቱ አንቀጽ 79/4//ሀ/ መሠረት ከዳኝነት ሥራቸው እንዲነሱ በጉባዔው የተሠጠ ውሳኔ
ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላልፏል ሹመታቸው ተነስቷል፤
 በሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚቀርቡ የሥነ ምግባር ጥሰትና የዲሲኘሊን
ግድፈት ጥቆማዎች፣ ቅሬታዎችና የዲስፕሊን ግድፈቶችን በማስተናገድ 40 የሚሆኑ የሥነ ምግባር
ጥቆማዎችን በማስተናገድ የማጣራትና ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርጉ ተግባራት
ተከናውነዋል፣
 በአምስት ሠራተኞች በፈጸሙት የዲስፕሊን ግድፈት ለዲስፕሊን ኮሚቴ ክስ ቀርቦ ሁለቱ
ጥፋተኛነታቸው በመረጋገጡ ከሥራ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፣ የቀሪዎቹ ጉዳይ በመታየት
ላይ ይገኛል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 18


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 ግምታቸው ብር 370‚9350.80 በሆነ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አምስት መደበኛ የፍትሐብሔር


ጉዳዮች ላይ ክስ ቀርቦ በ 2 መዝገቦች ላይ ብር 320‚351.34 ለፍ/ቤቱ በመወሰኑ የአፈጻጸም ሂደቱ
እንዲቀጥል ተደርጓል፣ ቀሪዎች 3 መዝገቦች በክርክር ሂደት ላይ ይገኛሉ፣
 በፍ/ቤቶች ውስጥ የተፈጸሙ አምስት የወንጀል ጉዳዮችን ለፖሊስ ሪፖርት በማድረግና ለምርመራ
የሚረዱ መረጃዎችን በማቅረብ የማጣራት ሥራ ተከናውኖ በሶስት ጉዳዮች ላይ ዓቃቢ ሕግ ክስ
እንዲመሰረት ተደርጓል፣ በሁለት መዝገቦች ላይ የማጣራቱ ሥራ ቀጥሏል፣
 አንድ የፍ/ቤት ሠራተኛ የዕምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽሞ ከመ/ቤቱ በመሰወሩ ለፖሊስ አሳውቆ
ተገቢው ክትትል ተደርጎ እንዲያዝ ከተደረገ በኋላ የምርመራ መዝገቡ ተጠናቅቆ የወሰደውን ገንዘብ
ወደ መንግሥት ካዘና እንዲመልስ ለማድረግ ተችሏል፣
 በአጠቃላይ በፌ/ፍ/ቤቶች የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች እና የሥነ ምግባር ግድፈቶች በማስረጃ
ተረጋግጠው ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል፣ ከዚህም በተጨማሪ በ 5 የሙስና ወንጀሎች ላይ
ማስረጃ የማሰባሰብ ስራ ተከናውኗል፡፡
 በፌ/ጠ/ሸሪዓ ፍ/ቤት የተገልጋዮችን ቅሬታ ማስተናገድ ይቻል ዘንድ የሃሳብ መስጫ መዝገብ
ተዘጋጅቷል፤

6.4 የኢንስፔክሽን ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል የሚያስችሉ አሠረሮችን ለማሻሻል ታቅዶ ፡-

 ዳኝነት የተጠየቀባቸው ጉዳዮች ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው በህግ የተቀመጡ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎችን
ተከትለው እየተፈጸመ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከችሎቶችና ከመዝገቦች መረጃ በማሰባሰብ
ለኢንስፔክሽን በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት ችግሮችን የለየና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ አማራጭ
መፍትሄዎችን የያዘ ሪፖርት ተዘጋጅቷል፣
 በዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በኩል የቀረቡ 72 የተገልጋይ ቅሬታ/አቤቱታዎችን በመመርመር የውሳኔ
መነሻ ሀሳቦች ተዘጋጅተው ለጉባዔው ቀርበዋል፣
 ዳኞችም ሆኑ ድጋፍ ሰጪ የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች በለውጥ ሥርዓቱ አተገባበር ንቁ ተሳታፊ
መሆናቸውንና ችግሮቻቸውን ለይተው መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጣቸውን
ማሻሻላቸውን በመከታተል፣ በመደገፍና በመገምገም ወርሐዊ የአፈጻጸም ሂደታቸውን በሪፖርት
እንዲገልጹ ተደርጓል፣
 በሁለም የፌዴራል ፍ/ቤቶች የችሎት ቦታዎች በመገኘት የኢንስፔክሽን ተግባር ተከናውኖ 3 የተሟላ
ኢንሰፔክሽን ሪፖርት እና አንድ ረቂቅ የቅኝት ሪፖርት ማዘጋጀት ተችሎአል፡፡
 በሁሉም የፌ/ፍ/ቤቶች የድሬዳዋም/ችሎቶችን እና የፌ/ሸሪዓ ፍ/ቤቶችን ጨምሮ የናሙና ቅኝት ስራ
ተከናወኖ በ 828 መዝገቦች ላይ በ109 የችሎት ቦታዎች ላይ ቅኝት የተደረገ ሲሆን ከችሎቶችና
ከፍርድ ሥራ መዝገቦች መረጃ በማሰባሰብ 3 የተሟላ የኢንስፔክሽን ሪፖርቶችና አንድ ረቂቅ የቅኝት
ሪፖርት ማዘጋጀት ተችሏል፤
 በዚህም በውስጥ አሰራር በፍርድ ቤቶቹ የታዩ የአሰራር ክፍተቶች በመለየትና ማመላከት ተችሎአል፡፡
 የፌደራል ፍ/ቤቶችን የአገልግሎት አሰጣጥ አስመልክቶ የባለድርሻ አካትን አስተያየት ማሰባሰብ ያስቻለ
የዳሰሳ ጥናት ተካሂዶ ረቂቅ የጥናት ሪፖርት ተዘጋጅቷል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 19


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

6.5 የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃግብር ድንጋጌዎችና የመልካም አስተዳደር መርሆችን


አተገባበር ለማጎልበት በተያዘው ዕቅድ፡-

 በአማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓት የተከፈቱ የማስማሚያ ጽ/ቤቶችን ጨምሮ በሁሉም ችሎቶች
እና የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች የሚሰጡ አገልግሎቶች በተለወጡ አሠራሮች የተቃኙና የሰብዓዊ
መብት ድርጊት መርሃግብር ድንጋጌዎችን ያስከበሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ክትትል፣
ድጋፍና ግምገማዎች ተካሂደዋል፣
 የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ የመልካም አስተዳደርና የሥነ ምግባር መርሆችን የተከተሉ መሆናቸውን
ለማረጋገጥ በተካሄዱ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማዎች አንጻራዊ በሆነ መልኩ ነጻ፣ ግልጽ፣ ገለልተኛ፣
ኪራይ ሰብሳቢነትን የሚታገል፣ ተገልጋዮችን በአግባቡ ማስተናገድ ያስቻለ አገልግሎት ለመስጠት
የሚያስችሉ ጅምሮች መኖራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፣
 በፍ/ቤቶች ውስጥ የሴቶችን ተሳታፊነት ለማሳደግ በሁሉም የሥራ ክፍል ዕቅዶች የሥርዓተ ጾታ
ጉዳዮች መካተታቸውን ለማረጋገጥና የሥርዓተ ጾታ ጉዳይ በየሥራ ዘርፉ ትኩረት እንዲሰጠው
(Gender Mainstreaming) ለማድረግ የሰው ኃይል አደረጃጀትን፤ ሥልጠናና የአቅም ግንባታን፤
የመረጃ አደረጃጀትና አሰባሰብን፤ ተቋማዊ አደረጃጀትን፤ የሥራ መመሪያዎችና ደንቦች ዝግጅትን፣
የዕቅድ ዝግጅት፤ ክትትልና ግምገማ አካሄድን ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብን በሚመለከቱ ነጥቦች
ላይ ያተኮሩ ክትትሎች፣ ድጋፎችና ግምገማዎች ተደርገዋል፣

ግብ 7. የአገልግሎት ቅልጥፍናን ማሻሻል (አፈጻጸሙ 93.49% ደርሷል)

7.1 የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ለማሳደግ በተያዘው ዕቅድ ፡-


በዕቅድ የተያዙ መዛግብት በተያዘላቸው ጊዜ ዕልባት ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ በተካሄዱ ክትትሎች፣
ድጋፎች፣ ግምገማዎችም ሆነ በተዘጋጁ ሪፖርቶች መሰረት የሁሉም ፍ/ቤቶች የውሳኔ ሰጪ ዘርፍ የዘጠኝ
ወር አፈጻጸም ሲታይ፡-

በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሁሉም ችሎቶች፡-


ፍ/ቤቱ ካለፈው በጀት ዓመት የተላለፉ 2,232 መዛግብትን መነሻ በማድረግ በበጀት ዓመቱ 7,406
አዲስ መዛግብት አንደሚከፈቱ አቅዶ በበጀት ዓመቱ 12,812 መዛግብት በመከፈታቸው አፈጻጸሙ
172.99%፣ በዓመቱ እንደገና ይከፈታሉ ተብለው ከታቀዱት 50 መዛግብት 42 በመከፈታቸው
አፈጻጸሙ 84%፣ በዓመቱ በአጠቃላይ 9,690 መዛግብት ለውሳኔ እንዲቀረቡ ታቅደው 15,087
በመቅረባቸው አፈጻጸሙ 155.69 % ደርሷል፣ በበጀት ዓመቱ ዕልባት ያገኛሉ ተብለው በዕቅድ
ከተያዙት 9,640 መዛግብት ውስጥ በበጀት ዓመቱ 10,480 መዝገቦች እልባት በማግኘታቸው
የፍ/ቤቱ አፈጻጸም 108.71 % መድረሱን መረዳት ተችሏል፣
 በዚህም መሰረት በፌ/ጠ/ፍ/ቤት የ2007 በጀት ዓመት የማጣራት አቅም 82%፣ የመጨናነቅ ሁኔታ
1.4 እንዲሁም የመዝገብ ክምችት 0.4 መሆኑን የዳታቤዝ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
ዕልባት ያገኙ መዝገቦችን ጊዜ የሚያመለክተው ዳታቤዝ ዕልባት ከተሰጠባቸው መዛግብት መካከል፡-

 ከ6 ወር በታች ቆይታ የነበራቸው 31.23%፣


 ከአንድ ዓመት በታች የሆነ ቆይታ የነበራቸው 80.7%፣
 እንዲሁም ከአንድ ዓመት በላይ ቆይታ የነበራቸው 19.02%

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 20


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

መሆናቸውን ያመላክታል፡፡

በከፍተኛ ፍ/ቤት ሁሉም ችሎቶች፡-

 ካለፈው በጀት ዓመት የተላለፉ 9,798 መዛግብትን መነሻ በማድረግ በበጀት ዓመቱ 16,883 አዲስ
መዛግብት እንደሚከፈቱ አቅዶ በበጀት ዓመቱ 15,830 በመከፈታቸው አፈጻጸሙ 94 %፣ በበጀት
ዓመቱ እንደገና ይከፈታሉ ተብለው ከታቀዱት 950 መዛግብት በበጀት ዓመቱ 1,153
በመከፈታቸው አፈጻጸሙ 121%፣ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 27,260 መዛግብት ለውሳኔ
እንዲቀርቡ ታቅዶ በበጀት ዓመቱ 26,721 መዛግብት በመቅረባቸው አፈጻጸሙ 98% ደርሷል፣
ዕልባት ያገኛሉ ተብለው ከተያዙት 26,310 መዛግብት ውስጥ 15,413 እልባት በማግኘታቸው
59% መፈጸም ተችሏል፣ ይህም ዳኞች በእረፍት የቆዩባቸውን 2 ወራት ያካተት በመሆኑ የ7 ወር
አፈጻጸም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፣
 በዚህም መሰረት በፌ/ከ/ፍ/ቤት የ2007 በጀት ዓመት አፈጻጸም የማጣራት አቅም 90.75፣
የመጨናነቅ ሁኔታ 1.73 እንዲሁም የመዝገብ ክምችት 0.73 ሆኗል፡፡
ዕልባት ያገኙ መዝገቦችን ጊዜ የሚያመለክተው ዳታቤዝ እልባት ከተሰጠባቸው መዛግብት መካከል፡-

