Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 6

ከጥቅምት 21 እስከ 27 ቀን 2013 ዓ.


ቅፅ 1 ቁጥር 2

Media Digest
ሚዲያ ዳሰሳ

በቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች


በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢትዮ ቴሌኮምን በዓመት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ሊያሳጣ በሚችል የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ
ሦስት ግለሰቦችን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን የብሄራዊ
መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።
የደህንነትና ፀጥታ አካላቱ በአዲስ አበባ
ከተማ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል
በሚፈፀምባቸው ቦታዎች ላይ ጥብቅ
የመረጃና የክትትል ሥራዎችን በመስራት
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት
እና ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት
በተካሄደ ዘመቻ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር
ስር ለማድረግ ተችሏል፡፡

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በህገ ወጥ መልኩ


ዓለምአቀፍ የስልክ ጥሪዎችን በመጥለፍና
በራሳቸው መስመሮች ለደንበኞች በማቅረብ
ህገወጥ ድርጊት ሲፈፅሙ የነበሩ ሲሆን
ተጠርጣሪዎች ከኢትዮ ቴሌኮም እውቅና
ውጪ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስልክ
ጥሪዎችን በማስተላለፍ የራሳቸውን ገቢ
ሲሰበስቡ መቆየታቸው ታውቋል፡፡
ይህ ህገ ወጥ ድርጊት ባይከሽፍ ኖሮ
ኢትዮ ቴሌኮምን በዓመት ከ200 ሚሊየን
ብር በላይ ገቢ ሊያሳጣው እንደሚችል ተገልጿል። ህገ ወጦችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በነበረው ሂደት ህብረተሰቡ ላሳየው
የላቀ ተሳትፎ ምስጋናውን ያቀረበው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በቀጣይም ህገወጦችን በማጋለጥ
ረገድ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።
ምንጭ፡ ኢቢሲ፤ ኤፍ ቢ ሲ እና ሌሎች ሚዲያዎች

በሚዲያ ስትራቴጂና ኤጀንሲ ማኔጅመንት ዲፓርትመንት የተዘጋጀ

1
አዲስ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ተደራሽነታቸው ተገምግሞ ፈቃዳቸው
እንደሚታደስ ተገለጸ
በቴሌኮም ሴክተር ዙሪያ
የሚደረገውን ሪፎርም ተከትሎ
ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው
በቴሌኮም አገልግሎት ዘርፍ
እንዲሰማሩ ፈቃድ የሚሰጣቸው
ሁለት ኩባንያዎች አገልግሎቱን
ማቅረብ ከጀመሩበት ዓመት
ጀምሮ በየዓመቱ መጨረሻ
ምን ያህል ተደራሽ ናቸው
የሚለውን ጉዳይ ታሳቢ ተደርጎ
ፈቃዳቸው እንደሚታደስ እና
ይህንንም ተከትሎ የተጠበቀውን
ያህል ያልተንቀሳቀሰ ኩባንያ
ፈቃዱን እስከመንጠቅ የሚያደርስ እርምጃ ለመውሰድ ወር አሸናፊው ይታወቃል ተብሎ የሚጠበቀውን
የሚያስችል ዝግጅት እንደተደረገ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን የሁለት ቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተሮች ፈቃድ ለመስጠት
ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ የሚያስችል የሬጉላተሪ ማዕቀፍ እና እስትራቴጂያዊ
መርህ ባለስልጣን መ/ቤቱ እንዳዘጋጀ አስታውቀዋል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የሦስት ወር ሪፖርቱን ኦፕሬተሮቹ ወደ አገር ገብተው ሥራ ሲጀምሩ ባለስልጣን
ባቀረበበት ወቅት ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጂነር ባልቻ ሬባ መ/ቤቱ የዋጋ ቁጥጥር ሥርዓት እንደሚዘረጋና
እንዳስታወቁት ባለሥልጣኑ በያዝነው ወር መጨረሻ ኦፕሬተሮች የታሪፍ ዋጋን አላግባብ እንዳይጨምሩም
አሊያም በህዳር ወር 2013 መጀመሪያ ላይ ጨረታውን ሆነ እንዳይቀንሱ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
አውጥቶ ከገመገመ በኋላ በመጪው መጋቢትና ሚያዝያ ምንጭ፡ አዲስ ማለዳ

