Forest Product Directive

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 15

መመሪያ ቁጥር… 2013

ለደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች፤ ለጣውላ ኮምፖንሳቶና ብርኬት ማምረት ንግድ ስራ


የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ

በደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች፤ ጣውላና ኮምፖንሳቶ እንዲሁም ብሪኬት ማምረት ላይ የተሰማሩ
ወይም የሚሰራ ማንኛውም ሰው የምርቶቹን የልማት ሂደት፤ ጥራትና ደህንነት በማሳደግ የአካባቢና
የማህበረሰብ ደህንነትን በማይጓዳ መልኩ ስራቸውን እንዲያካሄዱ ማድረግ በማስፈለጉ፤

ለደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች፤ ለጣውላ ኮምፖንሳቶና ብርኬት የማምረት ሥራ ምዝገባና ፈቃድ
አሰጣጥ እንቅስቃሴዎች የተለዩ መስፊርቶችን በመከታል ማካሄድ የደን ዘርፍ ለኢኮኖሚ የሚሰጠውን ድርሻ
የሚያሳድግ መሆኑ ስለታመነበት ፤

የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የደን ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/2010 አንቀጽ 27
መሰረት ይህ መመሪያ ወጥቷል

የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የደን ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ
36(17) መሰረት ይህ መመሪያ ወጥቷል

1. አጭር ርእስ
ይህ መመሪያ “ለደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች፤ ለጣውላ ኮምፖንሳቶና ብርኬት ማምረት
ንግድ ስራ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ’’ ቁጥር ----- /2013” ተብሎ
ሊጠቀስ ይችላል፡፡ የደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች ንግድ ስራ የብቃት ማረጋገጫ
መስፈርቶችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር……/2013” በሚል ቢስተካከል ተገቢ ይሆናል
2. ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-
1. “አመልካች'' ማለት ለደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች ወይም ለጣውላ ኮምፖንሳቶና
ብርኬት ማምረት ንግድ ስራ ለመሰማራት የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ለኮሚሽኑ ወይም
አግባብ ላለው የክልል ባለሥልጣን ያመለከተ ሰው ነው፤
2. ‘‘የጣውላ ኮምፖንሳቶ’’ ማለት በማንኛውም ሰው ተመርቶ፣ ተገዝቶ ወይም ተቀነባብሮ በሀገር ውስጥ
የሚመረት፣ በሀገር ውስጥ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ለንግድ የሚዘዋወር ወይም ወደ ውጭ ሀገር የሚላክ
የእንጨት ውጤት ነው፤
3. ‘‘ብርኬት’’ ማለት ከደንና እፅዋት፣ከእንጨት ኢንዱስትሪ ፣ ከቀርከሃና ፣ከሸንበቆ ፣ እና
ከመሳሰሉት ተረፈ ምርቶች የሚመረት ባለ ቅርፅ ከሰል ነው፤
‘‘ንጥረ ነገር’’ ማለት ማንኛውም መደበኛ የእንጨት ምርት ለማምረትአጣና የጣውላ ኮምፔንሳቶና ተዛማች
ምርቶችን ለማጠናከር በቀላሉ ለማለስለስ፣ ለማሰንጠቅና ለመቁረጥ በጥቂቱ የሚቀላቀል ወይም ጥቅም ላይ
የሚውል ንጥረ ነገር ሆኖ በምርት ሂደቱ ላይ፣ አካባቢና ማህበረሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማያስከትል
የተረጋገጠ ንጥረ ነገር ነው
ከሰል…. የሚለው ቢተረጎም
ከሰል ብዙ አየር በሌለበት እንጨት በማቃጠል የተገኘ ጥቁር ንጥረ ነገር ነው