 ከ6 ወር በታች ቆይታ የነበራቸው 20.55%፣


 ከአንድ ዓመት በታች ቆይታ የነበራቸው 56.00%፣
 እንዲሁም ከአንድ ዓመት በላይ ቆይታ የነበራቸው 43.99%፣

መሆናቸውን ያመላክታል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሁሉም ምድብ ችሎቶች፡-


 ካለፈው በጀት ዓመት የተላለፉ 21,478 መዛግብትን መነሻ በማድረግ በበጀት ዓመቱ 45,871
አዲስ መዛግገብት አንደሚከፈቱ ታቅዶ በበጀት ዓመቱ 99,929 መዛግብት በመከፈታቸው
አፈጻጸሙ 217.84%፣ በዓመቱ እንደገና ይከፈታሉ ተብለው ከታቀዱት 18,000 መዛግብት በበጀት
ዓመቱ ውስጥ 20,808 በመከፈታቸው አፈጻጸሙ 115.06%፣ በዓመቱ በአጠቃላይ 86,130
መዛግብት ለውሳኔ እንዲቀርቡ ታቅዶ በበጀት ዓመቱ 142,132 መዛግብት በመቅረባቸው አፈጻጸሙ
165.02% ደርሷል፣ ዕልባት ያገኛሉ ተብለው ከተያዙት 68,130 መዛግብት በበጀት ዓመቱ
112,196 መዛግብት እልባት በማግኘታቸው 164.67% መፈጸም ተችሏል፣ ይህም ዳኞች በእረፍት
የቆዩባቸውን 2 ወራት ያካተት በመሆኑ የ10 ወራት አፈጻጸም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፣
 በዚህም መሰረት በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የ2007 በጀት ዓመት የማጣራት አቅም 92.09%፣ የመጨናነቅ
ሁኔታ 1.2 እንዲሁም የመዝገብ ክምችት 0.2 ሆኗል፡፡
ዕልባት ያገኙ መዝገቦችን ጊዜ የሚያመለክተው ዳታቤዝ በሰባት ወር ውስጥ እልባት ከተሰጠባቸው
መዛግብት መካከል፡-

 ከ6 ወር በታች ቆይታ የነበራቸው 49.52%


 ከአንድ ዓመት በታች ቆይታ የነበራቸው 80.32%፣
 እንዲሁም ከአንድ ዓመት በላይ ቆይታ የነበራቸው 19.67%

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 21


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

በፌ/ጠ/ሸሪዓ/ፍ/ቤት

 በበጀት ዓመቱ በቀጥታ እና በይግባኝ ክሶች አዲስ ፋይሎች ይከፈታል ተብሎ በዕቅድ ከተያዘው
7,512 ውስጥ 7,158 ፋይሎች አዲስ ተከፍቷል፡፡ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 95.28%
ፐርሰንት ተከናውኗል፡፡
 በበጀት ዓመቱ በቀጥታና በይግባኝ ፋይሎች ይወሰናሉ ተብሎ በዕቅድ ከተያዘው 7,512 ውስጥ
7,138 ፋይሎች ውሣኔ አግኝተዋል፡፡ ይህም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 95.02% ፐርሰንት
ተከናውኗል፡፡
 314 መዝገቦች ወደ ቀጣዩ በጀት ዓመት በቀጠሮ ተላልፏል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ስታትስቲክስ ሰንጠረዥ 1


በአጠቃላይ የማጣራት የመጨ
የፌደራል ካለፈው አዲስ እንደገና በአጠቃላይ በቀጠሮ የመዝገብ
ዕልባት አቅም በ ናነቅ ክምችት
ፍርድ ቤቶች የመጡ የተከፈቱ የተከፈቱ የቀረበ የተላለፉ
ያገኙ % ሁኔታ
ፌ/ጠ/ፍ/ቤት 2,233 12,812 42 15,087 10,480 4,607 82 1.4 0.4

ፌ/ከ/ ፍ/ቤት 9,738 15,830 1,153 26,721 15,413 11,308 90.75 1.73 0.73

መ/ደ/ፍ/ቤት 21,395 99,929 20,808 142,132 112,196 29,936 92.09 1.2 0.2

አጠቃላይ 33,366 128,571 22003 183,940 138,089 45,851 91.70 1.3 0.3
ድምር

የዕቅድ አፈጻጸም ንጽጽር ሰንጠረዥ 2


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የበጀት ዓመቱ ዕቅድ የበጀት ዓመቱ አፈፃፀም የበጀት ዓመቱ አፈፃፀም
በመቶኛ
ፌ/ጠ/ፍ/ቤት 9,640 10,480 108.71 %
ፌ/ከ/ ፍ/ቤት 26,310 15,413 58.58%
መ/ደ/ፍ/ቤት 68,130 112,196 164.67%
የፌዴራል ፍ/ቤቶች 104,080 138,089 132.675%
አጠቃላይ ድምር

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዕልባት ያገኙ መዝገቦች ዕድሜ ሰንጠረዥ 3


ከ6
ከ3ዐ ቀን ከ6 ወር ከ1-3 ከ3-6
ከ1-2 ወር ከ2-6 ወር ዓመት ድምር
ችሎት ጉዳይ በታች 1ዓመት ዓመት ዓመት
በላይ
ፍ/ብሄር 1ኛ 10 15 120 211 109 0 0 465

ፍ/ብሄ 2ኛ 7 21 112 206 41 0 0 387


ፌ/ጠ/ፍ/
ቤት
ወንጀል 1ኛ 2 57 361 666 125 1 0 1212

ወንጀል 2ኛ 0 0 0 19 57 0 0 76

ሰበር አጣሪ 1ኛ 88 115 993 1848 348 0 0 1198

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 22


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ከ6
ከ3ዐ ቀን ከ6 ወር ከ1-3 ከ3-6
ከ1-2 ወር ከ2-6 ወር ዓመት ድምር
ችሎት ጉዳይ በታች 1ዓመት ዓመት ዓመት
በላይ
ሰበር አጣሪ 2ኛ 86 105 1118 1898 510 0 0 3392

ሰበር 0 1 52 329 811 4 1 3717

ድምር 193 314 2756 5177 2001 5 1 10447

ፌ/ከ/ፍ/ቤት ፍ/ብሄር 38 166 1020 2094 3351 179 48 6896

ወንጀል 207 277 1147 2830 2483 172 29 7145

የሥራ ክርክር 1 9 303 540 518 1 0 1372

ድምር 246 452 2470 5464 6352 352 77 15413

ፌ/መ/ደ/ ፍ/ብሄር 14,602 4,511 20,318 16,982 5,362 159 16 50,903


ፍ/ቤት
ወንጀል 3,555
1,309 9,503 15,195 12,542 1,929 639 55,719
የሥራ ክርክር 606
120 1,044 2,380 1,405 15 4 5,574
ድምር 18,763 5,940 30,865 34,557 19,309 2,103 659 112,196

የፌጠ//ሸ/ፍ/ቤቶች አጠቃላይ ስታስቲክስ ሰንጠረዥ 4


ተ.ቁ ፍ/ቤቱ ካለፈው አዲስ የተንቀሳቀሰ ድምር የተወሰነ በቀጠሮ ምርመራ
የዞረ የቀረበ የዞረ

1 ጠ/ሸ/ፍ/ቤት 1 186 1 188 178 10

2 ከ/ሸ/ፍ/ቤት 7 38 45 33 12

3 መ/ደ/ሸ/ፍ/ቤት 100 5384 5484 5364 120

4 ድ/ደ/መ/ደ/ሸ/ፍ/ቤት 185 1735 1735 1563 172

ድ ም ር 293 7452 1 7452 7138 314

7.2 የፍርድ አፈጻጸም ቅልጥፍናን ለማሳደግ በተያዘው ዕቅድ

ለአፈፃፀም የቀረቡ አቤቱታዎችን በማስተናገድ፡-

 ግልጽ ባልሆኑ ወይም በሚቃረኑ 1,050 ውሣኔዎች /ትዕዛዞች/ ላይ የአፈጻጸም ሂደቱ ከመከናወኑ
በፊት ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍ/ቤት በማቅረብ መብራሪያ መጠየቅና ግልጽ ማድረግ ተችሏል፣
 በ 744 አቤቱታዎች ላይ የማጣራት ሥራ ተሠርቷል፣
 ርክክብ የሚደረግባቸውን 885 ንብረቶች ፍርድ ያረፈባቸው መሆናቸው፣ አድራሻቸው መለየቱና
በፍ/ባለዕዳው ስም የተመዘገቡ መሆኑን ከሚመለከተው አካል ጋር በማጣራት የማስፈፀም ተግባር
ተከናውኗል፣
 301 በሀራጅ/ጨረታ/ እንዲሸጡ የቀረቡ ንብረቶች በህጉና በመመሪያው መሠረት ተሸጠዋል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 23


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

የማይንቀሳቀሱ እና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ግምትና ክፍፍል ስርዓትን ከማጠናከር አንፃር፡-

 692 በባለሙያዎች የተገመቱ፣ 105 በመሬት አስተዳደር የተካፈሉ፣ 445 በመሬት አስተዳደር
የተገመቱ፣ 110 ጉዳዮች በግራ ቀኙ ስምምነት ያለቁ፣ 316 መዝገቦች ወደ ሐራጅ የተመሩ እና
7032 እንደፍርድቤቱ ትዕዛዝ ተፈፅመው እንዲዘጉ የተደረጉ ሲሆን በአጠቃላይ 8700 ጉዳዮችን
ለማስተናገድ ተችሏል፡፡
 የፍ/ቤት ውሣኔዎች /ትዕዛዞች/ የተሟሉና ግልፅ መሆናቸውን በማረጋገጥ እና በአፈጻጸም ሂደት
መዝገቦችን በማጥራት ተግባር የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ጥረቶች
ተከናውነዋል፣
 በ 300 ለአፈፃፀም አስቸጋሪ የሆኑ የፍ/ቤት ውሣኔዎችና ትዕዛዞችን በጥራት እና በቅልጥፍና
አጣርቶ ለባለጉዳይ አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ እንዲጎለብት ተደርጓል፣
 የህግ ጉዳዮች በተመለከተ ከየሥራ ክፍሎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ሙያዊ አስተያቶች ተሰጥተዋል፣

7.3 ለዳኝነት ቅልጥፍና የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ለማጠናከር በተያዘው ዕቅድ፡-

