Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 10

Financial jurisprudence on hanafi mezhab

የገበያ ህግጋት
ገበያ አንድን እቃ ሸጨልሃለሁ ወይም ገዝቸሀለሁ በማለት ይፈጸማል፣ ቃላቶቹ ያለፈ ነገርን አመላካች
መሆን ይኖረባቸዋል። አንደኛዉ ገበያተኛ ገበያዉን በፈጸመ ጊዜ ሌላኛዉ ምርጫ አለዉ ከፈለገ ከዛዉ ቦታ
እያለ ግበይቱን ይቀበል ከፈለገ ይመልስበት፣ ከሁለት አንዳቸዉ ግብይቱ ሳይፈጸም ከመቀመጫቸዉ ከተነሱ
ግብይቱ ይበላሻል። የግብይት ቃላቶች በሁለቱም በኩል ከተገኙ በኋላ ግብይቱ ይጸናል፣ የእይታ ምርጫ
ወይም እቃዉ ጉድለት ካልተገኘበተ በሰተቀር ለሁለቱም ተገበያዮች ምርጫ የላቸዉም። በአይተሽ የሚገዛ
ነገር ገበያዉ ለመብቃቱ መጠኑ መታወቅ አለበት አይባልም። ማንኛዉም እጅ በእጅ ወይም በታወቀ ጊዜ
አቆይቶ በመስጠት የሚደረግ ግብይት ይበቃል። እህል ወይም ጥራጥሬን በስፍር፣ በአይተሽ፣ ግምቱ
በማይታወቅ በተለየ እቃ፣ ግምቱ በማይታወቅ በተለየ ሚዛን ድንጋይ መገበያየት ይበቃል።
አንድን ቁልል እህል እያንዳንዱን ኩንታል(98KG)በ 100 ብር ብሎ ቢሸጥ ግብይቱ የሚበቃዉ ለአንዷ
ኩንታል ብቻ ነዉ፣ ይሄን ያህል ኩንታል ብሎ እስካልተናገረ ድረስ። አንድን ልቅ ጨርቅ በሜትር መቶ ብር
ቢሸጥና የጠቅላላ ሜትሩን ብዛት ሳይናገር ቢቀር ግብይቱ በአጠቃላይ ዉድቅ ይሆናል። አንድን ቁልል እህል
መቶ ኩንታል ነዉ ተብሎ በ 1000 ብር ቢገዛና እህሉ ከ 100 ቁምጣ አንሶ ቢገኝ ፣ ገዥዉ ሰዉ ምርጫ
ይኖረዋል ከፈለገ የተገኘዉን መጠን በዋጋዉ ይዉሰድ ከፈለገም ገበያዉን ያበላሽ፤ ከ 100 ኩንታል በልጦ
ቢገኝ ግን ጭማሬዉ ለሻጩ ተመላሽ ይሆናል። ልቅ የሆነንጨርቅ 10 ሜትር ነዉ ተብሎ በ 10 ብር ቢገዛ
ወይም አንድን መሬት 100 ካሬ ነዉ ተብሎ በመቶ ብር ቢገዛና ከተባለዉ አንሶ ቢያገኘዉ፣ ገዥዉ ምርጫ
አለዉ ከፈለገ በሙሉዉ ገንዘብ ይያዛት ከፈለገም ይተዋት ላሻጩ ግን ምንም ዓይነት ምርጫ የለዉም።
ቦታን የሸጠ ግቢዉ ዉስጥ ያለዉን ግንባታ ባይጠቀስም ግብይቱ ዉስጥ አብሮ ይገባል፣ እንዲሁ መሬትን
ቢሸጥ መሬቷ ላይ ያሉት ዛፎችና አትክልቶች ባይጠቅሳቸዉም ግብይቱ ዉስጥ ይገባሉ። አዝመራ በመሬት
ሽያጭ ላይ ካልተጠቀሰ ግብይት ዉስጥ አይገባም፤ ፍሬ ያለዉን የተምርን ዛፍ ወይም የማንጎን ዛፍ የገዛ
ገዥዉ መስፈርት እስካላደረገ ድረስ ፈሬዉ ለሻጭ ይሆናል፣ ሻጭ ፍሬዉን ቆርጠህ ንብረቱን አስረክብ
ይባላል። በመብሰል ላይ ያለን ወይም የበሰለን ፍሬ ቢሸጥ ይበቃል፣ በገዥዉ ላይ ባለበት ሁኔታ ቆርጦ
መዉሰድ ግዴታ ይሆንበታል፣ ገዥዉ ፍሬዉ እዛዉ ላይ መቆየቱን መስፈርት ቢያደርግ ግብይቱ ይበላሻል።
ፍሬን ከሸጠ በኋላ የተወሰነ ኪሎ ሲቀር ማለት አይበቃም። ስንዴን ከነዘለላዉ ባቄላን ከነቅርፊቱ መሸጥ
ይበቃል። ቤትን የሸጠ የቤቱ ቁልፍ አብሮ ይገባል።

ኺያሩ ሸርጥ(የምርጫ መስፈርት)


ኺያሩ ሸርጥ ከሁለቱ ተስማሚወች አንዱ ወይም ሁለቱም ለራሳቸዉ ወይም ለሌላ ሰዉ በታወቀ ግብይትና
ጊዜ ዉስጥ ግብይቱን ዉድቅ የማድረግ ስምምነት ነዉ። ለምሳሌ ሸማቹ ለሻጩ ይሄን እቃ በ መቶ ብር
ገዝቸዋለሁ ነገር ግን እስከ ሶስት ቀን ድረስ የመመለስ መብት ሊኖረኝ ብሎ መስማማት ማለት ነዉ። ለሻጭ
ወይም ለገዥ ሶስትና ከዛ በታች ቀን የምርጫ መስ ፈርት ማድረግ ይችላሉ። ሻጩ የምርጫ መስፈርት ካደረገ
የእቃዉ ባለቤትነት ከራሱ አይወጣም በዚህ ጊዜ እቃዉ በገዥዉ እጅ ላይ ቢጠፋ ግምቱን ለሻጭ
ይከፍላል። ገዥዉ የምርጫ መስፈርት ቢያደርግና እቃዉ እጁ ላይ እያለ ቢጠፋ የራሱን ገንዘብ ይከስራል።
የምርጫ መስፈርት የተደረገለት ሰዉ የምርጫ የጊዜ ገደቡ እስካላለቀ ድረስ ግብይቱን ዉድቅ ማድረግ
ወይም መስፈርቱን መተዉ ይችላል። ሻጭ በሌለበት የምርጫ መስፈርቱን መተዉ ይችላል ነገር ግን ሻጭ
በሌለበት ግብይቱን ዉድቅ ማድረግ አይችልም። በምርጫ መስፈርት አንድን እቃ የገዛ ሰዉ ከሞተ የምርጫ
መስፈርቱ ይበላሻል።

1
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

ኺያሩ ሩእያ(የእይታ ምርጫ)


