Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 10

¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

4 ኛ
ትምህርት ከጥር 9-15 2007 ዓ.ም

መለኮታዊ ጥበብ

ን ት ከሰዓት
ሰንበት

ለዚህ ሳምንት ጥናት ምሳሌ 8፡1-21፣ ማቴ. 16፡26፣ ምሳሌ 8፡22-31፣ ዘፍጥረት
1፡31፣ ምሳሌ 8፡32-36፣ ምሳሌ 9፡1-18ን ያንብቡ፡፡

መታሰቢያ
ቢ ጥቅስ፡-
ስ “እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ
በቀድሞ ስራው መጀመሪያ፡፡” ምሳሌ 8፡22

እ ዚህ ጋ በምሳሌ መጽሐፍ ጥበብ እንደገና ትመጣለች (ምሳሌ 1፡20-21)፡፡


እናም ከዚህ ሳምንት ጥቅሶች በግልጽ እንደምንረዳው ጥበብ እውነት ነው፡-
የእውነት ሁሉ ምንጭና መሠረት በሆነው በእግዚአብሔር ያለ እውነት፡፡

ይህ “ፍፁም” የሆነው የእውነት ባህሪ ዘመናዊ ከሆኑ አስተሳሰቦች ጋር ይጋጫል፡፡


በተለይም በምዕራቡ ዓለም ማለትም እውነት እንደ አንፃራዊ፣ ተለዋዋጭ፣ በየባህሉ
የሚለያይ፣ የአንድ ሰው እውነት ከሌላው የሚለይ በሆነበት ዓለም ማለት ነው፡፡

ይህ ጽንሰ-ሀሳብ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ የእኔ እውነት ከእናንተ እውነት


ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም በቀላል አማርኛ “እውነት” አለም

መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም


37
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

አቀፋዊ ስለሆነ ነው፡፡ ለአንድ ሰው ብቻ የተለየ ሳይሆን አስተዋሉትም


አላስተዋሉትም ለሰብአዊ ዘር ሁሉ የተሰጠ ነው፡፡

አስገራሚው ነገር ጲላጦስ ኢየሱስን የጠየቀው ታዋቂው ጥያቄ “እውነት ምንድን


ነው?” (ዮሐንስ 18፡38) ኢየሱስ “ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል” (ዮሐንስ
18፡37) ብሎ ለተናገረው ቃል የተሰጠ ምላሽ መሆኑ ነው፡፡ እውነት ማለትም ፍፁም
የሆነ እውነት አለ፤ እኛንም ይናገረናል፡፡ ለእኛ የሚጠቅመን ግን መስማት ወይም
አለመስማታችን እና የተባልነውን መታዘዛችን ነው፡፡

ለጥር 16 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ፡፡

እሁድ
ሁ ጥር 10 2007 ዓ.ም

ጥበብ ትጮሃለች

ምሳሌ 8፡1-
8፡1-21ን
211ን ያንብቡ፡፡
ን በነዚህ
ነዚ ጥቅሶች መሠረት የጥበብ ዋጋ ምን ያክል
ሶች መ ክ ነው?
ነው?

__________________________________________________
__________________________________________________

ጥበብ እጅግ አስፈላጊ ከመሆኗ የተነሳ ሁሉም ሰው ጋ ልትደርስ ይገባታል፡፡


እግዚአብሔር ሰብአዊ ዘርን ሁሉ ፈጥሯል፡፡ ክርስቶስም ለእያንዳንዳችን
ሞቶልናል፡፡ ስለዚህ ጥበብ ማለትም እግዚአብሔርንና የሰጠንን ማዳን ማወቅ
ለሁሉም ሰብአዊ ዘር የተሰጠ ነው፡፡

