የፈንቅል ውሸት ሲጋለጥ

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

‹‹ፈንቅል›› - ወዴት?

(አደይ ብዙ)

የዚህ ጽሁፍ ውልደት ከጥላቻ ስሜት የመነጨ አይደለም፡፡ ለትግራይ ህዝብ ካለኝ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ መጪው የትግራይ
የፖለቲካ መንገድ ቀና እንዲሆን ከመሻት ነው ጽሁፉን የጻፍሁት፡፡ አንድም የዓላማ ጽናት፣ ሁለትም ድርጅታዊ መዋቅር
የሌላቸው፤ ሆዳቸውን ብቻ ያስቀደሙ ሰዎች በሚያመጡት ጦስ ህዝቡ፣ በተለይም ወጣቱ እንዳይጎዳ ከማሰብም
ጭምር ይህንን መጠነኛ ጽሁፍ ላሰናዳ ችያለሁ፡፡ ጽሁፉን በትዕግስት ታነብቡት ዘንድ እጠይቃችኋለሁ፡፡

‹‹ፈንቅል›› አመጣጡ ከየት እንደሆነ ለመገመት ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፡፡ ምንም ውስጠ-ምስጢር የለውም፡፡
‹‹ፈንቅል›› - የትግራይ ‹‹ምናባዊው›› ርዕሰ-መስተዳድር፣ በአካል ግን አዲስ አበባ የተሸከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ ቢሮ
የሚያሞቀው ነቢዩ ስሑል ሚካኤል አዋልዶ፣ ከ‹‹ብልጽግና›› የሚያገኘውን ረብጣ ብር በስመ-‹‹የትግራይ ብልጽግና
ፓርቲ ጽ/ቤት›› በየሚዲያው ቀርበው ለሚናገሩት ሰዎቹ ፈሰስ በማድረግ ያቋቋመው ‹‹ንቅናቄ›› ነው፡፡እንደሌሎች
ህዝባዊ ንቅናቄዎች እዛው - ከህዝቡ ጋር ሆኖ ‹‹ትግል›› እንደማድረግ፣ አዲስ አበባ ላይ ሆነው ግን በገዢው ፓርቲ ልሳናት
እየቀረቡ ‹‹ብሶት››ን ማንቃረር የመምረጣቸው አጋጣሚ አንድ ነው፡፡ ከትግል ይልቅ ሆድን፣ ከፈተና ይልቅ ድሎትን
በማስቀደማቸው!

‹‹ፈንቅል›› ለትግራይ ህዝብ ሞትን አውጆ፣ እርሱን በምላሹ ለሚሰግረው ድርጅት ገባርነቱን ያሳዬው ‹‹ኢሳት››
የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በተወካዮቹ አማካይነት እየቀረበ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል በህዝቡ ላይ ፈጽሟል፡፡
ይኸውም፣ የትግራይ ህዝብ ጥንካሬ ለሚያሳምማቸው፣ መልፈስፈሱ ለሚያስደስታቸው ሃሳዊ ‹‹ኢትዮጵያውያን››
ጀርባቸውን አመቻችተው በመስጠት ቅጥረኛነታቸውን አስመስክረዋል፤ ለታሪክ አተላነት ዕጩ ሆነዋል፡፡

