Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 5

ትምህርታቸውን ላሻሻሉ የመንግስት ሠራተኞች/ ባለሙያዎች አመዳደብና የደመወዝ አከፋፈል በሚመለከት

የተሻሻለ መመሪያ ቁጥር 5/2013


~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ግን ይህንን ፔጅ Like አድርገዋል? Like ቢያደርጉ ስለቴክኖሎጅ ይማራሉ ያውቃሉ!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መግቢያ
ትምህርት የአንድን አገር ልማት ለማፈጠን እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ በአገር ደረጃም ሆነ በክልላችን ትኩረት
ተሰጥቶት እየተሰራባቸው ከሚገኙ ዘርፎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ስለሆነም የትምህርት ተቋማትን በመጠቀም የፈጻሚውን አቅም ማጎልበት በሲቪል ሰርቪሱ የሚታየውን
የመፈጸም አቅም ክፍተት መሙላት ስለሚያስችል የትምህርት ደረጃቸውን አሻሽለው የሚመለሱ የመንግስት
ሠራተኞችን/ባለሙያዎችን በአግባቡ ምደባ ለመስጠትና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያሥችል መመሪያ ተሻሽሎ
ከሰኔ 2011 ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል የተደረገ ቢሆንም እንደገና ማሻሻል አስፈልጓል፡፡
ስለሆነም፡-
በተለያዩ ጊዚያት የወጡ ሰርኩላሮችን የዚህ መመሪያ አካል በማድረግ ለተጠቃሚው ምቹ ሁኔታ
ለመፍጠርና በአፈጻጸም የታዩ ግድፈቶችን ለማረም በማስፈለጉ፣
ከነጥብ የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ጋር የተዛመደ የመመሪያ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ ፡
በየደረጃው ትምህርታቸውን አጠናቀው ለሚመለሱ ባለሙያዎች የትምህርት ዝግጅታቸውን መሠረት
ያደረገ ምደባ በወቅቱ መስጠት በማስፈለጉ፣
በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በመንግስት ድጋፍ ትምህርታቸውን አሻሽለው ለሚመለሱ ባለሙያዎች
ተገቢ የስራ ምደባና አቅምን ያገናዘበ ማበረታቻ በመስጠት አቅማቸውን አሟጠው እንዲጠቀሙ ማስቻል
በማስፈለጉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በተሻሻለው የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ 253/2010 አንቀጽ 96 ንዑሥ
አንቀጽ 2 በተሰጠው መመሪያ የማውጣት ስልጣን መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1.1 አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርታቸውን ያሻሻሉ የመንግስት ሠራተኞች
አመዳደብና የደመወዝ አከፋፈል መመሪያ ቁጥር 5/2013 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
1.2 ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፣
1.2.1 "የመንግሥት መ/ቤት" ማለት በየትኛውም የአስተዳደር እርከን እራሱን ችሎ በአዋጅ ወይም በደንብ
የተቋቋመ እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከመንግስት በሚመደብለት በጀት የሚተዳደር የመንግስት መስሪያ
ቤት ነው፡፡
1.2.2 "ኮሚሽን" ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነው፡፡
1.2.3 “የመንግስት ሠራተኛ ” ማለት በመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት/በጊዚያዊነት ተቀጥሮ
የሚሠራ ሰው ነው ፡፡
