Professional Documents
Culture Documents
Dhaabbii Abaaboo
Dhaabbii Abaaboo
Dhaabbii Abaaboo
ማኅሌተ ጽጌ
የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡
በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ
ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት
በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው
የጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስ ገድል የጽጌን ጾም አስመልክቶ የሚከተለውን ይተርካል፣ “አቡነ ዜና ማርቆስ
የምሁርን ሕዝብ አስተምረውና አሳምነው ካጠመቁ በኋላ እንደገና ለማስተማር ወደ ይፋት ሄዱ፡፡ በዚያም
ክርስቶስ ሥጋ ለብለሶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰለኛ ኃጢአት ተሰቅሎ ሞተ፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን
ተነሣ እያሉ ሲያስተምሩ አንድ አይሁዳዊ ሰማ፡፡ ይህም አይሁዳዊ እንዴት እነዲህ እያለ ያስተምራል ሲል
ተቃውሞ አቀረበባቸው፡፡ እርሳቸውም የብሉይና ሐዲስ ዐዋቂና ብልህ ስለነበሩ የሚከተለውን ጥቅስ እየጠቀሱ
ያስረዱት ጀመር፡፡”
“ትወዕዕ በትር እምሥርወ እሴይ፣ ወየዓርግ ጽጌ እምጒንዱ”፣ ትርጓሜውም “ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች
ከግንዱም አበባ ይወጣል ያቆጠቁጣል” ማለት ነው፡፡ በትር አመቤታችን ድንግል ማርያም ስትሆን ጽጌ ደግሞ
ከእርስዋ የተወለደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ሲሉ አቡነ ዜና ማርቆስ በትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ
ተቀበለ፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስም ሐዲስ ኪዳን አስተምረው አሳምነው ካጠመቁት በኋላ አመነኮሱት፣ ስሙንም ጽጌ ብርሃን
ምሁረ ኦሪት ስለ ነበር መጻሕፍተ ሐዲሳትን ለማጥናት ምቹ ሆነለት፣ ቀጥሎም ከርሳቸው ጋረ እየተዘዋወረ
ይህንንም ከፈጸመ በኋላ እንደ መዝሙረ ዳዊት መቶ ሃምሳ አድርጎ ማኅሌተ ጽጌ ደረሰ፡፡ አባ ጽጌ ብርሃን
ይህንን በደረሰበት ጊዜ የወረኢሉ ተወላጅና የደብረ ሐንታው አባ ገብረ ማርያም አማካሪው ነበር፡፡ ድርሰቱንም
ሲደርስ ቤት እየመታና በአምስት ስንኝ እየከፋፈለ ነው፡፡ አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም መስከረም 26
ኀ.ስላሴ Page 1
DHAABBII ABAABOO
ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ማኅሌት ጽጌ ለመቆምና የጽጌን ጾም ለመጾም በየዓመቱ በደብረ ብሥራት
ይህም ማኅሌተ ጽጌ ድርሰት በሰምና ወርቅ የተደረሰ ሆኖ አበባን ሰም፣ ጌታንና እመቤታችንን ወርቅ እያደረገ
እንግዲህ ከላይ ከቀረበው የአባታችን የገድል ክፍል ለመረዳት እንደሚቻለው አባ ጽጌ ማኅሌት መቆም
ከዚያ ወዲህ ግን ጥቂት በጥቂት እያለ አብያተ ክርስቲያናት በወርኃ ጽጌ የጽጌን ማኅሌት መቆም ጀመሩ፡፡
ጥቂት መነኮሳትና አንዳንድ ምእመናንም በገዛ ፈቃዳቸው ወቅቱን መጾም ያዙ፡፡ በዘመናችን በወርኃ ጽጌ
የጽጌን ማኅሌት መቆም ስለ ተለመደ ከማታው በሦስት ሰዓት ይደወላል፡፡ ሴቱ ወንዱ፣ ትንሹም ትልቁም
ይሰበሰባል፣ ማኅሌተ ጽጌ እየተዜመ፣ አስፈላጊ የሆነው በጸናጽል በከበሮ እየተመረገደና እየተወረበ እየተሸበሸበ
እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ተቁሞ ይታደራል፡፡ የጽጌ ጾም የውዴታ /የፈቃድ/ እንጂ የግዴታ አይደለም፡፡
የእመቤታችንን ስደት በማሰብ ከትሩፋት ወገን የሚጾም ስለሆነ ምእመናን ሁሉ እንዲጾሙት አይገደዱም
አይገባውም፡፡ የፈቃድ መሆኑንም የሚያሳየው ይኸው ነው፡፡ የማይጾመውም በልቡ ያመሰግናል፣ስደቷን እያሰበ
ለ. ጾመ ዮዲት
ይህን ጾም በሀገራችን ምእመናን ጾመ ጳጉሜን በማለት ይጠሩታል፡፡ እንደ ጽጌ ጾም የታወቀ ባይሆንም በዓመቱ
መጨረሻ ወር በጳጉሜን የሚጾም ነው፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ የፋርስ ንጉሥ
ናቡከደነፆር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ፣ ድንበር አሰፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን
እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፣2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው
መቅደሱ መፍረስና ሰለ ንዋያተ ቅድሳት መርከሰ ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው ከቤተ መቅደሱ በር ወድቀው
ኀ.ስላሴ Page 2
DHAABBII ABAABOO
ፈቅደው እጃቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ የውኃውን ጉድጓድ ተቆጣጥሮ በሠራዊቱ አስጠበቀ፡፡ በመሆኑም
የእሥራኤል ልጆች በውኃ ጥም ከመቸገርና ከመሞት ይልቅ እጃቸውን ለጠላት ለመስጠት ወሰኑ፡፡ ነገር ግን
ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም፣ በቀኖና፣ በትኅርምት፣ በኀዘን፣ በጸሎት ተወስና
አለቀሰች፡፡
የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ ቸር አምላክም ሕዝቡን የሚያድንበትን ዕውቀትና ጥበብ ግብር በገባች በሦስተኛ
ቀን ገለጸላት፡፡ ዮዲ. 8፣2፡፡ ዮዲት እጅግ መልከ መልካም ፍጹም ደመ ግቡ ስለነበረች እግዚአብሔር በሰጣት
ከዚያም “ወዴት ትሔጃለሽ አትበሉኝ አምላክ እሥራኤል ይከተልሽ ብሉኝ”ብላ የኀዘን ልብሷን ጣለች፡፡
ሰዎች ሁሉ እስክታስት ድረስ ፈጽማ አጌጠች፡፡ ዮዲ.10፣2-3፡፡ ስትጨርስም እግዚአብሔር በመልክ ላይ መልክ
ጨምሮራት ለመንገድ ስንቅ የሚሆናትን ወይንና የስንዴ አምባሻ ብላቴናዋን አስይዛ ከእየሩሳሌም ቅጥር ወጥታ
ሸማ አጣቢዎች አገኟትና “ ዛሬስ እስራኤል መዋጋት ቢሳናቸው አንዳንድ እያሉ ወባት ሊገቡ መጡብን?”
