Professional Documents
Culture Documents
ወዴት ነህ
ወዴት ነህ
ወዴት ነህ
መልክአ ሕማማት ማለት ስለ ጌታችን መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሕማም፥ መከራ፥ ስቃይ፥
የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን፤ ደራሲው ታላቁ ሊቅና የደብረ ባሕርይ ጋሥጫ
መምህር #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_ ነው፡፡
መልክአ ሕማማት በባለ 3 ት መስመር አርኬ የተደረሰ ግጥማዊ ድርሰት ሲሆን፤
የተደረሰውም በ 7 ቱ የጸሎት ጊዜያት አንጻር በመሆኑ ‹‹#ጸሎት_ዘሰባዐቱ_ጊዜያት›› በሚል
መጠሪያም ይጠራል፡፡
የእያንዳንዱ ጊዜ ድርሰትም በዋነኛነት 3 ት ክፍሎችን የያዘ ነው።
እነርሱም፤ 1 ኛ) ስብሐተ እግዝእትነ ማርያም /የእመቤታችን ምስጋና/
2 ኛ) ስበሐተ ኢየሱስ ክርስቶስ /የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና/
3 ኛ) ስብሐተ ሥሉስ ቅዱስ /የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና/
በ 7 ቱ ጊዜያት ጸሎት ማድረስ እንደሚገባን ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 118 ላይ ‹‹ሰባት ጊዜ
በቀን አመሰግንሃለሁ ይላል››፤ አባቶቻችን ሐዋርያትም ይህንኑ ደንግገዋል፡፡ /ዲድስቅልያ
37፣ ቀሌምንጦስ 1 ና 7፣ አቡሊዲስ 25 ኛና 27 ኛ፣ ባስልዮስ 28 ኛ አንቀጽ፣ ፍትሐ ነገሥት
ገጽ 21/፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መልክአ ሕማማትን ሲደርስም በ 7 ቱ የጸሎት ጊዜያት
የተፈጸሙትን ድጊቶች ከ 3 ቱ የየጊዜያቱ የድርሰቱ ክፍሎች ምስጋና (የማርያም፣ የጌታ፣
የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና) ጋር እያመሠጠረና እያራቀቀ፥ እያስዋበና ምሥጢር እያመጣ፤
እንደ ወርቅ እያንከባለለ፥ እንደ ሸማ እየጠቀለለ፥ በግጥም እያስጌጠ፥ በቃላት እየሰደረ፥
በዜማ እያሸበረቀ፥ መንፈስን እየመሰጠ፤ ነው የደረሰው፡፡
7. #የ 7 ቱ_የጸሎት_ጊዜያት_የሚባሉትም
8. ፬ቱ #ስግደታት
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ
ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ
ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣
በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ
የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ። በዚህ
ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና
ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር
ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም
በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት
ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦
የሰሙነ ሕማማት ሥርዓቶች
የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች;-
1. እሑድ ፦ የሰሞነ ሕማማት የመጀመሪያው ቀን ሆሣዕና ይባላል። ትርጉሙም ‹‹እባክህ አሁን አድን
አንድም መድኃኒት›› ማለት ነው፡፡
2. ሰኞ
ሀ. መርገመ በለስ የተፈጸመበት = በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ
ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም
ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ
ይባላል።
ለ.አንጽሖተ ቤተ መቅደስ = ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና
የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተ መቅደስ ገርፎ
አስወጥቷቸዋልና።
3. ማክሰኞ
ሀ. የጥያቄ ቀን = ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ
ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥
፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።
ለ. የትምህርት ቀን= በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን
ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።
4. ረቡዕ
ሀ. ምክረ አይሁድ = ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው
የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል
የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት
ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው
ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።
ለ. የመልካም መዓዛ ቀን = ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ
ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው
እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯
የመዓዛ ቀን ይባላል።
ሐ. የእንባ ቀን= ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች
በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።
5. ሐሙስ
ሀ. ጸሎተ ሐሙስ = ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ
ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም
ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።
ለ. የምስጢር ቀን = ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ
ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።
ሐ. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ= መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም
ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።
መ. የነጻነት ሐሙስ = ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ
ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
6. ዓርብ
ሀ. የስቅለት ዓርብ= ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ
በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።
ለ. መልካሙ ዓርብ= ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት
የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ
ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
7. ቅዳሜ
ሀ. ቀዳም ስዑር፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ
ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
ለ. ለምለም ቅዳሜ፦ ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም
ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ
ያስሩታል።
ሐ. ቅዱስ ቅዳሜ፦ ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት
ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ
ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን
ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።
እንበለ ፦ ደዌ ወህማም እንበለ ጻዕር(ጻማ) ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሃነ ያብጽሐክሙ
እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም አሜን።
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው፡- በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ
ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡
የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
ኪርያላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ»
ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል
አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም
ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
እብኖዲ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ
ሆይ ማረን» ማለቱ ነው።
ታኦስ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ
ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
ማስያስ፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም
«መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው።
ትስቡጣ፦ «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው።
አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ
መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ
-ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ
በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
ይቆየን….