1.2.4 “መደበኛ ፕሮግራም “ ማለት በመንግስት ድጋፍም ይሁን በግል ስፖንሰር አድራጊነት ከመደበኛ ስራቸው
ውጭ ሆኖ ትምህርቱን ለመከታተል የመረጠው መርሀ-ግብር ነው፡፡
1.3 “በርቀት፤በማታ፤በክረምት ፕሮግራም”ማለት በመንግስትድጋፍምይሁንበግልስፖንሰር አድራጊነት መደበኛ
ስራውን እያከናወነ ትምህርቱን ለመከታተል የመረጠው መርሀ-ግብር ነው፡፡
1.4 ማንኛውም በወንድ ፃታ የተገለፀው የሴት ፆታንም ያካትታል፡፡
1.5 የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ ተፈፃሚነት የሚኖረው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010
በሚተዳደሩ መ/ቤቶችና ሠራተኞች ላይ ብቻ ነው፡፡
ክፍል ሁለት
ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች/ሰራተኞች አመዳደብና የደመወዝ አከፋፈል ሁኔታ
2.1. የአመዳደብ ሁኔታ
2.1.1 በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ኘሮግራም በየትኛውም ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመጡ
ባለሙያዎች ምደባ የሚያገኙት ወደ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ይሰሩበት በነበረው ወይም ውል አስይዞ
በላካቸው ወይም በስልጠናው ወቅት ለሰልጣኙ ደመወዙን ይከፍል በነበረው መ/ቤት ይሆናል፡፡
2.1.2 በነጥብ የስራ ምዘና ዘዴ ደረጃ ከተሰጠው በኋላ ወደ ትምህርት የሄደ ባለሙያ ትምህርቱን አጠናቆ
ሲመለስ ይዞት የነበረው የስራ ደረጃ ተጠብቆለት ምደባ ይደረግለታል፡፡ሆኖም ግን ይዞት የነበረው የስራ ደረጃ
ተሻሽሎ ከሆነ የተሻሻለውን የስራ ደረጃ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ማሟላቱ ተረጋግጦ ከተሻሻለው የስራ
ደረጃ ላይ ይመደባል፡፡
2.1.3 በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ኘሮግራም ሁለተኛ ዲግሪና በላይ ትምህርታቸውን ያሻሻሉ
ባለሙያዎች በንኡስ አንቀጽ 2.2.1. የተፈቀደላቸውን ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ በማድረግ በነበራቸው ደረጃ
ላይ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ ይህም ሆኖ ከትምህርት መልስ ይዘውት ከነበረው ደረጃ በላይ ከፍ ብለው
በጊዚያዊነት የሚመደቡ ሠራተኞች ቢኖሩ ከፍ ብለው የተመደቡበትን የስራ ደረጃ የሚያገኙት ከሌሎች
ሰራተኞች ጋር በደረጃ ዕድገት ተወዳድረው አሸናፊ ሲሆኑ ነው፡፡
2.1.4 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.1.1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ኘሮግራም
በየትኛውም ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመጡ ባለሙያዎች ምደባ የሚያገኙት ወደ ትምህርት
ከመግባታቸው በፊት ይዘውት ከነበረው ደረጃ አቻ በሆነ ደረጃ ላይ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ ማሟላታቸውን
በማረጋገጥ ይሆናል፡፡ ሆኖም ክፍት የሥራ መደብ ካልተገኘ እስከ ሁለት ደረጃ ከፍ ወይም እስከ ሁለት ደረጃ
ዝቅ ብለው በጊዚያዊነት እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ ከፍ ብለው የሚመደቡት የሥራ ደረጃውን ወይም ጥቅሙን
የሚያገኙት በደረጃ እድገት አግባብ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር ተወዳድረው ሲያሸንፉ ብቻ ይሆናል፡፡ ዝቅ ብለው
የተመደቡትም ሆነ ከፍ ብለው የተመደቡት በተሸሻለው የመንግስት ሰራተኞች ምልመላና መረጣ መመሪያ
