Professional Documents
Culture Documents
የወጪ መደብ ዝርዝር
የወጪ መደብ ዝርዝር
1
የወጪ መደብ
መለያ ቁጥር 6220 የተዘለለው አዲስ የወጪ ንዑስ ክፍልን የሚያመለክት ባለመሆኑ ነው፡፡
1
ግዙፍ ሀልዎት የሌላቸው ንብረቶች የሚባሉት ከዕዳ ጋር ባለመዛመዳቸው በሌሎች ላይ የይገባኛል ጥያቄ
የማያስነሱ ናቸው፡፡ እነዚህ የማዕድን ክምችቶች እና የዓሣ ሀብት የመጠቀምን መብቶች እና መሬትን፤
የፈጠራ መብትን የድርሰትና የኪነ ጥበብ መብትን እና የንግድ ምልክቶችን በኮንትራት ወይም በሊዝ የመያዝ
መብትን ይጨምራል፤
መሳሪያዎች ተብለው በወጪ መደብ 6219 የተመደቡት አነስተኛ ዋጋ ያላቸው/ ከብር 200 በታች/ እና ከአንድ
ዓመት በላይ አገልግሎት የሚሰጡ መሣሪያዎች ይካተታሉ፡፡ ግዥዎች መታየት ያለባቸው በጥሬ ገንዘብ ክፍያ
ወይም የእዳ ግዴታ በመግባት እንደተፈጸሙ፤ እንዲሁም ተመላሽ የሚደገረውን ወይም ቅናሽን ጨምሮ
ታሳቢ በማድረግ ማሳየት ይገባል፡፡
ይህ የወጪ ክፍያ በስድስት ንዑስ የወጪ ክፍሎች የተከፋፈለ ነው፡፡ እነዚህም ዕቃዎች እና አቅርቦቶች፤ የጎዞ
እና የመስተንግዶ አገልግሎት፤ የዕድሳት እና የጥገና አገልግሎት፤ኮንትራታዊ አገልግሎቶች የስልጠና
አገልግሎቶች፤ አደጋ እና የስትራቴጂካዊ እቃዎች ክምችት ናቸው፡፡ የዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥ ዋጋ
በጥቅል የሚታይ ሲሆን፤ ይህም ቀረጥና ታክስ እንዲሁም ማናቸውንም አግባብነት ያላቸውን እና የተለመዱ
ወጪዎችን/ ለምሳሌ ትራንስፖርት/ ይጨምራል፤
6210-20 መሳሪያዎች እና አላቂ እቃዎች
ይህ ንዑስ የወጪ ቁጥር ክፍል በዕለት ተእለት የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ አላቂ
ዕቃዎችን ይጨምራል፡፡ አላቂ ዕቃዎች ከአንድ ዓመት በላይለሆነ ጊዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ሊኖራቸው
የሚችል ቢሆንም በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚያልቁ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች እና
ምግብ ለዚህ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
6211 የደንብ ልብስ፤ የሥራ ልብስ፤ ፍራሽና አልጋ ልብስ
ይህ የወጪ መደብ ለመከላከያ እና ለፖሊስ ሠራዊት አባላት የደንብ ልብስ፤ የሆስፒታል ሠራተኞች የሥራ
ልብስ እንዲሁም የሥራ ልብስ ለሚገባቸው ሠራተኞች እና ለቴክኒሻኖች የሚውል ወጪ ነው፡፡ ድንኳን
የአልጋ ልብስ፤ አንሶላ ፤የትራስ ልብስ፤ ብርድ ልብስ እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጥይት ለመያዝ
የሚጠቀሙባቸው በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
6212 የቢሮ አላቂ እቃዎች
ይህ የወጪ መደብ የቢሮ ስራን ለማካሄድ ጥቅም ላይ የሚውሉ አላቂ እቃዎችን ሁሉ ያካትታል፡፡ የፅሕፈት
