Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የእንስሳት በሽታ በእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ላይ ያለው አደጋ

የእንስሳትን ብዝሀ ሕይወት ዘላቂነት እና ዋስትና የሚፈታተኑ በርካታ ተግዳሮቶች አሉ፡፡ በእንስሳት ብዝሀ

ሕይወት ላይ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ የመኖሪያ አካባቢ መጥፋትና መመናመን፣


ከመጠን በላይ ብዝበዛ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ከውጭ/መጤ ዝርያዎች ጋር ማዳቀል፣ የእንስሳት በሽታ ወዘተ

ይጠቀሳሉ፡፡ የእንስሳት በሽታ በለማዳም ሆነ በዱር እንስሳት ውስጥ ዋነኛው የጤና እና ደህንነት ስጋት ነው፡፡

በተለይም በሽታው በጣም አጣዳፊ፣ በለማዳና በዱር እንስሳት መካከል ተላላፊና ከፍተኛ የሞት ደረጃ

የሚያስከትል እንዲሁም በሰዎች ላይ የመተላለፍ እድል ያለው ከሆነ ደግሞ የበሽታውን አሳሳቢነት ደረጃ ከፍ

ያደርገዋል፡፡ በርካታ ወረርሽኞች በብዙ የዓለማችን ክፍሎች ላይ አስከፊ ጉዳት ያስከተሉ ሲሆን እነዚህም

የተለያዩ ገፅታዎች አሏቸው፤ ወደ ሰው ተላላፊ (ለምሳሌ በርድ ፍሉ፣ ኢቦላ …)፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ
የሚፈጥሩ (ለምሳሌ አባሰንጋ፣ ኤፍ-ኤም-ዲ …) እና እንዲሁም ከባድ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራን የሚያደርሱ
ናቸው፡፡

ተላላፊ የእንስሳት በሽታዎች በተለይም አጣዳፊ ወረርሽኞች በሺታዎች የሚቆጠሩ በተወሰነ አካባቢ ወይም

በተለያዩ ሥፍራዎች የሚገኙ እንስሳትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊገድሉ ይችላሉ፡፡ ተላላፊ፣ አጣዳፊ የሆኑና

በወረርሽኝ ደረጃ ሊከሰቱ የሚችሉ በርካታ በሽታዎች የሚገኙ ሲሆን በለማዳም ይሁን በዱር እንስሳት ላይ
ከፍተኛ ጉዳትና ሞት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ በሽታዎች ከዚህ ቀደም ተጠቅተው ወደማያውቁ እና በተለያዩ

መንስኤዎች ስጋት ላይ በሚገኙ ዝርያዎች ጭምር እየተስፋፉ ይገኛሉ፡፡ በሽታው በእንስሳት ዝርያው ላይ

የሚያደርሰውን ተፅዕኖ በጣም ከባድ የሚያደርገውና አገራዊ/አለም አቀፋዊ ትኩረትን የሚጠይቀው በተለይም

የእንስሳቱ ዝርያ አናሳ ቁጥር ብቻ ያለው ከሆነና እንዲሁም በአንድ ሥፍራ ላይ ብቻ የሚገኝ ከሆነ ነው፡፡

የእንስሳት ዝርያዎችን ከሚያጠፉ ወይም ስጋት ላይ ከሚጥሉ አምስት ዋና ዋና ተፅዕኖዎች መካከል የእንስሳት

በሽታ ይጠቀሳል፡፡

በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የሚሰራው አለም አቀፉ ሕብረት (IUCN) ለአንዳንድ የተመናመኑ የእንስሳት ዝርያዎች

በሽታ ዋነኛው መንስኤ እንደሆነ ጠቅሶ ስጋቱ ግን በአብዛኛው ዝርያዎች ላይ እንደሚገኝ ያትታል፡፡ በአጠቃላይ

በሽታ በእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ላይ ያለውን ስጋት ሲገልፅ ዝርያቸው ከተጎዱ እንስሳት መካከል፤ የወፍ

ዝርያዎች በ 5% ወይም 67 ዝርያዎች እና ከ 26 በላይ በሚሆኑ የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች፣ እንዲሁም


በ 17% ወይም 317 የእንቁራሪት-አስተኔ ዝርያዎች ላይ በሽታ ዋነኛ ስጋት ነው፡፡ እንደ “ራቢስ እና ካናይን
ዲስቴምፐር” አይነቶቹ በሽታዎች ደግሞ ለትላልቅ ስጋበል እንስሳት ትልቅ ስጋት መሆናቸውን ያስረዳል፡፡

በእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ላይ ትልቅ ስጋትና ተፅዕኖ ማድረስ የሚችሉ ብዙ የበሽታ አይነቶች አሉ፡፡ የስጋት

