Professional Documents
Culture Documents
Stock MGT
Stock MGT
ባህር ዳር
መግቢያ
አባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ኃላፊነቱን በሚገባ ለመወጣት እንዲሁም ራዕይና
ተልኮዉን ለማሳካት ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ የሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤የፋብሪካዉ
ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ መመሪያ ሌሎች መሰል ተቋማት ከሚጠቀሙበት የንብረት አስተዳደርና አወጋገድ
መመሪያ እንዲሁም የካይዘን አሰራሮችን ጋር በማገናዘብ በፋብሪካዉ ባለቤትነት ስር ለሚገኙ ንብረቶች አንድ ወጥ
እና ዘመናዊ በሆነ አሰራር ስርዓት ለማስተዳደር እንዲቻል ይህን ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ መመሪያ እንዲወጣ
አድርጓል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
2. አዉጪዉ ባለስልጣን
አባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አመራር ቦርድ በፋብሪካዉ
መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ---- የተሰጠዉ ስልጣን መሠረት ይህን የንብረት አስተዳደር መመሪያ
አዉጥቷል፡፡
3. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ አባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ንብረት አስተዳደር
መመሪያ ቁጥር----/2010 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል
4. ትርጓሜ
ያቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠዉ ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ዉስጥ
1. “ፋብሪካዉ” ማለት አባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ነዉ፡፡
2. “የፋብሪካዉ ንብረት” ማለት ከጥሬ ገንዘብና መሬት በስተቀር በግዥ፤በስጦታ ወይም በሌላ
መንገድ የተገኘዉን ማንኛዉም የፋብሪካ ሀብት የሆነዉን ቋሚና አላቂ ማለት ነዉ፡፡
3. “ቋሚ ንብረት” ማለት ግዙፋዊ ህልዎት ያለዉ የተናጠል ዋጋዉ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ)
እና ከዚያ በላይ የሆነ፤አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
የሚኖረዉ እንደ ህንፃ፤የቢሮ ዕቃዎች፤መሣሪያዎች፤ተሸከርካሪ፤ ማሽነሪዎች እና
የመሳሰሉትን ይጨምራል፡፡
4. “አላቂ ዕቃ” ማለት ከቋሚ ዕቃ ዉጪ የሆነ ማናቸዉም ንብረት ሲሆን ለኮንስትራክሽን
