Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ቃለአብ መብራቱ ገ/እግዛብሄር አማርኛ የክፍል ስራ

ደራሲው በአዲስ አበባ ማደግን አስደሳችና መልካም አድርጎ ያቀረበባቸውን መንገዶች ተንትን?

ይህ መለያየት ሞት ነው የሚለው መጽሀፍ በ 2017 ለአንባብያን የተበረከተው በአለማየሁ ገላጋይ ሲሆን መቼቱ
ደግሞ አዲስ አበባ ላይ ነው። በምንባቡ ውስጥ ደራሲው በአዲስ አበባ ማደግን አስደሳች እና መልካም አድርጎ በብዙ
መንገዶች አቅርቦታል። በዋነኝነት አዲስ አበባ ማደጉ የጠቀመው አንደኛ ብሄርተኝነት እና ወገንተኝነትን ይዞ
አላደገም እና ኢትዮጵያዊ ነኝ ብቻ ብሎ ነው የሚያስበው። የምንባቡ ዋነኛ ጭብጡ የአዲስ አበባ ነዋሪ ዘረኛነትን
አያቅም እና የሚያድገው በብዙ ሰው እጅ ነው ማለትም የሁሉም የብሄር ብሄረሰቦች አስተዋጾ አለበት።ይህንን
ጭብጥ ለማሳየት ደራሲው ንጽጽር፣ ለዋጭ እና ከፊል ሙሉ ዘይቤዎችን በዋነኝነት ተጠቅሟል።

በምንባቡ መጀመርያ ላይ ተራኪው የአዲስ አበባን የመሬት ይዘት ወይም አቀማመጥ አጠር ባለች ሁኔታ
ይገልጽልናል። እንዲህ ሲልም አስቀምጦታል “አዲስ አበባ ደረቅ ደሴት ናት” ማለትም አዲስ አበባ ብቻዋን ምንም
አታመጣም እና የላትም እናም ጥገኝነቷ በዙርያዎቿ ባሉት ለምለም የሆኑ ሜዳዎች እና ተራራዎች ነው። ካለነሱ
ባዶ ነች ማለት ነው። በሌላ መልኩ ስናየው አዲስ አበባ ከተለያየ ቦታዎች የመጡ ሰዎችን በፍቅር ይዛ የምትገኝ
ከተማ ናት እናም እሷም ካለህዝቦቿ ህዝቦቿም ካለ እሷ መሄጃ የላቸውም። ደራሲው ይህንን አጉልቶ ለማሳየት
በጣም የብዙ ቦታዎችን ስም ጠቅሶልናል። ተራኪው ደግሞ የዚ ማህበረሰብ ተካፋይ በመሆኑ ትልቅ ደስታ
ይሰማዋል።

በመቀጠልም ደግሞ ደራሲው ስለ ዙርያዋ መናገር አቁሞ ስለ እራሷ አዲስ አበባ እና ስለ ነዋሪዎቿ ይተርክልናል።
የአዲስ አበባ ነዋሪ ወይ ደግሞ እሱ እንደሚለው “አዲስ አበቤ” ካለበት ቦታ መንቀሳቀስ አይፈልግም። ይህንንም
የምንመለከተው “ከአራት ኪሎ አልወጣሁም፣ ከካዛንቺስ አላለፍኩም’ በሚልበት ወቅት ነው። ይህን ብሎ ከጨረሰ
በኋላ ወደ ምንባቡ ዋና ጭብጥ ያመራል እሱም “ኢትዮጵያዊነት” ነው። በሱ አይን “ኢትዮጵያዊነት” ማለት ከቦታ
ቦታ መንቀሳቀስ ወይም ሰውን በዘር ከፋፍሎ ማናቆር ሳይሆን “ኢትዮጵያዊነት” ማለት የ “ ደም፣ የ “አጥንት” እና “
የአእምሮ” ጉዳይ ነው። ይህም የሚያሳይን “ኢትዮጵያዊነት” ለሱ እስትንፋሱ እና ከምንም በላይ እንደሚበልጥበት
ነው። ሰው ካለደም በህይወት ሊቆይ እንደማይችል ሁሉ እሱም ኢትዮጵያዊነቱን ጥሎ ሊኖር አይቻለውም።
ይህንንም ሊረዳ እና ሊማር የተቻለው እዛው አዲስ አበባ ውስጥ ጎረቤት እየተቀባበለ ስላሳደገው እና ጥልቅ የሆነ
ፍቅር ስላሳየው ነው። እንደዛ ሆኖ ስላደገ አይምሮ ውስጥ ምንም አይነት ክፋት፣ ጥላቻ እና አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ
ያማድረግ ዝንባሌ አይታይበትም።