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ
ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን
ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን
የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ
የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን
ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡
ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን
ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ
የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ
ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ
ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ
መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
ምንጭ፡-
ስምዐ ተዋሕዶ (ልዩ ዕትም ዘሰሙነ ሕማማት)
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ ያስተምራል፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን
እየተናገረች ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለች!!
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አያናውጧትም
ቤተክርስቲያን አ..ት..ታ..ደ..ስ..ም! ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ
ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ
ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር) ቤተክርስቲያን.... መሰረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው
ሙሽራዋ መስቀል ላይ የሞተው ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘላለም አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም! •••
እንበለ ደዌ ወሕማም፥ እንበለ ጻማ ወድካም፥ ያብፀሓነ አመ ከመ ዮም። በፀሎታችሁ አስቡኝ
አትርሱኝ።
ቅዳሜ_ቀዳም_ሥዑር_ይባላል፡-
በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው
ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን
አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡
ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን
መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡
በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ
መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
ለምለም_ቅዳሜ፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም
ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል
/ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ
በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን
ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም
በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ
ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር
የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ
የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት
ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ
ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡
ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ
በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው
በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም
ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ይባላል። ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።
አርያም ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ ትፍሥሕት
እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ። ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ
ወለመንፈስ ቅዱስ ይገብሩ በዓለ ሰማያት ይገብሩ በዓለ ደመናት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ
ክርስቶስ።አንገርጋሪ ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታንቀደሳ ወአክበራ
እምኲሎን መዋዕል አልዓላ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን። አመላለስ አማን በአማን ተንሥአ አማን
በአማን ተንሥአ እምነ ሙታን ወረብ ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን
መዋዕል እስመ ለዓለም ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ። አመላለስ
ትንሣኤከ ለእለ አመነ ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ የኪዳን ሰላም
ይዘመማል ይመረገዳል። የኪዳን ሰላም ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ
ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ ሰአሊ በእንቲአነ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ ያስተርኢ
ኂሮቶ ላዕሌነ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ። አመላለስ ሠርዓ ለነ ሰንበት
ለዕረፍተ ዚአነ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ መዝሙር ትትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር ወይንፍሑ
ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይበውኡ አድባር ወአውግር ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ
በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። ሰላም ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ
ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት
ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት። እንኳን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
ፋሲካ_ፋሲካ_ፋሲካ፤ ተዝካረ_ትንሣኤሁ_ለክርስቶስ፡፡ ትንሣኤ_ትርጉም_በዓሉና_አከባበሩ_
«ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ
ይሆናል፡፡ «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን
ያመለክታል፡፡ «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል
አለው፡፡
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ፥ ሰይጣንን አሰረው፥ አዳምን ነፃ አወጣ፥ ከእንግዲህ ወዲህ