የጥበብን አጠራር ለመግለጽ የተጠቀመባቸውን ቃላት ይመልከቱ፡- “መጮህ”፣


“ድምጽን ከፍ ማድረግ”፣ “መጣራት”፣ “ድምጽ”፣ “መናገር”፣ “አፍን መክፈት”፣
“ከንፈር”፣ “ቃላት”፡፡ አንድ ሰው እነዚህን ዘይቤያዊ አገላለፆች በየትኛውም መንገድ

መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም


38
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ቢረዳቸው ግልጽ መሆን ያለበት ነገር ጥበብ ልናስተላልፈው የሚገባ ነገር ነው፤
መስማት ለሚችሉ ሁሉ ሊነገር ይገባዋል፡፡ ደግሞም ባለፈው ሳምንት እንዳየነው
ጥበብ የምትናገረው የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው፡፡

ስምንት ጊዜ ጥበብ ስለ ቃሎቿ እውነተኛነት ትናገራለች፡፡ እዚህ ጋ ያለው የጥበብ


አገላለፅ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ዘዳግም 32፡4 ላይ ስለ አምላካችን ካለው አገላለፅ
ጋር ትይዩ ነው፡፡ ይህ መመሳሰል በእርግጥም ሊያስደንቀን አይገባም ምክንያቱም
እግዚአብሔር የሁሉም ነገር ፈጣሪ እንደመሆኑ (ዮሐንስ 1፡1-3) የእውነት ሁሉ
መሠረት ነው፡፡

ምሳሌ 8፡10፣
8፡10 11 ያንብቡ፡፡
ያ ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች
ቅ ስለ ጥበብ
በ ምን ይናገራሉ?

__________________________________________________
__________________________________________________

ብዙዎች በቸልተኝነት፣ በአለማወቅና በጨለማ እስከዛሬ ኖረዋል፤ እየኖሩም ነው፡፡


ብዙ ሰዎች ያለ ምንም ተስፋ ወይም ከሐሰተኛ ተስፋዎች ጋር እየኖሩ ነው፡፡ ይህንን
የሚያሳዝን ሁኔታ የበለጠ አሳዛኝ የሚያደርገው ደግሞ ጥበብና እውነት እጅግ ውብ
በዚህም ምድር ሆነ በአዲስ ሰማይና በአዲስ ምድር ውስጥ ለዘላለም የመኖርን
ዋስትና በያዙ ተስፋዎችና ቃል ኪዳኖች የተሞሉ ናቸው፤ ለኢየሱስ መስዋዕትነት
ምስጋና ይሁን!፡፡ እግዚአብሔርን ከማወቅ ጋር ሲነፃፀር በዓለም ያለው ሀብት ሁሉ
(መክብብ 2፡11-13 ይመልከቱ) ምንም ማለት አይደለም፡፡

ማቴ. 16፡26ን ያንብቡና የነዚህን ቃላት ወሳኝ እውነት ህይወትዎ የሚያንፀባርቀው


ምን ያክል እንደሆነ ራስዎን ይጠይቁ፡፡

መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም


39
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ሰኞ ጥር 11 2007 ዓ.ም

ጥበብና
ጥ ና ፍጥረት
ፍጥ ት
ምሳሌ
ምሳ 8፡22--31ን ያንብቡ፡፡
፡ ጥበብና ፍጥረት የሚገናኙት
ሚገ እንዴት ነው?

__________________________________________________
__________________________________________________

በነዚህ ጥቅሶች ጥበብ ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ከፈጣሪያችን ጋር ተገናኝቷል፡፡ ይህ


ግጥም በዘፍጥረት 1 እና 2 ላይ ስለ ፍጥረት ከተፃፈው ጋር ብዙ ቃላትን ይጋራል፡፡
እንዲሁም በሶስቱ መሠረታዊ አካላት በሰማይ፣ ውሃና የብስ (መሬት) ዙሪያ
የተቀናጀውን ስነ ፅሑፋዊ ውህደት ይገልፃል፡፡ የዚህ መመሳሰል አላማ የጥበብ
ከፍተኛ ሚና ላይ ማተኮር ነው፤ ማለትም እግዚአብሔር ራሱ ለመፍጠር ጥበብን
ከተጠቀመ፣ ጥበብም የጥንት መሳሪያ ከሆነች፣ ከራሱ ከዩኒቨርስ በላይ ከመፈጠሩም
በፊት ከነበረች እኛም በህይወታችን በምናደርገው ሁሉ ጥበብን የበለጠ ልንጠቀም
ይገባል፡፡