መሳሪያ፤ የታተሙ ቅፆች፤ የታይፕራይተር ሪበኖች፤ የፕሪንተር ካርትሬጅ፤ዲስኬት ወዘተ በምሳሌነት ሊጠቀሱ
ይችላሉ፡፡
6213 ሕትመት
ይህ የወጪ መደብ በመንግስት ወይም በግል ማተሚያ ቤቶች ለሚከናወን ለማንኛውም የሕትመት ሥራ
የወጣውን ወጪ ሁሉ ይጨምራል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የሚያሳትማቸው የመማሪያ መፃህፍት ግን
በዚህየወጪ መደብ ሳይሆን በወጪ መደብ 6215 ‹‹ የትምህርት አቅርቦት›› በሚለው ስር የሚመደቡ
ይሆናል፡፡
ይህ የወጪ መደብ በሕክምና ተቋሞች ውስጥ ሕመምን ለማዳን ወይም ለመከላከል እንዲሁም የመንግስት መ/ቤቶች
በሽታን ለመከላከል አገልግሎት ላይ የሚውል ማንኛውንም ዕቃዎች እና መድሃኒቶች ይጨምራል፡፡ለምሳሌ የህክምና
ዕቃዎች የሚባሉት የደም ናሙናዎች ለመቀበያነት የሚያገለግሉ መስታወቶችና መርፌዎችን ይጨምራል፡፡
ኦፕራሲዮን ክፍል ውስጥ የሚለበስ ልብስ እና ጓንት ጨምሮ የስራ ልብሶች በወጪ መደብ 6211 ‹‹ የደንብ ልብስ፤
የስራ ልብስ፤ፍራሽና አልጋ ልብስ›› በሚለው ሥር ይመደባሉ ለምሳሌ መድኃኒት የሚባሉት ፔኒስሊን፤ክሎሮኪን እና
ቴታነስን ይጨምራል፡፡ ለሆስፒታሎች ፤ለጤና ጣቢያዎች ፤ለጤና ማዕከሎች እና ለሕክምና ላብራቶሬዎች የስራ
ማከናወኛ የሚያገለግሉ አላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶችን ለመግዛት የሚወጣው ወጪ ሁሉ በዚሁ የወጪ መደብ ስር
ይመዘገባል፡፡ አንደማይክሮስኮፕ፤ ራጂ፤ ማቀዝቀዣ ያሉ መሳሪያዎችን ለመግዛት የሚወጣውን ወጪ ሁሉ በወጪ
መደብ ቁጥር ‹‹6313›› የፕላንት የማሽነሪ እና የመሳሪያ ግዥ በሚለውስር ይመዘገባል፡፡
6215 አላቂ የትምህርት መሣሪያዎች
ይህ የወጪ መደብ በመማር ማስተማር ተግባር በማመሳከሪያነት የሚያገለግሉትን የተፃፈ፤ በጆሮ የሚደመጡ እና
በዓይን የሚታዩትን ሁሉ ይጨምራል፡፡ ለትምህርት መሣሪያዎች ምሳሌ ሲሆኑ የሚችሉ መማሪያ መፃሕፍትን፤
ማመሳከሪያ መፃሕፍትን፤ ጆርናሎችን መድሃኒቶችን ጋዜጣዎችን፤ጠመኔ፤ ወረቀት፤እርሳስ፤ መዛግብት፤ የሥነ ጥበብ
እቃዎች ወዘተ ይጨምራሉ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የሚያሳትማቸው የመማሪያ መፅሐፍት በዚህ የወጪ መደብ
ይካተታሉ፡፡ እንደ ፕሮጀክተር፤ቴሌቭዥን፤የቪዲዮ መሳሪያዎች፤ የፎቶ ኮፒ ማሽን ያሉ ለትምህርት አገልግሎት
የሚወሉ መሳሪያዎች በወጪ መደብ 6313 ‹‹የፕላንት የማሽነሪ እና የመሣሪያ ግዥ›› በሚለው ሥር ይመደባሉ፡፡
6216 ምግብ
ይህ የወጪ መደብ በሆስፒታሎች ውስጥ ተገኝተው ለሚታከሙ ህሙማን፣ በወይኒ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ
እሥረኞች እና በትምህርት ተቋማት ውስጥ ላሉ ተማሪዎች የሚውለው ምግብ ይጨምራል፡፡ በአደጋ ጊዜ ወይንም
በአደጋ ጊዜ ወይም ለምግብመጠባበቂያ ክምችት በብዛት የሚገዛው ወይም በእርዳታ የሚገኘው ምግብ በዚህ የወጪ
መደብ ስር ሳይሆኑ በወጪ መደብ 6281 ስር ይጠቃለላል፡፡
ይህ የወጪ መደብ በችርቻሮ እና በጅምላ የሚገዛውን ነዳጅ እና ቅባት ያካትታል፡፡ ለጋራ አገልግሎት ለሚውሉ