********************

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ወቅታዊ የሃገራችን ሁኔታን


ምክንያት በማድረግ የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ

በሃገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ ከምንጊዜውም


በላይ ሊቃጡ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል
እና ለመቆጣጠር ዝግጁ መሆኑን ያስታወቀው ኤጀንሲው
ሁሉም ኢንተርኔትና ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ
የሆኑ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ሕብረተሰቡ
ሊከሰቱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን በንቃት በመከታተል
የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣ አሳስቧል፡፡

በሚዲያ ስትራቴጂና ኤጀንሲ ማኔጅመንት ዲፓርትመንት የተዘጋጀ

2
በተለይም ቁልፍ የሃገራችን ተቋማትና መሰረተ ልማቶችን (የፋይናንስ፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ የልማት ድርጅቶች
እንዲሁም መሰል ተቋማትን) ዒላማ ያደረጉ የሳይበር ጥቃቶች ሊሰነዘሩ የሚችል በመሆኑ ተቋማቱ አስፈላጊውን
ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተቋማትም ይሁኑ ህብረተሰቡ ማናቸውም ዓይነት የሳይበር ጥቃት ሙከራም ሆነ አጠራጣሪ
ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ከዚህ በታች በተገለጹት አድራሻዎች በማንኛውም ሰዓት በሚከተሉት አድራሻ በፍጥነት
ጥቆማ እንዲያደርጉ ኤጀንሲው ጥሪ አቅርቧል፡፡

• ስልክ፡ 0900896448, 0936825343, 0944336802


• ኢ-ሜይል፡ ethiocert@insa.gov.et
• ነጻ የስልክ መስመር፡ 933
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ

ምንጭ፡ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንና ሌሎች ሚዲያዎች

********************
የሞባይል መገጣጠሚያ ኩባንያዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑ ተገለፀ

በሀገራችን 16 የሚሆኑ የተንቀሳቃሽ ስልክ መገጣጠሚያ ዓመት ጀምሮ ተጨማሪ አምስት በመቶ ቀረጥ
ኩባንያዎች የነበሩ ሲሆን፤ ብዙዎቹ ዘግተው አምስት እንደጣለበት የገለጹት አቶ አብይ፣ በተጓዳኝ ደግሞ
የሚሆኑት ብቻ በአሁኑ ሰዓት በሥራ ላይ እንደሆኑ የኮንትሮባንድ ንግዱ ጭራሽ ቁጥጥር እየተደረገበት
ተገልጿል፡፡ እንዳልሆነና በአሁኑ ሰዓት እየጨመረ
መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
አዲስ ማለዳ የተሰኘው ሚዲያ
የአይ.ሲ.ቲ ኢቲ ሃርድ ዌር ይሁን እንጂ ዘገባው
ቡድን ባለድርሻ የሆኑትን በጉዳዩ ዙሪያ
አቶ አብይ ምንውየለትን የሚመለከታቸው
ጠቅሶ እንደዘገበው የ መ ን ግ ስ ት
አምራች ኩባንያዎች ተ ቋ ማ ት
ከገበያ የወጡበት የሚኖራቸውን
የመጀመሪያው እና አ ስ ተ ያ የ ት
ዋነኛው ምክንያት አላካተተም፡፡
ለተንቀሳቃሽ ስልኮች
መገጣጠሚያ ግብዓቶች በአገር
ውስጥ አለመኖራቸው ሲሆን፤
በዚህም ምክንያት ከውጪ ሀገር ማስገባት
ስለሚያስፈልግ ይህንን ለማድረግ የውጪ ምንዛሬ ምንጭ፡ አዲስ ማለዳ
እጥረት ከፍተኛ ተግዳሮት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በፊት ለሞባይል መገጣጠሚያ የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን


ሲያስገቡ ቀረጥ እንዳልነበረውና መንግስት ከባለፈው

********************
በሚዲያ ስትራቴጂና ኤጀንሲ ማኔጅመንት ዲፓርትመንት የተዘጋጀ

3
የመንግሥት ተቋማትን አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለተጠቃሚው
ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
በ2013 በጀት ዓመት መንግስት
የሚሰጣቸውን የኤሌክትሮኒክስ
አገልግሎቶችን ለማሳደግ
እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና
ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ
፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ
የዲጂታል አገልግሎትንና
ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን
አስመልክቶ ለኢዜአ በሰጡት
ቃለ ምልልስ አስታውቋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ
በመንግሥት ተቋማት የሚሰጡ
አገልግሎቶች ለምተው
ለተጠቃሚዎች ዝግጁ መሆኑን
ገልፆ፣ ተገልጋዮች የለማውን
www.eservices.gov.etን
በማንኛውም የኢንተርኔት
መጠቀሚያና መፈለጊያ በመጠቀም ገብተው ማየት የሚያስችሉ ሥራዎች የዚሁ ዕቅድ አካል መሆናቸውን
እንደሚችሉ አብራርቷል፡፡ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ አስገንዝቧል።
ሚኒስቴር የዲጂታል አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን
ተቋማት በመለየትና በማጥናት ወደ ስራ የገባ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት ለአገራዊ ኢኮኖሚ
የዲጂታል አገልግሎትን መሠረተ ልማት ለማስፋፋትና ከሚያስገኘው ትሩፋት አንዱ የዲጂታል ግብይት
ለተገልጋዮች ማድረስ የሚያስችሉትን ተግባራትንም ስርዓትን በመተግበር አገር በቀል ኢኮኖሚውን ማገዝ
እያከናወነ ይገኛል። መሆኑን እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ግብይትና
ተያያዥ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት የመኖሪያና
በተያያዘ ዜና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን ለማሳካት የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች የዲጂታል አድራሻ
የሚያስችሉ መሰረታዊ መደላድሎችን የመፍጠር ሊኖራቸው እንደሚገባም የተገለጸ ሲሆን፣ የዲጂታል
ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስርዓቱ ሲያድግ በዛው ልክ የሳይበር ጥቃቶች እያደጉ
አስታውቋል፡፡ ለዲጂታል አገልግሎቶች በመሠረታዊነት እንደሚመጡ ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጵያ የሳይበር
የሚወሰደው የዲጂታል መለያ ጉዳይ ነው። ከዚህ አኳያ ደህንነት አቅሟን እንድታጎለብት የማድረግ ሥራ
ዜጎችን ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ከወዲሁ እየተከናወነ መሆኑንም ተጠቁሟል።
ተጠቃሚ ለማድረግ ከሠላም ሚኒስቴር ጋር እየተሠራ
መሆኑን የገለፀው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ፣ በዚህ ዓመት
20 ከመቶ ለሚሆኑ ነዋሪዎች አገልግሎቱን በሙከራ ********************
ደረጃ ለማቅረብ በብሔራዊ ዳታ ማዕከል የመመዝገብ
ስራ እንደሚከናወን አስረድቷል።

ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሳካት ቁልፍ ሚና


ካላቸው ጉዳዮች አንዱ የኢንተርኔት ግንኙነት አቅም
(ኮኔክቲቪቲ) መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገለፀ
ሲሆን፣ የግሉ ዘርፍ ወደ ቴሌኮም ዘርፉ እንዲገባ

በሚዲያ ስትራቴጂና ኤጀንሲ ማኔጅመንት ዲፓርትመንት የተዘጋጀ

4
ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
• አፕሊኬሽኖችን እና ሶፍትዌሮችን ከትክክለኛዉ
መረጃ ቋት ማዉረድ (download ማድረግ)፡-
የምናወርዳቸውን ሶፍትዌር እና የአፕሊኬሽን
ቋት ህጋዊና ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ፤
• ለማህበራዊ ሚዲያ አካዉንቶች ባለሁለት ደረጃ
የትክክለኛነት ማረጋገጫ መጠቀም (Two-Fac-
tor Authentication)፡- የማህበራዊ ሚዲያዎች
ስንጠቀም ባለሁለት ደረጃ የትክክለኛነት
ማረጋገጫ ተግባራዊ ከማድረግ ባሻገር
አገልግሎት ተጠቅመን ስንጨርስ Logout
ወይም Sign out ማድረጋችንን አለመዘንጋት፤