ስለ ጥበብ መለኮታዊ ምንጭም ጠንካራ ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡ የግጥሙ


የመጀመሪያው ቃል ጌታ፣ ያህዌ የጥበብ መገኛ ሆኖ የተገለጠው ነው፡፡
የእብራይስጡ qanah ቃናህ በእንግሊዝኛው “መያዝ” ተብሎ የተተረጎመው
ከ”መፈጠር” ይልቅ “የራስ መሆን”ን የሚያመለክት አንድምታ አለው (ዘዳ. 32፡6፣
ዘፍ. 4፡1ን ይመልከቱ)፡፡ ቀጣዩ ቃል ከዘፍጥረት መጽሐፍ የአፈጣጠር ታሪክ ጋር
ማለትም ከዘፍጥረት የመጀመሪያው ቁጥር “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና
ምድርን ፈጠረ” በሚለው ውስጥ የሚገኘው ሬሺት (“መጀመሪያ”) የሚለው ቃል
ነው፡፡

ሆኖም “መጀመሪያ” የሚለው ቃል በዘፍጥረት 1 ላይ ከተጠቀሰበት መንገድ በተለየ


መልኩ ነው በምሳሌ 8፡22 ላይ የተጠቀሰው፡፡ በዘፍጥረት 1፡1 ቃሉ ከፍጥረት ታሪክ
ጋር የተገናኘ ሲሆን በምሳሌ 8፡22 ላይ ግን ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ጋር
40 መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ማለትም ከመንገዱና ከማንነቱ ጋር ተገናኝቷል፡፡ ስለዚህ ጥበብ የእግዚአብሔር


ማንነት አካል ነች፡፡

ስለዚህ ጥበብን በጊዜ ውስጥ ብናስቀምጣት ዓለም ከመፈጠሩ በፊትም እንደነበረች


እንረዳለን፡፡ እግዚአብሔር ብቻ በነበረበት ጊዜ ጥበብ መገኘቷ የጥበብን
“ዘላለማዊነት” እንድናስተውል ይረዳናል፡፡

ስለዚህ ጥበብ ከእኛ የተገኘች ሳትሆን ለእኛ የተገለጠች፣ የምንማራት ነገር ነች፡፡
ከራሳችን ያፈለቅናት ነገር አይደለችም፡፡ በእርግጥም በራሳችን ብርሃን መራመድ
ማለት በጨለማ መመላለስ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ “ለሰው ሁሉ የሚያበራው
እውነተኛው ብርሃን” (ዮሐ. 1፡9) መሆኑን ሰምተናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ይህ ብርሃን
ያስፈልገዋል፡፡

ማክሰኞ
ክ ጥር 12 2007 ዓ.ም

በተፈጥሮ መደሰት

በዘፍጥረት 1 እያንዳንዱ የፍጥረት ደረጃ “እግዚአብሔርም መልካም እንደሆነ አየ”
በሚል ሀረግ ይደመደማል (ዘፍ. 1፡4፣ 10፣ 12፣ 18፣ 21፣ 25፣ 31)፡፡ የመጨረሻው
ደረጃ (ቁ. 31) የበለጠ ሄዶ “እጅግ መልካም ነበር” ሲል እንመለከታለን፡፡ “መልካም”
የሚለው ቃል እብራይስጡ የመደሰትን ሃሳብና ግንኙነትን ያመለክታል፡፡ በፍጥረት
ሳምንት መጨረሻ እግዚአብሔር በፈጠረው ለመደሰት ቆም ብሏል (ዘፍ. 2፡1-3)፡፡
ይህ የእረፍት ጊዜ-- ሰንበት የተባረከ ነው፡፡ እንደዚሁ ይህ የስንኝ ቋጠሮም
የሚደመደመው ጥበብ በፍጥረት ሲደሰት ነው፡፡