ኺያሩ ሩእያ አንድ ሸማች በአይኑ ሳያይ ግብይት የፈጸመበትን ነገር ካየዉ በኋላ ግብይቱን የማፍረስ ወይም
የማጽደቅ መስፈርት ማለት ነዉ። በዚህ መሰረት አንድን ነገር ሳያይ የገዛ ሰዉ ካየዉ በኋላ ግብይቱን
የማፍረስ ወይም የማጽደቅ መብት ይኖረዋል። የራሱን ንብረት ሳያይ የሸጠ ሰዉ ግን ኺያሩ ሩእያ
አይኖረዉም። አንድን እቃ ለማየት በሚያስችል ሁኔታ ላይ እያለ በደንብ ሳይመለከት ከገዛዉ በኋላ ኺያሩ
ሩእያ አይኖረዉም። አንድን ቦታ ሲገዛ ግብዉን ካየዉና ከግቢዉ ዉስጥ ያለዉን ቤት ሳያየዉ ቢቀር ኺያሩ
ሩእያ አይኖረዉም። አይነስዉር ለሆነ ሰዉ የሚገዛዉም የሚሸጠዉም ነገር ይበቃለታል ነገር ግን በሚገዛዉ
ነገር ላይ ኺያሩ ሩእያ ይኖረዋል። አይነ ስዉሩ ሰዉ ግብይቱን ሲፈጽም የሚገዛዉ ነገር በመዳበስ የሚለይ
ከሆነ ዳብሶ፣ በማሽተት የሚለይ ከሆነ አሽትቶ ወይም በመቅመስ የሚለይ ከሆነ ቀምሶ ከገዛ ኺያሩ ሩእያ
አይኖረዉም። አይነስዉር ለሆነ ሰዉ ቦታ ሲገዛ የቦታዉ ሁኔታ በትክክል ካልተነገረዉ ኺያሩ ሩእያ
ይኖረዋል። አንድ ሰዉ የራሱ ያልሆነን ንብረት ያለባለቤቱፈቃድ ቢሸጥ የንብረቱ ባለቤት ግብይቱ የማጽደቅ
ወይም ዉድቅ የማድረግ መብት አለዉ። ሁለት ተመሳሳይ የሆነን እቃ አንዱን ብቻ አይቶ ሁለቱንም ከገዛ
በኋላ ልዩነት ቢያገኝባቸዉ ሁለቱንም የመመለስ መብት አለዉ።

ኺያሩል አይብ(የእንከን ምርጫ)


ኺያሩል አይብ የግብይት ስምምነት በተደረገበት ነገር ላይ እንከን በመገኘቱ ከሁለቱ ተገበያዮች አንዱ
ግብይቱን ዉድቅ የማድረግ መስፈርት ማለት ነዉ። አንድ ሸማች በገዛዉ እቃ ላይ እንከን ካገኘበት ላሻጩ
የመመለስ ወይም ግብይቱን የማጽደቅ መብት አለዉ። እቃዉን ይዞ ግን ዋጋ ማስቀነስ አይችልም።
በነጋዴወች ልምድ አንድን እቃ ከመደበኛ ዋጋዉ በቅናሽ እንዲሸጥ የሚያደርግ ነገር ሁሉ እንከን ይባላል።
አንድ ሸማች እቃ ከገዛ በኋላ በራሱ ምክንያት እንከን ቢያጋጥመዉና እቃዉ ሲፈተሽ ከመግዛቱ በፊት ሌላ
እንከን እንደነበረበት ከተረጋገጠ ሸማቹ ከገዛበት ዋጋ ላይ ማስቀነስ ይችላል። በዚህ ጊዜ ሻጩ እቃዉን
ለመመለስ ካልፈለገ እንዲመልስ አይገደድም።

በይኡል ፋሲድ (ህገወጥ፣ ብልሹ ግብይት)


ከሁለቱ ተለዋዋጮች(ገንዘቡ ወይም ውቃዉ)አንዱ ወይም ሁለቱም ሀራም ከሆኑ ግብይቱ ዉድቅ
ይሆናል። ለምሳሌ በኸምር፣ በአሳማ፣ በደም ወይም በሞተ እንስሳ የሚደረግ ግብይት ዉድቅ ነዉ።
ያልተወለደን የእንስሳ ሽል ወይም ሽሉ ከተወለደ በኋላ የሚወለደዉን እንስ ሳ መግዛት አይበቃም። አንድን
ቤት የተወሰነ ጊዜ ሊኖርበት ወይም ገዥዉ ስጦታ እንዲሰጠዉ ወይም እንዲያበድረዉ መሸጥ አይበቃም።
አንድን እቃ ከሸጠ በኋላ ርክክቡን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘም ግብይቱን ዉድቅ ያደርገዋል። በማንኛዉም
ፋሲድ ግብይት ግብይቱ ከተፈጸመ በኋላ ገዥዉ ለገዛዉ እቃ ሀላፊነቱን ይወስዳል። በፋሲድ ግብይት ጊዜ
ሁለቱም ተገበያዮች ገበያዉን ዉድቅ የማድረግ መብት አላቸዉ። በፋሲድ ግብይት የገዛዉን እቃ ለሌላ ሰዉ
ቢሸጠዉ ሁለተኛዉ ግብይት ይጸድቃል። ረሱል(ሰ.አ.ወ)ማስቦጨቅን ማለትም ለማይገዛዉ እቃ የሚገዛ
መስሎ ገዥዉ እንዲበላ ዋጋ ማስጨመርን፣ በሌላ ሰዉ ስምምነት ላይ ጣልቃ መግባትንና በጁሙ አዛን
ከተደረገ በኋላ መሸጥን ከልክለዋል። ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩት ነገሮች ግብይቱን ከረሀ(የተጠላ)እንጅ
ሀራም አያደርጉትም።

ሙራበሀና ተዉሊያ
2
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

ሙራበሀ(አትርፎ መሸጥ)የሚባለዉ በመጀመሪያዉ ስምምነት በመጀመሪያዉ ዋጋ እጁ ዉስጥ


ያስገባዉን ንብረት ከጭማሪ ጋር ወደ ሌላ ሰው ማረማመድ ማለት ነው። ተዉሊያ ማለት ደግሞ
በመጀመሪያዉ ስምምነት በመጀመሪያዉ ዋጋ እጁ ዉስጥ ያስገባዉን ንብረት ያለምንም ጭማሪ ወደ ሌላ
ሰው ማረማመድ ማለት ነው። ሙራበሀና ተዉሊያ የሚበቃዉ ልዋጩ አምሳያ ባለዉ ነገር ላይ ብቻ ነዉ
ምሳሌ የሚሰፈር፣ የሚመዘን፣ የሚቆጠር።
በሙራበሀ በሚደረግ ግብይት ገዥዉ እንደተጭበረበረ ካወቀ እቃዉን የመመለስም ሆነ ግብይቱን የማጽደቅ
ምርጫ አለዉ። ማጭበርበሩ የታወቀ በተዉሊያ ከሆነ ግን ገዥዉ ከገዛበት ዋጋ ማስቀነስ ብቻ ነዉ ያለዉ።
ተንቀሳቃሽ የሆነን ነገር የገዛ ንብረቱን በእጁ ካላስገባ ግብይቱ አይበቃም፣ የመሬት ቦታን ግን በእጁ ሳያስገባ
ግብይቱን መፈጸም ይችላል። ገንዘብ በእጁ ሳይዝ በራሱ ገንዘብ መጠቀም ይበቃል። ገዥዉ ላሻጭ ገንዘብ
መጨመር ወይም ሻጭ ለገዥ ዋጋ መቀነስ ወይም ከሚገዉ ነገር ጨምሮ መስጠት ይበቃል። ሻጭ እጅ
በእጅ(ካሽ)ከሸጠ በኋላ መክፈያዉ የታወቀ የሆነን ጊዜ ቢያራዝምለት ግብይቱ በዛ ጊዜ የሚከፈል
ይሆናል።