ማደያዎች በጅምላ የሚገዛው ነዳጅ እና/ ቅባት ወይም ለጄነሬተሮች የሚገዛው ነዳጅ ለዚህ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ይህየወጪ መደብ ሌሎች ማንኛቸውንም አላቂ እቃዎችን ወይም አቅርቦቶችን ያካትታል፡፡የሚከተሉትን በምሳሌነት
ሊጠቀሱ ይችላሉ፤ የእንስሳት መኖ እና የጽዳት እቃዎች /ሳሙና፤ የመፀዳጃ ቤት መርዞች፤ ቡሩሾች ወዘተ/
ይህ የወጪ መደብ ዋጋቸው ከብር 200 በታች የሆነ ወይም በመደበኛ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት የሚሰጡ
መሣሪያዎች ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ አነስተኛ የእጅ መሣሪያዎች እና እንደ
ስቴፕር ያሉ የቢሮ መሳሪያዎች፡፡
ይህ የወጪ መደብ የመንግስት የግብርና፤ የደን፤የባህር እና ምርትን ለማምረት ተቋሞች የሚጠቀሙባቸው ግብዓቶች
ሁሉ ይጨምራል፡፡ የሚከተሉትንበምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፤ ማዳበሪያ፤ዘር፤ተባይማጥፊያ እና የግብርና፤ የደን እና
የባሕር ሀብት ምርቶችን የሚረዱ የመንግስት ተቋማት የሚጠቀሙባቸው ሌሎች ማናቸውም ግብዓቶች፡፡እንዲሁም
በምርት ማምረት ላይ የተሰማሩ የመንግስት መ/ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ግብዓቶች ያካትታል፡፡
6222 የእንስሳት ህክምና አላቂ እቃዎች እና መድሃኒቶች
ይህ የወጪ መደብ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት ተቋሞች የሚጠቀሙባቸውን የእንስሳት
ህክምና አቅርቦቶች እና መድሃኒቶች ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ሰው ሰራሽ ዘር
ማራቢያ መሳሪያዎች፤ ስሪንጅ እና የዘር ማስቀመጫዎች ፡፡
ይህ የወጪ መደብ በፖሊስ ሠራዊት፣ በሕዝብ ፀጥታ ሠራተኞች እና በመከላከያ ሰራዊት የሚገዙትን ጥይቶች እና
የጦር መሣሪያዎች ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የቀላል መሣሪያ ጥይቶች፤ የመድፍ
ጥይት እና ተወንጫፊ መሳሪያዎች፡፡
ይህንዑስየወጪክፍልየመንግስትሠራተኞችከሚያደርጉትጉዞጋርየተያያዙወጪዎችንየሚያጠቃልልሆኖየሚከተሉትንአይጨምርም፤የወ
ጪመደብ 6241 ‹‹የተሸከርካሪእና የሌሎች መጓጓዣዎች እድሳት እና ጥገና›› እና የወጪ መደብ 6217 ‹‹
ነዳጅ እና
ቅባቶች›› የመስተንግዶ አገልግሎት ወጪ የሚመለከተው ከመንግስት ሥራ ጋር የተያያዘውን ብቻ ነው፡፡
6231 ውሎ አበል
ውሎ አበል ማለት ጎዞ ለሚያደርጉ የመንግስት ሠራተኞች የሚከፈል መጠኑ የተወሰነ ክፍያ ሲሆን፤ የመኝታ፤ የምግብ
እና ተጓዳኝ ወጪዎች ያጠቃልላል፡፡
ይህ የወጪ መደብ ቀጥተኛ የሆነ የመጓጓዣ ወጪዎችን ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
የአውሮፕላን ትኬቶች፤ የአውቶቢስ ወጪ፤ የታክሲ ወጪ፤ የኮቴ ክፍያ እና የጓዝ ማዘዋወሪያ ክፍያ፡፡ ይህ የወጪ
