Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

የኦጋዴን ድመቶች በይስማዕከ ወርቁ መጋቢት 21/2012

መግቢያ
ገፀባህሪያት በአንድ የፈጠራ ፅሁፍ ውስጥ የታሪኩ ባለቤት ሆነው የሚቀርቡ ናቸው፡፡ እነዚህ የታሪክ
ባለቤት የሆኑ ገፀባህሪያት በደራሲው ምናብ የሚፈጠሩና ከገሀዱ አለም ሰዎች ጋር በአካልና በምግባር
የሚመሳሰሉ ሰዎች አልያም ሌሎች ፍጡራን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የምናብ አለም ፍጡራን የሰውን
አጠቃላይ ባህሪ የሚወክሉ ናቸው፡፡ ዳኛቸው ወርቁ እንደሚለው ”ባለታሪኮች የታሪኩ ባለቤት
እንደመሆናቸው በአብዛኛው ሰዎች ሲሆኑ እንስሳትና ግዑዝ ነገሮች እንደሚጨመሩ
ጠቁመዋል፡፡” / ዳኛቸው 324፣1977/
ከዚህ ተነስተን ገፀባህሪ ማለት በሰው አምሳል በፈጠራ ስራ ውስጥ ተቀርፀው የሚገኙ የታሪኩ ባለቤቶች
ናቸው ማለት እንችላለን፡፡ ከሳቴ ብርሃን ተሰማ በፃፉት የአማርኛ መዝገብ ቃላት ላይ “ገፀባህሪይ ማለት
በልቦለድ፣ በትያትር…. ድርሰት ውስጥ የሚገኝ ሰው ማለት ነው፡፡” /ካሰቴ ብርሃን፣1981/
በልቦለድ ውስጥ ያሉ ገፀባህሪያት ከሚኖራቸው የታሪክ ድርሻ ወይም በታሪክ ውስጥ ካላቸው ዘላቂነት
በመነሳት በሁለት እንከፍላቸዋለን፡፡ ዋና ገፀባህሪያት እና ንዑስ ገፀባህሪያት በማለት፡፡
ዋና ገፀባህሪ ታሪኩን በዋናነት የሚመለከተው፣ የልብወለዱ አጠቃላይ ሀሳብ በሱ ህይወት ዙሪያ
የሚያጠነጥን ከሆነ ዋና ገፀባህሪ አልያም ዋና ባለታሪክ ልንለው እንችላለን፡፡ እንዳዚህ አይነት ገፀባህሪያት
በልበወለድ ታሪክ ውስጥ ከመነሻ እሰከ መድረሻ ታሪኩን ይዘውት የሚዘልቁ ናቸው፡፡
ንዑስ ገፀባህሪያት የጠነከረ የባህሪ ውስብስብነት የማይታይባቸው የሚሳሉትም አንድ ተደጋጋሚ ልምድ
እንዲኖራቸው እና በቀላሉ እንዲታወቁ ተደርገው ነው፡፡ ንዑስ ገፀባህሪያት በታሪኩ ውስጥ በተከሰቱ
ቁጥር ወዲያው ሊለዩ የሚችሉ ናቸው፡፡

1
የኦጋዴን ድመቶች በይስማዕከ ወርቁ መጋቢት 21/2012

በኦጋዴን ድመቶች በሚለው ልቦለድ ውስጥ የዋና ገፀባህሪው “ዶ /ር ዲዲሞስ” አሳሳል እና አቀራረብ
በመጀመሪያ የኦጋዴን ድመቶች ከክቡር ድንጋይ ከሚለው መፅሀፍ ታሪክ የቀጠለ ልቦለድ ነው፡፡ በክቡር
ድንጋይ መፅሀፍ ላይ ታሪኩ ያለቀው ደ/ር ዲዲሞስ ከሚስቱ ጋር ተጣልቶ ልጆቹን ይዞ አዲስ ቤት ገዝቶ
መኖር ሲጀምር ነበር፡፡ ይህም በኦጋዴን ድመቶች ላይ እንደሚከተለው ቀርቧል፡
“እጅግ አፈቅራት የነበረችው ባለቤቴ ኤፍራታ፣ እጅግ በምድር ላይ ጠላቴ የነበረውን የቀድሞ
ጓደኛዬን አግብታ ጠበቀችኝ፡፡ ሞቷል ተብዬ ኖሯል፡፡ ሁለተኛ ገደለችኝ፡፡ ልጆቼ አጥብቄ
በምጠላው ሜንጦ በሚባል አጋሰስ ሰው እጅ ወድቀው ጠበቁኝ፡፡ አንገታቸው እንደ መቃ
መንምኖ፣ ራሳቸው እንደ ጅብ ጥላ ተንጠልጥሎ በውሻ ዓይኖቼ ተመለከተኳቸው፡፡ ሚስቴ ግን
ከባላንጣዬ ጋር አዲስ አበባን በአንድ እግሯ አቁማት ነበር፡፡ ለአሸሸ ገዳሜው፣ እድሜ ልካቸውን
የሚቀልባቸው ሀብቴን ከየባንኩ አውጥታ ቀርቅባለች፡፡ በራሴ መኪና በራሴ ቤት
እየተንፈላሰሰ፣ በዛ ላይ በራሴ አልጋ ላይ ሚስቴን እያፈሰ የጠበቀኝ ባላንጣዬ፣ የድሮ ጓደኛዬ
ነበር፡፡”
“…ዘመን ከሚባለው ባንክ ያስቀመጥኩት ጠቀም ያለ ሀብት ግን አልተነካም ነበር፡፡ እሱን
አውጥቼ ለሰው ልጅ የሚያስፈልጉት ነገሮች አደረኩ፡፡ ቆንጆ ቤት ገዝቼ ካስተካከልኩ በኋላ
ልጆቼን ይዤ ብቻዬን መኖር ጀመርኩ፡፡”