ሪባ
ሪባ በሸሪአ ህገወጥ(ብልሹ)የሆነ የገበያ ስምምነት ማለት ሲሆን ገንዘብን በገንዘብ አቆይቶ
መሸጥ(ጭማሬ ባይኖረዉም) ሪባ ይባላል። በሌላ አገላለጽ ሪባ ገንዘብ በገንዘብ በሚደረግ ልዉዉጥ
መሀል እቃ ያልገባበት የገንዘብ ትርፍ ማለት ነዉ። የሪባ አይነቶች ሪበነሲአ እና ሪበልፈድል በመባል በሁለት
መሰረታዊ ምድቦች ይከፈላሉ። አንድ ሰዉ ለተወሰነ ጊዜ ብድር ከተበደረ በኋላ የመክፈያ ጊዜዉ ሲደርስ
አበዳሪዉ ለተበዳሪዉ ገንዘቤን አምጣ ወይም ጊዜ ልጨምርልህና ገንዘብ ጨምረኝ ካለዉ ሪበነሲአ ይባላል።
ሪበልፈድል አንድን ነገር በአምሳያዉ አበላልጦ መሸጥ ሲሆን ምሳሌዉ አንድን ብር በሁለት ብር ወይም
አንድን ኪሎ ስኳር በሁለት ኪሎ ስኳር መሸጥ ማለት ነዉ።
ሪባ ማንኛዉንም የሚመዘንም ሆነ የሚሰፈር ነገር በአይነቱ አበላልጦ መሸጥ ሲሆን ሁክሙ ሀራም ነዉ።
ለሪባ ምክንያቱ ስፍሩ ከጎሳዉ ጋር ወይም ሚዛኑ ከጎሳዉ ጋር መገኘቱ ነዉ። የሚሰፈረዉ ወይም
የሚመዘነዉ ነገር በጎሳዉ እኩል በእኩል ቢሸጥ ይበቃል፣ ከተበላለጡ ግን አይበቃም። ገንዘብን ማዘርዘር
ገበያዉ ከተፈጸመበት ቦታ ላይ ልዋጩን ካልተቀበሉ ሪባ ይሆናል።
ማንኛዉም ረሱል(ሰዐወ)በስፍር ላይ ማበላለጥ ሀራም ነዉ ያሉት ነገር በሙሉ ሰወች ያንን ነገር መስፈር
ቢተዉ እንኳን ያነገር ሁክሙ ሁልጊዜ በስፍር ይሆናል። ምሳሌ ስንዴ፣ ገብስ፣ ተምር እና ጨዉን ይመስል።
ማንኛዉም ረሱል(ሰዐወ)በሚዛን ላይ ማበላለጥ ሀራም ነዉ ያሉት ነገር በሙሉ ሰወች ያንን ነገር
መመዘን ቢተዉ እንኳን ያነገር ሁክሙ ሁልጊዜ በሚዛን ይሆናል ምሳሌ ወርቅ እና ብርን ይመስል። ሁክሙ
በቁርአን ወይም በሃዲስ ያልመጣ ነገር ከሆነ ግን እንደ ሰወች ልምድ መደረግ ይችላል።
ስንዴን በዱቄት(በተፈጨ ስንዴ)ወይም በተቃራኒዉ መሸጥ አይበቃም። ስጋን በእንስሳ መሸጥ ይበቃል፣
እሸት ተምርን ወይም ወይንን በበሰለዉ እኩል በእኩል መሸጥ ይበቃል። ዘይቱና ፋጉሎዉ ከዘይት
ፍሬዉ(ሰሊጡ)እስካልበለጡ ድረስ የቅባት እህሎችን በተጣራ ዘይት መሸጥ አይበቃም። የተለያዩ
እንስሳወችን ስጋ አበላልጦ መሸጥ ይበቃል እንዲሁ የከብትና የግመል ወተትን አበላልጦ መሸጥ ይበቃል።

ሰለም(የዱቤ)ግብይት
ሰለም በሚሰፈሩ፣ በሚመዘኑና በሚቆጠሩ ነገሮች እስካልተበላለጡ ድረስ ይበቃል። የሚበላለጡ እንደ
እንቁላል፣ አዝእርት እና ፍራፍሬ ከሆነ አይበቃም። ሰለም በቤት በእንስሳት ላይም አይበቃም። ግብይት

3
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

የሚደረግበት ንብረት ሰለሙ በሚፈጸምበት ጊዜና ቦታ ካልተገኘ ሰለሙ አይበቃም። ሰለሙ የሚከፈልበት
ቀን ተለይቶ ካልታወቀም እንዲሁ ስምምነቱ አይበቃም። ሰለሙን የምከፍለዉ በእገሌ መስፈሪያ፣ በእገሌ
አዝመራ፣ በዚህ ሃገር እህል ወይም በዚህ ሀገር ፍራፍሬ ነዉ ካለ ስምምነቱ አይበቃም።
በሰለም ግብይት ጊዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ካልተሟሉ ስምምነቱ ዉድቅ ይሆናል። የእቃዉ
ጎሳ መታወቅ፣ የእቃዉ አይነት መታወቅ፣ የእቃዉ ባህሪ መታወቅ፣ የእቃዉ ብዛት መታወቅ፣ የግብይቱ ጊዜ
መታወቅ፣ የዋና ገንዘቡ መጠን መታወቅ(ግብይቱ በስፍር፣ በሚዛን ወይም በቁጥር ከሆነ)እና ሰለሙን
የሚረካከቡበት ቦታ መታወቅ ናቸዉ። ሰለም ለመብቃት ግብይቱ በተከናወነበት ቦታ የሰለም ገንዘቡን
መረከብ አለበት። በሰለም ገንዘቡም ሆነ በልዋጩ ንብረቱ እጁ ላይ ሳይገባ በፊት በጠቀም አይበቃም።
ሰለም ሰጭዉ ንብረቱን ሳይረከብ በፊት እጁላይ በሌለዉ ንብረት ሌላን ሰዉ ማጋራት አይበቃም ለምሳሌ
አንድ ንብረቱን በዱቤ የሰጠ ሰዉ ለሌላ ሰዉ የዱቤዉን ገንዘብ ግማሽ ስጠኝና ከዱቤዉ ንብረት ላጋራህ
እንደማለት።
የአንድ ጨርቅ እርዝመቱ፣ ስፋቱና ዉፍረቱ እስከታወቀ ድረስ በሰለም መሸጥ ይበቃል። ከመሬት የሚወጣ
ማእድንን በሰለምመሸጥ አይበቃም። የሸክላ ብሎኬት ወይም ጡብን ቁጥሩእስከታወቀ ድረስ በሰለም መሸጥ
ይበቃል። በማንኛዉም መጠኑንና ባህሪዉን ለማወቅ በሚመች ነገር ላይ ሁሉ የሰለም ግብይት ይበቃል።
እንደዚሁ ዉሻንም ሆነ የዱር እንስሳትን ከከርከሮ ወይም አሳማ ዉጭ በሰለም መሸጥ ይበቃል። የሃር ትልን
ያለድሩ ወይም ንብን ያለ ቀፎዋ በሰለም መሸጥ አይበቃም።

ሶርፍ (የገንዘብ ዝርዝር)


የሶርፍ ሸሪአዊ ትርጉም ትርፍን አመላካች ሲሆን የተለየ ባህሪ ባለዉ ነገር ላይ ልዋጩን መመለስ ማለት
ነዉ። ሁለቱም ልዋጮች የገንዘብ አይነት እስከሆኑ ድረስ ሶርፍ እንደ ገበያ ይቆጠራል። በአሰራርም ሆነ
በጥራት ቢለያዩም ወርቅን በወርቅ ወይም ብርን በብር መሸጥ አይበቃም፣ እኩል በእኩል ከሆነ ግን ችግር
የለዉም። በሶርፍ ግብይት ጊዜ ሁለቱም ተገበያዮች ልዋጫቸዉን ግብይቱ ከተፈጸመበት ቦታ መያዛቸዉ
ግድ ነዉ። ወርቅን በብር መሸጥ ይበቃል ልዋጩን እዛዉ ቦታ ላይ መያዝ ዋጅብ ሲሆን አቆይቶ መስጠት
ግን ሀራም ነዉ። በሶርፍ ለመገበያየት ተስማምተዉ ልዋጫቸዉን ሳይረካከቡ ከቦታዉ ቢለያዩ ወይም
አንደኛዉ ሰዉ ተነስቶ ቢሄድ ግብይቱ ይበላሻል። በሶርፍ ግብይት ልዋጩን በእጁ ሳያስገባ ወይም ገንዘቡ
ሌላ ሰዉ ላይ እያለ በገንዘቡ መጠቀም አይበቃም።