መደብ፤ በወጪ መደብ 6217 ነዳጅ እና ቅባት በሚለው ስር የሚጠቃለሉትን የተሸከርካሪዎች ማንቀሳቀሻ ወጪዎች
እንዲሁም በወጪ መደብ 6241 የተሽከርካሪዎች እና የሌሎች መጓጓዣዎች እድሳት እና ጥገና እና በወጪ መደብ
6242 የአውሮፕላን እና የጀልባዎች እድሳት እና ጥገና ስር የሚካተቱትን የመጓጓዣ ወጪዎች የሚመለከት
አይደለም፡፡
6233 መስተንግዶ
ይህ የወጪ መደብ ለመንግስት ሥራ ለሚመጡ እንግዶች የሚደረግን መስተንግዶ የሚያካተት ነው፡፡ የሚከተሉት
በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ለውጭ የልዑካን ቡድን ወይን ከሀገር ውስጥ የመንግስት ሥራ በተያያዘ ለሚዘጋጅ
መስተንግዶ /ለምግብ፤ ለመጠጥ፤ ለመታሰቢያ ስጦታ እና ከዚህ ጋር ለሚዛመድ ሌሎች ጉዳዮች/ የሚወጣ ወጪ
ይካተታል፡፡
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍል ለተሸከርካሪዎች እና ለሌሎች መጓጓዣዎች/ ለምሳሌ ለሞተር ብስክሌቶች፤ ለብስክሌሎቶ/
ለአውሮፕላን፤ ለጀልባ፤ ለፕላንት፤ ለማሽን፤ ለመሳሪያ፤ ለሕንፃ፤ ለመሰረተ ልማት አውታር እድሳት እና ጥገና
የሚደረገውን ወጪ ያካትታል፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች በመንግስት ወይም በግል ድርጅቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ እድሳት
የጉልበት እና የዕቃ/ መለዋወጫን ጨምሮ/ ዋጋን ያካትታል፡፡ የጥገና አገልግሎት ቀላል እና ከፍተኛ ጥገናን
ይጨምራል፡፡
ይህ የሚከተሉትን ወጪዎች ይጨምራል፡፡ የእድሳት እና የጥገና ዕቃዎች ግዥ፤ የወለል ዕድሳት፤ የአጥር ዕድሳት፤
የቤት ዕቃዎች ዕድሳትእና በቤት ውስጥ የሚገጠሙ ልዩ ልዩ ነገሮች ዕድሳት፡፡
ይህ የወጪ መደብ የመንገድ፤ የግድብ፤ የአውሮፕላን ማረፊያ መንገዶች ማስተናገጃ፤ የድልድይ፤ የውሃ ቦይ፤ የመኖ
ሥራ፤ የፍሳሽ ማስወገጃ እና የሌሎች መሠረት ልማት አውታሮች ቀላል እና ከፍተኛ ዕድሳትን ይጨምራል፡፡
6246 የወታደራዊ መሣሪያዎች ዕድሳት እና ጥገና
ይህ የወጪ መደብ የማንኛቸውንም ወታደራዊ መሣሪያዎች ዕድሳት እና ጥገና ያካትታል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት
ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡የወታደራዊ የጭነት መኪናዎች፤ የታንኮች፤ የተሽከርካሪዎች መደበኛ ዕድሳት እና የጠመንጃ ጥገኛ
ወ.ዘ.ተ
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍል በሀገር ውስጥ ወይም በውጭ አገር ከግለሰቦች ወይም ከድርጅቶች የሚፈፀም ማንኛውንም
የአገልግሎት ግዥ የሚመለከት ነው፡፡ የሕትመት ውሎች እና የምክር አገልግሎት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ይህ የወጪ መደብ በንግድ ሥራ ከተሰማሩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በመንግስት ባቤትነት ስር ወይም ከመንግስት