ሠላም ደስታ ሆነ አሜን።
ከትንሳዔ እሁድ በኋላ ያሉት እለታት ስያሜ ፦
1. ሰኞ ማዕዶት ይባላል፦ ማዕዶት ማለት መሻገር ፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ እለት በፋሲካችን
በክሮስቶስ ትንሳዔ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሀን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል
ወደ ገነት፣ ከአሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
2. ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፦ በዚህ እለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ ጌታዬና አምላኬ ብሎ
መመስከሩ ይዘከራል፡፡ (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)
3. ረቡዕ አልአዛር ይባላል፦ በዚህ እለት ትንሳዔ እና ህይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን
ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን። ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ የመቃብርን
ስርዐት ያጠፋ ትንሳዔ በድልም ያደረገ ንጉስ መሆኑን እንመሰክራለን።
4. ሀሙስ አዳመ ሀሙስ ይባላል፦ በዚህ እለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን
እንደተፈፀመ አዳምና ልጆቹ ነፃ እንደወጣን እናሶባለን፡፡
5. አርብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይባላል፦ በዚህ እለት ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትሳዔ
ስለመመስረቷ ይሰበካል። ክርስቶስ ስለ እርሷ እራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንፅቶ
በትንሳዔው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል። ቤተ ክርስቲያን ስንል ህንፃውን ሳይሆን
አማኞችን ነው ክርስቶስ ለህንፃው አልሞተምና፡፡
6. ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ይባላል፦ በዚህ እለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ
ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውን እና ትንሳኤውንም ቀድመው
ማየታቸው ይሰበካል፡፡
7. እሁድ ዳግም ትንሳዔ ይባላል፦ በዚህ እለት ክርስቶስ ለሶስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ
ሠላምን መስበኩ እና ስልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
"በቀናች ሃይማኖታችን እንጸናና እንጠነክር ዘንድ የአባቶቻችንን ትምህትና ተግሳፅ እናስተውል፤ የእለት
እለት መርሃችን ይሆኑን ዘንድም እንተግብራቸው፡፡"
ብሂለ አበው
☞ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ› /አባ
እንጦንስ/
☞‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል››
/ቅዱስ አትናቴዎስ/
☞ ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ
ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ
ነደደ ይኖራል›› /ቅዱስ ሚናስ/
☞‹‹በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍረዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና›› /ታላቁ አባ
መቃርስ/
☞ ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
/ቅዱስ አርሳንዮስ/
☞ ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ
ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል›› /ቅዱስ እንድርያስ/
☞ ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ
መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/
☞‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››
/ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
☞ ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ
የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
☞‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ
አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር›› /ቅዱስ ይስሀቅ
ሶርያዊ/
☞‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን
የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል›› /ቅዱስ እንጦስ/ የአባቶቻችን ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር
ይሁን::
ነገር ግን አንቺ ፍጹም የኾነውን የባሕርይ አምላክ እግር፣ ራስ እና መላ አካል ይዘሻልና፤ ሰማይ ታላቅ የኾነ
ቢኾንም ግን ያንቺ አቻ አይኾንም “ሰማይ ዙፋኔ ነው” ተብሎ ተጽፏልና (ኢሳ 66፡1)፤ አንቺ ደግሞ
የአምላክ ማደሪያ ነሽ፤ መላእክት እና የመላእክት አለቆች ታላቅ ናቸው ብልም አንቺ ከኹሉም ታላቅነት
በላይ ነሽ፤ ይኸውም መላእክት እና ሊቃነ መላእክት ባንቺ ማሕፀን ላደረው ለርሱ በረአድ የሚያገለግሉ
በመኾናቸው በፊቱ መናገር የማይችሉትን አንቺ በነጻነት ታናግሪዋለሽ፡፡ ኪሩቤልን ታላቅ ናቸው ብንልም
አንቺ ከነርሱ ታላቅነት በላይ ነሽ፤ ኪሩቤል የእግዚአብሔርን ዙፋን ይሸከማሉ (መዝ 80፡1፤ 99፡1)፤ አንቺ
ግን እግዚአብሔርን በእጅሽ ያዝሽው፤ ሱራፌልንም ታላቅ ናቸው ብልም አንቺ ከነርሱ ታላቅነት በላይ
ታላቅ ነሽ፤ ሱራፌል በክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ (ኢሳ 6፡2)፤ ፍጹም የኾነውን ጌትነቱን ማየት
አይችሉም አንቺ ግን ፊቱን እያየሽ እና እየዳሰስሽ ጡትን በከበረ አፉ ውስጥ አጥብተሻልና ከነርሱ
ትልቂያለሽ፡፡
But you carry within you the feet, the head, and the entire body of the perfect God. If I
say that heaven is exalted, yet it does not equal you, for it is written: “Heaven is my
throne” (ibid.), while you are God’s place of repose. If I say that the angels and
archangels are great—but you are greater than them all, for the angels and archangels
serve with trembling the One who dwells in your womb, and they dare not speak in his
presence, while you speak to him freely. If we say that the cherubim are great, you are
greater than they, for the cherubim carry the throne of God (cf. Ps 80:1; 99:1), while you
hold God in your hands. If we say that the seraphim are great, you are greater than them
all, for the seraphim cover their faces with their wings (cf. Is 6:2), unable to look upon
the perfect glory, while you not only gaze upon his face but caress it and offer your
breasts to his holy mouth….