በሶርፍ ግብይት አይነቱን ባይለየዉም ሰዎች የሚጠቀሙበት የገንዘብ አይነት ከሆነ ግብይቱ ይበቃል።
ገንዘቡ የመግዛት አቅም ከሌለዉ ግን ስምምነቱ ላይ ግልጽ እስካላደረገዉ ድረስ ግብይቱ አይበቃም። ሰወች
በሚገበያዩበት ገንዘብ ሽጦ ልዋጩን ሳይረከብ በፊት ገንዘቡ የመግዛት አቅም ቢያጣ ግብይቱ ይበላሻል።

ረህን(ዋስትና፣መያዦ፣አደራ ተቀማጭ)
ረህን ሸሪአዊ ትርጉሙ በገንዘብ መተማመኛ የሚደረግ ስምምነት ወይም ባለቤቱ መስፈርቱን ካሟላ
ማስለቀቅ የሚችለዉን ነገር መስፈርቱን እስከሚያሟላ ድረስ ንብረቱን መከልከል ማለት ነዉ። ረህን
ተገበያዮቹ ሰጥቻለሁ ወይም ተቀብያለሁ በማለታቸዉ ስምምነቱ ሲፈጸም ረህኑን በመረካከብ ደግሞ
ስምምነቱ ይሞላል። ረህኑን እስካልተረካከቡ ድረስ ረህን ሰጭዉ ረህኑን የመስጠት ወይም ያለመስጠት
4
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

ምርጫ አለዉ። ረህን ተቀባዩ ረህኑን ከተረከበ በኋላ በረህኑላይ ሙሉ ሃላፊነት ይወስዳል። ረህን ተከፋይ
ባልሆነ እዳ አይበቃም። ረህኑ ቢጠፋ ከእዳዉ ወይም ከረህኑ ዋጋ ትንሽ በሆነዉ ተከፋይ ይሆናል። ረህኑ
ከረህን ተቀባዩ እጅ ላይ ቢጠፋና የረህኑ ዋጋ ከእዳዉ ዋጋ ጋር እኩል ከሆነ ባለእዳዉ እዳዉን እንደከፈለ
ይቆጠራል፤ የረህኑ ዋጋ ከእዳዉ ከበለጠ ግን ጭማሪዉ እንደ አማና ይቆጠራል(ከእዳዉ የበለጠዉን ትርፍ
ገንዘብ አይከፍልም)፣ የረህኑ ዋጋ ከእዳዉ ያነሰ ከሆነ ከባለ እዳዉ ላይ የረህኑን ዋጋ ያህል ተቀናሽ
ይደረግለታል። የጋራ የሆነን ንብረት ረህን ማስያዝ አይበቃም። ፍራፍሬ ያለዉን ዛፍ ያለፍሬዉ ረህን
መስጠት አይበቃም፣ አዝእርትንም ያለ መሬቱ ረህን መስጠት አይበቃም፣ መሬትና ዛፍንም ያለ አዝመራዉና
ያለፍሬዉ ረህን ማስያዝ አይበቃም።
ረህኑን ከታማኝ ሰዉ ዘንድ ለማስቀመጥ ከተስማሙ ይችላሉ ነገር ግን ረህን ሰጭዉም ሆነ ተቀባዩ
ብቻቸዉን ከባለአደራዉ እጅ መዉሰድ አይችሉም። ረህኑ ከባለአደራዉ እጅ ላይ እያለ ቢጠፋ ረህን ተቀባዩ
እጅ ላይ እንደጠፋ ይቆጠራል። በወርቅ ሳንቲሞች፣ በብር ሳንቲሞች እና በሚመዘኑም ሆነ በሚሰፈሩ ነገሮች
ረህን ማስያዝ ይበቃል።
ረህን ሰጭዉ ረህን ተቀባዩን ወይም ሌላን ሰዉ እዳዉን ሳይመልስ ለመመለስ የተዋዋሉበት ጊዜ ካለቀ ረህኑን
ሸጠዉ እዳዉን እንዲከፍሉለት ወኪል ቢያደርጋቸዉ ዉክልናዉ ይበቃል። ዉክልናዉን የሰጠዉ የረህን
ስምምነቱ በሚፈጸምበት ጊዜ ከሆነ ዉክልናየን አንስቻለሁ ማለት አይችልም፣ አንስቻለሁ ቢልም ዉክልናዉ
አይነሳም፣ ረህን ሰጭዉ ቢሞትም ዉክልናዉ አይነሳም። ረህን ተቀባዩ ረህን ሰጭዉን በእዳ መፈለግና
ማሳሰር ይችላል፣ ረህኑን ሽጦ እዳዉን እንዲከፍለዉ ማስመቸት ግን የለበትም።
ረህኑ የሚጠበቅበት ቤት ኪራይ ክፍያ በረህን ተቀባዩ ላይ ሲሆን የዘበኛዉ ደምወዝ ግን በረህን ሰጭዉ ላይ
ይሆናል፣ ከረህን ላይ ሌላ ረህን መጨመር የሚቻል ሲሆን ከእዳ ላይ ሌላ እዳ ግን መጨመር አይቻልም።
ከሁለት የተለያዩ ሰወች ላይ እዳ ያለበት ሰዉ ለሁለቱም አንድ ረህን ማስያዝ ይችላል፣ ረህኑ በሁለቱም
መካከል ይሆናል። ረህኑ ተከፋይነቱ ለሁለቱም እንደየድርሻቸዉ በፐርሰንት ይሆናል። ባለእዳዉ
የአንደኛዉን እዳ ሙሉ ለሙሉ ከከፈለ ረህኑ ረህኑ እዳዉ ወዳልተከፈለዉ ሰዉ ይሸጋገራል።
ረህን ተቀባዩ ረህኑን በራሱና እሱ ስር ባሉ ቤተሰቦቹ ማስጠበቅ ይችላል። ከነዚህ ዉጭ ላለ ሰዉ ሰጥቶት
ረህኑ ቢጠፋ ከፋይ ይሆናል። ረህን ተቀባዩ ረህኑን ለረህን ሰጭዉ መልሶ በዉሰት መልክ ቢሰጠዉ ከክፍያ
ነጻ ይሆናል፣ ባለ እዳዉ ረህኑን እንደተዋሰ ቢያጠፋዉ ኪሳራዉ በራሱ ላይ ይሆናል። ረህን ተቀባዩ ረህኑን
ለባለእዳዉ ካዋሰዉ በኋላ የማስመለስ መብት አለዉ ልክ እንደመለሰለት ለረህኑ ሀላፊነቱን ይወስዳል። ባለ
እዳዉ ቢሞት የሟች ተወካይ ንብረቱን ወይም ረህኑን ሽጦ ያለበትን እዳ ይከፍላል።