ፍም ውሃ እና ሌሎች ተለዋዋጭ ንጥረ ነገሮችን ከእንስሳትና ከእፅዋት ንጥረ ነገሮች በማስወገድ


የተገኘ ካርቦን እና ማንኛውም ቀሪ አመድ ቀላል ጥቁር ቅሪት ነው

4. ‘‘የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት’’ ማለት የጣውላ ኮምፖንሳቶና እና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች፣
ብርኬት ማምረት፣ ደን ማልማትና ተዛማች አገልግሎቶች ንግድ ስራ ላይ ለመሰማራት በዚህ
መመሪያ የተቀመጡ መስፈርቶችን ለሚያሟላ አመልካች የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ነው፤
5. ‘‘ አረጋጋጭ አካል ’’ ማለት የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ወይም አግባነት
ያለው የክልል ባለሥልጣን ነው፤
6. ‘‘አዋጅ’’ ማለት የደን፣ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/ 2010 ነው፤
7. በአዋጅ አንቀፅ 2 ስር የተሰጡት ትርጉሞች ለዚህ መመሪያ ተፈፃሚ ይሆናሉ
3. የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በሀገሪቱ ደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች ወይም ለጣውላ ኮምፖንሳቶና ወይም


ብርኬት በማምረት በተሰማራ ወይም በሚሰማራ ማንኛውም ሰው ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ይህ መመሪያ በመላ ሀገሪቱ በደን ማልማት፣ በጣውላ፣ ኮምፓንሳቶ፣ ብርኬትና ተዛማጅ ስራ ላይ


በተሰማራ ወይም በሚሰማራ ማንኛውም ሰው ላይ ተፈፃሚ ይሆናል

4. የብቃት ማረጋገጫ የመያዝ ግዴታ


1. ማንኛውም ሰው ከአረጋጋጭ አካል የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሳያገኝ ደን ማልማትና
ተዛማጅ አገልግሎቶች፤ ለጣውላ ኮምፖንሳቶና ብርኬት ማምረት ንግድ ሥራ ላይ መሰማራት
አይችልም፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ሰው ደን ማልማትና
ተዛማጅ አገልግሎቶች፤ ለጣውላ ኮምፖንሳቶና ብርኬት ማምረት ንግድ ሥራ ላይ ለመሰማራት
ከሚመለከታው የፌዴራል ወይ ክልል መስሪያ ቤት የንግድ ፈቃድ ማግኛት አለበት፡፡

5. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለመስጠት


1. አረጋጋጭ አካል የአመልካች ማመልከቻ የተሟላ ስለመሆኑ የማጣራት ሥራ ማከናወን
ይኖርበታል፡፡
2. አረጋጋጭ አካል የብቃት ማረጋጋጫ ምስክር ወረቀት ከመስጠቱ በፊት የአመልካች ማመልከቻ
የተሟላ ስለመሆኑ ማጣራት አለበት
3. አመልካች አስፈላጊውን መስፈርት ስለማሟላቱ በአረጋጋጭ አካል ከተረጋገጠ ተገቢውን
የአገልግሎት ክፍያ ከከፈለ በኋላ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ለአመልካች በሦስት የስራ ቀናት
ውስጥ መሰጠት አለበት፡፡
4. አመልካች ያቀረበው የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጠኝ ማመልከቻ የተሟላ መሆኑ
ሲረጋገጥና በህግ አግባብ መክፈል ያለበትን የአገልግሎት ክፍያ ሲከፍል አረጋጋጭ አካል የብቃት
ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱን በሦስት የስራ ቀናት ውስጥ ለአመልካች መሰጠት አለበት፡፡
5. አረጋጋጭ አካል የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ጥያቄውን ውድቅ ካደረገ የዚህን ምክንያት
በጽሁፍ ለአመልካች ማሳወቅ አለበት፡፡
6. በዚህ አንቀዕ ንዑስ አንቀዕ 3 የተመለከተው እንደጠበቀ ሆኖ ማመልከቻው ውድቅ የተደረገበት
አመልካች የተጓደሉትን መስፈርቶች አሟልቶ ለአረጋጋጭ አካል ሲያቀርብ ማመልከቻው
በድጋሚ እንዲታይ ሊደረግ ይችላል፡፡
7. አረጋጋጭ አካል አመልካችየብቃት ማረጋገጫ ሲያገኝ የተቀመጡለትን ቅድመ ሁኔታዎች
ስለማክበሩ ወቅታዊ የመስክ ግምገማ የማድረግ ሀላፊነት አለበት፡፡

6. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚያበቁ አጠቃላይ መስፈርቶች


1. ማንኛውም ሰው ደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች፤ ለጣውላ ኮምፖንሳቶና ብርኬት ማምረት
ሥራ ላይ ለመሰማራት የሚያስችል የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማግኘት ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን አጠቃላይ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡-
የረቂቅ መመሪያው አንቀፅ 6

ሀ. የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ለኮሚሽኑ ወይም አግባብነት ላለው ባለሥልጣን ማቅረብ፤

ለ. ንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይነት ማስረጃ የንግድ ምዝገባና የግብር ከፋይነት ምስክር
ወረቀት ማቅረብ

ሐ. ምርቶች ለማደራጀትና ለማከማቸት የሚያስችል ቦታ መኖሩንና ቦታው የግል፣ የማህበር


ወይም በኪራይ ወይም በሊዝ የተገኘ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ፣
መ. የስራ ቦታው ወይም መጋዘኑ በአካባቢው ሕብረተሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
እንቅስቃሴ እንዲሁም በአካባቢ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማያስከትል ሁኔታ መስራት ስለ
መቻሉ ማረጋገጫ ማቅረብ፣ አሉታዊ ተፅዕኖ የማያስከትል ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል
ማረጋገጫ ማቅረብ

ሠ. ለሰራተኞች ምቹ የሆነ የልብስ መቀየርያ፣የመፀዳጃ እና የንፁህ ዉሃ አገልግሎት


የመሳሰሉትን ያሟላ ወይም የሚያሟላ ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ
ማቅረብ፣

ሸ. የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ እና የክሊኒክ አገልግሎት ስለመኖሩ ወይም የሚያሟላ


ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ማቅረብ፣

ቀ. የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ስለመኖሩ ወይም የሚያሟላ


ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ማቅረብ፣

በ. የአካባቢን ደህንነት የጠበቀ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ሁኔታ መኖሩ ወይም የሚያሟላ
ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ማቅረብ እና፡፡

ተ. በስራው የሰለጠነ በቂ ልምድ ያለዉ የሰዉ ኃይል ያካተተ ስለመሆኑ ማስረጃ


ከሚመለከተው አካል ማቅረብ

7. በደን ዘር መሰብሰብ ላይ ለመሰማራት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ

1. በዚህ መመሪያ አንቀዕ 6 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በደን ዘር መሰብሰብ ላይ ለመሰማራት


የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች
ማሟላት አለበት፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት ለአረጋጋጭ አካል ማቅረብ
አለበት.

ሀ) የዝርያ ዓይነት፣ የአሰባሰብ ሰንሰለት፣ የግብይት አቅጣጫና የመሳሰሉት የሚገልፅ መረጃ፣


ለ) የስራ ቦታው የዘር ጥራትና ብቅለት መሞከሪያ ፣የዘር ማስጫ፣ መውቂያ፣ ማጣሪያና ማሸጊያ እና
ማከማቻ ክፍሎች እንዳሉት ማረጋገጫ ወይም ለማዘጋጀት ያለውን ዝግጅት የሚያሳይ መግለጫ፣
ሐ) የደን ዝርያው ስያሜ፣ ዘሩ የሚለቀምበት ቦታ፣ የዘሩ ምንጭ ዓይነትና ደረጃ፣ ዘሩ

የሚለቀምበት ቀንና ቆይታ ጊዜ፣ የዘሩ የብቅለትና የጥራት መጠን ጠብቆ ለመስረት ያለው

ዝግጁነት የሚያሰይ መግለጫ፣


መ) የዛፍ ዘር የሚለቀምባቸው እናት ዛፎች የሚገኙበት ቦታ ወይም የታወቀ የራሱ የሆነ ደን
ወይም ከሌላ የደን ባለቤት ዘር መሰብሰብ የሚችል ስለመሆኑ የሚገልፅ ማረጋገጫ፣

ሠ. የዛፍ ዘር ለመሰብሰብ የተለየ ስልጠና ለመስጣት ወይም አግባብነት ካለው ተቋም የሰለጠነ የሰው
ኃይል ለመቅጠር እንደሚችል የሚያሳይ ማረጋገጫ እና፣

ሸ. የዛፍ ዘር ለመሰብሰብ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች ለመሟላታቸው እንደሚችል