ውጪ ካሉ ተቋሞች ጋር የሚደረግን የሙያ አገልግሎት ውል ያካትታል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
የምክር አገልግሎት፤ ጥናት፤ የሕክምና ምርምር፤ በመንግስት መ/ቤቶች የሚከናወን የካርታ እና የቅየሳ ሥራ
እንዲሁም የምህንድስና ምክር አገልግሎት፡፡ ከዚህም ሌላ የመረጃ ክትትል የሚደረግ ወጪን ይጨምራል፡፡
6252 ኪራይ
ይህ የወጪ መደብ ለቋሚ ንብረት በጥሬ ገንዘብ የሚከፈል የኪራይ ወጪን ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት
ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ኮምፒውተሮች፤ ማሽን፤ ህንፃ እና የመሰረተ ልማት አውታሮች ሊዝ/ ለምሳሌ ወደብ እና
መጋዘን/
6253 ማስታወቂያ
በሕዝብ መገናኛ ዘዴዎች፤ በሬድዮ፤ በጋዜጣ እና በቴሌቭዥን ለሚነገር ማስታወቂያ የሚደረግ ማናቸውም ክፍያ
በዚህ የወጪ መደብ ስር ይጠቃለላል፡፡ ለክፍት የሥራ መደቦች፤ ለጨረታ እና ለተመሳሳይ ጉዳዮች የሚነገር
ማስታወቂያ የሚደረግ ክፍያ ለዚህ ዓይነቱ ወጪ በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
6254 ኢንሹራንስ
ከመንግስት ሥራዎች ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ልዩ ልዩ ወጪዎች የአገልግሎት ክፍያዎች በመባል ይታወቃል፡፡ እነዚህም
የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡፡ የባንክ ክፍያዎች/ በወጪ መደብ 6432 ‹‹ ለውጭ ዕዳ የወለድ እና የባንክ ክፍያ›› እና
በወጪ መደብ 6434 ለሀገር ውስጥ ዕዳ የወለድ እና የባንክ ክፍያ በሚሉት ውስይ ከሚካተተው የውጭና የሀገር
ውስጥ ብድር በስተቀር/ ኮሚሽን፤ የዳኝነት ክፍያ፤ የወኪሎች ክፍያ፤ የተሸከርካሪ ምርመራ እና ምዝገባ ክፍያዎች
፤የፓርኪንግ ክፍያ፤ የፖስታ ቴምብር፤ የጋዜጣና የመጽሔት አባልነት ክፍያ እዚህ ይካተታል፡፡
ለቴሌፎን፤ለቴሌክስ፤ ለፋክስ አገልግሎትና ለመስመር መዘርጊያ የሚደረጉ ክፍያዎች ይጨምራል፡፡ ተጨማሪ መስመር
ለማስዘርጋት ወይም ለማስፋፊያ የሚደረግ ክፍያ ወጪ መደብ 6324 ‹‹ የመሰረተ ልማት አውታር ግንባታ›› በሚለው
ስር ይጠቃለላል፤
ለውሃ፤ መስመር መዘርጊያ እና በሌሎች የአገልግሎት ክፍያ የወጪ መደቦች ያልተመለከቱት ክፍያዎች ያጠቃልላል፡፡
የፖስታ ሳጥን ኪራይ ክፍያን በእነዚህ የወጪ መደብ ስር ይጠቃለላል፡፡
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍያ ለመንግስት ሠራተኞች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚሰጠውን ስልጠና ያካትታል፤
ለሀገር ውስጥ ስልጠና የሚደረገውን ወጪ ይመለከታል፤ ለዚህም የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላል፡፡ ወደ
ስልጠናው ቦታ ለመሄድ እና ከስልጠናው ቦታ ለመመለስ ለሚደረግ የመጓጓዝ ወጪ፤ ለአሰልጣኖች ክፍያ፤ ለስልጠና