 የግምገማ ነጥቦችን በማዘጋገጀት ለዳኝነት ሥራው የሚያስፈልጉ ድጋፎችን የሚያደርጉ የሲቪል


ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች የሰው ኃይል፣ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሥርዓት፣
የማቴሪያልና የፋይናንስ አቅርቦቶችን በሚፈለገው ቅልጥፍና፣ የጥራት ደረጃና መጠን መቅረባቸውን
ለማረጋገጥ የሚያግዙ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማዎች ተደርገዋል፣
 ከችሎቶች ጋር ቀጥተኛ የሥራ ግንኙነት ያላቸውን የሬጅስትራርና የችሎት አገልግሎቶችን
የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና ለማሳደግ የተገልጋዮችን አስተያየት ማሰባሰቢያ ሥርዓት ተዘርግቶ
በመተግበር ላይ ይገኛል፣
 በዚህ መሰረት የተገልጋዩን እርካታ ለማሻሻል፣ የመልካም አስተዳደርና የሥ ምግባር መርሆዎችን
የዕለት ተዕለት የሥራ አካል ለማድረግና ቅሬታዎችን ለመቀነስ በተደረገው ጥረት ተገልጋዮች
ሳይፈራና ሳይሸማቀቅ አስተያየት እንዲሠጡ ለማድረግ ተችሏል፣
 ከተገልጋዮች የተገኙ አስተያየቶችን/መረጃዎችን በመገምገም ጠንካራ አፈጻጸሙችን ይበልጥ
ለማጠናከርና ድክመቶችን ለማስወገድ በተደረጉ ጥረቶች ለዳኝነቱ ቅልጥፍና የሚያግዙ የአሰራር
ማስተካከያዎች ለማድረግ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለቀረቡ ቅሬታዎች ተገቢ ምላሾችን
ለመስጠትና የተገልጋዮችን ዕርካታ 70% ለማድረስ ተችሏል፣
 የዳኝት አገልግሎት የሚፈልጉ ተገልጋዮችን አቤቱታዎች በአግባቡ መርምሮ በሥነ ሥርዓት ሕጉ
መሰረት የተሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ አዳዲስ ፋይሎች እንዲከፈቱና ያልተሟሉ መረጃዎች
ተሟልተው እንዲቀርቡ ለማድረግ ተችሏል፣
 በፍ/ቤቶች ትዕዛዝ መሰረት መልስና የመልስ መልሶችን የማቀባበል ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን
የተከፈቱ መዝገቦች በኮምፒውተር በመታገዝ በዳታ ቋጥ እንዲገቡ፣ በጊዜ ገደቡ መሰረት
መጥሪያ፣ ትዕዛዝ፣ የውሳኔ ግልባጭ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ እንዲደርስ፣ በሥ.ሥ.ህ.ጉ መሰረት
የቀረቡት የቃለ መሃላ አቤቱታዎች ለችሎት እንዲመሩ፣ አዲስ የተከፈቱ፣ በቀጠሮ ላይ ያሉ፣
የተዘጉ፣ የተወሰኑ መዝገቦችን የሚጠቁሙ/የሚያመላክቱ ቅጾች አጠቃቀም ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣
 የችሎት አገልግሎት ሥራና የሪከርድ መረጃ አገልግሎት በዘመናዊ አሰራር ዘዴዎች ተደግፎ
ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ እንዲደራጅና የዕለት ተዕለት ሥራዎች
በአግባቡ እንዲከናወኑ ተደርጓል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 24


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 በአፈጻጸም የሚከሰቱ ችግሮችን ለይቶ መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ በኢፋይሊንግ የፋይል


አከፋፈት ዙሪያ ላጋጠሙ ችግሮች ከበላይ ኃላፊዎች፣ ከክፍል ኃላፊዎችና ከባለሙያዎች ጋር
የቅርብ ግንኙነት እያደረጉ በመወያየት ያጋጠሙ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ ተደርጓል፣
 ከኢኮቴ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ተገልጋይ
በሚገኝባቸው አካባቢዎች በፕላዝማ እንዲተላለፉና በሬጅስትራር ጽ/ቤት አካባቢ እንዲገኙ
ተደርጓል፣
 በርካታ ባለጉዳዮች የሚፈልጉትን መረጃ በአካልም ሆነ በስልክም ምላሽ እንዲያገኙ ከመደረጋቸውም
ሌላ በፕላዝማ የሚታዩ መዝገቦች በቀጠሮ ቀን ቀርበው እንዲታዩ ተደርገዋል፣
 አላስፈላጊ የሆኑ ንብረቶች እንዳይወጡ ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን በቁጠባ የማውጣት
ልምድ እንዲኖር በችሎት አገልግሎት በኩል ለሁሉም ክፍሎች በቁጠባ እንዲሰጥ ተደርጓል፣

ግብ 8. የአገልግሎት ጥራትን ማሳደግ (አፈጻጸሙ 80.9% ደርሷል)


8.1 የዳኝት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማጎልበት በተያዘው ዕቅድ ፡-

 በአገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርድ የተቀመጡ የጥራት አመላካች ነጥቦች (Indicators)


በተጠቃሚዎቻቸው ዘንድ ግንዛቤ አግኝተው በዕቅድ ዝግጅትም ሆነ በአፈጻጸም ተገቢው ትኩረት
የተሰጣቸው መሆኑን መለየት ያስቻለ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ተካሂዷል፣
 የአገልግሎት ጥራት መለኪያ እንዲሆኑ በዕቅድ የተቀመጡ የጥራት መለኪያ መስፈርቶችን
በመጠቀም የዕቅድ አፈጻጸም ውጤታመነት ማደጉን ከተሰባሰቡ የአፈጻጸም ክትትል፣ ድጋፍና
ግምገማ ሪፖርቶች መረዳት ተችሏል፣
 የጥራት አመላካች ነትቦችን ያካተቱ የተገልጋይ አስተያየት ማሰባሰቢያ ቅጾችን በማሰራጨት
የዳኞችን አፈጻጸም የጥራት ደረጃ መመዘን የሚያስችሉ መረጃዎች ተሰባስበዋልና ሪፖርት
ተዘጋጅቶ ለበላይ አመራር ቀርቧል፣

የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በተመሳሳይ ሁኔታ ለመገምገም የሚያስችል
ሥርዓት ቢዘረጋም የሥራ ክፍሎች የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራታቸውን መለካት የሚያስችሉ መስፈርቶችን
የያዘ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርድ ዝግጅት ባለመጠናቀቁ የተገልጋዮችን አስተያየት ማሰባሰብ
አልተቻለም፡፡

ግብ 9. የፋይናንስና የንብረት አጠቃቀምን ማሻሻል (አፈጻጸሙ 90.69% ደርሷል)


9.1 ዕቅድን ከበጀት ጋር አሥተሳስሮ መፈጸም የሚያስችል አሠራርን ለማጠናከር በተያዘው ዕቅድ፡-

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

 በመደበኛ በጀት ለክርክሮች ውሳኔ መስጠት ብር 16,369,502.00፣ ለሥራ አመራርና አስተዳደር


ብር 28,152,115.00 በአጠቃላይ ለበጀት ዓመቱ ብር 44,521,617.00 ተፈቅዶ ብር
44,273,254.29 በሥራ ላይ እንዲውል በመደረጉ 99.44% መጠቀም ተችሏል፡፡
 በበጀት ዓመቱ ለፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ፕሮጀክት ከተፈቀደው ብር 12,000,000.00 ውስጥ
10,673,940.73 ሥራ ለይ እንዲውል በማድረግ 88.95% መጠቀም ተችሏል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 25


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 ለፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ለበጀት ዓመቱ ከተፈቀደው ብር 1,527,114.00 ብር


ውስጥ ብር 1,122,729.91 ሥራ ላይ በማዋል 73.52% መጠቀም ተችሏል፡፡
 ገቢን በተመለከተ ከዳኝነት እና ከልዩ ልዩ ገቢ ብር 10,848,000.00 ለማሰባሰብ ታቅዶ ብር
9,717,071.65 በማሰባሰብ አፈጻጸሙ 89.57% ደርሷል፡፡
 ከዋስትና ተመላሽ ይሰበሰባል ተብሎ የታቀደው ብር 500‚000.00 ሲሆን ብር 325000.00
በማሰባሰብ ከተያዘው እቅድ 65% መፈጸም ተችሏል፡፡
 የዋስትና ተመላሽ ክፍያ ይፈፀማል ተብሎ በእቅድ የተያዘው ብር 900‚000.00 ሲሆን የተከፈለው
ብር 602‚000.00 በመሆኑ ከእቅዱ 66.9% ተፈጽሟል፡፡

ፌ/ከ/ፍርድ ቤት

 በመደበኛ በጀት ለክርክሮች ውሳኔ መስጠት ብር 22,753,793.00፣ ለሥራ አመራርና አስተዳደር


ብር 10,695,801.00 ፣ተጨማሪ በጀት 2,000,000.00 በአጠቃላይ ለበጀት ዓመቱ ብር
35,449,594.00 ተፈቅዶ ብር 38,279,669.25 በሥራ ላይ እንዲውል በመድረጉ 114.43%
መጠቀም ተችሏል፣
 ለበጀት ዓመቱ በካፒታል በጀት ብር 6,000,000 የተፈቀደ ሲሆን ብር 5,265,875.79 በሥራ ላይ
እንዲውል በማድረግ 87.76% መጠቀም ተችሏል፣
 ከዚህ በተጨማሪ ከቅጣት ብር 2,943,857.25፣ ከዳኝነት ብር 23,568,602.41 እንዲሁም ከልዩ
ልዩ ገቢዎች ብር 411,918.04 በማሰባሰብ በአጠቃላይ ብር 26,512,459.66 ገቢ ተደርጓል፣
ፌ/መ/ደ/ፍርድ ቤት

 በመደበኛ በጀት ለክርክሮች ውሳኔ መስጠት ብር 42,398,247.00፣ ለሥራ አመራርና አስተዳደር ብር


17,300,534.93 በአጠቃላይ ለበጀት ዓመቱ ብር 59,698,781.93 ተፈቅዶ ብር 57,347,038.05
በሥራ ላይ እንዲውል በማድረግ 96.06% መጠቀም ተችሏል፡፡
 ለበጀት ዓመቱ በካፒታል በጀት ብር 25,000,000 የተፈቀደ ሲሆን 5,322,825.38 ሥራ ላይ
በማዋል አፈፃፀሙ 21.29% ደርሷል ፡፡
 ለዳኝነት ተመላሽ የተፈቀደና ጥቅም ላይ የዋለው በጀት ለክርክሮች ውሳኔ መስጠት በሚለው
ፕሮግራም ውስጥ ተጠቃላሏል፡፡
በፌዴራል ጠ/ሸሪዓ/ፍ/ቤት

በመደበኛ በጀት ለክርክሮች ውሳኔ መስጠት ብር 1,931,900.00፣ ለሥራ አመራርና አስተዳደር ብር


5,890,800.00 በአጠቃላይ ለበጀት ዓመቱ ብር 7,822,700.00 ተፈቅዶ ብር 6,842,338.03 በሥራ ላይ
እንዲውል በማድረግ 87.47% መጠቀም ተችሏል፡፡

ዘመናዊ የኦዲት ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ የበጀትና የንብረት አስተዳደርና አጠቃቀምን ከዕቅድና
አፈጻጸምና ከተጠያቂነት ሥርዓት ጋር እንዲያያዝ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት፡-
 የፋይናንስ ኦዲት፣የጥሬ ገንዘብ እና ሠነድ ቆጠራ በማድረግ የፈሰስ ሪፖርት በማዘጋጀት፣ በደረሰኝ
ላይ ምልክት በማድረግ /Cut off/፣ቋሚና አላቂ ንብረቶች ቆጠራ በማካሄድ፣ በጠቅላይ ፍ/ቤትና
በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የግል ማህደር እና ከደመወዝ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ ምርመራ
በማድረግ፣ በስጋት ዳሰሳ ላይ ተመስርቶ ለስጋት የተጋለጡ አካባቢዎችን በመለየት፣ በጠቅላይ

