Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

፲፬፪ ገብረ ክርስቶስ (ገብረ መርዓዊ)

ገብረ ክርስቶስ አባቱ የቁስጥንጥንያ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ እናቱ


መርኬዛ ይባላሉ፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈሩ በሃይማኖት የጸኑ ነበሩ፡፡
ልጅ በማጣታቸው ኢየሩሳሌም ወርደው ቅዱሳት መካናትን እጅ
ነሥተው ልጅ ብትሰጠን ብለው ብፅዐት ገብተው ተመለሱ፡፡ በዓመቱ
ወንድ ልጅ ወለዱ፡፡ ስሙን አብደል መሲሕ አሉት፡፡ ገብረ ክርስቶስ
ማለት ነው፡፡ ሥጋዊና መንፈሳዊ ትምህርትን እያስተማሩ አሳደጉትና
አካለ መጠን ሲደርስ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ አጭተው አጋቡት፡፡
ሌሊትም በኾነ ጊዜ ወደ ሙሽራይቱ ገብቶ እጇን ይዞ ጸሎተ
ሃይማኖትን እስከ መጨረሻው ደግሞ እንዳትናገር ቃል አስገብቶ
የተሞሸረበትን ልብስ አውልቆ እኅቴ ሆይ እንደ ጉም ተኖ እንደ ጢስ
በኖ ከሚጠፋ ተድላ ሥጋ አልገባም፤ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ
ይኑር ከሰይጣን ሥራ ያድንሽ የአባቴ መንግሥት ኀላፊ ጠፊ ነውና
እኼዳለኹ እንዳትናገሪ ብሎ በሌሊት ወጥቶ ኼደ።
ከዚያም በመርከብ ተሳፍሮ የብዙ ቀን መንገድ የሚኾን ጐዳና
በ፩ ቀን ተጉዞ አርማንያ ደረሰ፡፡ በነጋ ጊዜ እናት አባቱ ጫጕላ ቤት
ቢገቡ ዕጡት፡፡ ወዴት ኼደ አሏት፡፡ በሌሊት መሐላ አስማለኝ፡፡
ራሴንም ስሞኝ ወጣ፡፡ እኔም እያለቀስኩ ብቻዬን ዐደርጉ አለቻቼው፡፡
እነሱም ወድቀው አለቀሱ። ንጉሡም ፭፻ አገልጋዮቹን ለምጽዋት
ገንዘብ ሰጥቶ ፈልጋችኹ አምጡት ብሎ ላካቸው፡፡ ኹለቱ እየፈለጉ
ሲኼዱ አርማንያ በእመቤታችን ስም ከታነጸች ቤተ ክርስቲያን
ደርሰው፡፡ ከስንቃቸው ለነዳያን ሲመጸውቱ፡፡ ለእርሱም መጸወቱት
መልኩ ተለውጦ አላወቁትም። በአባቴ ባሮች ለመመጽወት ያበቃኸኝ
አምላኬ ተመስገን አለ፡፡ መልሶ ለሌላ መጽውቶታል። እኽል
የሚቀምስ ሰዕለተ ሰንበት ብቻ ነበር፡፡ እንደዚህ ኹኖ ፲፭ ዓመት ሲኖር
እመቤታችን ለገበዙ ተገልጻ ቦታውን አመልክታ ገብረ ክርስቶስን ይዘኽ
ከቤተ ክርስቲያን አግባው አለችው፡፡ ኺዶ እመቤቴ አዝዛኛለችና
ገብተኽ ሥጋውን ደሙን ተቀበል አለው፡፡ ገብረ ክርስቶስም ገብቶ
ተቀብሎ ከተነጠፈውና ከተጉዘጉዘው ቤት ውሎ ዐደረ፡፡ ኋላ ግን ዋጋዬ በውዳሴ ከንቱ ሊጠፋብኝ ነው ብሎ ከእመቤታችን ፊት
ቁሞ
«ለምንት ከሠትኪ ኅቡአትየ ወይእዜኒ ምርሕኒ ኀበ ዘይኄይሰኒ»
እንዲል ትርጕም «ምስጢሬን ለምን ገለጽሽ አኹንም ወደ ሚሻለኝ
ምሪኝ” ጸለየና ሥዕሏን ተሳልሞ ወጥቶ ወደ ሌላ ሀገር ሊኼድ
በመርከብ ተሳፈረ ከእናት ከአባቱ ሀገር ደረሰ፡፡ የጌታ ፈቃድ ነው ብሎ
ሳያውቁት ከደጃቸው ወድቆ ፲፭ ዓመት ኖረ፡፡ የአባቱ ባሮች ‹‹አሰስሉ
ለነ ዘንተ ምስኪነ ጼና ጺአቱ ኢያሕስመነ›› ይላል፡፡ ትርጕም ‹‹ይህን
ምስኪን አስወግዱለን ሽታው አያስቸገረን›› እያሉ ወጭትና ድስት
አጥበው ይደፉበታል፡፡ ውሾች እንዲናከሱበት የሥጋ ትራፊና ዐጥንት
ይጥሉበታል። ውሾች ግን ቁስሉን ይልሱለት ነበር፡፡ እሱም በደል
እንዳይኾንባቸው እያለ ሲጸልይ ኖረ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ጌታችን ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን
ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው። እሱም ታሪኩን ከመጀመሪያው እስከ
መጨረሻው ጽፎ በእጁ ጨብጦ ዕርፋል። ሊቀ ጳጳሱ በቅዳሴ ሳለ
ብእሴ እግዚአብሔርን በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ቤት ፈልጉት የሚል ቃል
ሰማና ቢኼዱ ባረፈበት ቦታ አገኙት። ክርታሱን ሊያዩ ሽተው
የማይለቅላቸው ኾነ፡፡ ፵፩ እግዚኦታ ፵፩ በእንተ ማርያም አድርሰው
ለቀቀላቸው፡ ሲያነቡት የንጉሥ
ኾኖ ተገኘ፡፡
እያለቀሱ
ደረታቸውን ይድቁ ጀመር፡፡ ሕሙማኑ ኹሉ ቢዳስሱት ከደዌያቸው
ተፈውሰዋል፡፡ ሕሙማኑ የማይተውት ቢኾን ወርቅ ብር በተነላቸው፡፡
ይኼንማ ገበሬም ይሰጠናል ብለው የማይመለሱላቸው ኾኑ። ዳሰውት
ከተፈወሱ በኋላ በአንጻረ መቅደስ ቀብረውታል፡፡ የዕረፍቱ መታሰቢያ
ጥቅምት ፲፬ ቀን ነው፡፡
ማጠቃለያ፡- ገብረ መርዓዊ ሚስቱን ጥሎ ወደ ገዳም መመነኑ
መልኩ መለወጡ በጾም በጸሎት ተወስኖ መኖሩ እመቤታችን ክብሩን
መናገሯ በእናት አባቱ ቤት እየተሠቃየ መኖሩ በወረቀት ስሙን
መጻፉ ወዘተ ይነገርለታል፡፡
ሰላም ለገብረ ክርስቶስ እንተ አንደየ አባሎ፡ በዴዴ አቡሁ አክልብት
እስከ ለሐሱ ቊስሉ፡ አዕረፈ ዮም ለእግዚአብሔር ከመ ሰአሎ፡ እምእደ አግብርት ተኮንኖ ወእምእደ አእማት ተጽእሎ፡ እምድኅረ
ፈጸመ ወሰለጠ
ገድሎ፡፡ እን ዐርኬ

You might also like