ወደ ዋናው ጭብጥ ስናመራ ደራሲው አዲስ አበባ መወለዱን ሲጠራጠር እንመለከታለን ይህንንም የምናየው
“ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ አይደል?” በሚልበት ጊዜ ነው። ይህንንም ያደረገው የአንባቢውን ልብ በማንጠልጠል
ውዝግብ ሊፈጥርበት ፈልጎ ነው ምክንያቱም አስቀድሞ አስታውቆን ነበር ከአዲስ አበባ መሆኑን። በተጨማሪም
እሱም እንደማንኛውም የአዲስ አበባ ነዋሪ እግሩ እንጂ ህልሙ አልታሰረም። ይህም የሚያሳየው ምንም እንኳን
እነዚህ ቦታዎችን እግሩ ረግጦ ባያቅም ልቡ ስለነዚህ ቦታዎች ፍቅር አለውም ያስባልምም። “ክልል ቀርቶ የሀገር
ድንበር አይፈነቅለኝም” ሲል ደግሞ እሱ ግድ ያለው ስለ ኢትዮጵያ እንጂ ስለ ክልሎች ልዩነት አይደለም። እና ሁሉም
ሰው በሱ አይን እኩል ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ “የፍቅር እጄ በየአቅጣጫው እንደ ጨረር ይበተናል” ሲል እዚጋ
አነጻጻሪ ዘይቤ ተጠቅሟል ማለትም መጀመሪያ ጨረር እንደምናቀው በተለያየ አቅጣጫ ነው የሚጓዘው እና ይህ
የሚያሳየው ፍቅሩ ገደብ እንደሌለው እና ሁሉንም ሰው እንደሚያጠቃልል ነው። ሲቀጥል ደግሞ ጨረር በተለምዶ
አይን ላይ ካረፈ ያውራል ስለዚህ የእሱ ፍቅርም እንደዛው ካለምክንያት የታወረ ነው እና ሰውን የሚወደው ደግሞ
ከውስጡ ነው እንጂ ከላይ ከላይ ወይ ደግሞ በማስምሰል አይደለም።ይህንን ሁሉ ሊማር የቻለው እዛው አዲስ አበባ
ውስጥ በፍቅር በማደጉ ነው ምክንያቱም አዲስ አበባ ሁሉም ሰው ዘር ከዘር ሳይለያይባት የሚኖርባት ከተማ ናት
እንደሌሎቹ ክልሎች ወገንተኛነት በፍጹም አይታይባትም።

