Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የባህረ ሰላጤው ጦርነት እና የቡሽ ቀመር

ቡሽ ወደ ባህረ ሰላጤው ጦርነት መቃረቢያ የአዲስ የአለም ስርአት መገለጫዎችን በመወሰን እና የአዲሱን የአለም
ስርአት ስኬት አለም አቀፍ ማህበረሰብ በኩዌት ጉዳይ ከሚሰጠው ምላሽ ጋር በማያያዝ ፤ የተነሳሽነቱን መንበር
ከጎርባቾቭ ለይ መንጠቅ ጀመሩ።

ሶቭየቶቸ በሳዳም ሁሴን ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ቀድመው መስማማታቸው ፤ በአዲስ የአለም ስርአት ስኬት እና
በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ምላሽ መካከል ያለውን ግንኙነት በጋዜጦች ጎልቶ ተነሳ። ዘ ዋሽንግተን ፓስት አንዳስነበበው
ይህ የልዕለ ሃያላኑ ትብብር ሶቪየት ህብረት የአለም አቀፉን ማህበረሰብ መቀላቀሏን እና በአዲስ የአለም ስርአት ሳዳም
ከአሜሪካ ጋር ብቻ ሳይሆን ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንደሚላተሙ ማሳያ ነበር (20)።የኒውዩርክ ታይምስ ርእሰ
አንቀፅ በጋራ ከሳዳም የተጠው ምላሽ መያዣ ያደረገው " ቡሽ እና ሌሎች መሪዎች ቅርፅ ለማስያዝ የለፋላትን የአዲስ
የአለም ስርአት" መሆኑን አስረግጦ ለማቅረብ የቀደመው አልነበረም (21)።

ስኮው ክሮፍት በተለወጠው አለም (A World Transformed) ላይ እንዳሰፈሩት ቡሽ ሌላው ቀርቶ ኩዌትን ነፃ
በሚያወጣው የጥምረቱ ሐይሎች የሶቭየት ወታደሮች ለማካተት ሐሳብ አቅርበው ነበር ። ቡሽ የአዲስ የአለም ስርአት
እጣ ፈንታ ላይ አሜሪካ እና ሶቪየት ህብረት ለሳዳም ጠብ አጫሪነት በሚሰጡት ምላሽ ጋር አቆራኝተውታል።
ሐሳባቸውም የፐርሺያ ባሕረ ሰላጤው ጦርነት የአዲስ የአለም ስርአት ወጥ የሆነ አቋም መያዝ እንዲጀምር እድል
ይሆናል።

ቡሽ እንደገለፁት "መነሻ ሐሳብ የሆነው የኢራቅ ችግር እንደማሳያ ተወሰደ አሜሪካ ከእንግዲህ ወዲህ የአለም ማህበረሰብ
ታይቶ ወደማይታወቀው ከፍታ መምራት ግዴታዋ ይሆናል። ከዚህም በላይ የብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስከበር
የምናደርገው ጥረት ከወዳጆቻችን እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ውስጥ እንዲሆን የተቻለንን ሁሉ
እናደርጋለን ።"

በመጋቢት 6, 1991, ፕሬዚዳንት ቡሽ በኮንግረሱ ፊት ቀርበው በተለምዶ የቡሽ አስተዳደር ዋና ፓሊሲ መግለጫ ተብሎ
የሚታወቀውን ንግግር አደረጉ ። መግለጫው ትኩረቱን ያደረገው የኢራቅ ሐይሎች ከኩዌት መባረራቸውን ተከትሎ
የአዲስ የአለም ስርአት በመካከለኛው ምስራቅ ያለበትን ሁኔታ ነበር። ማይክል አፌን የፕሬዚዳንቱን ንግግር ፍሬ ሃሰቦች
በዚህ መልኩ አቅርቦታል። "ፕሬዚዳንቱ የአሜሪካንን የባህር ሐይል በፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ያለውን ይዞታ ለማስጠበቅ ፣
ለመካከለኛው ምስራቅ እድገት ድጋፍ ለማቅረብ እና ከነፍስ ወከፍ በላይ ያሉ የጦር መሣሪያዎችን ስርጭትን ለመጠበቅ
እቅዳቸውን ይዘው ቀርበዋል። የእቅዳቸው ማጠንጠኛ የነበረው ግን በግዛት በሰላም መርህ (Territory- for- peace
principle) መሰረት በአረቦች እና እስራኤል መካከል ስኬታማ ስምምነት መፍጠር እና የፍልስጤማውያንን መብቶች
ማሟላት ነበር።" እንደ መጀመሪያ እርምጃ, ቡሽ ማድሪድ ላይ የአለም አቀፉን የሰላም ኮንፈረንስ በድጋሚ ለመገናኘት
ያላቸውን ፍላጎት አሳወቁ ።

በመስከረም 11, 1990 ኮንግረደጅ የጋራ ስብሰባ ባቀረቡት "ወደ አዲስ የአለም ስርአት" (Toward a New World Order)
ከተሰኘው ንግግራቸው ጋር————በወቅቱ ሀሳባዊነታቸው ከዊድሮ ዊልሰን እና ከፍራንሊን አዲ ሩዝቬልት የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት ምስረታ ጋር የተነፃፀሩት ጎርባቾቭ ሳይሆን ቡሽ ነበሩ። በመገናኛ ብዙሃኑ የተነሱ ቁልፍ ሃሳቦች ፦