ለሚያገለግሉ ቁሳቁስ፤ ስልጠናው ለሚካሄድበት ቦታ ኪራይ፤ ለሠልጣኖች እና ለአሰልጣኙ ውሎ አበል እና
ሥልጠናውን ለማካሄድ ለሚስፈልጉ ለተጓዳኝ ወጪዎች፡፡ በተጨማሪም ለአንድ የመንግስት መ/ቤት ሠራተኛ
የሚፈፀም የትምህርት ቤት ክፍያ በዚህ የወጪ መደብ ስር ይጠቃለላል፤
ለውጭ ሀገር ለሚሰጥ ሥልጠና የሚደረግ ወጪን ይመለከታል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡ ወደ ስልጠናው
ቦታ ለመሄድ እና ከሥልጠናው ቦታ ለመመለስ የሚያፈልግ የመጓጓዣ ወጪ፤ የት/ቤት ክፍያ፤ ለሥልጠና የሚያገለግሉ
ቁሳቁስ ወጪ በት/ቤት ክፍያ ውስጥ ያልተጠቃለለ ከሆነ/ ለሠልጣኞች የውሎ አበል እና ወደ ስልጠናው ቦታ ጎዞ
በሚደረግበት ጊዜ እንዲሁም የሥልጠናው ፕሮግራም በሚቆይበት ጊዜያት የሚደረጉ ተጓዳኝ ወጪዎች፡፡
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍል ለመጠባበቂያ የሚቀመጥ እህል እና ለሀገሪቱ ልዩ ጠቀሜታ ላላቸው ሌሎች ሸቀጦች
የተደረገ መግዣ ቀጥታ ክፍያ እና/ ወይም እነዚህ እቃዎች ከመግዛት ወይም ከመረከብ ጋር በተያያዘ የተደረገውን
ወጪ እንዲሁም ገበያን የማረጋጋት ተግባር ያላቸው የመንግስ አካላት ለገዙዋቸው በመጋዘን ለሚገኙ ዕቃዎች
የተደረገውን ወጪ ይይዛል፡ በብዛት ለሚገዙ እህል እና ነዳጅ በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ይህ የወጪ መድብ
የሚያካትተው የሸቀጡን የፎብ ዋጋ ሲሆን፤ የትራንስፖርት፤ የመጋዘን እና የማከፋፈያ ወጪን መደብ 6252
‹‹ኪራይ›› ስር የሚጠቃለል ነው፡፡
ለመጠባበቂያ እህል ክምችት ግዥ የመውለውን ወጪ የሚመለከት ነው፡፡ የወጪ መደቡ የግዥውን ዋጋ እንጂ
የመጋዘን፤ የመጓጓዣ ወይም የማከፋፈያ ወጪን አይጨምርም፡፡
በመጠባበቂያነት በክምችት ለሚገኙ ሌሎች እቃዎች የወጣውን ወጪ ይመለከታል፡፡ የወጪ መደብ የግዥውን ዋጋ
እንጂ የመጋዘን፤ የማጓጓዣ ወይም የማከፋፈያ ወጪን አይጨምርም፡፡
ቋሚ ንብረት የሚባለው ከገበያ ውስጥ የሚገዙ ዕቃዎች ወይም ከመንግስት መ/ቤቶች ለሚመረቱ አዳዲስ ወይም
ነባር ቋሚ ንብረቶች የሚደረገውን ክፍያ ይጨምራል፡፡ ይህም የሚካትተው በመደበኛነት ከአንድ ዓመት በላይ
የሚያገለግሉ እና ዋጋቸውም ከብር 200 በላይ የሆኑትን እቃዎች ብቻ ነው፡፡ የዚህ ዓይነቶቹ ቋሚ ንብረቶች
የማንቀሳቀሱ ቋሚ ንብረቶች/ የመኖሪያ እ ለመኖሪያ የሚያገለግሉ ህንፃዎች፤ የመሰረተ ልማት አውታሮች፤ የቤት
ዕቃዎች እና በቤት ውስጥ የሚገሙ ልዩ ልዩ ነገሮች/ እንዲሁም የመጓጓዣ ተሸከርካሪዎችን እና እንስሳት፤ መሳሪያን
እና ማሽንን የሚካተቱ ተንቀሳቃሽ ዕቃዎች ቢሆኑም ዋጋቸው ከብር 200 በታች የሆኑ አነስተኛ የእጅ መሳሪያዎች
ናቸው፡፡እነዚህ መሣሪያዎች በወጪ መደብ 6219 ‹‹ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች›› በሚለው ስር መጠቃለል አለባቸው፡፡
የቋሚ ንብረቶች እና የግንባታ እቃዎች ግዥ ዋጋ ታክስ፤ ቀረጥ፤ ኢንሹራንስ እና ማጓጓዣን ጨምሮ ሌሎች