ብለው ለእኔ ትገባለች ለእኔ ትገባለች እያሉ ተሻሙባት፡፡ የንጉሥ ጃንደረባ ጋይ የሚባል ይህችስ ለጌታዬ
ትገባለች አለ፣ ለምን እንደመጣች ጠይቀዋት ለመልካም ነገር እንደመጣች ሲረዱ ከጦር አበጋዙ አደረሷት፡፡
ዮዲ.10፣12-22፡፡ እርሱም የጾመኛ ምቀኛ እንዲሉ ለምን መጣሽ ቢላት እስራኤል ሊገቡ ጥቂት ቀርቷቸዋል፣
እርስት ሄዶብኝ እንድትመልስልኝ አስቀድሜ ደጅ እጠናለሁ ብዬ መጣሁ አለችሁ፡፡ እርሱም ወገን ለመርዳት
ምግብ እንዲሰጧት አዘዘ፡፡ እርሷ ግን የአህዛብ ምግብ በልታ እንዳትረክስ በቂ ስንቅ የያዘች መሆኗን ገልጻ
ኀ.ስላሴ Page 3
DHAABBII ABAABOO
አሕዛብ በዚህ ቀን ተወልደን ከዚህ ማእረግ ደርሰን ከጨለማ ወደ ብርሃን ከጠባብ ወደ ሰፊ የወጣንበትን ሲሉ
የተወለዱበትን ቀን ያከብራሉ፡፡ በአንዲትም ዕለት ቢትወደዱ የአሽከሮች የምሣ ግብዣ አድርጎ ሲያበላ
ሲያጠጣ ያችን እብራዊት ጥሩ ብሎ አስጠርቶ ከፊቱ አስቀምጦ ሲበላ አብዝቶ ሲጠጣ ውሏል፡፡ ዮዲ. 12፣1-
20፡፡ ከዚያም አሽከሮችን ከሁሉ አስወጥቶ ድንኳኑን ቆልፎ እንደተኛ ከባድ እንቅልፍ ያዘው ዮዲትም በሃያሉ
አድረህ ሥራ ብትሠራ አትመሰገንም ነገር ግን በእኔ በደካማይቱ አድረህ ሥራ ብትሠራ ትመሰገናለህ እያለች
ከፀለየች በኋላ ከራስጌው ያለውን ሰይፍ አንስታ የራስ ጠጉሩን ይዛ አንገቱን ቆርጣ በድኑን ከመሬት ጥላ
ቸብቸቦውን በአቁማዳ ቋጥራ ለብላቴናዋ አሸክማ ግንዱን በታች ገልብጣ ዙፋኑን በላይ አድርጋ ወደ ሃገሯ
ተመለሰች፡፡ ዮዲ 13.1-10፡፡
ሕዝበ እሥራኤል በዚህ ድርጊቷ እጅግ ተደነቁ፣ ጠላታቸውን በእጃቸው የጣለላቸውን አግዚአብሔር
እሥራኤል ወንዳ ወንድ ሆኑብን ይህቺ ዕብራዊት የሌሊቱ አልበቃ ብሏት ቀኑንም ልትደግመው ነውን? ሒደህ
ንጉሣችንን አስነሣው ብለው ብላቴና ቢልኩ ግንዱ በታች ዙፋኑ በላይ ሆኖ አገኘው፡፡ አውራ የሌለው ንብ አለቃ
የሌለው ሕዝብ መቆም አይሆንለትምና ይህች ዕብራዊት እንዴት ተጫወተችብን ብለው ሸሽተዋል፡፡ እግር
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጦምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ
ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንንና ፈቃደ ስጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን
ብለው በጳጉሜ ወር ይጾማሉ፡፡ ኃጢያታቸውን ለንስሐ አባታቸው ተናገረው ተናዝዘው ቀኖና ተቀብለው
የሚጾሙም አሉ፡፡ በሌላም በኩል በጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባት በመሆንዋ ያን እያሰቡ የሚጾም
አያሌ ናቸው፡፡ ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ እንደሆነች ምጽአትም ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ
ነውና፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ኀ.ስላሴ Page 4