ሔዋን የሙታን እናት ናት “ኹሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲኹ ኹሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን
ይኾናሉና” (1 ቆሮ 15፡22) እንደተባለ፤ ሔዋን ከዛፍ ፍሬ ወስዳ ባሏ ከርሷ ጋር እንዲበላ አድርጋለች፤
በዚኽ ምክንያት እግዚአብሔር “ከዚኽ በበላችኊ ጊዜ ትሞታላችኊ” ካላቸው ዛፍ በሉ (ዘፍ 2፡17)፤
ሔዋን ፍሬውን ወስዳ የተወሰነውን በልታ የተወሰነውን ለባሏ ሰጠችው፤ ርሱም በላው ሞተም፡፡ አንቺ
ብልኅ ድንግል ሆይ በአንቺ ግን የእግዚአብሔር ልጅ የኾነው የሕይወት ዛፍ ዐደረ፤ በእውነትም አካሉን
ሰጥቶናል እኛም ከርሱ በልተናል፤ ሕይወት ለኹሉም እንዲኽ ተሰጠ፤ ባንቺ በተወደደው ልጅሽ
በእግዚአብሔርነቱ ምሕረት ኹሉም ወደ ምሕረት መጣ፤ በዚኽም ምክንያት ነው መንፈስሽ በአምላክሽ
በመድኀኒትሽ ሐሤት ያደረገው"
As for Eve, she is the mother of the dead, “for as in Adam all die, even so in Christ shall
all be made alive” (1 Cor 15:22). Eve took from the tree and made her husband eat of it
along with her. And so they ate of that tree of which God had told them: “The day you
eat of it, you shall die” (Gen 2:17). Eve took from it, ate some of it, and gave some to her
husband with her. He ate of it, and he died. In you, instead, O wise Virgin, dwells the Son
of God: he, that is, who is the tree of life. Truly he has given us his body, and we have
eaten of it. That is how life came to all, and all have come to life by the mercy of God,
your beloved Son. That is why your spirit is full of joy in God your Savior!
St. Athanasius, Fourth Century Homily of the Papyrus of Turin, ed. T. Lefort, in Le
Muséon 71 (1958): 216-217 .