ኢጃራ (ኪራይ)
ኢጃራ ሸሪአዊ ትርጉሙ የሚገኘዉ ጥቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ በመለያየቱ ዉሉ የሚታደስበት ጥቅምን
የመለዋወጥ ስምምነት ነዉ። የሚገኘዉ ጥቅም ወይም የሚከፈለዉ ክፍያ እስካልታወቀ ድረስ ኢጃራ
አይበቃም። በግብይት ጊዜ በገንዘብነት የሚያገለግል ነገርን በሙሉ በኢጃራ ጊዜም በክፍያነት መጠቀም
ይበቃል። ጥቅም የሚባለዉ አንዳንዴ በጊዜ ይገኛል ለምሳሌ ቤትን ማከራየት፣ መሬትን ለእርሻ ማከራየት
በዚህ ሰአት ስምምነቱ በታወቀ የጊዜ ገደብ ይፈጸማል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጥቅሙ በስራ ይገኛል ለምሳሌ
5
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

ስራን በኮንትራት ማሰራት፣ ልብስን በልብስ ሰፊ ማሰፋት፣ መጓጓዣን(መኪናን)ለተወሰነ ጊዜ ወይም


ኪሎሜትር ማከራየት። አንዳንድ ጊዜ ጥቅሙ በመለየት ወይም በመጠቆም ሊሆን ይችላል ለምሳሌ አንድን
ሰዉ እቃዉን እንዲያጓጉዝለት ማድረግ።
አንድን ግቢ ወይም ኮንቲነር ለምን አገልግሎት እንደሚያዉለዉ ሳያሳዉቅ መከራየት ይቻላል ነገር ግን ቤቱን
ሊጎዳ የሚችል የስራ አይነት ከሆነ ለምሳሌ ብረታብረት ስራ፣ ወፍጮ አይነት ስራወችን መስራት አይችልም።
በመሬቱ ላይ ምን እንደሚዘራበት እስካልታወቀ ድረስ መሬት ለአዝእርት መዝሪያነት ለማከራየት የሚደረግ
ስምምነት አይበቃም። መሬት ተከራዩ የፈለገዉን እንዲዘራ ከተስማሙ ግን የአዝእርቱ አይነት ባይታወቅም
ችግር የለዉም። በገጠር ያለን ሰፊ መሬት ግንባታ እንዲገነባበትና ዛፍ እንዲተከልበት ማከራየት ይበቃል፣
የኪራዩ ዉል ጊዜ በተጠናቀቀ ጊዜ ተከራዩ ግንባታዉን ማፍረስና አትክልቶችን በመንቀል ቦታዉን ንጹህ
አድርጎ ለባለቤቱ ማስረከብ ግድ ይለዋል። አከራዩ የንብረቱን ዋጋ መክፈል ከቻለ ባፍረሱና መንቀሉ ግዴታ
አይሆንም(የአትክልቶቹ ግምት የሚሰራዉ ተነቅለዉ እንዳሉ ታስቦ ነዉ)። አከራዩ ንብረቱ ባለበት
ሁኔታ እንዲቀመጥ ከፈቀደ መሬቱ ለአከራዩ ሁኖ ንብረቱ ለተከራዩ ይሆናል። መጓጓዣን ለሰዉ ወይም ለእቃ
ትራንስፖርትነት ማከራየት ይበቃል። ለትራንስፖርት ብቻ ብሎ ካከራየ ተከራዩ ወይም ሌላ ሰዉ
ሊገለገልበት ይችላል፣ ስምምነቱ ተከራዩ ብቻ ሊገለገልበት ከሆን ግን ሌላ ሰዉ እየተገለገለበት መጓጓዣዉ
ጉዳት ቢደርስበት ተከራዩ ለደረሰዉ ጉዳት ኪሳራዉን ይከፍላል። ማንኛዉም በዚህ መንገድ የሚሰራ ስራ
ሁሉ በዚህ ምሳሌ መሰረት ሸሪአዊ ሁክም ይሰጠዋል።
አንድ መኪና ተከራይ ሰዉ የጭነቱን አይነትና ብዛት ከተንገረ የጭነቱን አይነት ተመሳሳይ የሆነ ሌላ ነገር
መጫን ይችላል ለምሳሌ 100 ኩንታል ስንዴ ለማጓጓዝ መኪና የተከራየ ሰዉ ተመሳሳይ ወይም ያነሰ ክብደት
ያለዉ ገብስ ወይም ሰሊጥ መጫን ይችላል። የሚጭነዉ ነገር ግን ለመኪናዉ ከስንዴ የበከጠ ጉዳት
የሚያመጣ ከሆነ መጫን አይችልም ለምሳሌ እንደ ጨዉና ብረታብረት ነገሮች።
ሁለት አይነት የኪራይ አይነቶ ች ሲኖሩ አንደኛዉ አጅሩልሙሽተረክ ሲባል ሌላኛዉ አጅሩልኻስ እባላል።
የመጀመሪያዉ ሰራተኛዉ ከተለያዩ ሰሰሪወች የተለያየ የስራ ስምምነት መፈጸም የሚችልበት የኪራይ አይነት
ኒሆን በዚህ ጊዜ ሰራተኛዉ ስራዉን ሰርቶ እስከሚጨርስ ድረስ ክፍያዉ አይሰጠዉም ለምሳሌ የህንጻ
ተቋራጭ፣ ልብስ ሰፊና የመሳሰሉት። አጅሩልኻስ የሚባለዉ የኪራይ አይነት ደግሞ አሰሪዉ ሰራተኛዉ
ለተወሰነና ለታወቀ ጊዜ የሚኮናተርበት ስምምነት ነዉ። በዚህ የኪራይ አይነት ድንበር እስካልተላለፈ ድረስ
ሰራተኛዉ በስራዉ ሂደት ለሚያጠፋዉ ንብረት ተጠያቂ አይሆንም ለምሳሌ የቀን ሰራተኛ ቅጥር።
መደበኛ ግብይትን ህገወጥ መስፈርት እንደሚያበላሸዉ ሁሉ ኢጃራንም ህጋዊ ያልሆነ ቅድመ መስፈርት
ያበላሸዋል። አሰሪዉ ስምምነቱ ላይ ሰራተኛዉ ስራዉን ራሱ ራሱ እንዲሰራለት መስፈርት ካደረገ ሰራተኛዉ
ስራዉን ለሌላ ሰዉ ማሰራት አይችልም ነገር ግን ምንም መስፈርት ካላስቀመጠ ለሌላ ሰዉ ማሰራት
ይችላል። ከሁለቱ ተዋዋዮች መካከል አንደኛዉ ቢሞት ስምምነቱ ይቋረጣል ማቹ ዉሉን የተዋዋለዉ ለሌላ
ሰዉ ከሆነ ግን ስምምነቱ አይቋረጥም። በአጃራ ሸርጡል ኺያር ወይም የምርጫ መስፈርት ስምምነት
ይበቃል። ኢጃራ በስምምነቱ ዉስጥ በሚከሰት ስምምነት ይበላሻል ለምሳሌ አንድ ሰዉ ለንግድ የሚሆን ሱቅ
ተከራይቶ የሚነግድበት ገንዘብ በአጋጣሚ ቢጠፋበት የኪራይ ስምምነቱ ይበላሻል።

ሸሪካ(የጋራ ንግድ)
ሸሪካ ሸሪአዊ ትርጓሜዉ ሁለት ወይም ከዛ በላይ ሰወች በሚያዋጡት ከንዘብ ወይም በሚገኘዉ ትርፍ
መጋራት ላይ የሚደረግ ስምምነት ነዉ። ሸሪካ በሁለት መሰረታዊ ክፍሎች ሸሪከቱል አምላክ እና ሸሪከቱል
አቁድ በመባል ይከፈላል። ሸሪከቱል አቁድ ሙፋወዳ፣ ኢናን፣ ሶናኢእ እና ዉጁህ በመባል በአራት ንኡስ
ክፍሎች ይከፈላል።