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 26


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ፍ/ቤት የአላቂና የቋሚ እቃዎች እንዲሁም የገቢ እና የወጭ ሂሣብ ምርመራ ሪፖርት በማዘጋጀት
ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ተልኳል፣
 በጠ/ፍ/ቤት እና በመ/ደረጃ ፍ/ቤት የተሰብሣቢና የተከፋይ ሂሣብ የማጣራት፣ የባንክ ሂሣብ
ማስታረቂያ ትክክለኛነት እና የበጀት ተግባራዊነት የማረጋገጥ ስራ ተከናውኗል፡፡
 በፌ/ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ በፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የግዢ ምርመራ ተከናውኖ እና
የመውጫው ስብሰባ ተደርጐ ሪፖርቱ ተዘጋጅቷል፣
 በህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ሂሳብ ስራ ላይ ምርመራ ተደርጓል፣
 የበጀት፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደርና አጠቃቀምን በተመለከተ በሶስቱም ፍ/ቤቶች የአላቂ
ንብረቶች ቆጠራ ተከናውኖ በተገኘው ውጤት መሠረት የፈሰስ ሪፖርት ተዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው
ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ቀርቧል፣
 የጥሬ ገንዘብ እና የሰነድ ቆጠራ በማድረግ በደረሰኞች መጨረሻ የመለያ ቀን ተወስዷል፣ የቋሚ እና
አላቂ ንብረቶች ቆጠራ ተከናውኗል፣
 በአጠቃላይ በኦዲተሮች የተለዩ የበጀት፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም ክፍተቶች
በአግባቡ ተጣርተው ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን የክዋኔ ኦዲትን በተመለከተ የግል
ማህደር ላይ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል፣ ከደመዝ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች
የመመርመር ተግባር በመከናወን ላይ ይገኛሉ፣ በስጋት ዳሰሳ ላይ ተመስርቶ ለስጋት የተጋለጡ
አካባቢዎችን የመለየት ተግባር ተከናውኗል፣ የግዥ እቅድ ጸድቆ ስራ ላይ መዋሉን የማረጋገጥ
ሰራ ተሰርቷል፡፡
በዚህም የፋይናንስና ከዋኔ ኦዲት ሪፖርቶች ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱ ለማድረግ
ከተያዘው ዕቅድ 84.97 መፈፀም ተችሏል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 27


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

መደበኛ በጀት

ፕሮግራሞች የካፒታል በጀት

በዘጠኝ
ወራት
ለክርክሮች ውሳኔ መስጠት ለሥራ አመራርና አስተዳደር በአጠቃ ላይ በአጠቃ ላይ በስራ
ለበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ላይ
ፍርድ ቤቶች ለበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ለበጀት ዓመቱ በዘጠኝ የተፈቀደ በስራ ላይ የዋለ የዋለ ለበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት የዘጠኝ
የተፈቀደ በስራ ላይ የዋለ የተፈቀደ ወራትዓመቱ በ% የተፈቀደ በስራ ላይ የዋለ ወራት በስራ
በስራ ላይ የዋለ ላይ የዋለ
በ%

የፌደራል ጠቅላይ 16,369,502.00 16,121,139.29 28,152,115.00 28,152,115.00 44,521,617.00 44,273,254.29 99.44% 12,000,000.00 16,369,502.00 59.68
ፍርድ ቤት

የፌደራል ከፍተኛ 22,753,793.00 25,305,299.39 10,695,801.00 12,974,369.86 33,449,594.00 38,279,669.25 114.43% 6000000.00 22,753,793.00 87.74
ፍርድ ቤት

የፌደራል 42,398,247.00 40,634,886.43 17,300,534.93 16,712,151.62 59,698,781.93 57,347,038.05 96.06% 25,000,000.00 42,398,247.00 79.35
መጀመሪያ ፍርድ
ቤት

የፌደራል ፍርድ
ቤቶች ጠቅላላ 81,521,542.00 82,061,325.11 56,148,450.93 57,838,636.48 137,669,992.93 139,899,961.59 101.61% 43,000,000.00 81,521,542.00
ድምር 75.03

የፌደራል ሸሪዓ 1,931,900.00 1,623,530.00 5,890,800.00 5,218,803.03 7,822,700.00 6,842,338.03 87.47% 1,931,900.00 -
ፍርድ ቤት

የዳኞች አስተዳደር 1,527,114.00 1,122,729.91 73.52% -


ጉባኤ

*ከተፈቀደው አጠቃላይ ብር ተጨማሪ ብር 2,000,000.00 ተጠይቋል

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም 2007ዓ.ም Page 28


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

9.2 ለዳኝነት ሥራው የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ለማሟላት በተያዘው ዕቅድ፡-

በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት
 የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሙያ የሥነ ምግባር ብቃት ያላቸው ዕጩ ዳኞችን
አወዳድሮና መልምሎ ለማሾም በአዋጅ ቁጥር 684/2002 በተሠጠው ስልጣን መሠረት
የጠቅላይ፣ የከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኞችን ለማሾም የሚያስችልና በግልጽ ውድድር
ላይ የተመሠረተ ምልመላ ተካሂዶ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተወዳዳሪዎች ምርጫ
በመጠናቀቁ ሰባት ወንዶች እና አንድ ሴት ዕጩ ዳኞች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሾሙ
ተደርጓል፡፡
 በሚያዝያ ወር መጀመሪያ 2007 ዓ.ም በተጠናቀቀ የዕጩ ዳኞች ምዝገባ ከየክልሉ የተላኩትን
ጨምሮ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 1243 ወንድና 277 ሴት በአጠቃላይ 1520
አመልካቾች፤ ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 387 ወንድና 68 ሴት በአጠቃላይ 455 አመልካቾች
እጩዎች ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 69 ወንድ እና 10 ሴት በድምሩ 79 አመልካቾች በአጠቃላይ
ለሶስቱም ፍ/ቤቶች 2056 አመልካቾች ለውድድር የተመዘገቡ ሲሆን ከፍተኛ የዳኞች እጥረት
ለሚታይበት የጠቅላይ ፍ/ቤት ተወዳዳሪዎች ቅድሚ በመስጠት መረጃዎቻቸውን አደራጅቶ፣
የጽሁፍእና የቃል ፈተናዎችን እንዲወስዱ አደርጎና የሕዝብ አሰተያየቶችን አሰባስቦ አሸናፊ የሆኑ
ተወዳዳሪዎችን የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ለማሾም ተችሏል፣
 በቀሩት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወዳዳሪዎች ላይ መረጃዎቻቸውን
የማደራጀቱ ሥራ ተጠናቅቆና ቅድመ ሹመት ምልመላዎች ተከናውነው አሸናፊ የሆኑ ዕጩ
ዳኞችን በቀጣዩ በጀት ዓመት እንዲሾሙ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ
ይገኛሉ፡፡
 በአጠቃላይ በፌደራል ጠ/ፍ/ቤት አዲስ የተሸሙትን ዳኞች እና ፕሬዝዳንቶች ጨምሮ 2 ሴት እና
30 ወንድ በአጠቃላይ 32 ዳኞች የሚገኙ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፣

የጠቅላይ ፍ/ቤት ድጋፍ ሰጪ የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች ክፍት የሥራ መደቦች በሰው ኃይል
ለመሙላት በተያዘው ዕቅድ፡-

 130 ሠራተኛ ለመቅጠር ታቅዶ 163 ቅጥር በመካሄዱ አፈጻጸሙን 125.3%፣


 40 መደቦችን በደረጃ ዕቅድገት ለመሙላት ታቅዶ 44 ክፍት የሥራ መደቦችን መሸፈን በመቻሉ
አፈጻጸሙን 110%፣
 10 የሥራ መደቦችን በዝውውር ለመሙላት በተያዘው ዕቅድ 6 ዝውውሮች በመፈጻማቸው
አፈጻጸሙነ 60%፣

ለማድረስ ተችሏል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 29


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 በአደረጃጀት ለውጥና አዳዲስ የስራ መደቦች በመፈጠራቸው ከሥራ ክፍሎች የቀረቡ ጥያቄዎችን
በማስተናገድ ለድምጽ ቀራጭ 10 የስራ መደብ ተጠይቆ 8 ማስፈቀድና ለሾፌር 29 የሥራ
መደብ ተጠይቆ ሁሉንም ማስፈቀድ በመቻሉ 37 ተጨማሪ የሥራ መደቦችን እንዲፈቀዱ
ተደርጓል፣
 ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በውክልና የሰው ኃይል በሚያሟላባቸው ከፕሳ 5 በላይ ባሉ የሥራ መደቦች
ለከፍተኛ ፍ/ቤት 7 በቅጥር፣ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 10 በቅጥር፣ ለሸሪዓ ፍ/ቤቶች 3 በቅጥር
እና 9 በደረጃ ዕድገት ማሟላት ተችሏል፣
 አዳዲስ የስራ መደቦች እንዲፈቀዱ ከስራ ክፍሎች የቀረቡ ጥያቄዎችን በማስተናገድ ለድምጽ
ቀራጭ 10 የስራ መደብ ተጠይቆ 8 ተፈቅዷል፤ ለሾፌር 29 መደብ ተጠይቆ ሁሉም ተፈቅዷል፡፡
የሚመለከተው ሥራ ክፍል (የሰው ኃይል አስተዳደር) የተፈቀዱ መደቦችን በሰው ኃይል
ለመሙላት የሚያስችል ቅጥር ለመፈጸም በሂደት ላይ ይገኛል፣
 ከተለያዩ ከ5 ያላነሱ የፊደራል ተቋማት የሰው ሃይል አስተዳደር ተሞክሮ ልውውጥ በሠራተኞች
አያያዝ፣ ጥቅማ ጥቅም ወዘተ ጥሩ ተሞክሮ ተሰባስቧል፡፡

በአጠቃላይ ድጋፍ ሰጪዎችን በተመለከተ 244 ሴት እና 178 ወንድ በአጠቃላይ 422 የሲቪል
ሰርቪስ ሠራተኞች በሥራ ላይ የሚገኙ ሲሆን 2 ሠራተኞች በጡረታ(1 ወንድ 1 ሴት)፣ 24 ሴት
እና 22 ወንድ በድምሩ 46 ሠራተኞች ደግሞ በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን ለቅቀዋል፣ አንድ ሠራተኛ
በሞት የተለዩ ሲሆን በጥቅሉ 26 ወንድ እና 23 ሴት ሠራተኞች ከመ/ቤቱ ተሰናብተዋል፡፡
የሚለቁበትን ምክንያት እንዲገልጹ በተዘጋጁ መጠይቆች አብዛኞቹ የተሻለ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም
በማግኘታቸው መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፣

በከፍተኛ ፍ/ቤት ደረጃ


 14 ሴት እና 64 በአጠቃላይ 78 ዳኞች እና 146 ወንድ 284 ሴት የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች
የሚገኙ ሲሆን ክፍት የሥራ መደቦችን በሰው ኃይል ለመሙላት በተደረጉ ጥረቶች 31 ሴት፣
25 ወንድ ሠራተኞችን በቅጥር፣ 7 ሴት፣ 3 ወንድ ሠራተኞችን ከሌሎች ፍ/ቤቶች በዕድገት፣ 11
ሴት 3 ወንድ ሠራተኞችን ከሌላ መ/ቤት በዝውውር ለማምጣት ተችሏል፣
 3 ሴት 1 ወንድ ሠረታኛ በሌሎች ፍ/ቤቶች የደረጃ ዕድገት በማግኘታቸው ከፍተኛ ፍ/ቤትን
ለቀዋል፣ 1 ሴት 1 ወንድ ሠራተኞች ወደ ሌላ መ/ቤት የተዛወሩ ሲሆን 16 ሴት፣7 ወንድ
ሠራተኞች በገዛ ፈቃዳቸውን ተቋሙን ለቅቀዋል፣ 2 ወንድ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች በጡረታ
የወጡ ሲሆን 1 ሴት ሠራተኛ በሞት ተለይተዋል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

 49 ሴት 76 ወንድ በአጠቃላይ 125 ዳኞች እና 988 የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች የሚገኙ ሲሆን
ክፍት የሥራ መደቦችን በሰው ኃይል ለመሙላት 81 ሠራተኞች ተቀጥረዋል፡፡
 48 ሠራተኞች በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን ለቀዋል፡፡
 ዕድሜያቸው 6ዐ የሞሉ 3 ሠራተኞች እና በ 55 ዓመታቸው ጡረታቸውን የጠየቁ 2 ሠራተኞች
በአጠቃላይ 5 ሰራተኞች በጡረታ ተቋሙን ለቀዋል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 30