- ገፅ 55-57

ዶ/ር ዲዲሞስ ዶሬ የተወለደው ከ 59 ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ቀበና ወንዝ አካባቢ በሚገኝ መንደር
ነበር፡፡ አባቱ አለቃ ዶሬ የታወቁ እና የተከበሩ ሰው ነበሩ፡፡ አባቱ የበፊት የቅርስ ምርመራ ቡድን አባል
ስለነበሩ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ጥበቦች እያመጡ ለዲዲሞስ ያስተምሩት ነበር፡፡ ከነዚህ አንዱ አስማት
ነበር፡፡ ይህንም ያወቅኩት በመፅሀፉ ላይ እንደሚከተለው ስለተገለጸ ነው፡

“… አዲስ አበባ ነው የተወለድኩት፡፡ ከቀበና ወንዝ ማዶ በምትገኝ መንደር ውስጥ፡፡ ቀበና


ወንዝ እየዋኘሁ አደኩ፡፡ አሁን ሃምሳ ዘጠኝ ዓመት ሆኖኛ፡፡
አባቴ አለቃ ዶሬ የታወቁና የተከበሩ ሰው ነበሩ፡፡ ገና በልጅነቴ ባህላዊውን የኢትዮጵያን
ትምህርት አስጠንተውኛል፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመን የተቋቋመው የቅርስ ምርመራ
ቡድን አባል ስለነበሩ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ጥበቦች በየጓዳውና በየጎድጓዳው እየገቡ
አስሰዋል:: ያልዞሩበት ጥበብ አለበት የተባለ ሀገር የለም፡፡ ከፋርስ እስከ ባቢሎን፣ ከሺናሻ እስከ
ሱዳን ለጥበብ ዘምተዋል፡፡ ከጥንቷ ኑቢያ እስከ ግብፅ እየዞሩ ጥንታዊ ጥበቦችን ቃርመዋል፤
ሌሎች የናቁትን ጥበብ፡፡ ሌሎች እንደኋላቀርና እንደ ዘበት የሚያዩትን የአስማት ጥበብ
ሳይቀር ሰብስበዋል፡፡”

- ገፅ 53

ዶ/ር ዲዲሞስ ዶሬ ከኢትዮጵያ ታዋቂ ከሚባሉ አርኪዮሎጂስት አንዱ ነው፡፡ ከላይ እንዳልኩት ባህላዊ
ትምህርቱን ከቀሰመ በኋላ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ገባ፡፡ በታሪክ ዘርፍ ላይ ስለተሳበ በዘመናዊ ትምህርቱም
ታሪክ ማጥናት ፈለገ፡፡ በዚህም መሰረት አርኪዎሎጂን የመጀመሪያ ምርጫው አድርጎ በጀርመን ሀገር፣
በቀጣይም አንትሮፖሎጂን በፈረንሳይ ሀገር፣ እንዲሁም ፊሎሎጂን በእንግሊዝ ሀገር አጠና፡፡ በመጨረሻም
በሶሻል አንትሮፖሎጂ የዶክትሬት ዲግሪዩን አግኝቶ ብዙ የምርምር ስራዎችን ለመስራት ችሏል፡፡ ይህም
ከገፅ 53 ቀጠል አድርጎ በገፅ 54 ላይ እንደሚከተለው ተገልፅዋል፡፡