ግብዓትነት የሚዉሉ፤ለህትመት አገልግሎት የሚዉሉ ጥሬ ዕቃዎች፤ለተሸከርካሪና ለማሽነሪ
ላይ የሚገጠሙ መለዋወጫዎች እና ሌሎች ከተገዛበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዓመት በሆነ ጊዜ
አገልግሎት ሰጥቶ የሚያልቅ እና ዋጋዉ ከብር 1,000.00 (ከአንድ ሺህ ብር) በታች የሆነ
ንብረትን ያካትታል፡፡
5. “የንብረት ምድብ” ማለት አጠቃላይ ዓይነት የሚመደብበት ክፍል (Class) ነዉ፡፡
6. “የጥበቃ ኃላፊነት” ማለት የፋብሪካዉ ንብረት እስከሚወገድ ወይም ከመዝገብ
እስከሚሰረዝ ወይም በሌላ ሠራተኛ ወይም መ/ቤት ጥበቃ ሥር እንዲዉል እስከሚተላለፍ
ድረስ የፋብሪካዉን ንብረት ለመያዝና ለመጠበቅ ለአንድ ዕቃ ግ/ቤት ሠራተኛ ወይም
የንብረት ተጠቃሚ የሚሰጥ ኃላፊነት ነዉ፡፡ ይህም ኃላፊነት መዝገብ የመያዝ ኃላፊነትን
ሊጨምር ይችላል፡፡
7. “ስቶክ” ማለት በፋብሪካዉ የተገዙ ወይም የተመረቱ ወይም በእርዳታና በሌሎች
መንገዶች የተገኙ ንብረቶች ሆነዉ በመደበኛ የስራ እንቅስቃሴ ዉስጥ አገልግሎት ላይ
እስኪዉሉ ድረስ በመጋዘን የተቀመጡ ቋሚ ዕቃዎች፤አላቂ ዕቃዎች፤የፋብሪካዉ ምርት
ግብዓቶች እና እስኪሸጡ ድረስ የተቀመጡ ምርቶች የቢሮ ዉስጥ መገልገያ መሳሪያዎች
ተሸከርካሪዎች ናቸዉ፡፡
8. “መጋዘን” ማለት የፋብሪካዉን ንብረት አገልግሎት ላይ እስከሚዉል ወይም ምርቶች
እስኪሸጡ ድረስ የሚቀመጥበት ቦታ ነዉ፡፡
9. “ንብረት አስተዳደር” ማለት ማንኛዉም በተገልጋዩ እጅ እና በስቶክ ወይም ምርት ሂደት
ላይ ያለ ዕቃና ተያያዥ አገልግሎቶችን ለማስተዳደር የሚዘረጋ የአሰራር ስልት ማለት ነዉ፡፡
10. “የእርጅና ቅናሽ” ማለት ቋሚ ንብረት ከሌሎች ተፈጥሮ ሀብት ተለይቶ በአገልግሎት
፤በጊዜ ማለፍ፤በብቃት ማጣት ወይም በሌላ ምክንያት ይኽንኑ ተከትሎ ከንብረቱ ዋጋ ላይ ወደ
ወጭ ማስተላለፍ ነዉ፡፡
11. “የንብረት ዋጋ” ማለት ቋሚና አላቂ ንብረትን ለመግዛት ወይም ለመገንባት ከተከፈለዉ
ገንዘብ በተጨማሪ ማለትም የትራንስፖርት፤የመጫንና የማራገፍ ወጪ፤የትራንዚት፤ የጥበቃ
ወጪ ኢንሹራንስና የመሳሰሉት ንብረቱን ለማግኘትና በሥራ ላይ ለማዋል የወጣ ወጪ ማለት
ነዉ፡፡
12. “የወቅቱ የገበያ ዋጋ” ማለት በንብረት ዋጋ ላይ ዕቃዉን ለማግኘትና ርክክብ
እስከሚደረግበት ባለዉ ጊዜ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ወጪዎች ተካተዉ የሚገኝ ዋጋ ነዉ፡፡
“ቀሪ ዋጋ” ማለት አንድ ዕቃ በአገልግሎት ምክንያት እየቀነሰ በመሄዱ የአገልግሎት ዘመኑን
ጨርሶ እስኪሸጥ ድረስ የመዝገብ ዋጋዉ ዜሮ እንዳይሆን ታስቦ የሚሰጥ አነስተኛ ዋጋ ነዉ፡፡
13. “የሐራጅ ሽያጭ” ማለት ለአንድ ዕቃ የሽያጭ መነሻ ዋጋ ከተወሰነ በኃላ
በማስታወቂያዉ መሰረት በተወሰነ ቦታና ጊዜ የተጋበዙ ተጫራቾች በተገኙበት በግልጽ