ደረጃውም አንድን ንዑስ-ዝርያ ከማጥቃት እስከ አጠቃላይ የእንስሳውን ዝርያ ማመናመን ሊደርስ ይችላል፡፡

የበሽታው ወረርሽኝ በአንድ አካባቢ ከሚገኙ ተጋላጭ እንስሳት አብዛኛውን ወይም ሙሉ በሙሉ ጠራርጎ

ሊገድል ይችላል፡፡ ለምሳሌ ሪንደርፔስት በከብቶችና የጎሽ ዝርያዎች ላይ፣ አባሰንጋ በአባዛኛው ሳርበል
ዝርያዎች ላይ፣ አፍሪካን ሆርስ ሲክነስ በጋማ ከብቶች ላይ፣ ኤቪያኒ ኢንፍሉኤዛ እና ኒውካስትል ዲዝስ
በአብዛኛው የወፍ ዝያዎች ላይ፣ ችትሪዲኦማይኮሲስ በእንቁራሪት-አስተኔ ዝርያዎች ላይ እንዲሁም ራቢስ እና

ካናይን ዲስቴምፐር በለማዳና የዱር ስጋበል እንስሳቶች ላይ ከባድ ወረርሽኝ ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ለብዝሀ ሕይወት መጥፋትና መመናመን ዋነኛውን መንስኤ የእርሻና ግጦሽ መሬት

መስፋፋት እና ፍላጎት መጨመር የመጀመሪያውን ደረጃ ይወስዳል፡፡ ሆኖም የእንስሳት በሽታዎች ከሌሎች

አስጊ ሁኔታዎች ጋር በመዳመር የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ዘለቄታና ጥበቃ ላይ እንቅፋቶች ናቸው፡፡ ብዙ

የእንስሳት በሽታዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍተው የሚገኙ ሲሆን አስከፊ

ወረርሽኝዎችንም ያስከትላሉ፡፡ ምንም እንኳን የእንስሳት እርባታው ዘርፍ ለአገሪቷ ኢኮኖሚ ብዙ አስተዋፅ

እያደረገ ቢሆንም እድገቱ ግን በብዙ የእንስሳት በሽታዎች (ቫይራል፣ ባክቴሪያል እና የጥገኛ ትላትል

በሽታዎች) ካለው ዝቅተኛ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት እና ዝቅተኛ የበሽታዎች ክትትል እና ቁጥጥር ጋር

ተዳምሮ የተስነካከለ ነው፡፡

በአገሪቱ ውስጥ የተለያዩ የበሽታ ወረርሽኞች በለማዳ እና የዱር እንስሳት ዘለቄታዊነት ላይ ስጋት ሆነው

ይከሰታሉ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የሪንደርፔስት ወረርሽኝ በወቅቱ ከነበረው ድርቅ ጋር

ተደማምሮ አብዛኛው የኢትዮጵያ ከብቶችን አጥፍቷል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1887 በኢትዮጵያ የባህር ወደብ

አማካኝነት ወደሀገራችን እንደገባ የሚታሰበው ይህ በሽታ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ከብቶችን እያጠቃና ወደ ቀሪው

የሀገሪቷ ክፍሎች ባልተለመደና አስገራሚ በሆነ ፍጥነት እየተስፋፋ መጣ፡፡ በሽታው በትግራይ እና ሸዋ ብሎም

ወደደቡብ በመስፋፋት ወደ 90% ያህል የሀገሪቱ ከብቶች እና የዱር እንስሳት ሞትን አስከትሏል፡፡ ገንዲ

(ትርይፓኖሶሞሲስ) የተባለዉ በሽታ ደግሞ በተለይም በኢትዮጵያ ምዕራባዊ እና ደቡብ ምዕራብ ዝቅተኛ
ቦታዎች እና ሸለቆዎች ውስጥ በሰፊው ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡ በነዚህ ሥፍራዎች የሚገኙ ሰፋፊ የመሬት

ሀብቶችን ለመጠቀምም ዋነኛው ችግርም ነው፡፡

በ 1990 ዎቹ በባሌ ተራራ ብሔራዊ ፓርክ የታየው አስደንጋጭ የቀይ ቀበሮ ቁጥር መቀነስ ውስጥ በሽታ

ዋነኛው ችግር ሆኖ ተግኝቷል፡፡ ራቢስ ለዱር ስጋበል እንስሳቶች ልዩ ስጋት ሆኖ የተገኘበትና በኢትዮጵያ ብቻ

በሚገኘው ቀይ ቀበሮ/ተኩላ ላይ መከሰቱ ነው፡፡ ከአጠቃላዩ 500 ገደማ ተኩላዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት

በሚኖሩበት በኢትዮጵያ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የራቢስ እና ካናይን ዲስቴምፐር ተደራራቢ

ወረርሽኞች ተከስቷል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2003/2004 የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በዚህ ለሀገራችን ብርቅዬ

በሆነውና በጣም እየተመናመነ በመጣው ቀይ ቀበሮ ወደ 74 ገደማ የሚሆኑ ቀበሮዎች ሞተው የተገኙ ሲሆን

ለዚህም “ራቢስ” ወይም የእብድ ውሻ በሽታ የሚባለው ወረርሽኝ ትልቁን ግምት ወስዷል፡፡ በላብራቶሪ

ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረትም ከ 15 ናሙናዎች በ 13 ቱ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ

አንትራክስ (አባሰንጋ) የተባለው ወረርሽኝ በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኘው በማጎ ብሔራዊ ፓርክ ከፍተኛ የዱር

እንስሳት ሞትን እንዳስከተለ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

You might also like