መቼም፣ እነየማነ ንጉሴን (ለእኔ ‹‹ኮሜዲያን›› ነው፡፡)፣ መለስ ብስራትን የምታውቋቸው ይመስለኛል፤ በየፌስቡኩ ፉከራ
የሚነዙት ሰዎች፡፡ እነርሱ ‹‹ምን ይዘው ነው የሚጮሁት›› ካላችሁ፣ ቅድም እንደተናገርሁት ‹‹ገንዘብ›› እላችኋለሁ፡፡
ወይም ‹‹የአፓርታማ ስጦታ!›› እላችኋለሁ፡፡ ይህም ሲተነተን፣ ለአብነት ያህል የማነ ንጉሴ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አዲስ
አበባ ተመልሶ፣ ለአስራ አምስት ቀናት ቀሳ ከወጣ (ከለይቶ ማቆያ ከወጣ) በኋላ ላረፈበት ‹‹ጁፒተር ሆቴል››
ከ‹‹ብልጽግና›› በተቆረሰ አበል ለሆዱ እና ለምኝታ ቀለብ እየተከፈለለት በመኖር ላይ ይገኛል፡፡ ሁለተኛ፣ አንድ ስሙን
የማልጠቅሰው፣ የ‹‹ፈንቅል›› አመራር የሆነ ግለሰብ አዲስ አበባ፣ ልዩ ስሙ ‹‹ሲ ኤም ሲ›› ተብሎ የሚጠራው ሰፈር
ከቀሪ የ‹‹ትግል›› አጋሮቹ ጋር እየኖረ ሲሆን፣ ከአንድ የትምህርት ተቋም ዲግሪ ተሰርቆ እንዲወጣለት ተደርጎ
ተሰጥቶታል፡፡ ማለትም ሳይማር የተማረ ‹‹ብጹዕ›› እንዲሆን ተገድዷል፡፡ እንግዲህ የዛሬው የ‹‹ብልጽግና›› ስርዓት
የህወሓት ባለስልጣናት የሃሰት ዲግሪ እና ዲፕሎም ‹‹አግኝተዋል!›› እያለ በሚያላዝንበት በዚህ ወቅት፣ አርሱም
ለምንደኞቹ የሃሰት የትምህርት መረጃ እያሰራ መስጠቱ፤ እርስ በራሱ የሚማታ ተቃርኖ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ሶስተኛ
የገብረ-ሚካኤል ተስፋይ፣ ጸጋይ ደስታ ኪስ የተሞላው እንደየማነ ከ‹‹ብልጽግና›› በሚቆረጥላቸው ገንዘብ ነው፡፡ እንዲህ
እያልን ብንዘረዝር፣ ገመናቸው ህልቆ-መሳፍርት ነው፤ ቢወራ አያልቅም፡፡

የትግል ስትራቴጂያቸው ደግሞ የተንተራሰው፣ የህዝብን የወረዳነት እና የዞንነት ጥያቄ ጠልፎ ለራስ የፕሮፖጋንዳ ፍጆት
በማዋል ላይ ነው፡፡ የ‹‹ፈንቅል›› የፌስቡክ ላይ ቡራ-ከረዩ ያመጣው አንገብጋቢ ጥያቄ ለማስመሰል ብዙ የውሸት ቅብ
በመጠቀምም ላይ ነው፡፡ ልዩ የፖለቲካም ሆነ የማህበረ-ኢኮሚያዊ ርዕዮት የላቸውም፡፡ ባዶ ፉከራ፣ ባዶ ጩኸት ነው
ውስጣቸውን የሞላው፡፡ የዚህ ተምኔታዊ ‹‹ንቅናቄ›› ሊቀ-መንበር ‹‹ኮሜዲያን›› የማነ ንጉሴ ለ‹‹አዲስ ሚዲያ
ኔትዎርክ›› በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ይህንን ባዶነታቸውን ለአደባባይ በግልጽ አስመልክቷል፡፡ የማነ በቃለ-መጠይቁ መሃል፣
የ‹‹ፈንቅል›› ዓላማ ህወሓትን ‹‹መፈንቀል›› ብቻ እንደሆነ በግልጽ ተናግሯል፡፡ ሆኖም ግን በ‹‹ተፈንቃዩ ድርጅት››
ምትክ፣ ማን እንደሚቀመጥ አልተናገረም፡፡ እርሱ ባይናገረውም፣ እኛ ‹‹ብልጽግና›› እንደሚሆን በሙሉ ልብ መናገር
እንችላለን፡፡ በጥቅሉ፣ የ‹‹ፈንቅል›› ዓላማ ወጣን በገንዘብ ደልሎ በመመልመል፣ የወጣቱን ጉልበት ለ‹‹ብልጽግና››
የስልጣን ጥማት ማገዶነት እንዲውል ማድረግ ነው፡፡ እና፣ ይህ ዓላማው የት ድረስ ያስሄደዋል?

መልሱ አንድ እና አንድ ነው!


እርሱም ወደ መጨንገፍ ወይንም ፈረንጆቹ እንደሚሉት ‹‹wither away›› ወደ ማድረግ ነው የሚያደርሳቸው፡፡
እንዳሰቡት ህወሓትን በቀላሉ ለመፈንቀል እንደማይቻላቸው ልባቸው ያውቀዋል፡፡ በያዙት መንገድ ዝንት-ዓለም
ቢጓዙም፣ መቼም ቢሆን እንደማይሳካላቸውም ተረድተዋል፡፡ ስለዚህ አሁን እያደረጉ ያሉት ነገር፣ ለ‹‹ብልጽግና›› ዱላ
ማቀበል - አቀብሎም ዝም ማለት - በዝምታም ሆድን መሙላት ነው፡፡ ‹‹የፌዴራሉ መንግስት በገንዘብም ይሁን በሞራል
ይደግፈን!›› እያሉ እያለቀሱ መኖር ነው፡፡ የአዙሪት ጨዋታ!

You might also like