Quantum Jumping

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

መንፈሳዊ ፍቅር

ቀደመት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ሕይወትን እንደ ህይወትነቷ አጣፍጠው ትርጉም ያለው ስራ ሰርተው እኛን ኢትዮጵያውያንን ወይም መላውን
የጥቁር ህዝብ ብቻ ሳይሆን የየትኛውንም ዓለም ህዝብ ቀልብ የገዛና ያስደነቀ ጥበባዊ ስራዎቻችው መነሻ የነበሩት  ጥበባቶች  እና ስኬታማ የነበረው
የህይወት ፍልስፍናቸውን ለየትውልዱ በቃልም ሆነ  በጽሁፍም እያስተላለፉ ከዚህ ከኛ ዘመን አድረስውልናል፡፡
አባቶቻችን ጥበባቸውን እና የህይወት ፍልስፍናቸውን ትተውልን ያለፉት እኛም እንደነሱ ስኬትን በስኬት ላይ እንድንጎናጸፍ በመሆኑ ተጽፈው
የተቀመጡትንም ሆነ ሌሎች በቃል እየተወራረሱ ከዚህ ዘመን የደረሱትን ምክራቸውን እና የኑሮ ዘይቤያቸውን አነፍንፍን በማግኘት የአባቶቻችን ታሪክ
መድገም ብቻ  ሳይሆን አባቶቻችን ከሰሩት በላይ ሰርተን የትውልድ ሃላፊነታችን መወጣት አለበን፡፡  ዋነኛው የአባቶቻችንን ትልቁ የህይወት ምስጢር
እና ፍልስፍና ፍቅር ነበር !! በመጽሀፍ ቅዱሳችን ቆሮ 14 ላይ እንተደተጻፈው አባቶቻችን በጽኑ ፍቅርን ይከተሉ ነበር ለፍቅር ኖረዋል ለፍቅር
ተሰውተዋል ለፍቅር ሞተዋል፡፡ በዚያ ደግ ዘመን ነገስታቱ ህዙቡን ህዝቡ ነገስታቱን ያፈቅር ነበር የሃይማኖት አባቶች ልጆቻቸውን ምእመኑም የመንፈስ
ወላጆቻቸውን ያፈቅሩ ነበር በትዳራቸውም ስጋዊ ፍልስፍናን ሳይሆን መንፈሳዊዉን የፍቅር ፍልስፍና ኖረውበት ስኬታማ ቤተሰባዊ ህይወትን
ተጎናጽፈዋል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደሮሜ በላከው መልእክቱ እንደመከረን (ሮሜ 12፡9)አባቶቻችን  ፍቅራቸው ያለግብዝነት ነበር የማህበራዊ
ህይወታቸው ሰንኮፋ የሆኑትን ክፉ ነገሮች በመቃወም  ከበጎ ነገር ጋር ሁሉ  ይተባበሩ ነበር ዘር ቀለም ጾታ ሃይማኖት ሳይለያዩ ተዋደው ተከባብረው
ይኖሩ ነበር ፡፡
መንፈሳዊ ፍቅር አንድ ባህሪ ብቻ አለው ˝ ፍቅር የእግዚአብሔር ባህሪይ ነው ˝ ሁሌም እውነተኛውን ፍቅር የሚያፈቅሩ ሁሉ እግዚአብሔር እና
ከእግዚአብሔር የሆኑ ናቸው ምክንያቱም የእግዚአብሔር ባህሪይ የተላበሰ ፍቅር ይታገሳል ቸርነትን ያደርጋል አይቀናም አይመካም አይታበይም
የማይገባውን አያደርግም የራሱን አይፈልግም  አይበድልም ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ አይበሳጭም በደልን አይቆጥርም ከእውነት ጋር ደስ
ይለዋል ሁሉን ይታገሳል ሁሉን ያምናል ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይጸናል( 1 ቆሮ 13)፡፡
ፍቅርን እየተከተልን የፍቅርን ባህርይ በሂደት እየተንሳፈፍን ስንሄድ ፍጹም እየሆንን እንሄዳለን የማይቻለውን እንችላለን የማይሸነፈውን እናሸንፋለን
ሁሉን እንችላለን፡፡ የአባቶቻችን ሁሉንም የመቻላቸው ምስጢርም ይህን ነበር . . . ፍቅር( መንፈሳዊ ፍቅር) !!! አባቶቻችን ጥልቅ በሆነ ፍቅር ውስጥ
ይኖሩ ነበር ሀገራቸውን ያፈቅሩ ነበር አምላካቸውን ያፈቅሩ ነበር ቤተሰባቸውን ያፈቅሩ ነበር ወገናቸውን ያፈቅሩ ነበር የእግዚአብሔር ፍጡር የሆነን