2
የኦጋዴን ድመቶች በይስማዕከ ወርቁ መጋቢት 21/2012

“… ለማንኛውም ታሪኬን ልቀጥልልሽ፡፡ ባህላዊውን ትምህርት በአባቴ እግር ስር ካጠናሁ


በኋላ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ገባሁ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሬ በጥንቱ እውቀት ላይ ስለተሳብኩ
በዘመናዊ ትምህርቴም ወደ ጥንቱ አለም ያጋደሉ ትምህርቶቼን የቀሰምኩት፡፡ አርኪዎሎጂን
በጀርመን ሀገር፣ አንትሮፖሎጂን በፈረንሳይ ሀገር፣ ፊሎሎጂን በእንግሊዝ ሀገር አጥንቻለሁ፡፡
በመጨረሻም በሶሻል አንትሮፖሎጂ የዶክትሬት ዲግሪዬን በመያዝ ብዙ የምርምር
ስራዎችን ሰርቻለሁ፡፡ ሁሉም ማለት ይቻላል፣ የጥንቱን አለም ምስጢር የሚመረምሩ
ናቸው፡፡”
- ገፅ 54
የውጪው ድርጅት የመረጠው ይህ ሁሉ ትምህርት ስላጠና ብቻ አይደለም፡፡ በስራዎቹ እውቅናም ነው፡፡
ከሀገር ውስጥ ስራዎቹ ውጪ በግብፅ ውስጥ የሰራቸው ስራዎች ታዋቂዎች ናቸው፡፡ የግብፅ ስራው
በቅንጭቡ እንደሚከተለው በመፅሀፉ ላይ ቀርቧል፡-

“ ቡናው የገለጠልኝ ይመስል የውጪው ድርጅት ሁነኛ ላለው ጥናቱ የጋበዘኝ በሁለት ዋና ዋና
ምክንያቶች እንደሆነ ተረዳሁ፡፡ አንደኛው በግብፅ በረሃ ውስጥ ያከናወንኩትና ዓለም አቀፍ
እውቅ ያስገኘልኝ ጥናት ይሆናል ስል ገመትኩ፡፡ ብዙ ምሁራን ያጣቀሱት ጥናት ነው፡፡ ጥናቱ
ብቻ ሳይሆን ፈታኝ በነበረው በረሃ ውስጥ የተከናወነ ምርምርም በመሆኑ፣ ድርጅቱ የበረሃ
ልምዴን ከግምት አስገብቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለተኛው ግን የሶሻል አንትሮፖሎጂ ሞያዬን
አጢኖ ሊሆን ይችላል የሚል ግምትም አጫረበኝ፡፡”

- ገፅ 46-47

የውጪው ድርጅት ባቀረበለት ጥያቄ መሰረትም ተስማምቶ በድርጅቱ ለመስራት ወደ ኦጋዴን መጣ፡፡ ዶ/ር
ዲዲሞስ ወደ ኦጋዴን ከመጣ በኋላ በሶማሊ ባንዳዎች ታፍኖ ይወሰዳል፡፡ ታፍኖ የተወሰደውም ብቻውን
አይደለም፤ ከአያን ጋር ነበር፡፡ እነሱን ለማምለጥም ትቶት የመጣውን የአስማት ታሪክ መጠቀም ነበረበት፡፡
በክቡር ድንጋይበሚለው መፅሀፍ ላይ ወደ ውሻ ተቀይሮ ብዙ ችግር ስለገጠመው ድጋሜ ወደ ውሻ
አልቀየርም በማለት አስማት ተጠቅሞ ከአያን ጋር ወደ ድመትነት ተቀይረው አመለጡ፡፡ ከአመለጡ በኋላም
በወደ ሰውነት የሚቀይራቸውን የአስማት መድብል ለማግኘት ሲባል ከኦጋዴን ወደ አዲስ አበባ
የሚመለሱበትን ታሪክ በሰፊ መልኩ መፅሀፉ ያጫውተናል፡፡ በመጨረሻም ይህን ሁሉ ታሪክ አብሮ
ያሳለፋበትን ባለ 39 ዓመቷን “አያንን” ያገባል፡፡ ታሪኩም በዚህ ይቋጫል፡፡

ማጠቃለያ
ገፀ ባህሪውን እና ታሪኩን እንዲህ ብዬ ከገለፅኩ መፅሀፉ አለባቸው ብዬ የማስባቸው ችግሮችን እገልፃለሁ፡፡
የመጀመሪያ ችግሩ እርግጠኛ የሆነ ዓመተ ምህረት አይሰጠንም፡፡ ታሪኩ የሚገለፀው በስንት ዓ.ም እንደሆነ
አናቅም፡፡ የምናቀው መቼት ቢኖር ታሪኩ ከኦጋዴን ጦርነት ማለትም ከ 1969 ዓ.ም በኋላ እንደነበር ብቻ
ነው፡፡ በዚህም ምክንያት መቼቱ ችግር እንዲኖርበት አድርጓል፡፡

3
የኦጋዴን ድመቶች በይስማዕከ ወርቁ መጋቢት 21/2012

ሌላው የመፅሀፉ ችግር ብዬ የማስበው የገፀ ባህሪያቱን መልክ በበቂ መልኩ አይገልፅም፡፡ በዚህም ምክንያት
የዶ/ር ዲዲሞስ ዶሬን የፊት ገፅታ ሆነ የሰውነት አቋም በጭንቅላታችን እንዳናስበው ያደርገናል፡፡
በአእምሮአችን የምናስበው የ 59 ዓመት ሽማግሌ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

You might also like