ምሳሌ 88፡30፣31ን
3 ፣ 1 ያያንብቡ፡፡
፡፡ የጥበብ
በብ መደሰት ምክንያቱ ምንድን ነነው?
ቱ ምን ነው?
__________________________________________________
__________________________________________________

መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም


41
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

የጥበብ መደሰት እግዚአብሔር በተፈጥሮ ያለውን ደስታ ያንፀባርቃል፡፡ ይህ ደስታ


በእያንዳንዱ የፍጥረት ስራ መጨረሻ “በየቀኑ” ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ስራ ሲጠናቀቅ
ደግሞ ስራውን ከብቦት ነበር፡፡

በምሳሌ 8 የጥበብን የደስታ ምክንያት እናገኛለን “ደስታዬ በሰው ልጆች ነበረ” (ቁ.
31) በፍጥረት ሳምንት መጨረሻ በሰንበት እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ግንኙነትን
ጀመረ፡፡ “የፈጣሪን መንገድ በመከተል የተፈፀመውን ስራውን በደስታና በእርካታ
ወደኋላ ሊያይ ይችላል፡፡ በዚህ መንገድ ሰው በእግዚአብሔር ፍጥረት እንዲሁም
ለማበላሸት ሳይሆን ለማስተዳደር በተሰጠውም ሃላፊነት ሊደሰት ይችላል፡፡
“Gerhard F. Hasel in Kenneth A.strand, The Sabbath in scripture (Review
and Herald publishing Association, 1982) ገጽ 23፡፡

ቆላስያስ 1፡15-
፡ 5 177፣ 2፡3፣
2 ራዕይ
ራ 3፡14
፡ 4 እና ዮሐ.
ሐ 1፡1-14
14ን ያንብቡ፡፡
ብ እነዚህ
ዚ ጥቅሶች
ኢየሱስ
ሱስ በፍጥረት ስራ ውስጥ ስለነበረው በረ ሚና ምን ይነግሩናል?
ይነግሩናል? የእርሱን
እር የአዳኝነት
የ ነ
ሚና ለመረዳት
ረ ት የፈጣሪነት
የ ት ሚናው
ሚና እጅግጅግ ጠቃሚ የሆነው
ሆነ ለምንድን ድ ነው??

__________________________________________________

ረቡዕ ጥር 13 2007 ዓ.ም

የጥበብ
ጥ ጥሪሪ
የዚህ ምዕራፍ የመጨረሻ ቁጥሮች ወደ ግል ጉዳዮች ይመለሳሉ- ጠቢብ መሆን
ማለት ምን እንደሆነ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ አቅጣጫዎችን ያሳያሉ፡፡ በሌላ
በኩል ደግሞ ጥበብ ከጥንት ጀምሮ የነበረች መሆኗ በፍጥረትም ሂደት መሳተፍዋን
ማወቅ በእርግጥም ጥልቅ ነው፡፡ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ሁልጊዜም ቢሆን
እውነት ወደ ሰብአዊ ዘር ደረጃ እንዲሁም በኢየሱስ ለተሰጠን ነገር እንዴት ምላሽ
እንደምንሰጥ በመንገር ሊወርድ ይገባዋል፡፡

42 መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም


¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ምሳሌ 8፡3
8፡32-
8፡32-36ን
36ን ያንብቡ፡፡
ን እዚህ ጋ ምን ዓይነት የህይወትና
እዚ ህ ወ የሞት መልዕክት
ክ ነው
የተሰጠን?
__________________________________________________
__________________________________________________