“እኛ” ሲል ለዋጭ ዘይቤ ተጠቅሟል ማለትም “እኛ” የሚለው ቃል የሚገልጽልን ኢትዮጵያኖችን ሲሆን
“ኢትዮጵያዊነት” ደግሞ ቦታ እና ጊዜ አይመርጥም። እሱ በተፈጥሮው ማንንም ሰው ከሰው አይለይም እናም
ከአዲስ አበባ ለሆነውም ቅድምያ አይሰጥም። ከየትም ና ኬትም ለ እሱ ያው አንድ ነህ። ለዚህ አስደሳች ማንነቱ
መንስኤ ሚሆነን በእናት እና በአባቱ እጅ ከማደጉ በተጨማሪ የጎረቤቶችም አስተዋጾ አለበት። ጎረቤቶቹ ደግሞ
ሁሉም ከአንድ ዘር አይደሉም ከተለያየ ስፍራ ነው የመጡት ማለትም ከትግራይ፣ ከአማራ፣ ከሀረሪ፣ እና
ከመሳሳሉት። በወላጆች እና በጎረቤታሞች መካከል ያለው ፍቅር ያስቀናል እና ስር የሰደደ ነው። ለምሳሌ ያህል እሱ
ቤት ሰላም ከሌለ ጎረቤቶች ናቸው መጥተው ሳይጠሩ ሰላም የሚያሰፍኑት እሱ ይቅርና የሚበሉት ምግብ ራሱ
ቃለአብ መብራቱ ገ/እግዛብሄር አማርኛ የክፍል ስራ

ከሌላቸው ጎረቤት አምጥቶ ይሰጣቸዋል። ታድያ ይህን ሁሉ ደግነት እና መተሳሳብ እያየ ያደገ ልጅ ዘረኛ ነው ለሰው
አያስብም ቢባል ዘበት ነው ደግሞ “ማን መርጦ ይወለዳል” ሲል እውነቱን ነው የተናገረው ምክንያቱም ማንም ሰው
ከዚህ ብሄር ነው መወለድ ነው ምፈልገው ስላለ ብቻ አይወለድም ስለዚህ እሱ ሁሉም ሰው ላይ ያለው አቋም ወጥ
ነው።

ሌላ ደግሞ በጎሮቤት መካከል ያለው ጥብቅ ቁርኘነት የምንመለከተው የጎሮቤት አባት “እኔን ግደል !” በሚልበት ጊዜ
ነው ይህ የሚያመላክተው የአዲስ አበባ ነዋሪ ከሱ ዘር ላልመጣ ሰው እንኳን አንገቱን አሳልፎ ይሰጣል እና ፍቅራቸው
ማብቅያ የለውም። ከእንደእዚህ አይነት አሳቢ እና አስደሳች ማህበረሰብ በመገኘቱ ኩራት ሊሰማው ይገባል።
የጎረቤቱ ማንነት እና ምንነት ለሱ ለውጥ የለውም ዋናው ሰው መሆኑ ብቻ ነው። ጎረቤታሞች ከፍቅር ሌላ
ሚረዳዱበት ነገር አላችው ለምሳሌ “እስክሪብቶ ገንፍሎብኝ አባዬ ከሰማ ይገድለኛል” ብሎ ለተጎራባች አባቱ ሲናገር
የሚያሳየው እስኪሪፕቶ መገንፈል ያን ያህል ትልቅ ነገር ሆኖ አይደለም ግን በተቃራኒው ይህ አረፍት ነገር የሚያሳየን
ጎረቤታሞች አስከፊ ላልሆነ ችግር እንኳን እንደሚረዳዱ ነው። ለእሱ ማደግ የሁሉም ብሄር ወዝ ነው የጠፋው።