ዉድድር የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች የሚመረጥበት ሽያጭ ዘዴ ነዉ፡፡
5. የተፈጸሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ አባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዉስጥ ባሉት በሁሉም ስራ
ክፍሎች ተግባራዊ ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለት
ክፍል ሦስት
ስቶክ ኮንትሮል ካርድ፤ ነፍስ ወከፍ ካርድ፤ የምርት ማስረከቢያ ካርድ፤ የሽያጭ
ካርድ ናቸው፡፡
2) ይህንን አሰራር በማይፃረር መንገድ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በመጠቀም የስቶክ መረጃ
መያዝና ማስተዳደር ይቻላል፡፡
20. ስቶክ ወይም ንብረት መረከብ
1. ማንኛውም በግዥ፤ በእርዳታ ወይም በስጦታ የተገኘ ንብረት ርክክብ ሲፈፀም በመጀመሪያ ደረጃ
እቃው ገቢ እንዲሆን ከሚመለከተው አካል ትእዛዝ የተሰጠ ወይም ገቢ ለማድረግ አስፈላጊ ህጋዊ
ሁኔታዎች የተሟሉ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ በገቢ ደረሰኙ ላይ የሚከተሉት ተሟልተዎ
መመዝገብ አለባቸው፡፡
ሀ. አቅራቢውን ወይም የላኪውን ድርጅት ስም
ለ. የእቃውን አይነትና ብዛት
ሐ. የእቃው የነጠላና ጠቅላላ ዋጋ
መ. እቃው የተገኘበት ሁኔታ /በግዥ፤በእርዳታ ፤ በተመላሽ፤ በትውስት ወዘተ…
ሠ. የተላከበት ኢንቮይስ/ደረሰኝ ወይም ደብዳቤ ቁጥር ቀንና የሚያስረክበው ግለሰብ ስም
ተለይቶ ሊፃፍ ይገባል፡፡
2. በግዥ ከአቅራቢ ድርጅት የተላኩትን ሰነዶች ከግዥ ሰነዶች ጋር ለማመሳከሪያነት ከሚሆኑት
መካከል የሚከተሉትን መጠቀም ይገባል፡፡
ሀ. የእቃ ግዥ ማዘዣ /Purchase order/
ለ. የግዥ ውል /Agreement/
ሐ. የእቃ ዝርዝር መግለጫ /Specification/
3. በባለሙያ ተፈትሸው የሚረጋገጡ እንደ ማሽን፤ የመለዋወጫ እቃዎች፤ ለምርትና ለላቦራቶሪ
ግብዓትነት የሚውሉ ኬሚካሎች፤ኮምፒዉተርና ሌሎች የቴክኒክ ባህሪ ያላቸዉ ዕቃዎች ከጠያቂዉ
ክፍል ወይም ለዚሁ ተግባር ከሚመደብ ባለሙያ በሚሰጥ ማረጋገጫ ርክክቡ ይፈጸማል፡፡
4. ዉስብስብነት የሌላቸዉ በተደጋጋሚ በመደበኛነት የሚገዙ ዕቃዎች/ንብረቶች/በግዥ ኦፊሰሩና
በንብረት አስተዳደር ኦፊሰሩ በጋራ በሚሰጡት ማረጋገጫ መሰረት ገቢ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
5. የጥራት ፍተሻ የሚደረገዉ አቅራቢዉ ድርጅት ያቀረበዉ ዕቃ እንዲገዛ ከታዘዘዉ ወይም በዉድድር
ወቅት ከቀረበዉ ወይም በዉሉ በተገለፀዉ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ጋር ማገናዘብ ይሆናል፡፡
6. በንብረት ርክክብ ወቅት ኦፕሬሽናል ወይም የልኬት ፍተሻ የሚያስፈልጋቸዉ እቃዎች በሙሉ