6
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

1. ሸሪከቱል አምላክ
ሁለት ሰወች አንድን ንብረት በዉርስ፣በኑዛዜ፣ በስጦታ አግኝተዉ ወይም በጋራ ገዝተው የጋራ ንብረታቸዉ
ካደረጉት በኋላ አንዱ በአንዱ ድርሻ ያለፍቃዱ መጠቀም አይበቃም። በዚህ የሸሪካ አይነት ጊዜ አንዱ
ለአንዱ ንብረት እንደ አጅነብይ ነዉ።
2. ሸሪከቱል ኡቁድ
2.1 ሸሪከቱል ሙፋወዳ
ሁለቱ ሰወች በመሻረኩ ሂደት ዉስጥ በሚያዋጡት ገንዘብ፣ በሚሰሩት ስራ፣ በሚያጋጥማቸዉ እዳ እኩል
ተሳትፎ ሊኖራቸዉ የሚያደርጉት ስምምነት ነዉ። ይህ አይነት ስምምነት የሚበቃዉ በሁለት አቅመ አዳም
በደረሱ ሙስሊሞች መካከል ሲሆን በህጻንና በትልቅ ሰዉ ወይም በሙስሊምና በካፊር መካከል አይበቃም።
ይህ ስምምነት በወኪል ወይም በዋስ አማካኝነት መፈጸም ይችላል። ከምግብና መሰረታዊ ፍጆታወች
በስተቀር ከሁለቱ ሸሪካወች በአንዱ የሚገዛዉ ንብረት ለሌላዉም ንብረት ይሆናል። ከሁለት አንዳቸዉ እዳ
ዉስጥ ቢገቡ አንዱ ለሌላኛዉ ከፋይ ነዉ። ከስምምነታቸዉ በኋላ አንደኛዉ በዉርስ ወይም በስጦታ ሌላ
ገንዘብ ቢያገኝ ስምምነቱ ከሙፋወዳ ወደ ኢናን ይቀየራል።
ሸሪካ በወርቅ፣ በብር ወይም የመግዛት አቅም ባለዉ ገንዘብ ካልሆነ ስምምነቱ አይፈጸምም። ሁለት ሰወች
የሸሪካ ስምምነት ለመፈጸም ፈልገዉ አንደናዉ ገንዘብ ሌላኛዉ ንብረት ቢኖረዉ ባለ ገንዘቡ የባለንብረቱን
ግማሽ ንብረት ከገዛዉ በኋላ የሙፋወዳ ስምምነቱ መፈጸም ይችላል።
2.2 ሸሪከቱል ኢናን
ሁለት ሰወች በገንዘባቸዉ በጋራ ለመነገድና የሚገኘዉን ትርፍ በመከከላቸዉ ለመከፋፈል የሚያደርጉት
ስምምነት ነዉ። የሚያገኙት ትርፍ ወይም የሚያዋጡት ገንዘብ እኩል መሆኑ ቅድመ መስፈርት
አይደረግም። ሸሪከቱል ኢናን በዉክልና መፈጸም ሲችል በዋስ ግን መፈጸም አይችልም። ተሻራኪወች
የሚያዋጡትን የገንዘብ መጠን ማበላለጥ ይችላሉ። የሚያዋጡትን ገንዘብ እኩል አድርገዉ የትርፍ ክፍፍሉን
ማበላለጥ ይችላሉ ለምሳሌ አንደኛዉ ገንዘብ ብቻ አዋጥቶ ሌላኛዉ ገንዘብና የሙያ አገልግሎት ከሰጠ።
ሁለቱም ተሻራኪወች ከሙሉ ገንዘባቸዉ በተወሰነዉ ብቻ ስምምነቱን መፈጸም ይችላሉ። በዚህ የሸሪካ
አይነትም እንደ ኢናን ሁሉ ስምምነቱ መፈጸም የሚችለዉ የመግዛት አቅም ባለዉ ገንዘብ ነዉ። አንደኛዉ
ሸሪክ ለሌላኛዉ እቃ ቢገዛለት ለክፍያዉ ሀላፊነቱን የሚወስደዉ እቃዉን የገዛዉ ሸሪክ ነዉ። የሸሪካ
ስምምነት የተደረገበት ገንዘብ ወይም ምንም ንብረት ሳይገዙ የአንዱ ሸሪካ ገንዘብ ቢጠፋ ስምምነቱ
ይፈርሳል። አንደኛዉ ሸሪክ በራሱ ወጭ ለጋራቸዉ የሆነ ንብረት ገዝቶ የሌላኛዉ ሸሪክ ገንዘብ ውቃዉ
ከመገዛቱ በፊት ከጠፋ የተገዛዉ እቃ የጋራ እንደሆነ ታስቦ በራሱ ገንዘብ የገዛዉ ሸሪክ ከጓደኛዉ
እንደስምምነታቸዉ ገንዘቡን በፐርሰንት ያስመልሳል።
የሸሪካ ስምምነቱ ለመብቃት የግድ የሁለቱም ተሻራኪወች ገንዘብ መቀላቀል አለበት ኧይባልም። ለአንደኛዉ
ሸሪካ ከሚገኘዉ ትርፍ ይህን ያህል ገንዘብ ብቻ ትወስዳለህ የሚል መስፈርት ካለ ሸሪካዉ አይበቃም።
በሙፋወዳና በኢናን የሸሪካ ስምምነቶች ለተሻራኪወች የሚከተሉት መብቶች አሏቸዉ፤ ከጋራ ንብረታቸዉ
ላይ ለሶስተኛ ወገን ሰጥተዉ ሸጦ እንዲከፍላቸዉ ማድረግ፣ ለሶስተኛ ወገን ትርፍ የጋራ መስጠትና ዉክልና
መስጠት፣ ዋስትና መስጠት፣ ማስነገድ፣ የእለት ወይም የረጅም ጊዜ ክፍያ ግብይት መፈጸም ይችላሉ።
2.3 ሸሪከቱ ሶናኢእ
በዚህ የሸሪካ አይነት ሁለት በተመሳሳይ የሙያ አይነት የተሰማሩ ሰወች አንደን ስራ ተቀብለዉ ለሁለት
የሚሰሩበት የሸሪካ አይነት ነዉ። አንደኛዉ ለሚቀበለዉ ስራ ራሱም ሸሪካዉም ሸሪካዉም የመስራት ግዴታ
አለባቸዉ። ስራዉን አንደኛዉ ብቻዉን ቢሰራዉ ክፍያዉን ሁለቱም እኩል ይካፈላሉ።

7
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

2.4 ሸሪከቱል ዉጁህ


ሁለት ሰወች ገንዘብ ሳይኖራቸዉ በዱቤ ለመግዛትና ለመሸጥ የሚያደርጉት ስምምነት ነዉ። አንደኛዉ
ለሚገዛዉ ነገር ለጓደኛዉ ወኪል ነዉ። የሚገዛዉ እቃ እኩል የሁለት ከሆነ በሚያተርፉት ትርፍ ላይም
እኩል ለሁለት ይካፈላሉ። የሚገዛዉ እቃ ላይ ሁለት ሶስተኛ ድርሻ ሊኖ ራቸዉ ከተስማሙ ከሚያገኙት
ትርፍ ላይም ክፍፍሉ ሁለት ሶስተኛ ይሆናል።
በሁሉም የሸሪካ አይነቶች የሚደረገዉ ስምምነት ህገወጥ ወይም ብልሹ ከሆነ ከሚገኘዉ ትርፍ ላይ
ድርሻቸዉ መጀመሪያ ካዋጡት ገንዘብ ላይ በፐርሰንት ተሰልቶ የሚካፈሉ ይሆናል። ከሁለቱ ሸሪካወች
አንደኛዉ ቢሞት ወይም በከፍር የሸሪካ ስምምነቱ ዉድቅ ይሆናል። አንደኛዉ ሸሪካ የሌላኛዉን ዘካተል
ማል ያለፍቃዱ ማዉጣት አይችልም።