አንቀጽ 1.3.4 መሠረት ማንኛውም ስምሪት ከመከናወኑ በፊት በትይዩ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡
2.1.5 በንዑስ አንቀጽ 2.1.1 እና 2.1.2 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግሥት ድጋፍ በማንኛውም
ፕሮግራም ሁለተኛ ዲግሪና በላይ ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች ለምደባ ሲመጡ በተመረቁበት
የትምህርት ዘርፍ ወይም የትምህርት ዝግጅት ሊያስመድባቸው የሚያስችል ክፍት የሥራ መደብ ካልተገኘ
በንኡስ አንቀጽ 2.2.1. የተፈቀደላቸውን ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ በማድረግ ከአሻሻሉት የትምህርት ዘርፍ
/ዝግጅት/ በፊት በነበራቸው የትምህርት ዝግጅት ሊመደቡ ይችላሉ፡፡
2.1.6. ከላይ በን/አንቀጽ 2.1.2 - 2.1.4 የተገለጸው ቢኖርም በመንግሥት ድጋፍ በማንኛውም ፕሮግራም
ከ 2 ኛ ዲግሪ በታች ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች ወደ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ይዘውት
የነበረው የስራ ደረጃ መነሻ ደመወዝ ከአሻሻሉት ትምህርት ደረጃ መነሻ ደመወዝ ደረጃ በታች የሚሆንበት
ሁኔታ ሲያጋጥም ያለ ስራ ልምድ የተሻሻለው ትምህርት ደረጃ መነሻ ደመወዝና ከዚያ በላይ ደመወዝ
ሊያስከፍል በሚችል ደረጃ ያለው ስራ መደብ ላይ ይመደባሉ፡፡ ሆኖም ግን ሊመደቡ የሚችሉበት የስራ መደብ
ከሌለ እየሰሩ ባሉበት የስራ ደረጃ ላይ የትምህርት ዝግጅት መነሻ ደመወዝ እንዲያገኙ በማድረግ በጊዚያዊነት
ይመደባሉ፡፡
2.1.7. ከላይ በን/አንቀጽ 2.1.2 - 2.1.6 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ባለሙያው ከሄደበት መ/ቤት
የሚመደብበት ክፍት የሥራ መደብ ከጠፋ ብቻ በየደረጃው ባለው የሲቪል ሰርቪስ መ/ቤት አማካኝነት
ባለሙያው ይሰራበት የነበረው መ/ቤት ባለበት የአስተዳደር አርከን ባሉ ሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች ባሉ ክፍት
ስራ መደቦች ላይ እንደአስፈላጊነቱ በጀቱን እንደያዘ ወይም ሳይዝ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡
2.1.8. ከላይ በን/አንቀጽ 2.1.7 በተገለጸው መልኩ ምደባ መስጠት ካልተቻለ የሚመጥናቸው ክፍት የሥራ
መደብ እስከሚገኝ ድረስ በተላኩበት የአስተዳደር እርከን ውስጥ በጊዜያዊነት በማንኛውም ስራመደብ ላይ
ተመድበው እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡ ይህም ሆኖ ጊዚያዊ የስራ መደብ ከጠፋ የወረዳና ከተማ አስተዳደር
ሠራተኞችን በዞን በኩል ዞን ሴክተሮች ላይምሆነ በዞኑ ውስጥ ባሉ ወረዳዎች ወይም ከተማ አስተዳደሮች ላይ
እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ የዞን ሴክተር መ/ቤት ሠራተኞች ምደባ ግን በዞን ሲቪል ሰርቪስ መ/ቤት አማካኝነት
ይጠናቀቃል፡፡
2.1.9 ከላይ በን/አንቀጽ 2.1.8 የተገለጸው ቢኖርም ሠራተኛው የሚመደብበት ክፍት የስራ መደብ ባለመገኘቱ
ከነበረበት የአስተዳደር እርከን ወደ ላይኛው አስተደር እርከን ተስቦ የሚመደብ ሠራተኛ ቢኖር ከነበረበት
አስተዳደር እርከን ከፍተኛ የስራ ደረጃ በላይ ሊመደብ አይችልም፡፡
2.1.10. የካርየር ተጠቃሚ የሆነ ሠራተኛ በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ፕሮግራም ከሁለተኛ ዲግሪ በታች
በሆነ የትምህርት ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ
ካሻሻለው የትምህርት ዝግጅት መነሻ ደመወዝ በታች ከሆነ በካርየሩ መነሻ ደመወዝ የሥራ ደረጃ ላይ