ቅንስናሾች ሳያደርጉ በጥቅል መታየት አለበት፡፡ ግንባታ ቋሚ ንብረት መስራት ይጨምራል፡፡
6310 ቋሚ ንብረት
ይህ ንዑስ የወጪ ክፍያ በመደበኛ ሁኔታ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት የሚጡና ዋጋቸው ከብር 200 በላይ የሆነ
ማናቸውንም ቋሚ ንበረቶች ይመለከታል፤ ተሸከርካሪ፤ መሳሪያ፤ የቤት እቃ እና በቤት ውስጥ የሚገጠሙ ልዩ ልዩ
ነገሮች ለዚህ በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ይህ የወጪ መደብ የመኪና፤ የሞተር ብስክሌት፤ የብስክሌት እና የተጎታች ተሸከርካሪ ግዢን ያጠቃልላል፡፡
ይህ የወጪ መደብ ለመታደራዊ አገልግት የማይውሉ አውሮፕላኖች እና ጀልባዎች ግዢን ይመለከታል፡፡ ለመታደራዊ
አገልግሎት የሚሉ አውሮፕላኖች እና ጀልባዎች ግዢ በወጪ መደብ 6316 ‹‹ የወታደራዊ መሣሪያ ግዥ›› በሚለው
ስር የሚካተት ነው፡፡
ለመንግስት አገልግሎት የሚውል የማናቸውንም ህንፃ፤ የቤት እቃ ወይም በቤት ለሚገጠሙ ልዩ ልዩ ነገሮች ግዢ
በዚህ የወጪ መደብ ስር ይጠቃለላሉ፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ለቢሮ ወይም ለመኖሪያ ወይም
ለሁለቱም አገልግት እንዲውል የሚገዛ ቤት፤ በውጭ እና በቤት ውስጥ የሚገጠሙ መብራቶች፤ የቤት እቃ፤ ምንጣፍ
እና መጋረጃዎች፤
ለእርባታ እና ለምርምር አገልግሎት የሚሉ የቁም ከብቶች እና ለመንግስት መጓጓዣ የሥራ እንቅስቃሴ የሚውሉ
እንስሳት ግዥ በዚህ የወጪ መደብ ሥር ይካተታል፡፡
ይህ የወጪ መደብ የወታደራዊ መሣሪያዎችን የሚያካትት ነው፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ቀላል
የጦር መሳሪያዎች ፣ መድፍ፣ ታንክ፣ የጭነት መኪና ፣ አውሮፕላን ፣ ጀልባ ወ.ዘ.ተ.
6320 ግንባታ
ይህ ንዑስ የወጪ መደብ የጉልበት እና የግንባታ ቁሳቁስን ጨምሮ ከቅድመ ግንባታ እና ከግንባታ ጋር የተያያዙ
ማናቸውንም ወጪ ይጨምራል፡፡
ለግንባታ ፕሮጀክት ዝግጅት የሚደረግ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት፤ ቅየሳ፤ የአዋጭነት ጥናት፤ የምህንድስና እና ሌሎች
የቴክኒክ ንድፎችን ወጪ ይመለከታል፡፡
ለሠራተኞች የመኖሪያ ህንፃ፤ ለመኖሪያ ቤት ሥራ ፕሮጀክት ወ.ዘ.ተ. የሚውለው ወጪ በዚህ የወጪ መደብ ውስጥ
ይካተታል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የመኝታ ህንፃ የሠራተኞች መኖሪያ ቤት እና ለመንግስት
ሠራተኞች መኖሪያ ቤቶች በሌሉበት አካባቢ የሚሰራ ካምፕ፡፡
ይህ የወጪ መደብ ለአስተዳደር ቢሮዎች እንዲሁም ለመጋዘኖች፤ ለመፅሐፍት ቤቶች፤ ለትምህርት ቤቶች፤
ለሆስፒታሎች፤ ለሙዚየሞች እና ለሀውልቶች ወ.ዘ.ተ. ግንባታ የወጣውን ወጪ የሚያካትት ነው፡፡
ይህ የወጪ መደብ ከህንፃዎች በስተቀር ማናቸውንም ሌሎች የመንግስት የግንባታ ሥራዎችን ያጠቃልላል፡፡
የሚከተሉትን በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ መንገድ፤ ድልድይ የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ፤ የውሃ ቦይ፤ የመስኖ