ተፈትሸዉና ተረጋግጠዉ ገቢ መደረግ አለባቸዉ፡፡
ሀ/ ከላይ በዚሁ አንቀጽ ተራ ቁጥር 7 የጠቀሰዉ ቢኖርም ከእቃዉ ብዛት ወይም መፈተሸ
አቅም ጋር በተያያዘ ለሚፈጠር ችግር የናሙና ፍተሻ ማድረግ ይቻላል፡፡
ለ/ የሚወሰደዉ ናሙና መጠንና አፈፃፀም እንደአስፈላጊነቱ በቴክኒክ ክፍል ማኔጀር
ወይም በምክትል ማኔጀር ወይም በእቅርቦትና ሎጅስቲክስ ኃላፊ መወሰን ይኖርበታል፡፡
7. በጥቅል (Packages) የመጡ ንብረቶች በክብደት ጭነት ማረጋገጫ በሌላ መሰል ሰነዶች መሠረት
ትክክል ስለመሆናቸዉ መረጋገጥ አለባቸዉ፡፡የዕቃዎች ሁኔታ /Condition/ አስረካቢዉ ወይም
አጓጓዡ ባለበት ጥቅሎችን በጥንቃቄ በመመርመር
የመጉደል፤የመሰበር፤የመጨራመት፤የመላጥ፤የመሰንጠቅ፤በመቀደድ፤እና ወይም ሌላ ጉዳት
እንዳልደረሰ መረጋገጥ አለበት፡
8. የንብረት ገቢ ደረሰኞች ኮፒ ንብረት ገቢ በተደረገ ጊዜ ሁሉ በወቅቱ ለሚመለከታቸዉ መሰራጨት
አለባቸዉ፡፡ ከሶስት ቀን በላይ ሳይሰራጭ ለቆየ ሰነድ ኃላፊነቱ የንብረት መጋዘን ሠራተኛ ይሆናል፡፡
9. ከጥገና በኃላ ተመላሽ የሚሆኑ ተሸከርካሪ ወይም ሌላ ቋሚ ዕቃ መለዋወጫዎችና አሩጌ ጎማዎች
የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ባገለገሉ ንብረቶች መመለሻ ሰነድ በመሙላት ገቢ መደረግ አለበት፡፡
10. በተለያዩ ሁኔታዎች የንብረት ርክክብ በሚፈፀመበት ጊዜ ከዋናዉ ዕቃ ወይም መሳሪያ ነቅሎ
ለማስረከብ የማይመቹ የሚገጠሙ የቋሚነት ባህሪ ያላቸዉ ዕቃዎች (Fixtures) ለምሳሌ የበር
ቁልፍ፤ጣራ ላይ የሚገጠም ቬንትሌትር፤የቢሮና የአደራሽ ሳዉንድ፤ሲስተምና የተገጣጠሙ የአደራሽ
ወንበሮች፤ጎማዎች፤መለዋወጫዎች እና ሌሎች ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸዉ ዕቃዎች ወጭ በደረገዉ
ስም ንብረቱ ተጠቃሚዎች የቋሚ ንብረት መዝገብ /Users Card/ ላይ ተመዝግበዉ አይያዙም፡፡
11. ከላይ በተራ ቁጥር 12 የተጠቀሰዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ንብረቶች ወጭና ገቢ ሲደረጉ የእቃዉ መለያ
የሆነዉ ሴሪያል ቁጥር እና ሞዴል መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
12. የአቅርቦትና የተከላ/Installation/ አገልግሎት የስራ ዉል ለተቋራጭ በሚሰጥበት ጊዜ ሥራዉ
ተጠናቆ ርክክብ ሲፈጸም በስራ ዝርዝሩ መሰረት አስፈላጊ ግብዓቶች ተሟልተዉ በትክክል የተተከለ
ወይም የተገጠመ/Install/ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አስፈላጊ ከሆነም በባለሙያ ድጋፍ ተፈትሾ
ከተረጋገጠ በኃላ በገቢ ሰነድ በዉል ተቀባይ ስም ገቢ ይደረጋል፡፡
13. ከላይ በተራ ቁጥር 14 ላይ የተገለጸዉን ባህሪ ያለዉ ቋሚ ዕቃ የንብረቱ ተጠቀሚዎች ወጭ