እንዲመደብ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ ካሻሻለው የትምህርት
ዝግጅት መነሻ ደመወዝ በላይ ከሆነ በሚያገኙ ደመወዝ ትይዩ ባለው የካርየር ሥራ ደረጃ ላይ ከመመደብ
በስተቀር የሚደረግለት ጭማሪ አይኖርም ፡፡
2.1.11. የካርየር ተጠቃሚ የሆነ ሠራተኛ በመንግስት ድጋፍ በማንኛውም ፕሮግራም ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ
በላይ በሆነ የትምህርት ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ የትምህርት ማስረጃውን ካያያዘበት ቀን ጀምሮ
ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ በነበረው ደመወዝ ላይ የሦስት ዕርከን ጭማሪ ተደርጎለት በካርየሩ ሊያርፍ
ወደ ሚችልበት የሥራ ደረጃ ላይ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡
2.1.12. ከላይ በንኡስ አንቀጽ 2.1.11 የተገለጸው ቢኖርም አንድ ትምህርቱን ያሻሻለ ጤና ባለሙያ በመንግስት
ድጋፍ ከስራ ገበታው በመለየት በመደበኛ ፕሮግራም የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ በሆነ የትምህርት ደረጃ
ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ ሊመደብ የሚችለው የትምህርት ማስረጃው የጤና ባለሙያዎችን ሙያ
በመመዘን የፓናል ደረጃ እንዲወስን ስልጣን በተሰጠው አካል የተወሰነ የፓናል ውሳኔ ሲያቀርብ ባቀረበው ደረጃ
መሰረት የሚመደብ ይሆናል፡፡
2.1.13 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.1.12 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሠራተኛው ለ 2 ኛ ዲግሪና በላይ ትምህርት
ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ በፓናል ከተወሰነለት ደረጃ መነሻ ደመወዝ አኩል ወይም የበለጠ
የሚሆነበት አጋጣሚ ሲኖር ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ በነበረው ደመወዝ ላይ በንኡስ አንቀጽ 2.2.1.
የተፈቀደው ጥቅማጥቅም ተጨምሮለት በካርየር መመሪያው ለትምህርት ደረጃው ሲባል በተዘጋጀ ደመወዝ
ስኬል አቻ መነሻ ደመወዝ ባለው ስራ ደረጃ ላይ ይመደባል፡፡ነገር ግን ለ 2 ኛ ዲግሪና በላይ ትምህርት ከመሄዱ
በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ በፓናል ከተወሰነለት ደረጃ መነሻ ደመወዝ ያነሰ ከሆነ ወደ ፓናል መነሻ ደመዎዝ
እንዲመደብ ይደረጋል፡፡
2.1.14 በመንግስት ድጋፍ በመደበኛ ፕሮግራም ከስራ ገበታው በመለየት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቱን
ያሻሻሉ የጤና ባለሙያዎች ት/ት ከመሄዳቸው በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ በፓናል ከተወሰነለት ደረጃ መነሻ
ደመወዝ አኩል ወይም የበለጠ የሚሆነበት አጋጣሚ ሲኖር ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ
እንደያዘ በተወሰነለት የፓናል ደረጃ ላይ ይመደባል፡፡ ነገር ግን ትምህርት ከመሄዱ በፊት ያገኝ የነበረው ደመወዝ
በፓናል ከተወሰነለት ደረጃ መነሻ ደመወዝ ያነሰ ከሆነ ወደ ፓናል መነሻ ደመዎዝ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡
2.1.15 ቀደም ሲል የካርየር ተጠቃሚ ያልነበረ ሰራተኛ በመንግስት ድጋፍ ከመደበኛ ስራው ተለይቶ የካርየር
ስራ መደብ ላይ በሚያስመድብ የትምህርት ዝግጅት አይነት ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ በሆነ ደረጃ
