Forofor

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

ፎረፎር ለማጥፋት የሚረዱ 4 ዘዴዎች

ውድ የሳይቴክ ቤተሰቦች ዛሬ ደግሞ ሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ መረጃ ይዘን ቀርበናል፤ ስለ ፎረፎር፡፡ በዚህም ዙሪያ በተደጋጋሚ በመልዕክት መቀበያችን ጥያቄ
ስታቀርቡልን የነበረ ሲሆን አንዳንዶቻችሁም ዝምታ አበዛችሁ ብላችሁ ስትበሳጩብን ነበር፡፡ “ለሁሉም ጊዜ አለው” እንዲል ያ ጠቢብ ሰለሞን እነሆ ጊዜው ደረሰና
እነሆ ዛሬ ይዘንላችሁ መጣን፡፡ እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች ፎረፎር እንደሚያሰቃያቸው እንገነዘባለን… ይህ መረጃም ለሁሉም እንዲደርስ እንፈልጋለን… እናንተም
ማንበብ ከመጀመራችሁ በፊት ሼር በማድረግ ተባበሩን፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ፎረፎር በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ይከሰታል። በተለይም በጸጉር ቆዳችን ላይ የሚገኙ ነጭ የደም ህዋሳቶች ሲሞቱ ነው ፎረፎር የሚከሰተው።

ፎረፎር ፀጉር እንዲያልቅና እንዲበጣጠስ ከማድረጉም በላይ የጸጉር ውበትንና ቆዳን ይጎዳል። ይሁን እንጂ በተለያዩ መንገዶች ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።

1. እርጎ እና በርበሬ

በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው እርሾ በአንዳንድ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ መጉረብረብ እና መንተብተብ ይፈጥራል። ለዚህም እንደ እርጎ ያሉ ጎጂ ያልሆኑ
ባክቴሪያዎችን የሚይዙ የምግብ አይነቶችን መጠቀም አይነተኛ መፍትሄ ነው።

ሁለት ማንኪያ የደቀቀ በርበሬ እና 1 ኩባያ እርጎ በመደባለቅ ፀጉራችን የሚበቅልበትን ቆዳ መቀባት እና ከአንድ ሰዓት በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ትልቅ ድርሻ
እንዳለው ይነገራል።

2. እሬት (ኦሊ ቬራ)

እሬት ፎረፎርን ለመከላከል በተለይም በኢትዮጵያ ለበርካታ ዘመናት ስንጠቀምበት ኖረናል።


በፎረፎር የተገጎዳ ቆዳን እሬት መቀባት የሞቱ ህዋሳቶችን ከማስወገዱም ባሻገር ለፀጉር እድገት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ይታመናል።

3. አፕል

አፕል ለፀጉር እድገት የሚረዳው ፕሮሳይኒዲን ቢ - 2 የተባለ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር የያዘ መሆኑን ተከትሎ ጤናማ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል።

ሁለት ማንኪያ የአፕል ጭማቂ ከሁለት ማንኪያ ውሃ ጋር በመቀላቀል መቀባት፤ ከዚያም ከ 15 ደቂቃ በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ብሎም የፀጉር እድገትን
ለማፋጠን ይረዳል።

4. ዝንጅብል

ዝንጅብል ለሰውነት መጉረብረብ ወይም መመረዝ የሚያጋልጡ ነገሮችን የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮች ይዟል። ስለሆነም ዝንጅብልን በመላጥና በማድቀቅ ከሰሊጥ ዘይት ጋር
በመደባለቅና የፀጉር ቆዳን በመቀባት ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።

5. መረጃዎቻችንን በየጊዜው ለማግኘት የሚከተሉትን ሁለት አማራጮች ይከተሉ

✔ ለቪዲዮ መረጃ ይሄንን ይጫኑ: https://goo.gl/PSjsCt


#On_Website - ለፅሁፍ መረጃ ይሄንን ይጫኑ: https://goo.gl/miGg4n
ወይም

#On_Facebook - ለፅሁፍ መረጃ ይሄንን ይጫኑ: https://goo.gl/PSjsCt

ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።


ጤና ለሁሉም!

You might also like