“ብፁዕ” ተብሎ የተተረጎመው የእብራይስጡ ጥሬ ቃል “ደስተኛ” ማለት ነው፡፡


በዚህ አንቀጽ “ብፁዕ” የሚለው ቃል ከሁለት ሁኔታዎች ጋር ተገናኝቷል፡፡
የመጀመሪያው ድርጊትን ይገልፃል፡፡ “መንገዴን የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው” (ቁ.
32)፡፡ በመዝሙር 119፡1-2 ላይ ከህጉ ጋር አያይዞ ተመሳሳይ አገላለፅን ይጠቀማል፡-
“በመንገዳቸው ንፁሐን የሆኑ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ብፁዓን ናቸው፡፡
ምስክሩን የሚፈልጉ በፍጹም ልብ የሚሹት ብፁዓን ናቸው፡፡”

ሁለተኛው ደግሞ አመለካከትን ይገልጻል፡- “የሚሰማኝ ሰው ብፁዕ ነው፡፡” (ቁ 34)


፡፡ በሁለቱም ሁኔታዎች የማያቋርጥ ጥረት እንደሚያስፈልግ እንመለከታለን፡፡
ትክክለኛውን መንገድ ማግኘት ብቻውን በቂ አይደለም ልንጠብቀው ይገባናል፡፡
የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ብቻውን በቂ አይደለም “በየቀኑ ተግተን”
በምናውቀው ልንኖር ይገባናል፡፡ ልክ ኢየሱስ እንደተናገረው “ብፁዓንስ
የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው” (ሉቃስ 11፡28)፡፡

“ይህ ደስታ ባለመታዘዝና የአካልንና የግብረ ገብን ህግ በመተላለፍ መንገድ የሚገኝ


ነውን? የክርስቶስ ሕይወት የደስታን እውነተኛ ምንጭ አሳይቶ እንዴት ልናገኘው
እንደምንችልም ይገልፃል፡፡ … በእርግጥ ደስተኛ መሆን የፈለጉ በጌታ የስራ ገበታ
ላይ በደስታ ሊገኙ፣ በታማኝነት ወደ እነርሱ የደረሰውን ስራ ልባቸውንና
ህይወታቸውን ከትክክለኛው መንገድ ጋር አዋህደው ሊሰሩ ይገባቸዋል፡፡ “Ellen G.
White, My Life Today” pg. 162

ደስታ አታላይ
ላይ ልትሆንን ትችላለች፤
ላለ ልናገኛት
ገ የበለጠ በተጋን
ጋ መጠን ለማግኘትግ
እየከበደን ይሄዳል፡፡
ዳል ደስታንታ ከመጠማት በተቃራኒ ለእግዚአብሔር
ለእ ዚ ር ታማኝ
ኝ መሆን
ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባ ተግባር
ተ መሆን ያለበት ለምንድንነው?
ድ ው ደግሞስግ ስ ደስታን
መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም
43
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

የበለጠ ሊሰጠን የሚችለው ው የቱ


የ ነው፡-
ው - ደስታን መ
ነው፡ መፈለግ
ግ (መሻት)
ሻ ወይስ
የእግዚአብሔርን መንግስት
ስት በቅድሚያ
ቅ መሻት?
ት ለምን?

ሐሙስ ጥር 14 2007 ዓ.ም

ወይ ይሄንን አልያም
ልያ ያንን

ከጥበብ ጥሪ በመቀጠል የምሳሌ 9 ፀሐፊ አንባቢዎቹን ከሁለቱ የህይወት መንገዶች
አንዱን እንዲመርጡ ይጠይቃል፡፡ ጥበብን ወይም ስንፍናን፡፡ የመጀመሪያዎቹና
የመጨረሻዎቹ ስድስት ቁጥሮች (ምሳሌ 9፡1-6፣ 13-18) ተመሳሳይ አካሄድ
(Symmetrical) ያላቸው እና በሁለቱ ጎራዎች መካከል ያለውን ልዩነት ይገልፃሉ፡፡

ምሳሌ 9፡1-6
1 ንና ምሳሌ
ምሳ 9፡13-18
፡1 ን ያነፃፅሩ፡፡
ነፅ በጥበብና በስንፍና(በሞኝነት) መካከል
ያለው ልዩነት
ዩ ት ምንድን
ን ነው?