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በማህበራዊ • ነፃ የህዝብ ዋይፋይ ስንጠቀም መጠንቀቅ፡- የተለያዩ


ሚዲያው ላይ እንዳሳፈረው ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል ነፃ ፐብሊክ ዋይፋዮች ለአደጋ ተጋላጭ በመሆናቸው
የሚጠቅሙ ዘዴዎችን ዘርዝሯል፡፡ የሳይበር ምህዳሩ ሚስጥራዊና እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በህዝብ
ከፈጠራቸዉ መልካም ዕድሎች ጎን ለጎን የተለያዩ ዋይፋይ ከመጠቀም መቆጠብ፤
የደህንነት ስጋቶችንም ያስከትላል ፡፡ • ከማህበራዊ ምህንድስና ማጭበርበሪያ ዘዴዎች
የሳይበር ምህዳር ያልተማከለ፣ ባልታወቁ አካላት መጠንቀቅ፡- የማህበራዊ ምህንድስና የማጭበርበሪያ
ሊንቀሳቀስ የሚችል፣ በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ ዘዴዎች የምንላቸዉ የሰዉ ልጆችን ስነ-ልቦና መሰረት
የሆነ እና ፍልስፍናዊ ባህሪ ያለው ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር ያደረጉና ሲስተሞችን በሀይል ሰብሮ ከመግባት ይልቅ
በተያያዘም በሀገራት ደህንነት፣ በሰብአዊ መብት፣ በዘዴ ማታለልን አማራጭ በማድረግ መረጃዎችን
በግላዊነትና ሉዓላዊነት በሚባሉ የአንድ ሀገር ብሔራዊ ለመውሰድ የሚዉል የሳይበር ጥቃት ዓይነት ነዉ፡፡
የደህንነት ጉዳዮች ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው።
እነዚህን የደህንነት ስጋቶች ለመቋቋም ሊወሰዱ ስለሆነም እርስዎም የሳይበር ምህዳሩ ከፈጠረዉ ምቹ
ከሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል የሚከተሉት ሁኔታ ባሻገር እጅግ ዉስብስብ እና አደገኛ መሆኑን
ይገኙበታል፡- በመረዳት ከላይ የቀረቡትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን
በመተግበር በራስዎ፣ በተቋምዎ እንዲሁም በሀገር ላይ
• ጠንካራ የሆነ የይለፍ ቃል መጠቀም፡- ጠንካራ የይለፍ- ሊደርስ የሚችልን የሳይበር ጥቃት ይከላከሉ፡፡
ቃል ለመጠቀም የቁጥር፣ የፊደላትና የምልክቶች
ጥምረት መጠቀም ሲሆን የይለፍ-ቃሉን ለማንም ምንጭ፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፌስቡክ ገጽ
አለማጋራት ነው፡፡
• ትክክለኛ ፀረ-ቫይረስ መጠቀም፡- ለኮምፒዉተሮቻችን፣ ********************
ስልኮቻችን እና መሰል ከኢንተርኔት ጋር ለተቆራኙ
ቁሶች ፀረ-ቫይረስ መጠቀም ይገባል፡፡
• የሚጠቀሙበትን ኮምፒዉተርም ሆነ ስማርት ስልኮች
ኦፕሬቲንግ ሲስተም (Operating Systems) ማዘመን
ያስፈልጋል፡፡
• መጠባበቂያ መያዝ (Backup)፡- አስፈላጊ የሆኑ
መረጃዎቻችንን መጠባበቂያ መያዝ ይገባል፡፡
• የምንጎበኘዉን ድረ-ገፅ ትክክለኛነት ማረጋገጥና
ሊንኮችን ስንጠቀም መጠንቀቅ፡- የድረ-ገፅ እና የተለያዩ
መልዕክት መለዋወጫ ዘዴዎችን ትክክለኛነታቸዉን

በሚዲያ ስትራቴጂና ኤጀንሲ ማኔጅመንት ዲፓርትመንት የተዘጋጀ

5
የአየር ሰዓት ለማስተላለፍ ከሚደረግ የቴሌኮም ማጭበርበር ተግባር ጋር
በተያያዘ ሀሰተኛ መልዕክቶችን በሚያሰራጩ ደንበኞች ላይ የሚወሰደው
እርምጃ ቀጥሏል
የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም እና ከኢትዮ ቴሌኮም የተላለፈ መልእክት በማስመሰል የአየር ሰዓት
እንዲተላለፍላቸው የማጭበርበር ተግባር በሚፈፅሙ ህገወጦች ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ሚዲያ ሞኒተሪንግ ክፍል ባሳለፍነው የሩብ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ የቴሌኮም ማጭበርበር
ድርጊት ለመፈፀም በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቁ ከ70 በላይ መልዕክቶችን በመለየት እና ወደ ኢንፎርሜሽን
ሴኩሪቲ ዲቪዥን በመላክ አስፈላጊው ርምጃ እንዲወሰድ አድርጓል፡፡

አብዛኞቹ ሃሰተኛ መልእክቶች ከተቋሙ ወቅታዊ ጉዳዮች ጋር በማያያዝ የሚተላለፉ የማጭበርበር መልዕክቶች
ሲሆኑ እንዲህ አይነት ሃሰተኛ መልእክቶች በደንበኞቻችን ላይ ከሚያስከትለው ችግር በተጨማሪም የተቋማችንን
መልካም ገፅታ የሚያበላሽ ስለሆነ የተቋሙ ማህበራሰብ ተመሳሳይ መልእክቶች ሲያጋጥማችሁ የመልእክቱን ሙሉ
ይዘት ኮፒ በማድረግ በኢሜል አድራሻ ወደ zzz Anti Fraud Section እንድትልኩ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

********************

ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮ ቴሌኮም ማህበራዊ ትስስር ገፆችና መገናኛ


ብዙኃን የተገለፁ መረጃች
• ደንበኞች በአጭበርባሪዎች ከሚደረጉ ዓለምአቀፍ ጥሪዎች እና አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች እንዲጠነቀቁ
የሚያሳስብ መልዕክት መተላለፉ፣

• የውጪ ማስታወቂያ ለመስራት ፍላጎቱ ያላቸው እና በአገልግሎቱ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እንዲሳተፉ


የሚጋብዝ ማስታወቂያ ፣

• ልዩ የመውሊድ ሞባይል ጥቅል አገልግሎት ከመጠናቀቁ በፊት ደንበኞች ለራሳቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው
በስጦታ እንዲያበረክቱ በ#My Ethiotel የሞባይል መተግበሪያ አሊያም *999# በመጠቀም የልዩ ቅናሽ
አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ እንዲሁም መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር ወይም ከhttps://t.m/ethio_tele
com በማውረድ በነፃ መጠቀም እንደሚችሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

• በተመረጡ የመገናኛ ብዙኃን (ጋዜጦች) የድረ ገፅ ማስታወቂያ ቦታ ላይ የሚከተሉት ምርትና አገልግሎቶች


እንዲተዋወቁ ተደርጓል፡-

- ከውጪ ሀገር ሆነው አገር ቤት ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶች የድረ ክፍያ የቴሌኮም አገልግሎት ወርሃዊ
ክፍያ መፈፀም እንዲሁም አየር ሰዓት መሙላት እንደሚቻል
- ደንበኞች በአነስተኛ ዋጋ የሞባይል ዳታ ጥቅል አገልግሎት ገዝተው እንዲጠቀሙ የሚገልፅ ማስታወቂያ

********************

በሚዲያ ስትራቴጂና ኤጀንሲ ማኔጅመንት ዲፓርትመንት የተዘጋጀ

You might also like