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

በፌ/ጠ/ሸሪዓ ፍ/ቤት
 በሸሪዓ ፍ/ቤት አዳዲስ ዳኞችን ለማሾም ለሚመለከተው አካል ጥያቄ የቀረበ ሲሆን የዳኞችን
የጥቅማጥቅም ጥያቄ ቀርቦ መልስ እየተጠበቀ ይገኛል፣
 የሸሪዓ ፍ/ቤት አዲስ መዋቅር እንዲዘጋጅ ለቀረበው ጥያቄ የይሁንታ መልስ በመገኘቱ አዲስ
መዋቅር የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተዋቅሮ እንዲሠራ ተደርጓል፣
 ያሉትን ክፍት የሥራ መደቦች በሰው ኃይል ለመሙላት በተያዘው ዕቅድ 13 መደቦች በደረጃ
ዕድገት፣ 15 መደቦችን ደግሞ በቅጥር ለመሙላት ተችሏል፤

የሰው ኃይልን በተመለከተ የፌ/ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የተሰጣቸው ውሳኔዎች

 የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ያቀረቡ 5 ዳኞች (2 የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኞች፣ 3
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች) ስንብት ተፈቅዷል፣
 1 ዳኛ ያለባቸው የዲሲፕሊን ክስ እልባት በማግኘቱ የመልቀቂያ ጥያቄያቸው እንዲስተናገድ
በጉባዔው በመወሠኑ ይኸው እንድፈጠም ተደርጓል፤
 8 የህግ ረዳቶች ያቀረቡትን የመልቀቂያ ጥያቄ በመቀበል ስንብቱ ተፈቅዶላቸዋል፣
 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሚሾሙዋቸው ዳኞች የጉባዔውን አስተያየት ለማግኘት
የሚልኩዋቸው ጥያቄዎችን በማስተናገድ ከደ/ብ/ብ/ህ/ክልል 32፣ ለሐረሪ 1፣ ከትግራይ 39፣
ከአማራ ክልል 71፣ ከጋምቤላ 13 ዕጩዎች ላይ በህግ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉባዔው
አስተያየት እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
9.3 ለዳኝነት አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንዲሟሉ ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ፡-

 የሸሪያ ፍ/ቤቶችን ጨምሮ ሁሉም የፊደራል ፍ/ቤት ዳኞች እና ቤተሰቦቻቸው የጤና መድህን
ሽፋን እንዲያገኙ የ225 ዳኞች የኢንሹራንስ መረጃዎች ተደራጅተው ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት
ጋር ውል ተገብቶ ተገብቷል፣
 የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ባካሄዳቸው ስብሰባዎች የጉባኤ ተሿሚዎች የቤት አበል
ጥያቄን ለማስተናገድ በተካሄደው ጥናት መሰረት ከሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ እንዲከፈል
ተደርጓል፣ የፌደራል ፍ/ቤት ረዳት ዳኞች ከሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪ
እንዲያገኙ ተፈቅዷል፣ በበጀት ዓመቱ መግቢያ መንግስት ለፌደራል መንግስት ሠራተኞች
ያደረገውን የደሞዝ ጭማሪ መነሻ በማድረግ ጉባዔው የዳኞችንና የተሿሚዎች ደሞዝ በመንግስት
መመሪያ መሠረት ተሠልቶ ተፈጻሚ ሆኗል፣ ድሬዳዋ የሚገኙ የፌዴራል ፍ/ቤት ዳኞችና
ተሿሚዎች ያቀረቡት ጥያቄ መሠረት በማድረግ ከሚያዝያ 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. ጀምሮ የበረሃ
አበል 2ዐ% እንዲከፈላቸው ተፈቅዷል፤
 የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ሃላፊ እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስትራቴጂክ
ስራ አመራር ዳይሬክተር ሹመት በጉባዔው በመጽደቁ ሹመቱ በደብዳቤ ለሚመለከታቸው አካላት
እንዲደርስ ተደርጓል፤
 ጉባዔው የዳኞችን ደሞዝ ስርዓት ለማሻሻል በጉባዔው አባላት የተከናወነ ጥናት (እንደተሻሻለ)
ተቀብሎ የዳኞችን ደሞዝ ያካተተ የጥቅማጥቅም ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ለአስፈጻሚው አካል ተልኳል፡
 የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት በሰጣቸው አገልግሎቶች 10 ዳኞች የስራ ልምድ ማስረጃ፣ የ 5
ዳኞች እና 8 ረዳት ዳኞች የሥራ መልቀቂያ ተሠጥቷል፣ 380 የተለያዩ ወጪ ደብዳቤዎች
ተልከዋል፣ 75 የተለያዩ ገቢ ደብዳቤዎች ለጽ/ቤቱ ቀርበዋል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 31


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞችን ፕሮፋይል በሶፍት ኮፒ እና ሀርድ ኮፒ ለፐብሊክ ሰርቪስ


ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በመላክ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ
ለማድረግ ተችሏል፣
 የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰው ኃይል መረጃ ዳታቤዝ ድህረ ገጽ ማሻሻያ ስራ ከአማካሪ
ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተግባራዊ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች የማመቻቸት ስራ ተሰርቷል፣
 የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የአስተዳደር መዝገብ ቤትን በዘመናዊ የፋይል አያያዝ ሥርዓት
ለማደራጀት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ግምገማ ተጠናቅቋል፣
 የሚያስፈልጉ ቋሚና አላቂ እቃዎች እንዲገዙ በማድረግ ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን
በቁጠባ የማውጣት ልምድ እንዲኖርና ለሁሉም ችሎቶችና ክፍሎች እንዲደርስ ተደርጔል፣
 ለአዲስ አበባ ሸሪዓ ፍ/ቤቶች ለተጨማሪ ክፍሎች ኪራይ በጀት ተጠይቆ የ350 ካ.ሜ ኪራይ
ተፈቅዷል፣ እንዲሁም ለድሬደዋ ሸሪዓ ፍ/ቤት ኪራይ በጀት እንዲፈቀድ ተጠይቋል፣.
 በጠቅላይ በፍርድ ቤት የሚገኙ የአይሲቲ መገልገያ መሳሪዎች ምዝገባ ተከናውኗል፤
 በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ወርሐዊ የነዳጅ፣የዘይትና የጥገና ወጪዎች ተሰርተው
ለሚመለከተው የመንግስት ተቋማት የማሳወቅ ሥራ ተሠርቷል፤የመስክ ስራ ለሚወጡ ሹፌሮች
ግልፅ የሆነ የስራ መድልድል በማውጣት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

ግብ 10. የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን ማሳደግ (አፈጻጸሙ 61.5% ደርሷል)


10.1 የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን አግባብነት ለማጎልበት የተያዘው ዕቅድ፡-
የዳኝነት ነጻነትና ገለልተኝነት መርህን ለመተግበር የሚያስችል ግንዛቤ ከማሰደግ ባሻገር የመርሁን
ተግባራዊነት በማጠናከር፡-

 የፍርድ ቤቶችን የበጀት ነፃነትና የአፈጻጸም ተጠያቂነት በማጠናከር የበጀት ዓመቱ ዕቅድ እና
የበጀት ፍላጎት ተዘጋጅቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኳል፣ የአፈጻጸም ሪፖርቶችም
በየመንፈቅ ዓመቱ ተዘጋጅተው ቀርበዋል፣
 ከሕዝብ ተወካዮች ምክር የሚሰጡ አስተያየቶችን ወይም ግብረመልሶችን በግብዓትነት በመጠቀም
በዓመታዊ ዕቅዱም ሆነ በአፈጻጸም ሪፖርቶች ላይ ማስተካከያዎችን በማደርግ የዳኝነት ነጻነትና
ገለልተንነትን ማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል፣
 የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ በተዘጋጁ መመዘኛ ነጥቦች አኳያ በተገልጋዮች
የተሰጡ የምዘና ነጥቦችን የሚያሳይ ሪፖርት ተዘጋጅቶ ለበላይ አመራር ቀርቧል፣

ግብ 11 የተገልጋይን ዕርካታ ማሳደግ (አፈጻጸሙ 84.49% ደርሷል)

11.1 የተገልጋዮችን ዕርካታ ለማሳደግ ከተያዘው ዕቅድ፡-


 በእቅድ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የተከናወኑ ተግባራትና የተሰጡ አገልግሎቶች መልካም
አስተዳደርን ለማስፈን፣ የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃግብር ድንጋጌዎችን ለመፈጸም፣
የመልካም አስተዳደርና የሥነ ምግባር መርሆችን በመተግበርና ሙስናን ለመከላከል
ማስቻላቸውን፣ በዚህም የተገልጋይን የእርካታ ደረጃ ለመለየት የሚረዳ የዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ
በዘተያዘው ዕቅድ መሰረት የተወሰኑ ክፍሎች ለምሳሌ ሬጅስትራር፣ የችሎት አገልግሎት፣
የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት፣ ፍርድ አፈጻጸም ወዘተ… የየዕለቱን ተገልጋዮች አስተያየት

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 32


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

በማሰባሰብ የዕርካታ ደረጃቸውንና የአገልግሎት አሰጣጥ ፍላጎታቸውን መለየት ያስቻለ ጥናት


አካሂደዋል፣
 በእነዚህ ሥራ ክፍሎች የተገልጋይን እርካታ ማሳደግ የሚያስችሉ ቼክሊስቶችን በማዘጋጀትና
ከተገልጋይ የተሰጡ አስተያየቶችን በማሰባሰብ ተንትኖና ገምግሞ አግባብነት ያላቸውን
ማስተካከያዎች በመጨመር ለትግበራ የመምራትና ለውጡን የመከታተል ሥራ ተከናውኗል፣
 በኢኮቴ ዙሪያ የተገልጋይ እርካታ ጥናት ለማካሄድ መጠይቆች ተዘጋጅተው፣ የቪዲዬ ኮንፈረንስና
የኢፋይሊንግ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አራት አቅጣጫዎች ላይ አራት ቡድኖች በመመስረት
ጥናቱ ተካሂዷል፡፡ አስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ድረስ ከትግራይ፤ ከደቡብና የምስራቁ የአገራችን
ክፍሎች በሰራጩ መጠይቆች መሰረት መረጃዎች የተሰባሰቡ ሲሆን በቀጣይም በምዕራብና
በሰሜን ምእራብ የአገራችን ክፍሎች ተመሳሳይ ተግባር ለማከናወን ዕቅድ ተይዟል፡፡
 በተቋም ደረጃ በተሰጡ አገልግሎቶች ላይ የሕብረተሰቡን አስተያየት ለማሰባሰብ የተያዘው ዕቅድ
የምዘና ሥርዓቱን በአግባቡ ተግብሮ የዳሰሳ ጥናቱን ማካሄድ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ለቀጣዩ በጀት
ዓመት እንዲተላለፍ ተደርጓል፣
የፌዴራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍ/ቤቶች በአፈጻጸም ሪፖርቶቻቸው የግቦችን አፈጻጸም ደረጃ የሚያሳይ
መረጃ ባለማቅረባቸው በዚህ ሪፖርት የተካተቱት የግቦች አፈጻጸም ደረጃዎች ከጠቅላይ ፍ/ቤት በቀረቡ
መረጃዎች ላይ ብቻ የተወሰነ ሲሆን የግቦች አማካይ አፈጻጸም 85.72% መድረሱን መረዳት ተችሏል፡፡
ክፍል ሁለት

2 የፕሮጀክቶች አፈጻጸም
1. የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ጥናት ፕሮጀክት፣