__________________________________________________
__________________________________________________

ጥበብ ውጤታማና በፍጥረት ስራ ላይ የተሳተፈች ናት፡- ይህንን ተግባሯን


ለመግለጽ ሰባት የድርጊት ገላጭ ቃላትን ተጠቅሟል (ከቁጥር 1-3)፡፡ የገነባቻቸው
ሰባት ምሰሶዎች (ቁ. 1) ሰባቱን የፍጥረት ቀናት ያመላክታል፡፡ ስንፍና በተቃራኒው
ምንም ሳትሰራ ቁጭ ብላ ደህና ሰው ለመምሰል ብትሞክርም እውነታው ግን “አሳብ
የላትም፤ አንዳችም አታውቅም፡፡”

ጥበብና ስንፍና ተመሳሳይ ሰዎችን እየጠሩ ቢሆንም (በቁ. 4 እና 16 መካከል


ያለውን መመሳሰል ልብ ይበሉ) የሚሰጡት ነገር ግን የተለያየ ነው፡፡ ጥበብ
ያዘጋጀችውን እንጀራና ወይን እንዲበሉና እንዲጠጡ እንግዶቿን ትጋብዛለች
(ቁ. 5)፡፡ ስንፍና የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገርን ሳታቀርብ በተሰረቀ ነገር
ትኮፈሳለች (ቁ. 17)፡፡

44 መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም


¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ጥበብ ሞኝነትን ትተን በውጤቱ ህይወት እንዲሆንልን ትመክረናለች፡፡ ስንፍና


የበለጠ ታጋሽ ሆና ምንም ነገር እንድንተው አትጠይቀንም ነገር ግን ውጤቷ ሞት
ነው፡፡ ጥበብን የሚከተሉ እያደጉ “በማስተዋል መንገድ” ይሄዳሉ (ቁ. 6)፡፡ ስንፍናን
የሚከተሉ ባሉበት የሚቆዩና “ምንም የማያውቁ” ይሆናሉ (ቁ. 18)፡፡

ምሳሌ 9፡7--9 ያንብቡ፡፡ ጠቢቡ


ጠ ሰውና ፌዘኛው ሰው ለጥበብ ምክር
ምክ ምላሽ
የሰጡት እንዴት ነበር? ጠቢቡን
ቢ ሰው
ሰ ከፌዘኛው ይልቅ
ል ጠቢብ
ቢ ያደረገው
ደ ገ ምንድን
ነው??
__________________________________________________
__________________________________________________

ወደ ጥበብ የሚወስደው ቁልፍ ነገር ራስን ዝቅ ማድረግ ነው፡፡ ጠቢቡ ሰው


ሲያስተምሩት የሚሰማና በተከፈተ ልብ መመሪያን የሚቀበል ነው፡፡ ጥበብ
የምትመጣው ልክ እንደ ትንሽ ልጅ የማደግ ፍላጎት ላለው ሰው ብቻ ነው፡፡
ለዚህም ነው ኢየሱስ “እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ ወደ መንግስተ ሰማያት ከቶ
አትገቡም፡፡” (ማቴ. 18፡3) ብሎ በግልጽ ያስተማረው፡፡