ነገር ሁሉ ያፈቅሩ ነበር በዚህም የተነሳ ከፍቅር ባለቤት ከእግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎችን መቀበል ችለዋል፡፡ ይህ ሰማያዊ ስጦታ ሰማያዊ ጥበብ
ነበር ዓለም በድንቁርና ጨለማ ውስጥ ተዘፍቆ በነበረበት በዚያ ዘመን የእውቀት እና የስልጣኔን ችቦ በመለኮስ ለምድራችን ብርሃን እንድንፈነጥቅ
ያስቻለን ሰማያዊ ጥበብ፡፡
በኃላ በኃላ ግን ይህቺ ምድር የሚያፈቅር ሰው እያጣች መጣች በፍቅር ሳይሆን በምድራዊ ድንቁርና የሚንሳፈፍ ትውልድ እየፈራባት ሄደ፡፡
በእግዚአብሔር እና በኛ መካካል ያለውን የፍቅር ገመድ እያሳሳነው መጣን መንፈሳዊው ፍቅርም እየሸሸን እየሸሸን ሲሄድ ስጋዊ ፍቅር እየቀረበን መጣ
በዚህ ምክንያት መንፈሳዊ አይናችን ታውሮ ስጋዊ አይናችን ተከፈተ በዚህ የተነሳ በመንፈሳዊነታችን ያገኘነው ሰማያዊ ስጦታን ማየት ተስኖን ስጋዊዉን
የኛ ያልሆነው ስጋዊ ስጦታ ለመቃረም እሩቅ መመልከት ጀመርን እጆቻችንም ለልመና መዘርጋት ጀመሩ፡፡
እስኪ ስለስጋዊው ፍቅር ባህሪ የተወሰነ እንመልከት፡ ስጋዊ ፍቅር ይቀናል ይታበያል ራሱን ይወዳል ይቅርታን አያውቅም ፈሪሃ እግዚአብሔር የለውም
አክብሮት እና መተሳሰብ የለውም የሚገባውን ትቶ የማይገባውን ያደርጋል መንፈሳዊውን ቁርኝነት ሳይሆን ወሲባዊ ቁርኝነትን ይመርጣል ይቅርታንም
አያደርግም ቂመኛ ነው፡፡  
መንፈሳዊውን ፍቅር በማጣታችን ሀገር እየፈረሰ ነው ትዳር እየፈረስ ነው ቤተሰቦች እየተበታተኑ ነው ማህበራዊ ህይወታቻን ለዛውን አጥቶ እየተናጋ
ነው ዘረኝነት ስግብግብነት በሰፊው ቦታቸውን ይዘዋል  ዝሙታዊነት እና ግብረሰዶማዊነት እየተንሰራፋ ነው የእግዚአብሔር ምድር የተባለችው
ምድራችን የወሲብ ደሴት እየተባለች ነው፡፡ አዛውንቶች መንፈሳዊ ቦታዎች ወይም የሽምግልና ችሎት ላይ ሳይሆን ለጋ ወጣት እህቶች ጋር ለመቅበጥ
በየመሸታ ቤቱ ማየት ወጣቶች ለፈጠራ እና ለእውቀት ሳይሆን በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆነው እድሜያቸውን በጭፈራ ሲገድሉ ማየት ሴት
እህቶቻችን ክብራቸውን ንቀው እንደ ምእራባውያን ሴቶች እርቃናቸውን በአደባባይ ላይ ማሰጣታቸው እንደ ስልጣኔ እየታየበት ያለበት ዘመን ላይ
እንገኛለን፡፡ ፍጹም ስጋዊ በሆነው አርቴፊሻል ፍቅር ቅኝ ግዛት ስር ወድቀናል !!
ውድ አንባብያን ወገኖቼ እንፋቀር የዛሬ መልእክቴ ነው  !! ይህ ያለንበት ዘመን በራሱ የውሸት እና የክህደት ዘመን ነውና እንደ አባቶቻችን ህይወታችንን
እንደ ህይወትነቷ አጣፍጠናት ትርጉም ያለው ቆይታ እንዲኖረን መንፈሳዊ እና እውነተኛውን ቅመም ፍቅርን በህይወታችን ውስጥ እንጨምርበት፡፡
ፍርቅ ደስታ ሰላም ጤና እውቀት እና ሀብት የእግዚአብሔር ናቸውና እንደ አባቶቻችን እጆቻችን ለጸሎት እንዘርጋ ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት እጅን
ለጸሎት መዘርጋት ነው፡

                                           እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ይባርክ !!