አድርገዉ ሲወስዱት የንብረት ምዝገባና ርክክብ ሥራ የሚያከናወን ቢሆንም ወጭ ባደረገዉ ስም
ወይም በንብረቱ ተጠቃሚዎች የቋሚ ንብረት መዝገብ /Users Card/ ላይ ተመዝግበዉ አይያዙም፡፡
14. በፋብሪካዉ ምርት ክፍል፤ጋራዥ፤በስክራፐክሬሸር ቦታዎች የሚመረቱ ዕቃዎች ንብረት ክፍል ገቢ
እና ወጪ ሳይደረጉና ዋጋዉ ሳይሰጣቸዉ ጥቅም ላይ እንዲዉሉ መደረግ የለበትም፡፡ለዚሁ ምርት
ግብዓትነት የሚያገለገሉ ጥሬ ዕቃዎችም ንብረት ክፍል በወጪና በገቢ ተመዝግበዉ መያዝ
ይኖርባቸዋል፡፡
2. ንብረት ከአንድ ንብረት ክፍል ሰራተኛ ወደ ሌላ ንብረት ክፍል ሰራተኛ በሚዛወርበት ጊዜ፤
3. ወደ ሌላ መ/ቤት የንብረት ዝዉዉር ሲፈጸም የሚከናወን ይሆናል፡፡
ፊርማ ሊያካትት በሚችል የርክክብ ሰነድ ወይም ቬርቫል የንብረት ዝዉዉር ሊፈጸም ይገባል፡፡
3. የአቅርቦትና ሎጅስቲክስ መምሪያ ኃላፊ የንብረት ርክክብና የኦዲት ዉጤቱ ለምክትል ስራ አስኪያጅ
ስም ማስተካካል አለበት፡፡
ይገባል፡፡
ስቶክ ከመጋዘን የሚወጣዉ መጀመሪያ የገባዉ መጀመሪያ ይወጣል /First in first out/
FIFO/የሚለዉን የንብረት አጠቃቀምና አሰራር መርህ መሰረት በማድረግ መሆን አለበት፡፡
1. ንብረት በተሟላ መልክና በተገቢዉ አካል ወጭ ማድረግ ይቻል ዘንድ የግዥ ኦፊሰሩ ወይም አስረካቢዉ
ለተገዛዉ ዕቃዉ ለየትኛዉ ስራ ክፍል እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ ለንብረት ኦፊሰሩ እና ለንብረት
ሠራተኛ መስጠት አለበት፡፡
2. የንብረት ወጪን የመፍቀድና የማጽደቅ ስልጣን በዋና ስራአስኪያጅ ወይም በምክትል ስራ አስኪያጆች
ወይም እንደአስፈላጊነቱ በመምሪያ ኃላፊዎች ሊሆን ይችላል፡፡
3. በሽያጭ ወጪ የሚሆን እቃ ክፍያ የተፈጸመለት ለመሆኑ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኙን በማየት
ማረጋገጥ፤ ከዚህ በተጨማሪ የሚሸጠዉን ዕቃ ዓይነት፤ ብዛትና ዋጋ የሚያሳይ ማመሳከሪያ ሰነድ መያዝ
አስፈላጊ ነዉ፡፡
4. ዕቃዉን በሽያጭ የሚረከበዉ ሰዉ የጹሁፍ ማስረጃ ወይም የዉክልና ማስረጃ ማቅረቡን ማረጋገጥ፡፡
5. ማንኛዉም እቃ በንብረት ወጭ ደረሰኝ ወጭ ከሆነ በኃላ ከመዝገብ ላይ ተቀናንሶ ከወጭ ቀሪዉ በግልፅ
ተለይቶ መያዝ ያለበት ሆኖ የዕቃ ወጪ ደረሰኞችም ለየሚመለከታቸዉ በወቅቱ መሠራጨት
አለባቸዉ፡፡
23. ንብረት በትዉስት ስለሚሰጥበት ሁኔታ
1) አስገዳጅና አስቸኳይ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር ፋብሪካዉ ዕቃ/ንብረት በሽያጭ ወይም በኪራይ
ካልሆነ በትዉስት አይሰጥም፡፡
2) አስገዳጅ ሁኔታ ኖሮ ዕቃ ወይም ንብረት በትዉስት ለሌላ አካል የሚሰጠዉ በፋብሪካዉ ዋና ስራ
አስኪያጆች ሲፈቀድ ብቻ ነዉ፡፡
3) በትዉስት የሚሰጥ እቃ በፋብሪካዉ የወጭ ሰነድ በትዉስት የተሰጠ ለመሆኑ ተገልፆና ሲመልስም