የትምህርት ደረጃውን አሻሽሎ ሲመለስ ለትምህርት ከመሄዱ በፊት ይከፈለው በነበረው ደመወዝ ላይ በንኡስ
አንቀጽ 2.2.1. የተፈቀደውን ጥቅማጥቅም እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ደመወዙ ለትምህርት ደረጃው
ከሚፈቅደው መነሻ ደመወዝ የሚያንስ ከሆነ በካርየር ስራ መደብ ላይ ተመድቦ ለትምህርት ደረጃው
የተወሰነውን መነሻ ደመወዝ እንዲከፈለው ይደረጋል፡፡
2.1.16 ከላይ በንኡስ አንቀጽ 2.1.10፤2.1.11፤ 2.1.14 ና 2.1.15 የተገለጸው ቢኖርም ደመወዙ በካርየር
መመሪያው ለትምህርት ደረጃው ከተወሰነው መነሻ ደመወዝ እኩል ወይም የሚበልጥ ከሆነ ሠራተኛው
ደመወዙን እንደያዘ በካርየሩ መነሻ የስራ ደረጃ እንዲመደብ ተደርጐ የካርየር ቆይታ ጊዜው ከተመደበበት ጊዜ
ጀምሮ ታስቦ የእድገት መሰላል ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
2.1.17 ቋሚ የመንግሥት ሠራተኛ ሆነው ወደ ትምህርት በመግባት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው
በተለያዩ ምክንያቶች በቋሚነት ትምህርታቸውን አቋርጠው የተመለሱ ሠራተኞች ቀድሞ የነበራቸውን
ደመወዝ እንደያዙ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ይደረጋል፡፡
ሆኖም ትምህርታቸውን በጊዜያዊነት አቋርጠው የተመለሱ ሠራተኞች ይሠሩበት በነበረው መ/ቤት
በጊዜያዊነት በተገኘው ክፍት የሥራ መደብ ተመድበው እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡
2.1.18 ከላይ በተራ ቁጥር 2.1.17 በተገለጸው አግባብ ምደባ የሚሰጠቸው ባለሙያዎች ትምህርታቸውን
ያቋረጡበትን ምክንያት የሚገልጽ ማስረጃ ከዩኒቨርስቲው ሪጅስትራር ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
2.2 የደመወዝ አከፋፈል ሁኔታ፣
2.2.1 በመንግስት ድጋፍ ከስራ ገበታቸው በመለየት በመደበኛ ፕሮግራም፤ እንዲሁም በስራ ላይ ሆነው
በየትኛውም ኘሮግራም/ በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምትና በርቀት/ የሁለተኛ ዲግሪያቸውንና ከዚያ በላይ
ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመለሱ ባለሙያዎች ትምህርት ቤት ከመግባታቸው በፊት ወይም
ትምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት ይዘውት ከነበረው ደረጃ እና ደመወዝ ላይ የሶስት እርከን ጭማሪ
ይደረግላቸዋል፡፡ ክፍያውም የሚፈጸመው የትምህርት ማስረጃቸውን ካያያዙበት ቀን ጀምሮ ሲሆን ከውጭ
አገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ግን በሚመለከተው አካል ከተሰጠ አቻ ግምት ማስረጃ ጋር ሲቀርብ ብቻ
ክፍያው የሚፈጸም ይሆናል፡፡
2.2.2 በግል ወጫቸው ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ባለሙያዎች ከያዙት
ደመወዝ ላይ የሶስት እርከን ጭማሪ ይደረግላቸዋል፡፡ ክፍያውም የሚፈጸመው የትምህርት ማስረጃቸውን
ካያያዙበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ነገር ግን ክፍያውን ለመፈጸም ትምህርቱን ከማጠናቀቃቸው በፊት ከሚሰሩበት
መ/ቤት አንድ ዓመትና በላይ ማገልገል ይጠበቅባቸዋል፡፡
2.2.3 በአንቀጽ 2.2.2 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም የካርየር ተጠቃሚ የሆኑ ባለሙያዎች በግል ወጫቸው ሁለተኛ
ዲግሪና ከዚያ በላይ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ የሶስት እርከን ጭማሪ አይደረግላቸውም፡፡