ይህ የ አኗኗር ዘዴ ዘላቂ የሆነ አዎንታዊ ጫና ነው የፈጠረበት ይህም የሚታየው “ የተመላለሰው እንጀራ ህያው
መረብ ሰርቶ፤ ህይወቴ ለዝንታለሙ አጥምዶታል”። ይህ ለዋጭ ዘይቤ ነው የሚታየውም “መረብ” በሚለው ቃል
ላይ ሲሆን መረቡ የሚገልጽልን የደረሰበትን አዎንታዊ የሆነ የማህበረሰብ ጫና ነው እና ይህ ጫና መቼም ከህይወቱ
አይለየውም ምክንያቱም “ለዝንታልሙ አጥምዶታል”። እንጀራን የመሳሰሉ ነገሮች ደግሞ ጓደኝነትን እና
ወዳጅነትን ያጠብቃሉ ማለትም ብዙ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው በምግብ ሰአት የመጠራራት ባህሪ አለው። አንድ
ኪሎ በርበሬ በ“ቅመሱ” ስም ስንት ደጃፍ ታንኳኳለች ሲል ደግሞ ደግነት እና ቅንነታቸውን ነው የሚያሳየው እና
ሰው ለመርዳት ሲሉ ምንም እንደማይሰስቱ ነው በተጨማሪም ያላቸውን ተካፍለው ነው የሚመገቡት። ደራሲው
የራሱን ህይወት ከከተማው ጋር በማነጻጸር ያሳየናል። አዲስ አበባ በተራራዎች ስትከበብ የሱ ህይወት ደግሞ
በሚያስቡለትና በሚጨነቁለት ሰዎች ነው የተከበበው እና ምንም እንኳን አዲስ አበባ ራሷ “ደረቅ ደሴት” ብትሆንም
የሱ ህይወት ግን ደስታ እና ተድላ የሞላበት ነው ይህም ሊሆን የቻለው አብረዉት በሚኖሩት ማህበረሰቦች
አማካኝነት ነው። ኩራተኛ ኢትዮጵያዊ መሆኑን በምንባብ ውስጥ ደግሞ ደጋግም ይነግረናል። ለምሳሌ “እትብቴ
አንድ ጉድጓድ አጥቷል” ሲል ከፊል-ሙሉ ዘይቤ ተጠቅሟል እትብት የሚለው ቃል የሚወክልልን ኢትዮጵያዊነትን
ነው። እትብት ሁልግዜ የሚወድቀው አንድ ቦታ ላይ ብቻ ነው ግን የሱ በየቦታው ነው የተዘራው ማለትም ለሱ
ኢትዮፒያዊነት ማለት ሁለመናው ነው እና እራሱን በዘር አይከፋፍልም። የሚያውቀው አንዳች እውነት ቢኖር
ኢትዮጵያዊ መሆኑን ብቻ ነው። በመጀመርያም የደግነታቸውን ጥግ የምናየው በአግባቡ የማያቁትን ሰው ማለትም
“ጅግሶ በዳሶ” የሚባል ከበሮ መቺ ሲሰክር አምጥተው አልጋቸው ላይ ያስተኙታል እሱ ደሞ በተራው ጠዋት ሲነሳ
ከበሮ መቶ ባገኛት አነስተኛ ገንዘብ ህጻናቶች ልጆችን ይጋብዛል ምንም እንኳን መሀን ቢሆንም ኢትዮጵያዊ እስከሆኑ
ድረስ የሱም ልጆች ናቸው እዚህ ላይ አያዎ ይታያል ምክንያቱም የመካን ወላድ ሆኖ ቀርቧል። ስሙ ትንሽ የከተማ
አይመስልም ደራሲውም ይህንን ስም የተጠቀመው ማንም ሰው ከየትም ክፍለ ሀገር መጥቶ ሰላማዊ ኑሮ በኣዲስ
አበባ ላይ ማድረግ እንደሚችል ለማሳየት ነው።

ለመቋጨት ያህል ደራሲው ልጅነቱ በምን አይነት ማህበረስብ ውስጥ እንዳለፈ ወለል አድርጎ አስያቶናል እና እሱ
ያደገበት ማህበረሰብ በጣም ለሰው ተቆርቋሪ እና ሰውን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በመደብ እና በአጭሩ በማንኛውም
ረገድ አይከፋፍልም እና ልዩነትን አቻችለው ነው በሰላም በፍቅር እና በመተሳሰብ የሚኖሩት። ይህ ጥሩ የሆነ ድርጊት
በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አይምሮ ውስጥ ቢቀረጽ ከመናቆር የጸዳ ኑሮ ይኖረናል ይህን ደሞ በግልጽ ልንረዳ
እንችላለን ምንባቡን በማንበብ።

You might also like