Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ሚስጢር

ቀን 16-09-2012 ዓ.ም

ለ ፡- ደቡብ ቀጠና ደህንነት ማስተባበርያ ዋና ክፍል

ከ ፡- ሀድያ ክላስተር ደህንነት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

ሆሳዕና

ጉድዩ፡- የሳምንት ኢንፎርሜሽን ሪፖርት ስለመስጠት ይሆናል፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመበት ቀን ፡-15-09 -2012 ዓ.ም

ኢንፎርሜሽን የተገኘበት ቀን ፡- 16-09-2012 ዓ.ም

አስተማማኝ ፡-ደረጃ A

ምንጭ ፡- ከተባባሪ እና ከፊል ምንጭ

ኢንፎ 01

በቀን 15 -09-2012 ዓ.ም ከምሽቱ 05፡40 ደቂቃ ላይ በጉራጌ ዞን ማረቆ ወረዳ አን መና ቀበሌ ማንነታቸው

ባልታወቁ ሰዎች በቁጥር 4 /አራት /የሳር መኖርያ ቤት በእሳት የተቃጠለ ሲሆን በሰውና በቁም ከብቶች ላይ የደረሰ
ጉዳት የሌለ መሆኑን መረጃ ለማግኘት የተቻለ ሲሆን ይህንኑ ጉዳይ በአካባቢው የሚገኘው የፀጥታ ሃይል ኮማንድ ፖስት
ክትትል እያደረገ ይገኛል ፡፡ በቀጣይ ሪፖርት ያለውን ሂደት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

በአካባቢው እየተፈጠረ በሚገኘው የፀጥታ ችግር በዚህ ሳምንት ብቻ ከመስቃን በቁጥር 2/ሁለት/ ሰዎች ከማረቆ

1/አንድ/ሰው ባጠቃላይ በቁጥር 3/ሶስት ሰዎች ህይወት ሊያልፍ የቻለ ሲሆን የቤት ቃጠሎ ፣ከመኖርያ ቀዬ መፈናቀሎች
በቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡

ኢንፎ 02

በስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ አዳም 01 ቀበሌ ለረጅም ግዜ የማብራት መቆራረጥ ምክንያት በማድረግ በማብራት ሃይል

በአገልግሎት መስሪያ ቤት አሰራር በመማረር ከዳሎቻ ወረዳ ወደ አዳም 01 ከተማ የሚወስደው መንገድ በቀን 12-09-

2012 ዓ.ም ከቀኑ 3፡00 ሰዓት አካባቢ በድንጋይ መዝጋት አዝማሚያ የታየ ሲሆን የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች

የኮቪድ 19 ምክንያት የወጣውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተላለፍ 2/ሁለት/ ሰው በመጫን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ

Page 1
ሚስጢር

እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን ይህን ህግ መተላለፍ በሚቆጣጠር ለትራፊክ አባላት ያለመታዘዝ ሁኔታ ሊታይ የቻለ መሆኑን
መረጃ ለማግኘት ተችሏል፡፡

ኢንፎ 03

በቀን 11-09-2012 ዓ.ም በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ መናከር ቀበሌ በመኖርያ ቤት ለረመዳን ሰደቃ ምክንያት በማድረግ
በነበረው ዝግጅት በሬ ታርዶ ስጋው ለታዳሚዎቹ ቀርቦ የተመገቡ ሲሆን ነገር ግን ምግቡ በመመረዝ ምክንያት በቁጥር

1/አንድ/ ህክምና እየተደረገለት በድንገት ህይወቱ ሊያልፍ ቢችልም በቁጥር ወደ 20 /ሀያ/ የሚጠጉ ሰዎች ግን
በተደረገላቸው የህክምና ድጋፍ ጤናቸው ወደነበረበት ሊመለስ መቻሉን መረጃ ለማግኘት ተችሏል፡፡

ኢንፎ 04

በቀን 11-09-2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ በሀድያ ዞን ዱና ወረዳ ዋገበታ ቀበሌ ተነስቶ ወደ
ዶየገና አንድ ግለሰብ ጭኖ ሲሄድ በነበረው ሞተረኛ ጋር በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዶየገና ወረዳ ዋገበታ ቀበሌ
ከነበሩ ወጣቶች ጋር በተፈጠረው ባለመግባባት ሞተረኛውን የከምባታ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች በመጉዳታቸው
ለህክምና ወደ ጤና ማዕከል የህክምና ድጋፍ እንዲያገኝ መወሰዱን የሰሙ የሀድያ ነዋሪ ወጣቶች ፀብ ለማስነሳት
ተደራጅተው ዱላ ይዘው ወደ አካባቢው በመጓዝ ላይ እያሉ የፀጥታ ሀይሉ መረጃ ደርሶት በሁለቱም ወገን
ጉዳት ሳይደርስ ማስቆም ችሏል ፡፡