2.2.4 በአንቀጽ 2.2.1፤ 2.2.2 ና 2.2.3 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም የካርየር ተጠቃሚ ለሆኑ ባለሙያዎች ይህ
ጥቅም የሚሰጠው በመንግስት ድጋፍ ከስራ ገበታቸው በመለየት በመደበኛ ፕሮግራም ትምህርታቸውን
ለተከታተሉ ባለሙያዎች ብቻ ነው፡፡ ይህ ማለት በትምህርት ጊዜው የካርየር እድገት ተጠቃሚ የሆኑ
ባለሙያዎች የሶስት አርከን ጭማሪ ተጠቃሚ አይሆኑም ወይም የሶስት እርከን ጭማሪ ጥቅም የሚሠጠው
በትምህርት ጊዜው የካርየር እድገት ጥቅም ተቋርጦ የነበረ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
2.2.5 በአንቀጽ 2.2.4 ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የትምህርት ደረጃው ያለሥራ ልምድ
ከሚያስከፍለው መነሻ ደመወዝ በታች ከሆነ የትምህርት ደረጃቸው ያለሥራ ልምድ የሚያስገኘውን መነሻ
ደመወዝ እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡
ክፍል ሦስት
ልዩ ልዩ ጉዳዮች
3.1 በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነትም ሆነ በግል ወጫቸው ትምህርታቸውን አሻሽለው ምደባ የሚያገኙ
ባለሙያዎች በስራ ላይ ያለው የምልመላና መረጣ መመሪያ የሚጋብዛቸው ከሆነ ተጨማሪ የመቆያ ጊዜ
ሳያስፈልጋቸው ለከፍተኛ የስራ ደረጃዎች በደረጃ እድገት አግባብ ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡ በውድድር ወቅትም
ወደ ትምህርት ከመሄዳቸው በፊት ባለው አንድ ዓመት ውስጥ የተሞላላቸው ሥራ አፈፃፀም ይያዝላቸዋል፡፡
3.2 በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነት 2 ኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃቸውን የሚያሻሽሉ
ባለሙያዎች የሶስት እርከን ጭማሪ የሚያገኙት ትምህርታቸውን ጀምረው እስከ ሚያጠናቅቁ ድረስ
ባስተማራቸው መ/ቤት ከቆዩ ብቻ ይሆናል፡፡
ሆኖም የነበሩበትን መ/ቤት በደረጃ ዕድገት፤ በዝውውርና በምደባ የለቀቁ ሰራተኞች/ባለሙያዎች የተመደቡበት
፤ያደጉበት ወይም የተዛወሩበት መ/ቤት በጀት ይዞ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን ሰራተኛው ሲመደብ ፣
ሲዛወርና ደረጃ እድገት ሲያድግ የነበረበት መ/ቤት ለተቀባይ መ/ቤት በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነት
ትምህርቱን እየተከታተለ የነበረ ስለመሆኑ ማሳወቅ አለበት፡፡ ከላይ የተገለፀው ቢኖርም በራሱ ፈቃድ
መልቀቂያ ጠይቆ የለቀቀን ባለሙያ/ሰራተኛ አይመለከተውም፡፡
3.3 በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 አንቀጽ 96 ን/አንቀጽ 2 መሠረት
ይህን መመሪያ የመለወጥ፣ የማሻሻል ወይም በሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ ማብራሪያ ወይም ትርጉም
የመስጠት ኃላፊነት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነው፡፡
3.4 ሰኔ 2011 ዓ/ም ወጥቶ በሥራ ላይ የነበረው ትምህርታቸውን ያሻሻሉ ባለሙያዎች አመዳደብና ደመወዝ
አከፋፈል አፈጻጸም መመሪያና ይህንን አስመልክቶ የተላለፉ ሰርኩላሮች በዚህ መመሪያ ተተክተዋል፡፡
3.5 ይህን መመሪያ በተዛባ መልኩ ወይም ያለአግባብ የሚያስፈጽም ማንኛውም አካል ወይም የስራ ኃላፊ
አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል
3.6 በዚህ መመሪያ ላይ አፈፃፀም ላይ የሚኖር ቅሬታ በስራ ላይ ባለው የቅሬታ ዓቀራረብ ስነ-ሥርዓት ተፈፃሚ
ይሆናል፡፡
3.7 ይህ መመሪያ ከህዳር /2013 ዓ/ም ጀምሮ የፀና ነው፡፡

You might also like