 አሜሪካ አለምን ሐይል ከመጠቀም ወደ የህግ የበላይነት እንድታመራ በቁርጠኝነት ማጠናከር። የባህረ ሰላጤው
ቀውስ አሜሪካ በመሪነቱ መቀጠል እንዳለባት እና የጦር ኃይል ጥንካሬ አስፈላጊ እንደሆነም አስታውሶ አልፏል።
ነገር ግን የተፈጠረው የአዲስ የአለም ስርአት ለወደፊት የጦር ኃይል ወሳኝነትን መቀነስ አለበት።
 የሶቭየት -አሜሪካ አጋርነት ትብብር አለምን ለዲሞክራሲ ምቹ ለማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት
ግቦችን ከምስረታው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስኬታማ እንዲሆኑ ማስቻል። በርካቶች ግን ይህ የማይሆን ነገር
ነገር እነደሆነ እና የርዕዮተ አለም ውጥረቱ የሚቀጥል ይህም ሁለቱ ልዕለ ሃያላን አጋርነታቸውን ለተወሰኑ እና
ለተመረጡ ግቦች ብቻ ይሆናል። የሶቭየት ህብረት ወደ ውጪ ሃይልን ለማንፀባረቅ አቅም ማጣት በእኩልነት ላይ
የተመሰረተ አጋርነትን አማራጭ የሚያደርግ ሌላ ነጥብ ነው ።
 ሌላው ሊታሰብበት የሚገባው ነገር ደግሞ አዲስ የአለም ስርአት የተመሰረተው በአሜሪካ -ሶቭየት ትብብር ላይ
ሳይሆን በቡሽ እና ጎርባቾቭ ላይ ነበር። እናም ይህ በግለሰቦች ላይ የተንተራሰ ዲፕሎማሲ ጠቅላላ ሐሳብን እጅግ
ተሰባሪ አድርጎታል።
 ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶች ምክንያቶች ርዕዮተ አለማዊ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ ነው።
ምክንያቱም የአንደኛው እና ሁለተኛው አለም ሐገራት በሶስተኛው የአለም ሐገራት ቀጠናዊ አለመረጋጋት
እንዳይከሰት ስለሚተባበሩ ነው።ራሺያ ከኤስያ ለሚከሰቱ ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች ፣ እስላማዊ ሽብርተኝነት እና
ከላቲን አሜሪካ ከሚዘዋወሩ እፆችን ለመመከት አጋር ልትሆን ችላለች።
 የሶቪየት እንደ ጂ –7 አይነት የአለም የኢኮኖሚ ተቋማትን መቀላቀል እና ከአውሮፓውያን ማህበረሰብ ጋር
ግኑኝነት መመስረት።
 የጀርመን ሉዓላዊነት መከበር እና ከንግግሩ አንድ ቀን በፊት ካምቦዲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው
ምክር ቤት የሰላም እቅድ መቀበል ከአዲስ የአለም ስርአት ምን መጠበቅ እንዳለብን እንደ ማሳያ ተወስዷል።
 የጀርመን እና ጃፓን ወደ ልዕለ ሃያላን ጎራ መመለሳቸው እና በተመሳሳይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት
ፀጥታው ምክር ቤት የተደረገው ማሻሻያ ፤ ለሀያላኑ ትብብር እና የተመድን አመራርነት ኃይል ፀመስጠት እንደ
ቅድመ ሁኔታ ታይተዋል።
 አሜሪካን ወደ ዳር በመግፋት አውሮፓ የራሷን የአለም ስርአት ስርአት ግንባታ ላይ መሪነት ይዛለች። አሜሪካ
በአህጉሩ ላይ ለመቆየት ያቀረበችው ምክንያት እየደበዘዘ እንዲሁም የፐርሺያው ባህረ ሰላጤ ችግር አውሮፓን
በአጋርነት ለማሰለፍ አቅመ ቢስ መስሏል።በምትኩ የአውሮፓ ውይይት ስለ ሲ ኤስ ሲ ኢ ፣ ከሶቭየት ህብረት ጋር
ግንኙነት እና ስለ አውሮፓውያን ህብረት ነበር።ሌላው ቀርቶ ጎርባቾቭ ሲ ኤስ ሲ ኢን ለመተካት
የአውሮፓውያን የፀጥታው ምክር ቤት ማቋቋም ሐሳብን አቀረቡ።በሂደትም ይህ ምክር ቤት ረብ የለሽነቱ
እያደገ የመጣውን ኔቶን ይተካዋል።
 ጥቂቶች አዲስ ስርአት ሁለትዮሽ እነደሆነ አስረዱ። የአሜሪካ ኃይል እና የተባበሩት መንግሥታት የግብረ—ገብ
ባለሥልጣናት ፤ የመጀመሪያው የአለም አቀፍ ህግ አስከባሪ ሲሆን ሁለተኛው የአለም አቀፍ ዳኛ እና የፍርድ
ሸንጐ ነው።

You might also like