Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦ/ማ

የኦዲት ማስታወሻ

ኦዲት ተደራጊው መ/ቤት፡-ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ

ኦዲት የሚደረገው ሂሳብ በጀት ዓመት፡- 2010

ኦዲት ሥም የኃላፊነት ደረጃ ቀን ፊርማ

የከለሰው ሰኢድ አ/ቃድር ከፍተኛ ኦዲተር 10/10/1


0

የከለሰው ሲሰይ ተክሉ የኦዲት ስራ አስኪያጅ

የከለሰው ሰይፉ ከበደ የኦዲት ዳይሬክተር

ለግርማ ግሩሙ፤ የሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

ማስታወሻው የተሰጠበት ቀን፡-06/11/10

የኦዲት ማስታወሻ ቁጥር፡- 04

የኦዲት ማስታወሻው አርዕስት ፡- የሰው ሀብት በቅጥር ሟሟላትን በተመለከተ

የታየው የገንዘብ መጠን ፡-አግባብነት የለውም

የሂሣቡ መደብ ፡- አግባብነት የለውም

የሂሳቡ ዝርዝር ሁኔታ፡- ዩኒቨርሲቲው የተፈቀደለትን ክፍት የስራ መደብ በሰው ኃይል ያላሟላ መሆኑን
ይመለከታል

የግኝቱ መግለጫ፣

የፌዴራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/1999 ክፍል ሦሥት ምዕራፍ አንድ አንቀጽ 12 ሠራተኛ
ስለመመልመል፤መምረጥና መቅጠር፤ ንዑስ አንቀጽ 1/ የሰው ኃይል ዕቅድ ዓላማ ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት
በስትራቴጂካዊ ዕቅድ የተቀመጡትን ዓላማዎች ለማሳካት የሠው ኃይል ፍላጎት ለመተንበይ፤የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል
በዓይነትና በብዛት ለማሟለት፤ለማልማት በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዙ እርምጃዎችን ለመውሰድና ውጤቱንም በጊዜው
እየገመገመ ማሸሻያ ለማድረግ ነው ይላል፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3/ ክፍት የስራ መደቦችን በሰራተኛ ማስያዝ
የሚቻለው የሰው ኃይል ዕቅድን መሰረት በማድረግ በደረጃ እድገት ወይም በቅጥር ወይም በዝውውር ወይም በድልድል ይሆናል
ይላል፡፡
በዚሁ መሰረት የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተፈቀደለትን የሰው ኃይል በቅጥር ስለማሟላቱ ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤-
 ለዩኒቨርሲቲው የተፈቀደ የአስተዳደር የሥራ መደብ ብዛት 1324 ሲሆን በሰው የተያዘ የስራ መደብ 578 ብቻ ስለሆነ
የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦ/ማ

እስከ አሁን በሰው ኃይል መሟላት ሲገባው ያልተሟላ ክፍት የስራ መደብ ብዛት 746 (56.34%) መኖሩን ፤
 በሰው ሀብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባለው ክፍት የስራ መደብ ላይ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል
ባለማሟላቱ ምክንያት ስራዎች እንዲጓተቱ እና መረጃዎችን በወቅቱ አጠናክሮ ማቅረብ ላይ ክፍተት ያለ መሆኑ፤
 በፋይናንስ እና በተለያዩ የስራ ክፍሎች ያለውን ክፍት የስራ መደብ በቅጥር፤በዝውውር ወይም በእድገት ማሟላት
እየተቻለ አጠቃላይ ከተፈቀደው የስራ መደብ 25 ውስጥ በ 9 ብቻ በሰው ኃይል የተየዘ የስራ መደቦች መሆኑ፤
 ዩኒቨርሲቲው ያለውን ክፍት የስራ መደቦችን በቅጥር አሟልቶ ማሰራት ሲገባው ያለአግባብ በየወሩ ለተለያዩ የስራ
ክፍሎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ እየከፈለ መሆኑ ታውቀዋል፡፡

ስጋት

ዩኒቨርሲቲው ያለውን ክፍት የስራ መደብ በሰው ኃይል ከላሟላ የተሰጠውን ራዕይና ተልኮ ላያሳካ ይችል ይሆናል፡፡

በሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት ዳይሬክተር መወሰድ ያለበት የማሻሻያ እርምጃ ፣

ዩኒቨርሲቲው በአዋጁ ላይ በተቀመጠው መሰረት ክፍት የስራ መደቦችን ለይቶ የቅጥር ማስታወቅያ አውጥቶ ቅጥር
በመፈጸም የተሰጠውን ራዕይና ተልእኮ ማሳከት ይኖርበታል ፡፡

የሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት ዳይሬክተር ምላሽ፣


የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦ/ማ

የሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት ዳይሬክተር ስም-------------

ፊርማ ----------------

ቀን ፡- --------------------

የኦዲተሩ አስተያየት፣

You might also like