መስመሮች የፍሻስ ማስተላለፊያ መስመሮች፤ መናፈሻዎች፤ የስፖርት ሜዳዎች፤ አጥር ወ.ዘ.ተ
6325 ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ግንባታዎች
ይህ የወጪ መደብ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎችን፤ የመሰረተ ልማት አውታሮች እና መከላከያ
ምሽጎችን ለመገንባት የሚውለውን ወጪ ያጠቃልላል፡፡
ይህ የወጪ ክፍል መንግስት በገባው ግዴታ መሰረት ለሀገር ውስጥ ወይም ለውጭ ሀገር ተቋሞች ወይም ለግለሰቦ
በጥሬ ገንዘብ የሚከፈለውን ድጎማ፤ እርዳታ ወይም የብድር እዳ ይመለከታል፤
ይህ የወጪ መደብ ለክልሎች እና ለመስተዳድር ምክር ቤቶች በጥልቅ የሚተላለፈውን ገንዘብ ይመለከታል፤
ይህ ወጪ መደብነፃ የአስተዳደር አቋም ላላቸው ተቋሞች በጥሬ ገንዘብ የሚከፈለውን ክፍያ እንዲሁም መንግስታዊ
ላልሆኑ፤የማህበራዊ፤ የሀይማኖት እና የባህል ተቋሞች የሚሰጠውንና ዝርዝር የሂሳብ መግለጫ የማይቀርብበት
የገንዘብ እርዳታን ይጨምራል፡፡ ይህ የገንዘብ እርዳታ መንግስት ለበጎ አድራጎት ወይም ለሀይማኖት ድርጅቶች
የሚሰጠውን እርዳታ ያካትታል፡፡
ይህ የወጪ የወጪ መደብ የመንግስታት ህብረት ለሆኑ ድርጅቶች /ምሳሌ ለተባበሩት መንግስታት፤ ለአፍሪካ አንድነት
ድርጅት፤ ለአፍሪካ ልማት ባንክ፤ ዓለምአቀፍ የቴክኒክ ድርጅቶች (የፖስታ ህብረት) እና ለዓለም ዓቀፍ የሙያ፤
የሣይንስ እና የባህል እድገት ድርጅቶች የሚደረገው መዋጮ ያካትታል፡፡
6415 መጠባበቂያ
ይህ የወጪ መደብ የገንዘብ ሚኒስቴር ብቻ እንዲጠቀምበት የተተወ ነው፡፡ የወጪ መደብ ሳይደለደል በጥቅል
የተቀመጠ በጀት ሆኖ፤ ላልታሰቡ ወጪዎችና ለዕዳ ሥረዛ መሸፈን የሚያገለግል ነው፡፡
በመንግስት ወይም በፍርድ ቤት በተወሰኑ የተለያዩ ጉዳዮች ለግለሰቦች፤ ለቡድኖች እና ለድርጅቶች ካሣ ለመክፈል
የሚደረገውን ወጪ ይመለከታል፡፡ ለዚህ ምሳሌ የሚሆነ መንግስት ለተለያዩ አገልግሎቶች ከግለሰብ ለሚፈልገው
መሬት የሚከፈል ካሣ ነው፡፡ካሣማለት ግለሰብ ወይ ድርጅት ለደረሰበት ኪሳራ በሕግ ወይም በሞራል ግዴታ ምክንያት
የሚከፈል ገንዘብ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ‹‹ ዳረጎት›› ይባል የነበረው የወጪ መደብ በዚህ ውስጥ ተካቷል፡፡
ይህ የወጪ መደብ በመንግስ ለተፈቀደለት ግለሰብ የሚደረገውን እርዳታ ይጨምራል፡፡ የሚከተሉት በምሳሌነት
ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ለዓይነ ሥውራን ተማሪዎች፤ በውጭ ሀገር ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች የሚሰጥ
እርዳታ እና ለሳይንስ ተመራማሪዎች እና ለስፖርተኞች የሚሰጥ ማበረታቻ እንዲሁም ለሌሎች ግለሰቦች
ከመንግስት የሚሰጥ ሽልማት፡፡
ይህ መለያ ቁጥር ለዕዳ ክፍያ እና ለቋሚ ሃብቶች መተኪያ እንዲውል ለሚቋቋመው የጥሪት ፈንድ የሚደረገውን
መዋጪ ይመለከታል፡፡
6419 ልዩ ልዩ ክፍያዎች