በተመላሽ (Return) ሰነድ ንብረቱ ቀደም ሲል ወጪ የተደረገበት ሰነድ ቁጥር ተጠቅሶ ገቢ መደረግ
ይኖርበታል፡፡
4) በትዉስት የተሰጠ ንብረት ዋጋ በተሰብሳቢ ሂሳብ መያዝ አለበት፡፡
5) በትዉስት የሚሰጠዉ ንብረት የሚመለስበት ጊዜ ገደብ መቀመጥ ያለበት ሆኖ በተወሰነ ጊዜ ገደብ
ዉስጥ መመለሱም ክትትል ተደርጎ በንብረት አስተዳዳር ኦፊሰር በኩል ለዋና ስራ አስኪያጅ ሪፖርት
መቅርብ አለበት፡፡
6) በትዉስት የተሰጠዉ ዕቃ/ ንብረት ብልሽት ቢደርስበት የተዋሰዉ አካል አስጠግኖ እንዲመልስ
እቃ/ንብረት ቢጠፋ ወይም በአደጋ ምክንያት ቢቃጠል፤ቢሰረቅ የተዋሰዉ አካል እቃዉን በአይነት
የሚተካ መሆኑ በቅድሚያ ለተዋሹ እንዲያዉቀዉ ተደርጎ ዉል መፈራረም ያስፈልጋል፡፡
7) ወደ ፋብሪካዉ በትዉስት የሚመጣ ዕቃ/ንብረት መቼ እንደመጣና ለምን ስራ እንደመጣ ታዉቆ
በጥንቃቄ በተለየ መዝገብ ተመዝግቦ መያዝ አለበት፡፡በትዉስት የመጣዉ ዕቃ የመጣበትን ተግባር
ከፈጸመ በኃላ በወቅቱ በሰጠዉ አካል መመለስ አለበት ይህንን ተግባር የንብረት አስተዳደር ኦፊሰሮች
ተከታትለዉ መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
8) በትዉስት የወሰዱትን ማሽነሪ በጊዜ ገደቡ የማይመልሱ ከሆነ ኪራይ ሊታሰብ ይችላል፡፡ የኪራይ
ስሌቱ የትዉስት ጊዜ ገደቡ በተጠናቀቀ በመጀመሪያዉ ቀን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ)
የሚያስከፍል ሆኖ በቀጣይ ቀናትም መሳሪያዉ ካልተመለሰ በየቀኑ 15% እየጨመረ የሚሄድ
ይሆናል፡፡
9) ማንኛዉም በትዉስት የሚሰጥ እቃ በዚህ አንቀጽ የተገለጹትን አስገዳጅ ሁኔታዎችና ሌሎች
ወቅታዊ ሁኔታዎችን ያካተተ የትዉስት ዉል መፈረም ይኖርበታል፡፡
24. የስቶክ ክምችት አወሳሰን
1. ማንኛዉም ለፋብሪካ አገልግሎት የሚዉል በመጋዘን ወይም በስቶክ መልክ የሚያዝ ንብረት
በዓይነት ተለይቶ መቼና ምን ያህል መታዘዝ እንዳለበት የሚወሰን አሠራር ያስፈልገዋል፡፡ይህ
አሰራር የሚከተሉትን ባገናዘበ መልክ መዘጋጀት አለበት፡፡
ሀ/ በእጅ የሚገኝ የክምችት መጠን
ለ/ በትዕዛዝ ያለ መጠን
ሐ/ ዕቃዉ ታዝዞ መጋዘን እስኪገባ ያለዉ ጊዜ
መ/የፍጆታ አዝማሚያ
ሠ/ የገበያ ወይም የአጠቃቀም ሁኔታን እና ጊዜዉን ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፡፡
25. የንብረት መጋዘን አጠቃቀም
1. ንብረትን ለረዥም ጊዜ በብዛት በመጋዝን በማከማቸት የንብረት ብልሽትና ብክነት እንዲሁም
የካፒታል እጥረት እንዳይደረስ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡
2. መደበኛ ወይም ዓመታዊ እቅድን ለማሳካት በግብዓትነት በስቶክ የሚያዙ ንብረቶች፤
ሀ/ እቃዎችን በአይነት ፈጣን እንቅስቃሴ፤ መካከለኛ እንቅስቃሴ እና ዝቅተኛ እንቅስቃሴ