ሙዳረባ(ትርፍ የጋራ)
ሙዳረባ በሁለት ሸሪካወች መካከል አንደኛዉ ገንዘብ ሲያዋጣ ሌላኛዉ ጉልበት ወይም የሙያ ስራ
የሚያዋጣበት የሸሪካ ስምምነት ነዉ። ከቅድመ መስፈርቱ መካከል ከሚያገኙት ትርፍ ላይ ሁለቱም እኩል
መካፈል መቻል አለባቸዉ። አንደኛዉ ከሚገኘዉ ትርፍ ላይ የተወሰነ ብቻ ድርሻ ሊኖረዉ አይችልም።
ገንዘቡ ሸሪካ ለሆነዉ ሰራተኛ ወይም ባለሙያ መሰጠት አለበት። ገንዘቡን ገንዘብ አምጭዉ የመያዝ ስልጣን
የለዉም። የሙዳረባ ስምምነቱ ሁሉን አቀፍ ከሆነ ለባለሙያዉ ወይም ሰራተኛዉ የመግዛት፣ የመሸጥ፣
ከቦታ ቦታ ጉዞ የማድረግ፣ ዉክልና የመስጠትና ንብረት ለሌላ ሰዉ አስሽጦ ገንዘብ የመቀበል ስልጣን
ይኖረዋል። ሰራተኛዉ በሙዳረባ ስምምነት የተቀበለዉን ገንዘብ ባለገንዘቡ ሳይፈቅድለት ለሶስተኛ ወገን
በሙዳረባ ስምምነት አሳልፎ መስጠት አይችልም። በስምምነታቸዉ ላይ የገንዘቡ ባለቤት ሰራተኛዉ
በተወሰነ ሀገር ዙሪያ ወይም በተወሰነ የስራ መስክ ላይ እንዲሰራ መስፈርት ማድረግ ይችላል። ሙዳረባዉ
የጊዜ ገደብ ካለዉ ጊዜዉ በማለቁ ስምምነቱ ይበላሻል። የገንዘቡ ባለቤት ወይም ሰራተኛዉ ከሞተ ወይም
ከከፈረ ሙዳረባዉ ይበላሻል። ከሰራተኛዉ እዉቅና ዉጭ ባለገንዘቡ ስምምነቱን ቢያፈርስ ሰራተኛዉ
የገዛዉ ወይም የሸጠዉ ነገር ተቀባይነት አለዉ። ስምምነቱን ማፍረሱን ካወቀ ግን እጁ ላይ ያለዉን ነገር
መሸጥ ሲችል በሚያገኘዉ ትርፍ ሌላ ነገር መግዛት አይችልም። ባገኙት ገንዘብ ላይ እዳ ኑሮባቸዉ
ለመለያየት ካሰቡ ገንዘብ ከመከፋፈላቸዉ በፊት ሰራተኛዉ ካገኘዉ ትርፍ ላይ መጀመሪያ እዳዉ መከፈል
አለበት። ያገኙት ትርፍ እዳቸዉን መዝጋት ካልቻለ ሰራተኛዉ ለባለ ገንዘቡ በእዳዉ ላይ ዉክልና ይሰጣል።
በሙዳረባ ስምምነት ላይ የሚጠፋ ገንዘብ ከትርፉ ላይ እንደጠፋ ይቆጠራል። የጠፋዉ ገንዘብ ካገኑት ትርፍ
በላይ ከሆነ ሰራተኛዉ ለመክፈል አይገደድም። የትርፍ ክፍፍል ካደረጉ በኋላ በስምምነቱ ላይ እያሉ
የሙዳረባዉ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ቢጠፋ የተካፈሉት ትርፍ ተመላሽ ሁኖ የመጀመሪያዉን
የሙዳረባ ገንዘብ እንዲተካ ይደረጋል። ገንዘቡ ከተተካ በኋላ ከተረፈ እንደገና ለሁለት ይካፈሉታል
በተቃራኒዉ ገንዘቡ አንሶ መተካት ባይችል ሙዳሪቡ ክፈል አይባልም። የትርፍ ክፍፍል ካደረጉ በኋላ
ስምምነታቸዉን አፍርሰዉ አዲስ ስምምነት ካደረጉ በኋላ የሙዳረባ ገንዘቡ ቢጠፋ በመጀመሪያዉ
ስምምነት ያገኙት ትርፍ አሁን የጠፋዉን ገንዘብ ይተካ አይባልም። ሰራተኛው እለታዊ ወይም በረጅም ጊዜ
የሚከፈል ግብይት መፈጸም ይችላል።

ወካላ(ዉክልና)
ዉክልና ሸሪአዊ ትርጉሙ በታወቀ ጉዳይ ላይ የጉዳዩ ባለቤት እሱን ተክቶ ለሚሰራለት ሌላ ሰዉ ስልጣን
መስጠት ማለት ነዉ። ማንኛዉም ሰዉ በራሱ መፈጸም የሚችከዉን ስምምነት ለሌላ ሰዉ ዉክልና ሰጥቶ