ለውሳኔ ሰጪ(ዳኝነት) ሥራ ዘርፍ የተዘጋጀው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ ተገምግሞና ዳብሮ በስራ
ላይ እንዲውል ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ፡-
o ረቂቁ በበላይ አመራር ተገምግሞና ለፌዴራል ዳኞች እንዲሁም የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ኃላፊዎች
ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ጸድቆ በሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡
o የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎችን የአገልግሎት አሰጥጥ ስታንደርድ ለማዘጋጀት ኮሚቴ ተቋቁሞ
የመጀመሪያውን ረቂቅ ለበላይ አመራር ያቀረበ ሲሆን በተሰጡ አስተያየቶች መሰረት
ማስተካከያዎችን አደርጎ የመጨረሻ መልኩን የማስያዝ ተግባር በመከናወን ላይ ይገኛል፣
o የዳኝነት ዘርፉንና የሲቪል ሰርቪሱን ሥራ ክፍሎች አገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርድ መነሻ
በማድረግ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለሕዝብ ማሳወቅ የሚያስችል የዜጎች ቻርተር
የማዘጋጀቱ ሥራ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርዱን መጠናቀቅ በመጠበቅ ላይ ይገኛል፣
o የፌዴራል ፍ/ቤቶችን የሥራ ባህሪና የለውጥ መሳሪዎችን አተገባበር መነሻ በማድረግ ተቋማዊ
የፍትህ ሠራዊት ግንባታ ለማካሄድ የሚያስችል የትግበራ መመሪያ ተዘጋጅቶና የግንዛቤ
ማስጨበጫ ስልጠናዎች ተሰጥተው ተበትግበራ ላይ ይገኛል፣
2. የተቀናጀ የኢኮቴ ኘሮጀክት
የኢሊትጌሽን አገልግሎትን ለማስፋፋት ታቅዶ፡-
 ሁሉንም የፌዴራል ፍ/ቤቶች በኔትወርክ በማገናኘት የመረጃ ልውውጥ ሥራን ቀልጣፋ
ለማድረግ የሚያስችል የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ሰነድ ዝግጅት ተጠናቅቆ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለበላይ
ሃላፊዎች ቢቀርብም ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ እስከ 100 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ በመሆኑ
የሚያስፈልገውን በጀት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፣
የአይሲቲና ሴኩሪቲ ፖሊሲዎችን ለማውጣትና ለመተግበር ታቅዶ፡-

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 33


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

 የፌዴራል ፍ/ቤቶች የአይሲቲ ፖሊሲና ስትራቴጂ ዶክመንት ለማዘጋጀት የሚያስችል ከሶስቱም


ፍ/ቤቶች አምስት አባላት ያለው ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራውን የጀመረ ሲሆን ከልዩ ልዩ መንግስታዊ
ተቋማት መረጃ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፣ድራፍት ፍሬም ወርክ በማዘጋጀት ሰነዱን ለማዘጋጀት
እንቅስቃሴ ተጀምሯል፣
 ነባር መዝገቦችን ወደ ዲጅታል ፎርማት ለመቀየር የሚያስችል ጥናት ተዘጋጅቶ የፀደቀ ሲሆን
ስራውን ለመጀመር የሚያስችሉ ዕቃዎች ግዥ ተጠናቅቋል፣

3. የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ኘሮጀክት


ዘመናዊ የሰው ሃብት ስራ አመራር/አስተዳደር ማኑዋል ለማዘጋጀትና ለማስተዋወቅ በተያዘው ዕቅድ፡-
 የሰው ሃይል መረጃ ዳታቤዝና ድረ ገጽ ማሻሻያ ሥራ ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር
ተግባራዊ የሚሆንባቸውን ሁኔታዎች በማመቻቸት ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፣
 በዚህም በሶስቱም ፍርድቤቶች ዘመናዊ የሰው ኃብት ሥርዓት ሶፍትዌሩ የተጫነ ሲሆን ለ15
የሰው ሃብት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፣ የሠራተኞች ማህደር ወደ ሲስተሙ በመግባት
ላይ ይገኛል፣
 ለህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እና ለፍርድ አፈጻጸም ዳሬክቶሬት የዳታ ቤዝ እና ኔትወርክ
ዝርጋታ ስራ ፕሮፖዛል ተዘጋጅቷል፣
 በዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት አማካኝነት የዳኞችን አፈጻጸም ምዘና ያካተተ ዳታቤዝ በውስጥ
ባለሙያ አቅም በመሰራት ላይ ሲሆን ስራውም ከ 95 ፐርሰንት በላይ ተጠናቋል፣ በፍርድ ቤቱ
አመራር በሚሰጥ አቅጣጫ በስራ ላይ እንዲውል ይደረጋል፣
 የዳኞችን የስልጠና ፍላጎትና ክፍተት ለማሟላትና የሚያስችሉ የተሻሉ አካሄዶችን ለመቀየስ
የሚያስችል ስትራቴጂ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፣
 የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የትምህርትና ስልጠና አፈጻጸም መመሪያ የማዘጋጀቱ ሥራ በሂደት ላይ
ይገኛል፣

4. አማራጭ የሙግት መፍቻ ስርዓት ኘሮጀክት

 የማስማሚያ ጽ/ቤቶች ተገቢው አደረጃጀትና አሰራር እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ጥናት


በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

5. የንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም ማሻሻያ ኘሮጀክት

 የንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም ችግሮችን መለየት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ


ማሻሻያዎችን የማድረግ ሥራ በሂደት ላይ ይገኛል፣

6. የህግ ጥናት ፕሮጀክት

 የሰበር ችሎት ሂደት የሚመራበት የሥነሥርዓት መመሪያ እንዲዘጋጅ ለማድረግ የሚያስችል


ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 34


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ክፍል ሶስት
የክትትልና ግምገማ ምዕራፍ
3.1 በአፈጻጸም ሂደት የተደረጉ ክትትልና ድጋፎች
 በሁሉም ፍ/ቤቶች ወጥ የሆነ አተገባበር ባይኖርም በውሳኔ ሰጪ ዘርፍም ሆነ በሲቪል ሰርቪስ
ሥራ ክፍሎች የምዘና ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዙና በዕቅድ ዝግጅትም ሆነ
በአፈጻጸም ሂደት ተገቢውን አቅጣጫ ለመከተል የሚያግዙ ክትትሎች በማድረግ የለውጡን
ቀጣይነት የሚያጎለብቱ ድጋፎች ተደርገዋል፣
 ለለውጥ አተገባበሮች እንቅፋት የሚፈጥሩ አሠራሮችና አደረጃጀቶችነ ተከታትሎ በመለየት
አስፈላጊ ማስተካከያዎች ተደርገዋል፣
 በምዘና መመሪያው የተዘጋጁ ቅጾችን በመጠቀም በየደረጃው ከተዘጋጁ ዓመታዊ ዕቅዶች
የተመነዘሩና በዳኝነት ዘርፉ ወርሃዊ፣ በቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች ደግሞ ሳምንታዊ ዝርዝር
ተግባራትን የሚያሳዩ ዕቅዶችን አፈጻጸም የሚያሳዩ ሪፖርቶች ተዘጋጅተው የውስጥ እና የጋራ
ግምገማ እንዲከሄድባቸው ተደርጓል፣
 በዚህም ዳኞችም ሆነ የሲቪል ሰርቪስ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ሠራተኞች በሰብዓዊ መብት
የድርጊት መርሃግብር፣ በመልካም አስተዳደርና የሥነ ምግባር መርሆች ዙሪያ የአመለካከት
ለውጦችን ማዳበር የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ
መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፣
 በምዘና መመሪያው መሰረት የግምገማ ነጥቦችን አሰባስቦ በየመንፈቅ ዓመቱ የምዘና ውጤቶችን
መስጠት ባይቻልም የጠቅላይ ፍ/ቤት ችሎቶችና ዳኞች ዕልባት የሰጡባቸውን መዛግብት መጠን
እና ከድጋፍ ሰጪ ክፍሎች የቀረቡ የአፈጻጸም ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት
ዳኞችን፣ ችሎቶችንና ድጋፍ ሰጪ ዘርፎችን የአፈጻጸም ደረጃ ለመለየት ተሞክሯል፣

3.2 በግምገማ የተለዩ ጥንካሬዎች እና ክፍተቶች/ድክመቶች

በዕቅድ ዝግጅት እና የትግበራ ምዕራፎች በየደረጃው የሚገኙ የተቋሙ አመራር አካለት፣ ዳኞች፣ የሲቪል
ሰርቪስ ሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያከናወኑዋቸውን ተግባራትና የተገኙትን
ውጤቶች በጋራ በመገምገም ወደ 2008 በጀት ዓመት ለመሻገር የሚረዱ ቅድመ ዝግጅቶችን ተደርገዋል፡፡
በዚህም በየፍ/ቤቶች በተናጥል እና ሶስቱም ፍ/ቤቶች በጋራ የበጀት ዓመቱን የፍ/ቤቶች አፈጻጸም
የገመገሙ ሲሆን በየደረጃው የተለዩ ጥንካሬና ድክመቶችን በማውጣት የጋራ መግባባት እንዲፈጠርበቸው
አድረገዋል፡፡

ግምገማው የተካሄደው የፌዴራል ፍ/ቤቶች የበላይ አመራር አካላት ካዘጋጁዋቸው የመወያያ ነጥቦች
በመነሳት ሲሆን የፍ/ቤቶች የበላይ አመራር አካላት መድረኮችን በባለቤትነት በመምራት የሁሉም
ችሎቶች ዳኞች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በንቃት እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ በዚህም በየደረጃው የሚገኙ
ኃላፊዎች፣ ዳኞችና ድጋፍ ሰጪ ሥራ ክፍሎች ድክመቶቻቸውን አሻሽለው የቀጣዩን በጀት ዓመት
ውጤታማነት ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡ እነዚህን በግምገማ የተለዩ ጥንካሬዎች ይበልጥ አጎልብቶ
ክፍተቶችን በመሙላት የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ቅልጥፍና፣ ጥራት፣ ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነትና
ተዓማኒነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ የአተገባበር አቅጣጫዎችንም ለይተዋል፡፡ በዚህ ግምገማ
በየምዕራፉና በየሥራ ደረጃው ከታዩ ጥንካሬና ድክመቶች መካከል ጎልተው የታዩት በሚከተለው ሁኔታ
እንዲቀርቡ ተደርገዋል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 35