ምንጭ: ክብረ ክህነት [ዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ] ፠((የንስሐ አባት መያዝ ለምን ያስፈልጋል???))፠
============================
ጌታችን " በወንጌል በቀን የሚሄድ ሰው አይሰናከልም የዚህን አለም ብርሃን ያያልና በጨለማ
የሚሄድ ግን ይሰናከላል!!” ብሎ ተናግል:: የዚህ ቃል ትርጉም አንድም በምክረ ካህን በ ፈቃደ ካህን
የሚኖር ሰው ነፍሱ ከሃጢአት እንደምትጠበቅ ያስረዳል፡፡ የዚህ አለም ብርሃን የተባሉት ጌታችን
“እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ” ያላቸው ካህናት ሲሆኑ "በቀን የሚሄድ" የተባለው ደግሞ በምክረ
ካህን የሚኖር ሰው ነው፡፡
በወንጌል “ ለወይን ስፍራዉ ሰራተኞችን ይቀጥር ዘንድ በማለዳ ወጣ በአስራ አንድ ሰአትም
ቀጠረ” የሚለዉ ምሳሌ፡ ማለዳ በተባለ የልጅነት እድሜ ላይ የሚጠብቅ የሚኮተኩት መምህረ
ንስሃ መያዝ እንደሚያስፈልግ ያሳያል፡፡ ዕድሜያችን ለሀጢአት በደረሰችበት ቅፅበት ለንስሃም(ለ
ኑዛዜም) ትደርሳለችና፡፡
በሲራክ 6-6 ላይ “ብዙ ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን
የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን፡፡” የሚለው ቃል ምእምናን ስለ ሐይማኖትና ምግባር
የሚያስተምሯቸው ብዙ ካህናት ሊኖሩዋቸው ቢችሉም ከብዙዎች አንዱ ግን ንስሃቸውን
የሚናዘዙለት መምህረ ንስሃ ሊሆናቸው እንደሚገባ ያጠይቃል፡፡
አዳም በገነት ለሰባት አመታት ከቆየ በሁዋላ በዲያቢሎስ ተፈትኖ እንደወደቀ፡
በሃጢያት መፈተንና መዉደቅ ለሰው የሚፀናበት ዕድሜ ከሰባት አመት ጀምሮ
ስለሆነ ወደ ንስሃ አባት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
በምክረ ካህን መኖር ራሱ ትልቅ መንፈሳዊ ማእረግ ነው የአዲስ ኪዳን
ክርስቲያኖች ከብሉይ ኪዳን ሰዎች የሚከብሩትን ያህል በምክረ ካህን የሚኖሩ ምእምናን
ከአማኒያን በላይ የከበሩ ናቸዉ፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ 12 አመቱ ከመምህራን ጋር መገናኘቱ እኛም
ከልጅነታችን ጀምሮ ከ መምህራን አባቶች ጋር እነድንገናኝ አብነት ይሆን ዘንድ
ነዉ (ማቴ 20-2) ይቀጥላል፡፡
#ሀጢያትን_መናዘዝ_ለምን_አስፈለገ??
-----------------------------------
ሀጢያትን ለእግዚአብሄር በካህን በኩል መናዘዝ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለዉ
ጠቃሚ ጉዳይ ነዉ፡፡ እግዚአብሄር አዳም በበደለ ጊዜ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ?”
ብሎ የጠየቀዉ አዳም እንዲናዘዝ ስለፈለገ እንጂ አዳም ያደረገዉን ሳያዉቅ ቀርቶ አልነበረም፡፡
“እምቅድመ ይፍጥሮ ለአዳም የአምር ግብሮ” ”አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ስራዉን ያዉቃል” እንዲል፡፡
አዳምም እግዚአብሄር በጠየቀዉ ጊዜ ”ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ”
በማለት ተናዝዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች ሰዎች ሀጢያታቸዉን ይናዘዙ እንደነበር
በመፅሀፍ ቅዱስ ተገልጿል፡፡ ሐዋ 19-18 ፡ማቴ 3 5-6፡ዘሌ 5-16፡ ኢያ 2- 19፡፡ ይሁን እንጂ “ሀጢያቴን
ለመተዉ ከፈቀድኩ አይበቃም ወይ? መናዘዙ ለምን አስፈለገ?” የሚሉ ሰዎች አሉ ሀጢያትን በካህን ፊት
መናዘዝ ግን የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት፡-
☞ሀጢያትን በዝርዝር በካህን ፊት መናዘዝ ዳግመኛ በዚያ ሀጢያት ላለመያዝ ሀይልን ይሰጣል፡፡ ቅዱስ
