Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 2

ክፉ፡ካህን

ከያሬድ ተሾመ ኖርዌ


ምነው በቀረብህ
ምን ነበር-ባልገባህ
የቅኔ-ዘረፋው፣
ድጓው-ፆመ ድጓው፣
አቋቋም-ሆረባው፣

ገድል-መዛግብቱ፣
ማህሌት-ቅኝቱ፣
መለከተ-ስልቱ፣
መቅደስ፡መስንበቱ፣
የምስጢር፡ ማየቱ፣
ካልበጀህ፡ዕውቀቱ፣

ምን፡ ነበር፡ባትዘልቅ...
ተምረህ-ከምታንቅ፣
ማልደህ፡ ላታስታርቅ፣
ሆነህ፡ ርዕቱህ፡ አፈ-ሊቅ፣
አስማምተህ፡ ላትመርቅ፣
መርቀህ፡ ላታስቅ፣
ምነው በቀረብህ ...
ምን፡ ነበር፡ ባልገባህ፣
እርም፡ በሆነብህ ...።

እንደ፡ በጐ፡ ካህን፣


ሲሆን፡ ክፉ፡ ዘመን፣
ተርፈህ፡ ለሃጽያን፣
ሰብከህ፡ ላታሳምን፣
ተግተህ፡ 'ዓታድን፣
እንዲህ፡ ልትሰጥነው፣
ዕውነትን፡ ልትክደው
ሰብ፡ ሰላም፡'ዓይኖር፣
ላቴቴው፡ ልትገብር፣
ጥላ-ወጊ፡ ያገር፣
ጠንቋይ፡ ሆነህ፡ ልትቀር፣
ያን፡ ኮከብ፡ ልትቆጥር፣
አውደ-ነገስት፡ ጠጠር፣
ምነው፡ በቀረብህ ...
ባልገባህ፡ በነበር።
አልያም፡ ባትወለድ
ውሀ-ሆነህ፡ ብትቀር
ከኖርክም፡ ለመኖር
ለማድመጥ፡ ብትማር
እንደኛው፡ ተራ፡ ሰው
እንደኛው፡ ምዕምን
ይበጅህ፡ በነበር፡
ከምትበድል፡ ሀገር
ሴጥነህ፡ ከምትቀር።

You might also like