Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 1

1 #ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው?

፠ጥምቀት በግእዝ ልሳን(አጥመቀ አጠመቀ ነከረ) ካለው ግስ የተገኘ ነው ። ትርጉሙ መላ ሰውነትን በውሃ ውስጥ መንከር
ወይም ማጥመቅ ማለት ነው።

2 ጥምቀትን የጀመረው ማነው?

፠እውነተኛዋን ጥምቀት የጀመረው ወይም የመሰረተው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

3 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛዋን ጥምቀት የመሠረተው መቼ ነው?

፠ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ከድንግል ማርያም በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ተወልዶ እድሜው 30 ዓመት ያህል
ሲሆነው በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ መሠረተው(ሉቃስ 3፥21-23)።

የጌታችን ጥምቀት ታሪክ በአጭሩ እንዲህ ነው፦

"ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ዮሐንስ ግን እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተ ግን
ወደ እኔ ትመጣለህ? ብሎ ከለከለው ኢየሱስም መልሶ አሁንስ ተው እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈፀም ይገባልና አለው። ያን
ጊዜ ፈቀደለት።ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሄር መንፈስ እንደ
ርግብ ሲወርድ በእርሱም ላይ ሲቀመጥ አየ እነሆም ድምፅ ከሰማይ መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው
አለ" (ማቴ 3፥13-17) ማር 1፥9 ሉቃ 3፥21 ዮሐ 1፥32።

5 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ?

፠ቅዱስ ዳዊት የተናገረው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ(መዝ 113፥3)።

፠ዮርዳኖስ ለጥምቀት ታሪካዊ ምሳሌ ያለው በመሆኑ።

፠ዮርዳኖስ ለምስጢረ ሥላሴ ምስጢራዊ መሳሌ ያለው በመሆኑ።

፠ ዲያቢሎስ በዮርዳኖስ የደበቀውን የአዳምንና የሄዋንን የእዳ የባርነት ደብዳቤ ይደመስስ ዘንድ(መፅሐፈ ቀሌምንጦስ)።

N.B የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በጌታችን የጥምቀት እለት የምንጠመቀው ከጌታ ጥምቀት እረድኤት በረከት እናገኝ ዘንድ
ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሄር

You might also like