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

በዕቅድ ዝግጅት፣ በአፈጻጸም፣ በክትትልና ግምገማ ምዕራፎች

የበላይ አመራሩ ጥንካሬዎች

 አሳታፊነትን ተግባራዊ ያደረገ የበጀት ዓመትን ዕቅድ ያለፈውን በጀት ዓመት አፈጻጸም ገምግሞና
የበጀት ዓመቱን የትኩረት አቅጣጫዎችን ለይቶ እንዲያዘጋጅ፣
 የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርድ ተዘጋጅቶና ከሚመለከታቸው አካላት በተገኙ ገንቢ
አስተያየቶች ዳብሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ፣
 በበጀት ዓመቱ ዕቅድ፣ በተቋሙ ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች እና በአጠቃላይ በአፈጻጸም ምዘና
ሥርዓት ላይ ካለፉት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ በርካታ የኦረንቴሽን መድረኮች ተዘጋጅተው ግንዛቤ
እንዲኖር፣
 የተቋሙን ዓመታዊ ዕቅድ በየደረጃው አውርዶ ከተቋሙ ዕቅድ ጋር የተሳሰረ የችሎቶች እና
የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች ዓመታዊ ዕቅድ እንዲዘጋጅ፣
 ዳኞች ከችሎቶች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ከሥራ ክፍሎች ያወረዱዋቸውን መጋቢ ግቦች
መሰረት በማድረግ የየራሳቸውን ዕቅዶች ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ድጋፎች እንዲሟሉ፣
 ከዓመታዊ ዕቅድ የተመነዘሩ ወቅታዊ ዕቅዶች (ዳኞች ወርሃዊ ለሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች
ደግሞ ሳምንታዊ) እየተዘጋጁና የአፈጻጸም መረጃዎች እየተያዙ እንዲተገበሩ፣
 ዕቅዱን ለመፈጸም የሚያስችል የሰው ኃይል፣ በጀት እና ሌሎች አቅርቦቸቶች እንዲሟሉ፣
 የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃግብር ድንጋጌዎች የተቋሙ ዕቅድ አካል ሆነው እንዲፈጸሙ
ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓት እንዲተገበር፣
 በየፍርድ ቤቶች ልዩነት ቢኖረውም በተወሰነ መልኩ በችሎቶችነ ሥራ ክፍሎች የተዘጋጁ
ዕቅዶችን አተገባበር ተከታትሎ በመገምገም የሥርዓቱ ትግበራ እንዲጠናከር፣
 የፍ/ቤቶቹ ፕረዚደንቶችና ምክትል ፕረዚደንቶች መደበኛ የሆኑ ሳምንታዊ ስብሰባዎችን በማካሄድ
ተቋማዊ የለውጥ አተገባበሩች እንዲሻሻሉ፣
 የዳኝነት አካሉ ከሌሎች የፍትህ አካላትና ባለድርሻዎች ጋር የሚያደረጋቸውን ግንኙነቶችና
ተከታታይ ውይይቶች የሚመሩበት ፕሮግራም ተቀርጾ ተግባራዊነታቸው እንዲሻሻል፣
 የዳኞችንና የሠራተኞችን የአመለካከትና የአቅም ክፍተቶች የሚሞሉ በርካታ ስልጠናዎች
እንዲዘጋጁ፣
ተገቢው ጥረት መደረጉ የበጀት ዓመቱ የበላይ አመራር አካላት ጥንካሬዎች ተደርገው የተለዩ ነጥቦች
ናቸው፡፡
ክፍተቶች/ድክመቶች
 የለውጥ መሳሪያዎችን በዕምነትና በቁርጠኝነት ተቀብሎ አርዕያ መሆን የሚያስችል የለውጥ
አመራር አለመኖር፣
 በጊዜው ተገምግሞ የተስተካከለ ቢሆንም ኦሬንቴሽን በሚሰጥበት ወቅት ተናቦ ተገቢውን
አመራር አለመስጠትና የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ወቅቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ አለማድረግ፣
 የፍርድ ቤቶችን ተልዕኮ ለማሳካትና የአመራሩን ድጋፍ የሚሹ ችግሮችን ለመፍታት
በስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ አትኩሮ የቅርብ ክትተልና ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ መደበኛ በሆኑ
የዕለት ተዕለት ሥራዎች በመጠመድ የዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ድጋፍ ሥራዎችን በጥብቅ
ዲስፕሊን አለመመራት፣
 የተቋሙን ዕቅድ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አቅርቦ በማስገምገም ገንቢ አስተያየቶችን
አለማሰባሰብ፣
 በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሰራተኞች ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ቢደረግም አመራሩ
አግባብነቱን አረጋግጦ አለመፈረም፣
 ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተወሰኑ ዳኞች አዘጋጅተው ያቀረቦለትን ዕቅድ ፈርሞ አለመመለስና
ያላዘጋጁትን ተከታትሎ ተገቢውን እርምጃ አለመውሰድ፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 36


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

በከፍተኛና መጀመሪያ ዳረጃ ፍርድ ቤት የዳኞች ምደባ ላይ አልፎ አልፎ ግልጽነት አለመኖሩ፣
በተቋም ደረጃ በዳኝነት ዘረፉና በድጋፍ ሰጪ ሥራ ክፍሎች መካከል የጋራና ተቀራራቢ
አመለካከትና ግንዛቤ እንዲኖር የሚያደረግ ጥረት አለመዳበር፣
 በተለያዩ ምክንያቶች በፍርድ ቤቶች የሚታየውን የሰው ኃይል ፍልሰት ለመግታትም ሆነ ብቃት
ያላቸውን ባለሙያዎች ለመሳብ የሚደረጉ ጥረቶች የሚፈለገውን ውጤት አለማምጣት፣
 ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ለመውጣትና የሙስና ምንጮችን ለይቶና የመታገል
ውስንነት መኖር፣
 የምዘና ሥርዓቱን ውጤታማነት የሚያጎለብቱ የማበረታቻ ሥርዓቶችን ዘርግቶ አለመተግበር፣
አመራሩ በበጀት ዓመቱ የታዩበት ድክመቶች መሆናቸው ተገልጾ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የችሎቶች እና ዳኞች ጥንካሬዎች


 በዕቅድ ላይ በተዘጋጁ የኦሬንቴሽን መድረኮች አብዛኛዎቹ ዳኞች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ተገቢውን
ግንዛቤ መያዛቸውና የማሻሻያ አስተያየቶችን መስጠታቸው፣
 የዳኞች እጥረት እና የተሟላ የግንዛቤ በሌለበት ሁኔታም ቢሆን የምዘና ሥርዓቱን ተከትሎ
ለማቀድና ለመተግበር የሚታየው ተነሳሽነትና ፍላጎት እመጨመረ መምጣቱ፤
 አብዛኛዎቹ ችሎቶችና ዳኞች ከተቋም ዕቅድ የሚመለከቱዋቸውን ግቦችና መጋቢ ግቦች
በመውሰድ በጋራ ተወያይተው የችሎቶች እና የዳኞችን ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀታቸው ፣
 በተሟላ መልኩም ባይሆን በየፍ/ቤት ችሎቶች እና ዳኞች የተዘጋጁ ዕቅዶችን ለመፈጸም ከየፍርድ
ቤቱ ፕሬዘዳንቶች ጋር የአፈጻጸም ስምምነት ውል ለመፈራረም መሞከራቸው፣
 በዳኝነት ነፃነት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ዙሪያ የነበረውን ግንዛቤ ለማዳበር የሚያስችሉ ጥረቶች
ተጠናክረው መቀጠላቸው፤
 በተወሰኑ ችሎቶች ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ክፍሎች (ሴቶች፣አረጋውያን፣አካል
ጉዳተኞችና፣ ሕጻናት…) ተገቢውን ትኩረት ለመስጠት የሚደረገው ድጋፍ ውጤታማነት
እየጨመረ መምጣቱ፣
 የመብራት እና የኔትወርክ መቆራረጥ ቢኖርም ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ
ውጤቶችን በመጠቀም ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠጥ የሚደረጉ ጥረቶች
መጨመራቸው፣
 አብዛኛዎቹ ዳኞች ከሥራ ሰዓት ውጭ እየሠሩ ለቀረቡላቸው መዛግብት በስታንደርዱ መሰረት
ዕልባት በመስጠት የዳኝት ጥራትና ቅልጥፍናን ማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ተቋማዊ
የሥራ ባህል እየሆነ መምጣታቸው፣
በጥንካሬነት ከታዩት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ክፍተቶች/ድክመቶች
በርካታ ችሎቶችና ዳኞች በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቅዳቸውን አዘጋጅተው ያለማቅረባቸው፣
አንዳንድ ዳኞች በኦሬንቴሽን ወቅት ባለመገኘትና ችግር የማይፈጥሩ ነጥቦችን በማንሳት ለውጡን
በቁርጠኝነት ተቀብሎ ለማቀድና ለሌሎች ዳኞችም ሆነ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች አርዓያ መሆን
አለመቻላቸው፣
 የዳኝነት አካሉ በሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ውስጥ የማይተካ
ሚና ያለው መሆኑን በአግባቡ አለመረዳት፣
 ለተገልጋዬች የሚገባውን ክብር ሰጥቶ አለማስተናገድ፣ የህዝብ አገልጋይነት ስሜት አለመዳበር፣
የመልካም ሥነ ምግባር እና የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን በአግባቡ ያለመፈጸም፣
 ከነበረው አሰራር ወጣ ያሉ አዳዲስ ለውጦችን ለመቀበል አለመፍጠን ወይም ከልማዳዊ አሰራር
በቀላሉ አመላቀቅ ፣
ችግሮች የታዩባቸው መሆኑ ተገልጾ ማስተካከያዎች ማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተይዘዋል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 37


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

የኮርት ማናጀሮች፣ የጽ/ቤት ኃፊዎችና ዳይሬክተሮች ጥንካሬዎች


የሰው ኃይል እና የግንዛቤ እጥረት ባሉበት ሁኔታም ቢሆን ስራዎችን በዕቅድ ለመምራትና
የምዘና ሥርዓቱን ለመተግበር የሚያሳዩት ተነሳሽነትና ፍላጎት እመጨመረ መምጣቱ፤
 በተቋም ዕቅድ ላይ ተመሥርተው፣ ተወያይተው እና ከችሎቶችና ከዳኞች በተሻለ ፍጥነትና
ጥራት ከተቋም ዕቅድ ጋር የተሳሰረ የሥራ ክፍላቸውን ዕቅድ አዘጋጅተው ከፍርድ ቤቱ የበላይ
አመራር ጋር መፈራረማቸው፣
 በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ዳይሬክተሮች ለሌሎች ዓርያ መሆን የሚችል ዕቅድ ማዘጋጀታቸው፣
 ክፍት የስራ መደቦችን የተሻለ ክህሎትና የትምህርት ዝግጅት ባለው የሰው ሃይል ለማሟላት
ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው፣
 የፍርድ ቤቶች ስኬታማነት ለማረጋገጥና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን ለመጠቃም የሚያግዝ
የኢኮቴ አጠቃቀም ስርዓት መስፋፋቱ፣
የሚሉት በጥንካሬነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ክፍተቶች/ድክመቶች
በኦሬንቴሽን ጊዜ አብዛኛዎቹ የነበራቸው ተሳትፎ አልነበረም ሊባል እስከሚቻል ደረጃ ድረስ
ዝቅተኛ መሆኑ፣
 አብዛኛዎቹ ሃላፊዎች በስራቸው ላሉት ሠራተኞች በዕቅድ አዘገጃጀት ላይ ኦሬንቴሽን
አለመስጠታቸውና ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ አለማድረጋቸው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ዕቅዳቸውን
ዘግይተው ማዘጋጀታቸው፣
 የተቋሙን ዕቅድም ሆነ የአፈጻጸም ሪፖርት ከዕቅዱ ፈጻሚዎች ጋር በጋራ ለመገምገምና ግልፅ
አሠራርን ለማዳበር የሚያግዙ የኦሬንቴሽን መድረኮች ቢዘጋጁም የዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት
ዝግጅቶች ውስንነቶች መታየታቸው፣
 ፈጻሚዎች በየዕለቱ የሚያከናውኑዋቸውን ተግባራት እየተከታተሉ የመደገፍ፤ ክፍተቶችን ለይቶ
የመሙላትና ተገቢውን የእርምት እርምጃ የመውሰድ ወይም እንዲወሰድ የማድረግ ልምድ
በሚፈለገው ደረጃ አለመዳበር፤
 ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር አለመውጣት እና በቁርጠኝነት፣ በፅናትና ቀጣይነት
ባለው መልኩ ለመዋጋት የሚያስችል አመለካከት አለመዳበር፣
 የውጭ ተገልጋይ የሚስተናገድባቸው የሥራ ክፍሎች የቢሮ ችግሮችና በአገልግሎት አሰጣጥ
ሂደት የሚፈጥሩትን አሉታዊ ተጽዕኖ አለመፍታት፣
ድክመቶች ሆነው ታይተዋል፣
የቡድን መሪዎችና ሠራተኞች ጥንካሬዎች
አብዛኛዎቹ ቡድን መሪዎችና ሠራተኞች ከተቋሙ ዕቅድ ግቦች የሚመለከቱዋቸውን ግቦችና
መጋቢ ግቦች ወስደው ተገቢውን በመወያየት ዕቅዳቸውን ማዘጋጀታቸውና የአፈጻጸም ስምምነት
ማድረጋቸው፣
 አብዛኛዎቹ ቡድን መሪዎችና ሠራተኞች ሥራቸውን በዕቅድ ለመምራት የሚያስችል ዝግጁነትና
ተነሳሽነት ማሳየታቸው፣
 በዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተደራሽነትን ማጎልበትና ቅልጥፍናን ለመጨመር የሚያስችሉ
ስራዎችን የመስራት ባህል እያደገ መምጣቱ፣
ጥንካሬዎቻቸው ሆነው ታይተዋል፡፡

