Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የኪነጥበብ እና የልዩ ዝግጅት ማስተባበሪያ ድርጀት በጋምቤላ ከተማ ለማቋቋም የተዘጋጀ ማጣቀሻ

ሰነድ

ለባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቀረበ

መስከረም፡2012 ዓ.ም

ጋምቤላ፤ኢትዮጵያ

መግቢያ

ኪነ ጥበብ ለአንድ ማህበረሰብ ባህላዊ፡የኢኮኖሚ፡ማሀበራዊና ፖለቲካዊ እድገትና ንቃተ ህሊና ለማተጋት


የሚጫዎተው ሚና በምንም የማይተካ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ እሰካሁን በክልላችን ያሉትን እምቅ የባህል ሃብቶች አንቅቶና በሀገር አቀፍም ይሁን
በሃገራችን ደረጃ እንዲሁም በክልሉ ወደ መድረክ በማውጣት በየሚዲያውና በሀገራችን ውስጥ ባሉ
ባለሙያዎች እውቅናና ትኩረት እንዲያገኙ ከማድረግ አንፃርና በክልሉ ውስጥ የተሰጠው የትኩረት
ውስንነትን ለማካካስ በጉልህ በተደራጀ እወቀት ፤ክህሎት እና ባለን አቅም ፋይናንስ በማደረግ
የክልላችን ብሔር ብሔረሰብ ወጣቶች ባህልና ወጋቸውን እንዲጠብቁ፡ እንዲየስተዋውቁ፡ከሌሎች
የሀገራችን ታላለቅ የዘረፉ ባለሙያዎች የመድረክ ልምድ እንዲያገኙ እድል በማመቻቸት እና ዘረፉ
በኢኮኖሚ በኩል ያላውን የስራ ዕድል ፈጠራና በህብረተሰቡ ከመጠጥና ከጫት መዝናኛ በሱስ ተገዥ
የሆነውን አማራጭ መዘናኛ እድል በመፍጠር ቁምነገር እያሰተማሩ የመንፈስ እረካታ በክልሉ
ወጣቶች ለማሥረፅ ይህ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

የፕሮጀክቱ ራዕይ

በክልላችን ስመጥር ፡ የማስታዎቂያ ፤ የኪነ-ጥበብ ማዕከል በመሆን በ 2015 ዓ.ም ከሌሎች የዘርፉ
ሀገር አቀፍ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ የሆነ ተቋም ተፈጥሮ ና የክልሉን ገፅታ ተገንብቶ ማየት፡፡

የፕሮጀክቱ ተልኮዎች

 የተለያዪ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን ቲያትረሮችን፡ሲኒማዎችን፡ፊስቲባሎችን፡ የስዕል ውድድሮችን


ማዘጋጀት
 የተለያዩ መንግስታዊና ህዝባዊ በዕላትን የሚያደመቁ የአደባባይ ትይንቶችን ማዘጋጀት
 በሀይማኖታዊ በዕላት ወቅት ባህልንና ሄማኖትን መሰረት ባደረገ መልኩ የስነ-ሠርዓት
ማድመቂያ ክንዋኔወቸን ማዘጋጀት
 የሙዚቃ ባንዶቸን ፡የባህል ኪነት አባላትን በመደገፍና በማቀናጀት ል ልዩ ዝግጅቶችን
ማስተባበር

የፕሮጀክቱ ግቦች
 የህፃናት ፌስቲባሎችን ማዘጋጀት በዓመት 4 አራት ጊዜ
 የመድረክ ቲያትሮችን ለክልሉ ማሀበረሰብ በጋመቤላ ከተማ ለዕይታ ማቀረብ በዓመት 2 ጊዜ
 የሥዕል እና ቅርፃቅርፅ በጋመቤላ ከተማ በዐውቅ ሰዓሊዎች እንዲቀርቡ በዓመት 1 ጊዜ
 የተመረጡ ሐገራዊና ሀይማኖታዊ ባዕላተን ምክንያት በማድረግ የሚዲያ ተቋማትን በመጋበዝ
በክልላችን ከሚገኙ ህዛባዊ ተቋማት ጋር የመዘናኛ ፕሮግራም ማዘጋጀት በዓመት 2 ጊዜ፡፡
 የክልሉን ገፅታ ሊገነቡ የሚችል የ 15 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም ማዘጋጀትና በሚኔስቲሩና በክልሉ
ባህላና ቱሪዝም ደህረገ ፅና እንዲለጠፍ ማስቻል፡፡
 የሴቶችን ጥቃትና የኤች አይ ቪ ኤዲስን መከላከያ ዘዴዎች ማንቂያ የመዝናኛ ፕሮግራም
ማዘጋጀት በዓመት 2 ጊዜ፡፡
 የስነ ግጥምና፡ ዲስኩር ወይም የወግ መድረኮችን በተዋቂና ተፅኖ ፈጣሪ ሰዎች ተጋባዥነት
ማዘጋጀት በዓመት 4 ጊዜ፡፡

የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካለት


 የክልሉ ባህልና ቱሪዝመ ቢሮ
 የክልሉ መንግሰት ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ቢሮ
 የክልሉ አልሚ ኢንቨስተሮች
 ሆቴሎች
 ሌሎች ባለሀፍቶች
 የክልሉ የኪነትና ባህል ማህበራት
 የክልሉ ንግድና ዘረፍ ማህበራት ምክር ቤት

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች

 የክልሉ ባህልና ቱሪዝመ ቢሮ


 የክልሉ መንግሰት ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ቢሮ
 የክልሉ አልሚ ኢንቨስተሮች
 የሆቴሎችና ሌሎች ባለሀፍቶች
 የክልሉ የኪነትና ባህል ማህበራት አባሎች
 በግል በፕሮጀክቱ ማናጀር፡፡

You might also like