ያላቸዉን ንብረቶች በቦታ መለያየት ያስፈልጋል፡፡
ለ/ አገልግሎት ሳይሰጡ የተቀመጡ ንብረቶች የመጋዘን ጥበት እንዳያስከትሉ በሽጭ
ወይም በሌሎች የማስወገጃ መንገዶች መወገድ ይኖርባቸዋል፡፡
ሐ/ መጋዝኖችን እቃ ለመረከብ፤ለማስቀመጥ፤በቀላሉ ለማግኘትና ለማስረከብ
በሚያመች መንገድ መደራጀት ይኖርባቸዋል፡፡
መ/ ሙቀት ወይም በቅዝቃዜ ምክንያት በቀላሉ የሚጎዱ፤እንዲሁም ለጤንነት አደገኛ
የሆኑ ዕቃዎች እንደየ እቃዎች ባህሪ ተለይተዉ በተዘጋጁ መጋዝኖች መቀመጥ አለባቸዉ፡፡
ሠ/ የንብረት መጋዘን ሠራተኞችም የመጠቀሚያ ጊዜ ገደብ ያላቸዉን ዕቃዎች በተለየ
መከታተየ በመመዝገብ ክትትል ሊያደርጉ ይገባል፡፡
ረ/ በቆይታ ጊዜ የሚበላሹ ንብረቶች ሳይበላሹ የሚቆዩበት ጊዜ ከመጠናቀቁ ከ 6 ወር
በፊት ለሚመለከታቸዉ ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡
ሸ/ መጋዝኖች ለንብረት ድህንት ሲባል በወቅቱ በርና መስኮቶች በሚገባ መዘጋታቸዉን
እና ኤሌክትሪክ መብራት መጥፋቱን ማረጋገጥ፤ከሚመለከታቸዉ ሠራተኞች በስተቀር
በመጋዝን ዉስጥ እንዳይገቡ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
34. ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የጠፋ ወይም የወደመ ንብረትን ስለመሠረዝ
ክፍል አራት
ክፍል አምስት
ክፍል ስድስት
ጋር በማየት፤-
2. ከሚፈልገዉ መጠን በላይ የሆነ አላቂ ንብረት ከሆነ የእቃ ማስተላለፊያ ፎርም በመጠቀም ወደ
6. ንብረቱን ወስዶ መጠቀም የሚፈልግ አካል ጥያቄ ሲያቀርብ የተፈለገው እቃ የመደበኛን ንብረት
በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ 50 %
ጥሩ ባልሆነ አቋም ላይ 75 %
ክፍል ስምንት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
53. መመሪያውን ስለማሻሻል
ይህ የንብረት አስተዳደር መመሪያ የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ስራ አመራር ቦርድ ሲታመንበት
ሊሻሻል ይችላል፡፡
1. የዉስጥ የስራ ማንዋል ስለማዉጣት
አፈፃፀሙም፡-
1. ቅጹ የሚሞላዉ እቃዉን በሚመልሰዉ ሠራተኛ ነዉ፡፡
2. እንዲመለስ የተጠየቀዉ እቃ ንብረት ክፍል ገቢ እንዲሆን በሚመልሰዉ ሠራተኛ የቅርብ
ኃላፊ መረጋገጥ አለበት፡፡
3. የሚመለሱት ዕቃዎች ሁኔታ ተጠግኖ ‘’አዲስ‘’ ‘’የሚያገለግል‘’ ‘’ተጠግኖ የሚያገላግል‘’
በሚል መለየት አለባቸዉ፡፡አስፈላጊ ሲሆን የተክኒክ ባለሙያዎችን አስተያየት መዉሰድ ተገቢ
ይሆናል፡፡
4. የንብረት ክፍል ሠራተኛዉ ተመላሽ የሆኑ ዕቃዎችን ሥርዓቱን ጠብቆ በንብረት ተመላሽ
ማድረጊያ ቅፅ በገቢ ይመዘግባል ለንብረት ምዝገባ የሚያገለግሉ ካርዶችንም ያስተካክላል፡፡