ዮሃንስ አፈወርቅ “በበደሉ ላይ ድፍረትና ሽንገላን የሚጨምር (ሀጢያት ሰርቶ እንዳልሰራ ዝም የሚል)
ከዚያች ሀጢያት መጠበቅ አይችልም፡፡ እርስዋን በምትመስል ሀጢያት ከመዉደቅም አይድንም” እንዳለ፡፡
በ ንጉስ የሚሽረዉና የሚሾመዉን ግራና ቀኝ አቁሞ የሚሽረዉን ወቅሶ የሚሾመዉን አሞግሶ
እንደሚያከብር ያለፈ ሀጢያታችንን በካሀኑ ፊት ስንዘረዝርም ያለፈዉን ሀጢያታችንን ሽረን
በሚመጣዉም ህይወት ያንን ሀጢያት ላለመድገም እየወሰንን ነው፡፡
☞ ኑዛዜ ያሳቅቃል፡፡ መሳቀቁ ደግሞ ለሰራነዉ ሀጢያት ዋጋ ነዉ፡፡ በፍርድ ቀን ጌታ በሰማይ መላእክት ፊት
ሀጢያታችንን ገልጦ ከሚያሰቅቀን ይልቅ እኛዉ እራሳችን እዚሁ እንደኛዉ ደካማ ሰዉ በሆነው በካህኑ
ፊት በመናዘዝ ለሰራነው እጅግ ግዙፍ ሃጢያት የምንቀበለው ኢምንት ቅጣት ነው፡፡
#ሀጢያታችንን_ለምን_በቀጥታ_ለእግዚአብሄር_ብቻ_አንናዘዝም??
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር አለመናዘዝ አይደለም፡፡ ሀጢያትን ለካህን መንገር
ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ እያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ክብርን ስጥ፡
ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7-19፡፡ ኢያሱ “ክብርን ስጥ” ያለው
ለእግዚአብሄር: “ተናገር” ያለው ግን ለራሱ መሆኑ ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር
መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በኋላ “እግዚአብሔር ይፍታህ”
እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ይህም ምንም በእሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ
ስርየት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ ”ሁለት ወይም ሶስት በሚሆኑበት በዚያ
በመካከላችሁ እገኛለሁ” ብሎ ቃል የገባ አምላክ በአናዛዡ ካህንና በተናዛዡ ምእምን መካከል ሆኖ
ይሰማል፡ ስርየትንም ይሰጣል፡፡
ሰው ሲታመም ሀኪም ቤት ሄዶ በሀኪሙ ፊት ”ቆረጠኝ ወጋኝ. . . ” እያለ
ህመሙን እንደሚያብራራው ሁሉ፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉት ካህናትም የነፍስ ሀኪሞች
ናቸውና እያንዳንዱን የነፍስ በሽታ (ሀጢያት) በዝርዝር በእነርሱ ፊት ልንናዘዝ ይገባል፡፡ በሀኪሙ
ፊት ምንናዘዘው የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ክደን እንዳልሆነው ሁሉ በካህናት ፊት
የምንናዘዘውም የእግዚአብሔርን ሰሚነት ክደን አይደለም፡፡
ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሔር አልናዘዝም ማለት በራሱ ትዕቢት ነው፡፡ ንስሃ የሚገባ ሰው ሊል
የሚገባው ”ከበደሌ ብዛት የተነሳ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ እንኩዋ አግባቤ አይደለም”
ነው(ፀሎተ ምናሴ)፡፡
በወንጌል እግዚአብሔር ”እርስ በርሳችሁ ሀጢያታችሁን ተናዝዙ” ያለው የሰው ልጅ ከፈጣሪ
ይልቅ ሰውን ስለሚፈራና ስለሚያፍር በሃጢያቱ እንዲሳቀቅ ስለፈለገ ነው፡፡
እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ሳይል የሰራውን ሀጢያት እንዴት
እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ብሎ ይናዘዛል? እነዚህ ከእግዚአብሔር ይልቅ
ሰውን የሚፈሩትን መጽሐፍ እንዲህ ይላቸዋል ”እስመ ዐይነ ሰብእ ያፈርሆሙ
ወኢየአምሩ ከመ አይነ እግዚአብሔር ያበርህ እምእዕላፍ ፀሀይ” ”የሰው ዐይን
ያስፈራቸዋል፡ የእግዚአብሔር አይን ግን ከብዙ አእላፍ ፀሀያት ይልቅ
እንደሚያበራ አያውቁም!!!”