8
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

ማስፈጸም ይችላል። በዉክልና ማንኛዉንም ጉዳይ ማስፈጸምና የፍርድ ክርክር ማድረግ ይቻላል።
ዉክልናዉ ሊበቃ ዘንድ ወካዩ ዉክልና በሚሰጥበት ነገር ላይ ሙሉ የባለቤትነት መብት ሊኖረዉና
ስምምነት ለማድረግ የሚያስችል የአእምሮ ንቃት ሊኖረዉ ይገባል። ወካዩ አቅመ አዳም ባይደርስም
መግዛትና መሸጥ የሚችል ከሆነ ዉክልና መስጠት ይችላል። በዚህ ጊዜ የዉክልናዉ ሃቅ የሚንጠለጠለዉ
በወካዩ ላይ ነዉ።
ዉክልና ተቀባዩ ሁለት አይነት ስምምነቶችን ማድረግ ይችላል። አንደኛዉ ማንኛዉንም ወካዩ ወደራሱ
የሚያስጠጋዉን ስምምነት ነዉ ለምሳሌ መሸጥ፣ መነገድ፣ ማከራየት እና የመሳሰሉት ስምምነቶች በወኪሉ
ላይ እንጅ በወካዩ ላይ አይንጠከጠሉም። ወኪሉ የሸጠዉን ነገር ያስረክባል፣ ገንዘብ ይቀበላል፣ እቃ ሲገዛ
ገንዘብ ይከፍላል፣ የገዛዉን ንብረት ይረከባል፣ ንብረቱ ጉድለት ካለበት ፍርድ ቤት ቀርቦ ይከራከራል።
ሁለተኛዉ ማንኛዉም ወኪሉ ወደ ወካዩ የሚያስጠጋዉ ስምምነት ነዉ ለምሳሌ ኒካህ ማሰር፣ የደም ካሳ
ስምምነት እና የመሳሰሉት ስምምነቶች በወካዩ እንጅ በወኪሉ ላይ አይንጠለጠሉም። አንድን ነገር
እንዲገዛለት ለሌላ ሰዉ ዉክልና የሰጠ ሰዉ የሚገዛለትን ነገር አይነቱንና ባህሪዉን ወይም አይነቱንና የዋጋ
ጣሪያዉን መናገር አለበት። ሙሉ ዉክልና ከሰጠዉ ግን ከላይ የተገለጹትን መስፈርቶች ባይናገርም ችግር
የለዉም። ሙሉ ዉክልና የሚባለዉ ወካዩ ለወኪሉ የፈለገዉን ነገር የመግዛት ወይም የመሸጥ በብት
ሲሰጠዉ ነዉ።
ወኪሉ አንድን ነገር ገዝቶ እጁ ዉስጥ ካስገባ በኋላ እንከን ቢያገኝበት እቃዉ እጁላይ እስካለ ድረስ መመለስ
ይችላል እቃዉን አሳልፎ ከሰጠዉ በኋላ ግን ያለወካዩ ፍቃድ መመለስ አይችልም። በሶርፍና በሰለም
ስምምነቶች ላይ ዉክልና መፈጸም ይቻላል። ወኪሉ የተወከለበትን ነገር ሳይረከብ ከወኪሉ ጋር ከተለያየ
ዉክልናዉ ይበላሻል። ወኪሉ አንድን ነገር ለወካዩ ገዝቶ ከራሱ ገንዘብ ወጭ ካደረገ ከወካዩ ያስመልሳል።
ወካዩ ለሁለት የተለያዩ ሰወች ዉክልና ቢሰጥ አንደኛዉ ወኪል በተወከለበት ነገር ላይ ብቻዉን መስራት
አይችልም ነገር ግን ዉክልናዉ አደራን ለመመለስ ወይም እዳን ለመክፈል ከሆነ ብቻዉን ቢፈጽመዉ ችግር
የለዉም።
ለአንድ ዉክልና ተቀባይ ያለወካዩ ፍቃድ ዉክልናዉን አሳልፎ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችልም።
ማንኛዉም ዉክልና ሰጭ ዉክልናዉን በፈለገዉ ሰአት ዉክልናዉን ማንሳት ይችላል። ወኪሉ ወካዩ
ዉክልናዉን ማንሳቱን እስካላወቀ ድረስ በዉክልናዉ መስራት ይችላል። ዉክልና ወካዩ ወይም ወኪሉ
በመሞቱ፣ አእምሮ በሽተኛ በመሆኑ ወይም በመክፈሩ ይበላሻል። ሁለት ሸሪካወች የሽርክና ስምምነታቸዉ
በመቋረጡ ዉክልናቸዉ ይቋረጣል። አንድ ዉክልና ሰጭ ዉክልና ከሰጠ በኋላ ዉክልና የሰጠበትን ነገር
ራሱ ከሰራዉ ዉክልናዉ ይበላሻል።

ከፋላ(ዋስ)
ከፋላ ሸሪአዊ ትርጉሙ የታማኙን በነፍስ፣ በእዳ ወይም በሌላ ነገር የሚደረግ ጥበቃ ወደ ዋሱ ጥበቃ ስር
ማስጠጋት ማለት ነዉ። ከፋላ የገንዘብና የሂወት ዋስትና በመባል በሁለት ይከፈላል።
የሂወት ዋስትና፡
ዋሱ ዋስ አምጭዉን በተፈለገበት ጊዜ ለዋስ አስጠሪዉ ይዞ የማስረከብ ስምምነት ነዉ። ይህ ስምምነት
በሸሪአ ይበቃል በዋሱ ላይም ዋስ የሆነለትን ሰዉ በተፈለገ ጊዜ ይዞ የማስረከብ ግዴታ አለበት። ዋሱ
በስምምነቱ መሰረት ዋስ አምጭዉን ይዞ ማስረከብ ካልቻለ ይታሰራል። ዋሱ ዋስ አምጭዉን ይዞ
ባስረከበበት ቅጽበት እራሱን ከዋስነት ነጻ ያወጣል። ዋስ አምጭዉ ከሞተ ዋሱ ከዋስነት ነጻ ይሆናል። ዋሱ
ዋስ አምጭዉን በተፈለገበት ሰአት ማምጣት ካልቻለ ገንዘብ ሊከፍል ከተስማማ ያንን ገንዘብ የመክፈል
ግዴታ አለበት።
9
Financial jurisprudence on hanafi mezhab

የገንዘብ ዋስትና፡
ዋስ የተገባለት ገንዘብ የታወቀ ቢሆንም ባይሆንም ትክክለኛ እዳ እስከሆነ ድረስ የገንዘብ ዋስትና መስጠት
ይበቃል። ለምሳሌ ዋሱ ለዋስ አስጠሪዉ ለእገሌ በአንድ ሽህ ብር ዋስ ሁኘዋለሁ ወይም ከአንተ ላይ ባለበት
እዳ ዋስ ሁኘዋለሁ ካለዉ ዋስነቱ ይረጋገጣል። በዚህ ግዜ ዋስ አስጠሪዉ ገንዘቡን ከዋሱ ወይም ከዋስ
አስጠሪዉ ማስከፈል ይችላል። በዋስትና ስምምነት ላይ ቅድመ መስፈርት ማስቀመጥ ይቻላል። አንድ ዋስ
ዋስትና የሰጠዉ በዋስ አምጭዉ ጥያቄ ከሆነ ስለሱ የከፈለዉን ገንዘብ ከዋስ አምጭዉ ማስመለስ ይችላል
ነገር ግን ዋስ የሆነዉ በራሱ ፍላጎት ከሆነ ዋስ ስለሆነዉ ሰዉ የከፈለዉን ገንዘብ ማስመለስ አይችልም።
አንድን እቃ ለገዛ ሰዉ ገንዘቡን እስከሚከፍል ድረስ ዋስ መሆን ይቻላል። እቃ ሽጦ እቃዉን
እስከሚያስረክብ ድረስ ግን ዋስ መሆን አይበቃም። ስምምነት ቦታዉ ላይ ዋስ አስጠሪዉ ዋሱን
ካልተቀበለዉ የከፋላ ስምምነቱ ዉድቅ ይሆናል።

ሀዋላ(የገንዘብ ዝዉዉር)
ሃዋላ እዳን ከባለ እዳ ወደ እዳ ተቀባይ ማዘዋወር ማለት ነዉ። ሃዋላ ያበደረዉን ገንዘብ ጠያቂዉ፣
የመጀመሪያዉ ባለእዳና እዳዉ የሚዛወርበት ሰዉ ከተስማሙ ስምምነቱ ይበቃል። ሃዋላዉ ከተፈጸመ በኋላ
የመጀመሪያዉ ባለእዳ ከእዳዉ ነጻ ይሆናል። በዚህ ጊዜ እዳዉ የተዛወረበት ሰዉ ካልሞተ ወይም በድህነት
ምክንያት እዳዉን መክፈል ካልቻለ በስተቀር ያበደረዉን ገንዘብ ጠያቂዉ ሰዉ ወደመጀመሪያዉ ባለእዳ
ተመልሶ ገንዘብ መጠየቅ አይችልም። የሃዋላ ምሳሌዉ አምር ከዘይር መቶ ብር ብድር ቢኖርበት አህመድ
ደግሞ ከአምር መቶ ብር ብድር ቢኖርበት ዘይድ አምርን ያበደረዉን ገንዘብ እንዲመልስለት ከጠየቀዉ
አምር ለዘይድ እዳየን ወደ አህመድ አዘዋዉሬያለሁ ማለት ይችላል። በዚህ ምሳሌ መሰረት ገንዘብ ጠያቂዉ
አምር፣ የመጀመሪያዉ ተበዳሪ ዘይድና እዳዉ የሚዛወርበት ሰዉ ደግሞ አህመድ ይሆናሉ ማለት ነዉ።

10

You might also like