ክፍተቶች/ድክመቶች
 በርካታ የቡድን መሪዎችና ሠራተኞች ዕቅዳቸውን በተቀመጠው ጊዜ አዘጋጅተው
አለማቅረባቸው፣
 የለውጥ አመራርንና አሰራርን በቁርጠኝነት ያለመቀበልና የለውጡን ቀጣይነት በጥርጣሪ
የመመልከት ዝንባሌ በማሳየት ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ አለመሆናቸው፣

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 38


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ውጤታማነትን ለማፋጠን የሚያስችል ቁርጠኛ የለውጥ አመለካከትን በሚፈለገው ደረጃ


ማጎልበት አለመቻል፣
 የለውጥ ስራውን በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም ያለው የዝግጁነትና በኃላፊነት የሚፈጽማቸውን
ተግባራት በባለቤትነትና በውጤታማነት ስሜት ለመፈፀም የሚታየው ተነሳሽነት ማነስ፣
ድክመቶች ያሉባቸው መሆኑ ተገልጾ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

3.3 ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራት


 ከግለሰብ ፈጻሚዎች የምዘና ውጤት በመነሳት በየደረጃው ለሚገኙ ክፍሎችና በተቋም ደረጃ
የተገኘውን የተጠቃለለ የአፈጻጸም ምዘና ውጤት ለመለየት የሚያስችሉ መረጃዎችን በተሟላ
መልኩ ማግኘት ባለመቻሉ የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ምዘና አልተካሄደም፣
የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ለመመዘን የሚያስችሉ ጥረቶች በመደረግ ላይ
ይገኛሉ፣
 የማበረታቻ ሥርዓት ተዘርግቶ ባለመተግበሩ ጥንካሬዎችን ለማሳደግም ሆነ ድክመቶችን
ለማስተካከል የሚያስችሉ እርምጃዎች አልተወሰዱም፣
 የከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰረቁ /የጠፉ/ የተለያዩ ንብረቶች (የደንብ ልብስ፣ የተሸከርካሪ መለወወጫ)
ላይ ምርመራ ረጂም ጊዜ በመውሰዳቸው እና መፍትሄ ያላገኘ የሰው ኃይል እጥረት በመኖሩ
በኦዲት ዳይሬክቶሬት የተያዙ ዕቅዶችን በሙሉ መፈጸም አልተቻለም፣

3.4 በዕቅድ አፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች


ከፌዴራል ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሰጪና የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች የቀረቡ የአፈጻጸም ሪፖርቶች
ካመላከቱዋቸው በአፈጻጸም ያገጠሙዋቸው ችግሮች መካከል የሚከተሉት ጎልተው የታዩ እንደነበሩ
መረዳት ተችሏል፡፡

3.4.1 ችግሮች
 በሁሉም ፍ/ቤቶች የሚታየውን ከፍተኛ የሠራተኛ ፍልሰት ለመከላከልም ሆነ ባለሙያዎችን
ከውጭ ለመሳብ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩ የሰው ኃይል እጥረት ችግሮችን መፍታት
አለመቻሉ፣
 ተደጋጋሚ የመብራት እና የኔትወርክ መቆራረጥ በመኖሩ በችሎቶችም ሆነ በድጋፍ ሰጪ
ክፍሎች አሠራሮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ መፈጠሩና በኢኮቴ መሳሪያዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ
መሆኑ፣
 በድሬዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚገኘው የቪዲዬ ኮንፈረንስ ማዕከል አገልግሎት በኔትወርክ ችግር
ምክንያት መስራት አለመቻሉ፣
 የማስችያ፣ የተገልጋይ ማስተናገጃ፣ የሰነድ ማስቀመጫ በአጠቃላይ በፍ/ቤቶች ውስጥ ተገቢውን
አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልና የሥራ ፍሰትን የተከተለ በቂ የቢሮ አደረጃት አለመኖሩ፤
 ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የመሬት አስተዳደር ለሚቀርብለት የአፈጻጸም ጥያቄ የተሟላ
መረጃ አለመስጠት /ማዘግየት/፣ ባለድርሻ አካላት የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አክብረዉ ወቅታዊ ምላሽ
አለመስጠት፤ በፍድ አፈፃፀም ሂደት ፖሊስና የቀበሌ መስተዳድር ተገቢውን ዕገዛና ትብብር
አለማድረግ፣ አንዳንድ ባለጉዳዮች ፍ/ቤት ያልተነሳና ውሣኔ ያልተሰጠበትን ጉዳይ በማቅረብ
አፈፃፀሙ በጊዜው እንዳይከናወን ችግር መፍጠር፤ የአፈፃጸም ውሳኔ የተሰጠበትን ንብረት
የፍርድ ባለዕዳዎች ማሸሽ/በሌላ መለወጥ/፤ በፍርድ አፈፃፀም ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ባለመበትም

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 39


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ሆነ ባለዕዳ በአፈፃፀም በተያዘላቸዉ ቀጠሮ አለመገኘት፣ የፍርድ ባለመብቶችና የፍርድ ባለዕዳዎች


በአፈፃፀሙ ቦታ/ ስፍራ/ ላይ ሁከትና ረብሻ መፍጠር ወዘተ…
 ለይግባኝ ወይም ለሠበር የሚቀርቡ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔዎች ተነባቢ አለመሆን፤ በስር ፍ/ቤቶች
የሚሰጡ ፍርዶች የአፃፃፍ ችግር ያለባቸው በመሆኑ በቅልጥፍና ላይ ተጽዕና ማሳደራቸው፤
 ባለው የሲቪል ሰርቪስ የሰው ኃብት አስተዳደር ሥርዓት ብቃት ያለው የሰው ሀይል አለመገኘቱ፣
 በሁሉም ፍ/ቤቶች አስተርጓሚ የሚፈልጉ ተጠቃሚዎችን ብዛትና የቋንቋዎችን ዓይነት ያገናዘበ
አስተርጓሚ መመደብ አለመቻል፣
የሚሉት በአፈጻጸም ሪፖርቶች ከቀረቡ ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

3.4.2 ችግሮችን ለማቃለል በተግባር ላይ የዋሉ የመፍትሄ እርምጃዎች


 በመብራት መቆራረት ምክንያት የችሎት ሥራዎች እንዳይቋረጡና በተገልጋዮች ዘንድ መጉላላት
እንዳይፈጠር የጀነሬተር ግዥ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፣ የኔትወርክ መቆራረጥ
በቪዲዮከንፍረንስ ክርክሮች ላይ የፈጠራቸውን ችግሮችም ለማቃለል ዳኞች በተዘዋዋሪ ችሎት
ወደ ክልሎች (ለምሳሌ የጠ/ፍ/ቤት ዳኞች ድሬድዋ ወደሚገኙ ችሎቶች) ሄደው አገልግሎቶችን
ሰጥተዋል፣
 የቋንቋ አስተርጓሚ ችግር በዘላቂነት እስኪፈታ በፍ/ቤቱ አካባቢ የሚገኙ ቋንቋውን ለማስተርጎም
የሚችሉ ሰዎችን ትብብር በመጠየቅ ለመገልገል ተሞክሯል፤
 በፍርድ አፈፃፀም ዙሪያ በአፈፃፀም ቦታ ሁከት እንዳይፈጠር የጸጥታ አካላትን በማበራከት
አስፈላጊውን ክትትል የማድረግ ስራ ተሰርቷል፤

3.4.3 ለቀጣዩ በጀት ዓመት የአመራሩን ውሳኔ የሚሹ ገዳዮች

የቀጣዮን በጀት ዓመት አፈጻጸም የተሳካ ለማድረግ የፍ/ቤቶች የበላይ አመራር አካላት ትኩረት ሰጥተው
መፍትሄ ሊሰጡባቸው ይገባቸዋል ተብለው በአፈጻጸም ሪፖርቶች ከቀረቡ ጉዳዮች መካከል፡-
 በችሎቶች እና በቢሮዎች እጥረት ምክንያት የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ
የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ማድረግ፣
 የሰው ኃይል ፍልሰቶችን ለመቀነስና የተሻለ አቅም ያላቸው ባለሙያዎችን ወደ ፍ/ቤቶች ለመሳብ
የሚያስችሉ አሰራሮችንና ጥቅማ ጥቅሞችን ማመቻቸት፣
 በአጠቃላይ የአፈጻጸም ምዘና ሥርዓቱን ለመተግበር የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት
ጠንካራ አፈጻጸሞች ይበልጥ የሚጎለብቱበት፣ የአፈጻጸም ክፍተቶች የሚሞሉበትና የተጠያቂነት
ሥርዓት የሚተገበርበትን ሁኔታ መፍጠር፣
የሚሉት ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ናቸው፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 40


የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ሪፖርት 2007ዓ.ም

ማጠቃለያ

ለዕቅድ አፈጻጸምና ለባህሪ ለውጥ እንዲረዱ የተሰጡ ስልጠናዎች በዳኞችም ሆነ ድጋፍ ሰጪ


በሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች ዘንድ የአፈጻጸም ውጤታመነት ዕድገትና የአመለካከት
ለውጥ ማምጣቱን፣ በሰብዓዊ መብቶች አከባበርም ሆነ በመልካም አስተዳደርና በሥነ ምግባር
መርሆች አተገባበር ዙሪያ የተሻለ አፈጻጸም በመታየቱ በኪራይ ሰብሳቢነት ላይ የሚደረጉ
ትግሎች መጠናከራቸውን ወዘተ…ከችሎቶችና የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍሎች የቀረቡ የዕቅድ
አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርቶች ያመላክታሉ፡፡ የእነዚህ ተግባራት አፈጻጸም ዕድገት በዕቅድ
አፈጻጸም ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ሂደት የተለዩ ክፍተቶችን ከመሙላት ጋር ተያይዞ
እየጨመረ የመጣ ሲሆን የምዘና ሥርዓቱ በተሟላ መልኩ በሚተገበርበት ደረጃ ላይ ሲደረስ
የአፈጻጸም ውጤታማነቱም ሆነ የአመለካከት ለውጡ በዚያው ልክ እያደገ ወደ ከፍተኛ ደረጃ
ይሸጋገራል ተብሎ ይታመናል፡፡

ለዚህም የፌዴራል ፍ/ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች፣ የውሳኔ ሰጪ እና የሲቪል ሰርቪስ ሥራ ክፍል


በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ሠራተኞች በፍ/ቤቶች ውስጥ የተጀመረውን የለውጥ
መሳሪዎች አተገባበር ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል አመለካከትና ቁርጠኝነት ማጎልበት
ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተቋም ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ አተገባበሮችን ለማጠናከር የአፈጻጸም ክትትል፣
ድጋፍና የተጀመሩ የተናጥልና የጋራ ግምገማዎችን አጠናክሮ መቀጠል፣ የተለዩ ክፍተቶችን መሙላት
ወይም እንዲሞሉ ማድረግ፣ ለተገኙ ውጤቶች ተገቢውን ዕውቅና መስጠት፣ የላቁ ፈጻሚዎችን በግንባር
ቀደምነት ለይቶ ዕውቅና መስጠት፣ ሌሎች ፈጻሚዎችንም በዙሪያቸው በማሰለፍ የፍትህ ለውጥ ሠራዊት
ማፍራትና የለውጡን ቀጣነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ከዚህም በላይ የፌዴራል ፍ/ቤቶች የሚሰጡዋቸውን አገልግሎቶች አስመልክቶ ከዳኝነት ዘርፉ ጋር


የተጣጣመና በተግባር የተፈሸ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንደርዶችን በማዘጋጀት ግዴታቸውን ለህዝብ
የሚያሳውቁበት የዜጎች ቻርተር አዘጋጅተው ለሕዝብ ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ
በፌዴራል ፍ/ቤቶች በሚሰጡ የዳኝነት አገልግሎቶች የተገልጋዮችን እርካታ መጨመር ከማስቻሉም ሌላ
በሕብረተሰቡ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው የፍትህ ሥርዓትን አጠናክሮ ለመቀጠል ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት Page 41

You might also like