Professional Documents
Culture Documents
Amharic G-1 Chap.1
Amharic G-1 Chap.1
በዚህ መጽሐፍ ሃያ ስምንት ምዕራፎችን የያዘ ሲሆን አስራ አራት ምንባቦች፣ ተረቶችና
ግጥሞችም ተካተዋል፡፡ ምንባቦች ከተማሪዎች ዕድሜና ልምድ ጋር እንዲ መጣጠኑና
ክሂሎቻችውን እንዲያሳድጉ ሆነው ተሰናድተዋል፡፡ ተከታታይነት እንዲኖራቸውም የተቻለውን
ሁሉ ጥረት ተደርጓል፡፡ ከዚህም በላይ ተማሪዎችን የሚስቡ እንዲሆኑ ተሞክሯ፡፡ ተማሪዎች
አስራ አራቱ ምንባቦች ላይ ብቻ ሳይገደቡ ሌሎች ተመጣጣኝ የሆኑ ጽሑፎችን እንዲያነቡ
ይገድፋቸዋል የሚል እምነት አለን፡፡ ከዚህ በላይ የማንበብ ችሎታ፣ ፍጥነትና ልምድ
እንዲያዳብሩም ይጠበቃል፡፡
ክፍል አንድ
የፊደል ገበታ
ፊደል የጽህፈትና የንባብ መጀመሪያ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውንም ጽሑፍ ለማንበብና ለመፃፍ
ፊደላትን ማወቅ ይጠይቃል፡፡
ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ
ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ
ኘ ኙ ኚ ኛ ኜ ኝ ኞ
ኀ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ
ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ
ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ
የ ዮ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ
ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ
ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ
ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ
ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ
ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ
ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ
ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ
ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ
በአማርኛ ፊደል ገበታ ላይ የሚገኙ ፊደላት እግር አልባ፣ ባለአንድ እግር፣ ባለ ሁለት እግር
እና ባለ ሶስት እግር ተብለው ሊጠኑ ይችላሉ፡፡
ሀ ዐ
መ ወ
ሠ ፀ
ረ ፈ
ተ ኀ ነ ገ
ቸ የ ኘ ፐ
መልመጃ አንድ
ሰ ዘ
ሸ ዠ
በ ደ
አ ጀ
ከ ጸ
ኸ ጰ
ቨ
መልመጃ 2(ሁለት)
ሁሉም የአማርኛ ፊደላት ሰባት ሰባት ቤተሰቦች አሏቸው፡፡ ሰባቱን የፊደላቱ ቤተሰቦች
የየራሳቸው መጠሪያ ስሞች አሏቸው፡፡
የመጀመሪያዎቹ = ግእዝ
የሁለተኛዎቹ = ካኢብ
ሦስተኛዎቹ = ሣልስ
አራተኛዎቹ = ራብዕ
አምስተኛዎቹ = ሃምስ
ስድሰተኛዎቹ = ሣድስ
ሰባተኛዎቹ = ሳብዕ ይባላሉ፡፡
ለምሳሌ፡-
ሀ = ግዕዝ
ሁ = ካኢብ
ሂ = ሣልስ
ሃ = ራብዕ
ሄ = ሃምስ
ህ = ሳድስ
ሆ = ሳብዕ ማለት ነው፡፡
፪ ቃላት መመስረት
ሀ. በእግር አልባ ፊደላት ቃላት መመስረት
እግር አልባ ፊደላትን በቃሉ መጀመሪያ ላይ መጠቀም ቃላት እንመሠርታለን፡፡
ለምሣሌ
መሰላል ፈረስ
ወንዝ ዐይን
ፀሐይ ሀገር
የተመሰረተባቸው ፊደላት ቡሉ እግር አልባ ፊደላት ናቸው፡፡
ለ. ለባለ አንድ እግር ፊደላት ቃላት መመስረት
ባለ አንድ እግር ፊደላትን የቃሉ መጀመሪያ ላይ በመጠቀም በርካታ ቃላትን
መመስረት ቻላል፡፡
ለምሳሌ፡-
ተማሪ ነብር ቀበሮ
ገመድ ቸርነት የኛ
መልመጃ አንድ
1. በሚከተሉት ቃላት ውስጥ የሚገኙትን እግር አልባ ፊደላት አስምሩባቸው፡፡
ሀ. ወጣት ሠ. ፈሳሽ
ለ. ፀጉር ረ. መኝታ
ሐ. ረጅም ሰ. ዐዞ
መ.ሠማይ ሸ. ሀሰት
2. በሚከተሉት ባለ አንድ እግር ፊደላት ቃላት መስርቱ፡፡
ሀ. ተ _______
ለ. ገ _______
ሐ. ቀ _______
መ. ገ _______
፫. በባለ ሁለት እግር ፊደላት ቃላት መመስረት
ለምሳሌ፡-
ሰው ጀንበር
ሸሚዝ ዘመድ
አበባ በር
ከበሮ ደጀን የመሣሠሉት
ከላይ በተዘረዘሩት ቃለት ውስጥ መጀመሪያ ፊደላቱ በሙሉ ባለ ሁለት እግር
ናቸው፡፡
ተግባር
ተማሪዎች እናንተም ከላይ በቀረበው ምሳሌ መሰረት በባለ ሁለት እግር ፊደላት
በርካታ ቃላት መስርቱ፡፡ስትጨርሱም ለመምህራችሁ አንብቡላቸው፡፡
፬. በባለ ሦስት እግር ፊዳላት ቃላት መመስረት
ለምሳሌ ሐብል
ጨጨብሳ
ጠርሙስ
ተማሪዎች በምሳሌው መሰረት በባለሦስት እግር ፊደላት ቢያንስ ሁለት ሁለት ቃላት
መሰርቱ፡፡
ሀ. _______
ለ. _______
ሐ. _______
መ. _______