ለፓስፖርት አገልግሎት መ

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 5

ለፓስፖርት አገልግሎት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

1. ለአዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች

1.1 እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ጠያቂዎች

 የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም፣

 አገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ ወይም፣

 ውጭ አገር ነዋሪ ሆነው በሊሴፓሴ የገቡ ከሆነ ወደአገር በገቡ በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ

ሊሴፓሴውን ይዘው በመቅረብ መስተናገድ ይችላሉ፡፡

1.2 እድሜያቸው ከ 18 አመት በታች ለሆኑ አዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች

o ፓስፖርት ሲጠየቅ ህፃኑ በአካል መቅረብ አለበት፣

1.2.1 ወላጆች ይዘው ሲቀርቡ ማሟላት ያለባቸው

 እድሜው ከ 6 ወር በታች ለሆነ ህፃን የሆስፒታል የልደት ማስረጃ በማቅረብ የሚስተናገዱ ሲሆን

ከ 6 ወር በላይ ለሆናቸው ህፃናት በወሳ„ኩነቶች የተዘጋጀ የልደት ሰርተፊኬት ማቅረብ

ይኖርባቸዋል፣

 መጠኑ ¾ የሆነ የህፃኑ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣

 የወላጅ የቀበሌ /የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት/፣

ፓስፖርት ለመቀየር በሚቀርብ ጥያቄ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች

እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በላይ ለሆኑ፣

1 የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ ወይም ገጽቹ ያለቁ ፓስፖርት ለመቀየር o የቀድሞው ፓስፖርት ከነኮፒው ተያይዞ ሲቀርብ፣
2 የጠፋ ወይም የተበላሸ ፓስፖርት ለመቀየር

- ፓስፖርቱ ከጠፋ የፖሊስ ማስረጃ ወይም ውጭ ሀገር የጠፋ ከሆነ የገቡበትን ሊሴፓሴ፣ - ፓስፖርቱ ከተበላሸ
የተበላሸውን ፓስፖርት ከነኮፒው አያይዞ ማቅረብ፣ ያስፈልጋል።

3 ለፓስፖርት እርማት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች

- ስም ለመለወጥ የፍ/ቤት ማስረጃ፣


- ፓስፖርቱ እና ለእርማት የሚያስፈልጉ መረጃዎች (የልደት ሰርትፍኬት) ዋናው ከነኮፒው መቅረብ አለበት፣ - ከ 18
አመት በታች ለሆኑ የፓስፖርት እድሳት ጠያቂዎች

- የህፃኑ ፓስፖርት ዋናው ከነኮፒው፣

- ለማስፈፀም የቀረበው አባት ከሆነ የአባት የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም

የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ፣

- እናት ከሆነች የህፃኑን የልደት ሰርትፍጄት፣ የእናት የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት

ወይም የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ፣ ማቅረብ ያስፈልጋል።

የህጻኑ የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ ከወላጅ ውጭ በሞግዚት ፣ በተወካይ እና በጉዲፈቻ የቀረበ ከሆነ

የሞግዚትነት የውክልና የአሳዳጊነት ወይም ጉዲፈቻ አድራጊነት የተፈቀደበት ማስረጃ አግባብ ካለው

መንግስታዊ አካል ማቅረብ ያስፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡-

- በጊዜያዊ መታወቂያ አገልግሎት አንሰጥም፣

- ማንኛውም ባለጉዳይ የሚያቀርበው ሰነድ ህጋዊ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፣

- በተጭበረበረ ሰነድ ለመስተናገድ መሞከር በህግ ያስጠይቃል፡፡

ለግንዛቤዎ

1. በተደጋጋሚ ወደ ውጭ የሚመላለሱ በመሆኑ ምክንያት የፓስፖርቶ ገጾች ከፓስፖርቱ የአገልግሎት

ጊዜ በፊት ቢያልቅብዎ ባለ 64 ገጽ ፓስፖርት በአገልግሎት ላይ ያዋልን ስለሆነ መጠየቅ ይችላሉ።

2 ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማግኘት የሚያስገድድ ሁኔታ ቢገጥሞት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ

እንዲሁም ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት የጠበቅበታል፦

 ለህክምና ከሆነ የሕክምና ማስረጃ

 የውጭ የትምህርት ዕድል ያገኙ የጀመሩት ፕሮሰስ የሚያሳይና የተምህርት ማስረጃ

 ለመንግስት ስራ ክሆነ የመስሪያቤቱ ደብዳቤና የመ/ቤት መታወቅያ

 የውጭ አገር ኗሪ ከሆኑ መኖሪያ ፍቃድ ወይም ቪዛ

 ለ DV ደርሶት ፕሮሶስ የጀመሩ


 ኢምባሲ ቀጠሮ ካላቸው የኢምባሲ ቀጠሮ ማቅረብ የሚችሉ ከሆኑ

 መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሰሩ የድርጅቱ መታውቅያና የሚሄዱበት ምክንያት የሚገልጽ

ደብዳቤ ካቀረቡ፣

ነጋዴ ክሆኑ

o የከፈሉበት LC

o የታደሰ ንግድ ፍቃድ

o ውል ያላቸው ከሆኑ ቅድሚያ መስተናገድ ይችላሉ።

3. መንግስት ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረገው ሕገወጥ ስደት በማስቆም ሕጋዊ የውጭ አገር የስራ

ስምሪት ለማጠናከር ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በመሆኑም ፓስፖርት ለማውጣት ወደ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ አገልግሎት

መስጪያ ማእከላት ለምትመጡ ዜጎች የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት

ይተበቅባቸዋል፦

ዕድሜያቸው ከ 18 እስከ 55 ዓመት ለሆኑ ዜጎች ላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶች(ምሳሌ የቀበሌ መታወቅያ)

በተጨማሪ፦

 የመንስግት ሰራትኛ መሆናቸው የመ/ቤት መታወቅያ

 ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ

 በግል ድርጅት ተቀጣሪ ከሆኑ የመ/ቤቱ ደብዳቤና መታወቅያ

 መንግስታዊ በልሆኑ ድርጅቶች (NGO) ተቀጣሪ ከሆኑ የድርጅቱ ደብዳቤና መታወቅያ

 ለህክምና ለሚሄዱ የሕክምና ማስረጃ

 ለትምህርት ለሚሔዱ የተጻጻፉበት ማስረጀ

 ለጉብኝት ከሆኑ የግብዣ ደብዳቤ

4. በሕጋዊ መንገድ ለሰራ ወደ ውጭ አገር የሚሄድ ማንኛውም ሰራተኛ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት
የጠበቅበታል፦

ሀ) ቢያንስ የስምንተኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ፣ እና

ለ) በሚቀጠርበት የሥራ መስክ አግባብ ካለው የምዘና ማዕከል (ቴክኒክና ሙያ) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
ማስረጃ የያዘ፣ መሆን አለበት፡፡

ሐ) ዕድሜው ከ 21 ዓመት በላይ የሆነ፣

መ) የጤና ምርመራ ያደረገ መሆን እንዳአበት ይደነግጋል።

2. አዲስ አበባ ከሚገኘው የዋና መምሪያው ጽሕፈት ቤት በተጨማሪ ከዚህ ቀጥሎ በተገለጹት

ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና እንዲሁም በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ማግኘት

ይችላሉ።

1 ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

2 ደሴ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

3 ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

4 ባህርዳር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

5 መቐለ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

6 ጅማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

7. ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

8. ሳመራ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

9. አዳማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

ለበለጠ መረጃ ወይም ለቅሬታ አድራሻችን

ነጻ ስልክ 8133

መደበኛ ስልክ 0111560167 ወይም 0118287216

website www.immigration.gov.et

Face book, MDINA Ethiopia

ኢሜይል support@ immigration.gov.et


ፖስታ 5741

You might also like