Quantum Jumping

Quantum Jumping ነጮች የስነልቦና ባለሙያዎች በስራ እና በትምህርት መስክ ላይ ድክመት የሚያሳዩ ሰዎችን አልያም ደግሞ በገጠማቸው አስከፊ
የህይወት ገጠመኝ ምክንያት ተስፋ ቆርጠው እጅና እግራቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ ሰዎችን ለተሻለ ስራ ለማነሳሳት እንዲሁም በተሰማሩበት
የትምህርት ወይም የስራ ዘርፍ ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚጠቀሙበት በዋጋ ውድ የሆነ ህክማና ወይም የስነልቦና እርዳታ ሲሆን ግለሰቡ በተመስጦ
በህይወቱ የሚፈልገውን አልያም የሚሻውን ነገር በተደጋጋሚ  እንዲያስብ ወይም visualize እንዲያደርገው በማደረግ ግለሰቡን ላይ የተነሳሽነት
ስሜትን የሚፈጥሩበት ሳይንስ ነው፡፡
ከ Quantum Jumping ሳይንስ በተሻለ አባቶቻችን  ስነልቦናዊ መነሳሳትን ብቻ ሳይሆን ግለሰቡን ከተዘፈቀበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ
መንጥቀው በማውጣት ለተሻለ ስራ እንዲነሳሳ የሚያደርጉበት የራሳቸው ጥበብ የነበራቸው ሲሆን

ትልቁን ሚና የሚጫወተው ደግሞ ለዚሁ እርዳታ የተዘጋጀው ጠልሰም  ነው፡፡

ተስፋ የቆረጡ ወይም ደግሞ በተሰማሩበት የስራ መስክ  ስኬትን መጎናጸፍ የሚፈልጉ ሰዎች ይህን ጥበብ ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን አጠቃቀሙም
እንደሚከተለው ነው፡

1. ተጠቃሚው ግለሰብ ለተመስጦ እንዲረዳው ንጹህ እንዲሁም ሁካታና ግርግር የሌለበት ቦታ ያዘጋጃል ብዙውን ጊዜ በቅጽረ ቤተክርስትያን
ውስጥ እንዲሆን ይመከራል
2. ግለሰቡ ለተመስጦ የሚረዳውን ጠልሰም እንዲሁም የጸሎት መጽሀፍ ያዘጋጃል
3. ምቹ የሆነ ቦታ ሲያገኝ አእምሮውን በመሰብሰብ አስቀድሞ አባቶች ያዘጋጁትን የጸሎት መጽሀፍ ይጸልያል
4. ጸሎቱን ከጸለየ በኃላ የተዘጋጀለትን ጠልሰም ፊት ለፊቱ አስቀምጦ ስእሉ ላይ ወይም ጠልሰሙ ላይ አተኩሮ በተመስጦ በህይወቱ
የሚፈልገውን ነገር ያስባል ወይም Attract ያደርገዋል፡፡ ጠልሰሞቹ ግለሰቡ ጥልቅ የሆነ ተመስጦ ውስጥ እንዲሆን የሚረዱት  በጠልሰሙ
ላይ ያሉት ቀለማት ሲሆኑ በግለሰቡ አእምሮ ላይ ጉልህ ተጽእኖን እንዲፈጥሩ ተደርገው በልዩ መንፈሳዊ ስርዓት ይቀመማሉ፡፡
5. ይህን የጸሎት እና እና የተመስጦ ሰርአት ግለሰቡ ለተከታታይ 15 ቀናት ቢያደርግ ግለሰቡ የስራ መነሳሳቱ እንደሚጨምርና ወዳሰበው
የህይወቱ የስኬት መድረሻ የሚሆነውን ስነአእምሮዋዊ መነቃቃትን እንደሚያገኝ አባቶች ይናገራሉ፡፡                                    

You might also like