ዓርብ
ር ጥር 15 2007 ዓ.ም

ተጨማሪ ጥናት፡-
ና “የዓለማት ሁሉ ገዢ በፍጥረት ስራው ብቻውን
አልነበረም፡፡ አላማውን የሚጋራውና ለተፈጠሩት ፍጥረታት ደስታን በመስጠት
ደስታውን የሚካፈለው ረዳት ነበረው፡፡ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም
በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፡፡ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡”
ዮሐንስ 1፡1-2 ክርስቶስ፣ ቃል፣ የእግዚአብሔር አንድ ልጅ ከዘላለማዊው አብ ጋር
አንድ ነበረ፡- በህልውና፣ በባህሪ፣ በአላማ- በእግዚአብሔር ምክርና አላማ ውስጥ
የሚገባ ብቸኛ እርሱ ነው፡፡ . . . የእግዚአብሔር ልጅ ስለራሱ ሲናገር “እግዚአብሔር
የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ በቀድሞ ስራው መጀመሪያ፡፡ ከጥንቱ ከዘላለም ጀምሮ
ተሾምሁ፣ . . . የምድርን መሠረት በመሠረተ ጊዜ የዚያን ጊዜ እኔ በእርሱ ዘንድ ዋና

መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም


45
¾ÔMTf‹ c”uƒ ƒUI`ƒ

ሠራተኛ ነበርሁ፡፡ ዕለት ዕለት ደስ አሰኘው ነበርሁ፡፡” ምሳሌ 8፡22-30” Ellen G.


white, patriarchs and prophets, p. 34

የመወያያ
ወያ ጥያቄዎች፡-

በዘፍጥረቱ
ፍ የአፈጣጠር መንን የመጽሐፍ
ፈ ጠ ታሪክ ማመን ቅዱሳዊው
ፍ ቅ ሳ ጥበብ መሠረት

የሆነው
ነ ለምንድን
ለ ን ነው? የዝግመተ ለውጥ
ለ ሐሳብ
ሐ ከመጽሐፍ
መጽ ቅዱስ
ቅ ስ ጋር በሁሉም

መንገድ ተፃራሪ
ፃ የሆነው
የ ለምንድንን ነው?

እውነተኛ
ኛ ጥበብ
ብ እኛ
ኛ የምናመነጨው
ና ሳይሆን
ሳ ለኛ ሊገለጥልን
ለ (ልንስተማረው)
ንስ )
የሚገባ የመሆኑ ሃሳብ
ሃ ላይ የበለጠ
በ ያሰላስሉ፡፡
ሉ በመለኮታዊው መገለጥ
መገለ ባይሆን
ይሆ
ኖሮ መቼም ልናውቃቸው
ል ው ቸው የማንችላቸው
ማ ቸ ጠቃሚቃ እውነቶች
እ ቶ መካከል የተወሰኑትን
ለምሳሌ ቢጠቅሱ?ቅ ለምሳሌሌ የክርስቶስን
የ ስ በመስቀል
ቀል መሞትናት ምን

እንደሚጠቅመን
ደ በቃሉ ባይገለጽጽ ኖሮ እንዴት
እ ት ልናውቅ
ና ቅ እንችል ነበር?
ር ስለለ
ሰባተኛው
ኛ ቀን ሰንበት ወይም ስለ ዳግም ምፃቱስ??

በዘፍጥረት
ፍ 1 እንደተገለጸው
ው መልካም
መ ከክፉ
ፉ ጋር መደባለቅ እንደማይችል

የእግዚአብሔር
ብ ስራ
ራ የሚመሰክረው
የ ክ እንዴት
እ ነው?
ነ ለምሳሌ በዘፍጥረቱ
ዘፍ ረ የፍጥረትት
ታሪክ
ሪ ውስጥ
ስ የዝግመተ ለውጥን
ለ አመለካከት ለመጨመር ለሚሞክር
ለ ክር ሰው

መልስዎ
ስ ምንድን ነው?

የእግዚአብሔር
ብ በፍጥረት መደሰት የጠለቀና ሰፊ የሰንበት
ት ልምምድ
ድ እንዲኖረን

የሚረዳን እንዴት
እ ት ነው?

መጽሐፈ ምሳሌ 1ኛ ሩብ ዓመት 2007 ዓ ም


46

You might also like