5. የንብረት ተመላሽ ማድረጊያ ቅፅ በማዕከላዊነት የንብረት አስተዳደር ኦፊሰር በሚመደበዉ
ሠራተኛ ኃላፊነት ተይዞ ንብረት በሚመልስ ሠራተኛ ጥያቄ ሲቀርብ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
6. ቅፁ በ 4 ኮፒ የሚሞላ ሲሆን
ዋናዉና የመጀመሪያዉ ለፋይናንስ
1 ኛዉ ኮፒ ለዕቃ ግምጃ ቤት ሠራተኛ
2 ኛዉ ኮፒ ለአስረካቢዉ ለፋይናንስ የሚሰጠዉ
3 ኛዉ ኮፒ ለአስረካቢዉ
4 ኛዉ ኮፒ ከጥራዙ ጋር ቀሪ ይሆናል፡፡
4) አገልግሎት ሰጥተዉ የተመለሱ እቃዎች ወጭ ማድረጊያ ቅፅ (Serviceable goods issue
voucher)
ይህ ቅጽ የሚያገለግለዉ አግልግሎት ሰጥተዉ ተመላሽ ከሆኑ ዕቃዎች ዉስጥ ለሥራ
የሚያስፈልጉ ቢኖሩ ወጭ አድርጎ ለመጠቀም ሲያስፈልግ፤ለሁለተኛ ጊዜ እቃዎች
ወጭ የሚሆኑበት ቅፅ ነዉ፡፡
አፈፃፀሙም፡-
1. እቃዎች ወጭ እንዲሆኑ ሲጠየቅ ከዚህ በፊት አገልግሎት የሰጡ መሆናቸዉ መጠቀስ
አለበት፡፡
2. የዕቃ መጠየቂያና መፍቀጃ ሂደቱ በአንቀጽ 27.2.1 በተጠቀሰዉ ሂደት መሰረት ይፈጸማል፡፡
3. የዉጭ ሰነድ በ 3 ኮፒ የሚሰራ ሆኖ፤
ዋናዉና የመጀመሪያዉ ለፋይናንስ መምሪያ
1 ኛዉ ኮፒ ለንብረት ሠራተኛ
2 ኛዉ ኮፒ ለተረካቢዉ
3 ኛ ኮፒ ከጥራዝ ቀሪ ይሆናል፡፡
አለበት፡፡
3. ቅፁ የሚሞላዉ በ 7 ኮፒ ሆኖ ሥርጭቱም፡-
ዋናዉና የመጀመሪያዉ ለፋይናንስ ኦፊሰር
1 ኛዉ ኮፒ ለንብረት ሠራተኛ
2 ኛዉ ኮፒ ለንብረት ሪከርድ ኦፊሰር
3 ኛዉ ኮፒ ለአድራሹ/ንበረቱን/ ለሚወስደዉ
4 ኛዉ ኮፒ ንብረቱ የተላከለት አካል የሚፈርምበት በአድራሹ ለፋይናስ
የሚሰጥ
5 ኛዉ ኮፒ ለንብረት ተቀባዩ ምዝገባ
6 ኛዉ ኮፒ ለጥበቃ ሠራተኛ
7 ኛዉ ኮፒ ከጥራዙ ጋር ቀሪ ይሆናል፡፡
1. የተላከዉ ዕቃ ለመድረሱ 4 ኛዉ ኮፒ ላይ የቀጠና ወይም የፕሮጀክት ንብረት ሠራተኛ
ተፈርሞበት እቃዉ ወጭ ከተደረገበት ንብረት ክፍል ላሉ ኦፊሰሮች ዋናዉ ጽ/ቤት ይመለሳል፡፡
የንብረት ኦፊሰሮች ለፋይናስ ያስተላልፋሉ፡፡
2. የተላከዉ ንብረት በትክክል የተፈለገበት ቦታ ለመድረሱ የንብረት አስተዳደር ኦፊሰሮች ክትትል
ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. የተላከዉ ንብረት ሙሉ በሙሉ ሳይደርስ ቢቀር ብልሽት ቢኖር ተቀባዩ አካል ወይም ንብረት
ክፍሉ፡-
ንብረቱ የተላከበትን ሰነድ ቁጥር ቀንና ዓ.ም
የአጓጓዡን ስም፤የአሽከርካሪዉን ሰሌዳ ቁጥር፤
የጎደለዉን ወይም ጉዳት /ብልሽት/ የደረሰበትን ዕቃ ዓይነትና ብዛት በመግለፅ
ወዲያዉኑ ለሚመለከታቸዉና ለዋናዉ ፋብሪካዉ ጽ/ቤት በደብዳቤ ማሳወቅ ግዴታ
ነዉ፡፡
በቀረበዉ ሪፖርት መሠረት ፋብሪካዉ ጽ/ቤት ተገቢዉን የዲሲፒሊን እርምጃ
ይወስዳል፡፡
6) የነዳጅ ዘይትና ቅባት መጠየቂያና ወጭ ማድረጊያ (Petroleum,Oil & Lubricants
Store Requisition & Issue voucher)