አንድ ምእመን ንስሃ በሚገባበት ጊዜ ሃጢያቱን ሳያድበሰብስ በዝርዝር ለካህኑ
በሚገባ መልኩ መናዘዝ አለበት ፡፡ እንዳው በደፈናው “እኔ ያልሰራሁት ሃጢያት የለም ” ”አድርጉ
ከተባለው ውስጥ ያደረግኩት አንድም መልካም ነገር የለም!” እያሉ የብልጠት ኑዛዜ መናዘዝ
አይገባም፡፡ አንድ በሽተኛ በሃኪም ፊት ”ታምሜአለሁ! ” ”በሽታ የተባለ ሁሉ አለብኝ!” በማለት
መድሃኒት እንደማያገኝ ሁሉ ሃጢያቱን በዝርዝር እና በግልፅ ያልተናገረም በትክክል ስርየት
አያገኝም፡፡
☞አንድ ምእመን ስለ ሃጢያቱ በግልፅ ሊናገር እና ሊዘረዝር ይገባል ሲባል ግን
በሆነው ባልሆነው ”እኔ ሃጢያተኛ ነኝ” ሊል ይገባል ማለት አይደለም፡፡ ”ድሃ ድህነቱን በአፉ
ይጠላታል” ሲራ 13-24 እንዳለ ”እንደኔ ሃጢያተኛ ማን አለ?” እያሉ ሃጢያትን በአፍ መጥላት ገና
ከሀጢያት ፍቅር ያለመላቀቅ ምልክት ነው፡፡ ሃጢያትን የሚጠላት በንስሃ ይርቃታልና፡፡ ሃጢያተኛ
ነኝ እያሉ በማወጅ ንጹሃን ትሁታን የሚመስላቸው አሉ፡፡ ትሁታን ግን ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ
እንዳለው:
#ሃጢያተኛ_ነኝ_የሚሉት_ሳይሆኑ_ሃጢያተኛ_ሲባሉ_የሚታገሱት_ናቸው፡፡
እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የኪዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ
7 ቱ ኪዳናት
=>'ተካየደ' ማለት 'ተስማማ: ተማማለ' እንደ ማለት ሲሆን 'ኪዳን' በቁሙ 'ውል: ስምምነት'
እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት
ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::
እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ ሆኑ ታስተምራለች::
ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን እነዚሁን 7 ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን::
=>አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት: የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው::
እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን
አባታችን በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1)
+አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ
አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)
+እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ
አድርጐ በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ ሞትን እስካሁን አልቀመሰም::
ይህም ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)
+እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ
የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን
ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2 ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ
ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን::
*" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ: ማርያም እሙ ለእግዚእነ: በኪዳንኪ: ወበስደትኪ
ድንግል ተማሕጸነ::"
"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ
ተማጽነናል::"
ለምን 55 ቀን ጾምን?
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይህንን የአብይን ፆም የቀናት ቁጥር 55 አድርገው ሲወስኑ ያለ
አንዳች ምክንያት ሳይሆን በምስጢር ነው። ይሄውም እንዴት ነው ቢሉ ፆሙ 55 ቀን የሆነበት
የመጀመረያው ምክንያት በነዚህ በሚፆሙት በ 55 ቱ ቀናት መሀከል (8 ቅዳሜና፣ 7 እሁዶች
በአጠቃላይ 15 ሰንበታት) አሉና እነዚህ ሰንበታት ደግሞ ስለማይፆሙ እነርሱን ጌታችን
ከፆማቸው ከ 40 ው ቀናት ጋር በመደመር 55 ቀናትን እንድንፆም አድርገውናል ።
ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የነፍስ ምግብ እንጅ አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ
ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ
የሚልበት እንጂ። ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም ጠባዩን ለመግራት
እንጂ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው ።
ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ ብቻውን አይጓዝም።
ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ። ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና
እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም፤ መብላት
ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ።