Professional Documents
Culture Documents
Agrement For Metku G05 B
Agrement For Metku G05 B
አከራይ በስሙ የተመዘገበውና የራሱ ንብረት ከሆነው አዲስ አበባ ከተማ_ቦሌ_ ክፍለ ከተማ ወረዳ_03___
የቤት ቁጥር _አዲስ_ የካርታ ቁጥር AA000060304609 ካርታው የተሰጠበት ቀን 09/10/08 ዓ.ም ተመዝግቦ
በሚገኘው ህንፃ ላይ በ_ ግራዉንድ ወለል _ የቢሮ ቁጥር _ NRE/AP/G05 B_፤ ስፋቱ _28_ካ.ሜ.፤ የሆነ ቦታ
ለማከራየት ፍላጎት ያለው በመሆኑ ሁለቱም ወገኖች ወደውና ፈቅደው ከዚህ እንደሚከተለው ተዋውለዋል፡፡
አንቀጽ ሁለት፡- የኪራይ ተመን እና አከፋፈል
2.1. የቦታው የኪራይ መጠን 15% ተጨማሪ እሴትን ጨምሮ በካሬ ሜትር ብር 522.00 (አምስት መቶ ሃያ
ሁለት ብር ከ 00/100) ነው፡፡
2.2. በወር 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ሳይጨምር ብር 12709.57 ( አስራ ሁለት ሺ ሰባት መቶ ዘጠኝ ብር
ከ 57/100) ብሎም ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ብር 1906.43 (አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ስድስት ብር
ከ 43/100) ሲሆን ይህ ዋጋ ከ የካቲት 20 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ጸንቶ
ይቆያል፡፡
2.3. የኪራይ አከፋፈል
2.3.1. ተከራይ የ 6 ወር ቅድሚያ ኪራይ ክፍያ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ብር 87696.00(ሰማንያ
ሰባት ሺ ስድስት መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከ 00/100) ከፍለዋል፤ አከራይም ለተከራይ ተገቢውን ደረሰኝ
ሰጥተዋል፡፡
2.3.2. ቅድሚያ ክፍያ የተከፈለበት የመጀመሪያው የ 6 ወር ጊዜ ካበቃ በኃላ ላሉት ቀሪ የኪራይ ዘመናት
ተከራይ የ 3 ወር ቅድሚያ ኪራይ ክፍያ ለአከራይ ይከፍላል፡፡
2.3.3. ተከራይ ቀድሞ የከፈለው የቅድሚያ ኪራይ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ቀጣይ ክፍያውን በ 10 (አስር) ቀናት
ይከፍላል፡፡
2.3.4. የቅድሚያ ኪራዩን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2.3.3. መሰረት ሳይከፍል ከዘገየ የውዝፉን ወይም
ያልተከፈለበትን የቅድሚያ ኪራይ 10% መቀጫ ጋር በ 10 (አስር) ቀናት ውስጥ ይከፍላል፡፡
2.3.5. ተከራይ የቅድሚያ ኪራዩን ከ 10% መቀጫ ጋር በ 10 (አስር) ቀናት ውስጥ ካልከፈለ አከራይ ውሉን
ለመሰረዝና እዳውን ለማስከፈል በህግ አግባብ መብት እንዳለው ሁለቱም ወገኞች ተስማምተዋል፡፡
አንቀጽ ሦስት፡- የኪራይ ንብረት አጠቃቀም
3.1. ተከራይ የተከራየውን ክፍል (ቦታ) ለ ንግድ ቤት አገልግሎት ብቻ ይውላል፡፡
3.2. ተከራይ የኪራይ ንብረቱን ወይንም ማንኛውንም የንብረቱ አካል ከሕግ፣ ከደንብ፣ ከዚህ ውል፣ ከመንግስት
መመሪያና በአብዛኛው ህዝብ ተቀባይነት ካለው ልምድና ባህል ውጪ ለሆኑ ጉዳዮች ወይም ተግባር መጠቀም
ወይንም ማዋል ጨርሶ አይችልም፡፡
3.3. ተከራይ የተከራየውን ንብረት ሲለቅ የተከራየውን ንብረት እንዲሁም በውስጡ የተገጠሙት ልዩ ልዩ
መገልገያ ዕቃዎች ብልሽትና ጉዳት ካላቸው ቀድሞ በተሰራበት ማቴሪያል ዓይነት በራሱ ወጪ በመለወጥና
በማስተካከል በነበሩበት አኳኃን በማድረግ ለአከራዩ መልሶ ያስረክባል፤ ግንባታውም ደረጃውን የጠበቀና በአከራዩ
ተቀባይነት ያለው መሆን ይገባዋል፡፡