ነገር ግን የጉዳዩ አሳሳቢነት በመረዳት የሁለቱም ዞን የሰላምና ፀጥታ ሃላፊዎችና የቀበሌያቱ የሁለቱም ወገን

የባህል ሽማግሌዎች በተገኙበት በቀን 12-09-2012 ዓ.ም በሰላም ዙርያ የጋራ ውይይቶችን በማድረግ

ውይይቱ ባለመጠናቀቁ በቀጣይ በቀን 18-09-2012 ዓ.ም ቀጠሮ ይዘው ለመለያየት መቻላቸውን መረጃ
ለማግኘት ተችሏል፡፡

ኢንፎ 05

በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ሴች ዱና ቀበሌ ውስጥ 42/ አርባ ሁለት / ሄክታር በከተማ ክልል የሚገኘውን
የእርሻ መሬት ለባለይዞታ ካሳ በመክፈል በክብር ተመላሽ ሰራዊት የመኖርያ ቤት በፌደራል መንግስት በተሰጠ

መመርያና የአፈፃፀም ደንብ መሰረት ጥር ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የዞኑ ሚልሻ የዱክመንት ማጣራት ካደረገ

በኃላ የከተማው ከንቲባ ፅ/ቤት ማህበራቱን በ 10፣12፣14፣16፣18 አባላት ያቀፈ 105 ማህበራት በማዋቀር

ለከተማው ህብረት ስራ ዩንየን እንዲያደራጅና የመሬት ሊዝ ዋጋ 5% /አምስት ፐርሰንት/እያንዳንዱ ግለሰብ

Page 2
ሚስጢር

6500/ስድስት ሺ አምስት መቶ /ብር በባንክ እንዲቆጥብ ተደርጎ በቀን 06-04-2012 ዓ.ም የተሸነሸነው
መሬት እጣ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

ማዘጋጃ ቤት ካለው በጀት በቅድሚያ ለባለይዞታዎች 30% ቅድመ ክፍያ በመክፈል ቀሪውን በ 2013 ዓ.ም

አዲስ በጀት ለመክፈል ውል በመግባት ሽንሸና አካሄዶ ከተደራጁት 105 ማህበራት ውስጥ 74 ማህበራት

ከፍርድ ቤት እገዳ ነፃ ሲሆኑ 27 ማህበራት ላይ ደግሞ ባለይዞታዎች ሙሉ ካሳ ካልተከፈለን ቤት መስራት


አይቻልም በማለት በፍርድ ቤት እገዳ እንዲወጣ ተደርጎ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡

የፍርድ ቤት እገዳ የሌለባቸው 74 ማህበራት ግንባታ ለማካሄድ የማህበሩ ሳይት ፕላን ማሰራት ፣የቦታ
ማረጋገጫ ካርታ እና ግንባታ ፈቃድ በማውጣት የቤት ግንባታ ለመጀመር ግማሽ ፐርሰንት ከቆጠቡበት ባንክ
በመውጣት የመንገድ ማውጣት ስራ ለመስራት በማዘጋጃ ቤት የሚገኙ ሎደር እና ግሬደር ነዳጅ በመሙላት
መንገድ የማስተካከል ስራ ለመስራት ሲሞከር ባለይዞታዎች ሙሉ ክፍያ ካልተከፈለን ቤት መስራት አትችሉም
በማለት ቅሬታ ለማቅረብ ተገደዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ሰራዊቱ ከማዘጋጃ ቤት ጋር በነበረው ባለመግባባት በቀን 07-09-2012 ዓ.ም ኮማንድ
ፖስት ጣልቃ በመግባት ሁለት ተለማሽ ሰራዊት ላይ የዱላ ድብደባ በማካሄዳቸው በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያ
በፅሁፍ በምስል መለጠፍ ሁኔታ የታየ ሲሆን በቀጣይ ቅሬታ ለማቅረብ ክልል ለመሄድ እንቅስቃሴ እያደረጉ
እንደሆነ መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢንፎ 06

በእስልምና እምነት ለተካዮች ዘንድ ትልቁ በዓል እንደሆነ የሚነገረው ኢድ አል ፈጥር 2010 ዓ.ም 1441 ኛው
ግዜ የሚከበር በዓል ሲሆን በአለም ብሎም በሀገራች የተከሰተውን ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመከሰቱ መንግስት
የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በማወጅ በተለይ ህዝብ ሊሰበሰብ ከሚችልባቸው ቦታዎች አንዱ የሆነው ቤተ እምነቶች
እንዲዘጉ ተደርጓል ፡፡

ነገር ግን የአስቸኳግዜ አዋጅ በመተላለፍ 1441 ኛው የሆነውን ኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ
በሀላባ ዞን ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በሚገኙ መስኪዶች ውስጥ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ሰተባስበው ስግደት
ለማካሄድ መቻላቸውን መረጃ ለማግኘት ተችሏል፡፡

Page 3

You might also like