የሚያሳይ ማረጋገጫ፣ የዛፍ ዘር ለመሰብሰብ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን ማሟላት
እንደሚችል የሚያሳይ ማረጋገጫ ተብሎ ቢስተካከል ግልጽነት ይኖረዋል

በረቂቅ መመሪያ አንቀጽ 7 ስር ከፊደል ሀ-ሸ ያሉትን ድንጋጌዎች እንደቅደም ተከተላቸው


ከንዑስ አንቀፅ (1) እስከ አንቀፅ(6) ተደርገው እንዲቀመጡ ቢደረግ

8. ችግኝ ለማፍላት ብቃት ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ችግኝ በማፍላት ስራ


የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ተብሎ ቢስተካከል

1. በዚህ መመሪያ አንቀዕ 6 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በችግኝ ማፍላት ለመሰማራት የብቃት


ማረጋገጫ ማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት
አለበት፡-
በዚህ መመሪያ የአንቀዕ 6 ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የተመለከተው እንደተጠበቁ ሆነው በችግኝ
ማፍላት ስራ ለመሰማራት የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት ለአረጋጋጭ አካል ማቅረብ አለበት
ሀ) የዝርያ ዓይነት፣ የአሰባሰብ ሰንሰለት፣ የግብይት አቅጣጫና የመሳሰሉት የሚገልፅ መረጃ
ማቅረብ ፣
ለ) ለስራዉ የሚያስፈልግ በቂ የሰዉ ሀይል ማሟላት የሚችል ስለመሆኑ መግለጫ ማቅረብ፤
ሐ) ለችግኝ ዝግጅት ስራ ተስማሚ የሆነ ቦታ መምረጥ ማግኛት የሚችል ስለመሆኑ መረጃ
ማቅረብ ፤
መ) በቂና ለችግኝ ልማት ተስማሚ የሆነ መሬት ስለመኖሩ አስተማማኝ ካርታና የሳይትፕላንማቅረብ ወይም
ማግኛት የሚችል ስለመሆኑ መግለጫ፤
ሠ) የሚያፈላው ችግኝ ፈቃድ ከተሰጣቸው በደን ዘር መሰብሰብ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጥራት ያለውና
ለአካባቢው ተስማሚ የሆነ የደን ዘር አቅርቦቶች ከአስተማማኝ ምንጭ የሚገኙ ስለመሆኑ ማረጋገጫ፤
ረ) የችግኝ ብዜትና የግብይት ሂደቱ በሰው ጤና እና በአካባቢ ላይ የጎላ ጉዳት እንደማያስከትል
እንዲሁም እንዲሁም የሚለው ቃል እንዲወገድ ተደርጎ ማረጋገጫ መቅረብ እንደሚገባ ይገለፅ
ሰ) የተፈጥሮ ሃብት ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮረ የልማት ሥርዓት የሚከተል ስለመሆኑ
ማረጋገጫ፤
ሸ) ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሠነዶችን አደራጅቶ ለመያዝ አሰራር ስለመኖሩ እና፣
ቀ) ችግኝ ለማፍላት የሚያግዙ አስፈላጊ ሥልጣና ለባለሙያዎች ለመስጣት የሚያስችል ዝግጅት
ስለመኖሩ የሚገልፅ ማረጋገጫ ፣

በረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 8 ስር ከፊደል ተራ ሀ-ቀ የተደነገጉትን እንደቅደም ተከተላቸው


ከንዑስ አንቀፅ (1) እስከ ንዑስ አንቀፅ(9) ተደርገው እንዲስተካካሉ ይደረግ

9. ለደን ልማት የብቃት መስፈርቶች በደን ማልማት ስራ የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት መሟላት
ያለባቸው መስፈርቶች ተብሎ ቢስተካከል
1) በዚህ መመሪያ አንቀዕ 6 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውምበደን ልማት ስራ
መሰማራት የሚፈልግ ሰው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡-
የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ለአረጋጋጭ አካል ማቅረብ አለበት በሚል ይስተካከል

ሀ) ዝርዝር የደን ልማት ዓይነት ለአጠና፣ ለጣዉላ፣ ለማገዶ፣ ለከሰል፣ ለኢንደስትሪ ግብአት
እና የመሳሰሉት ምርቶች እንዲሁም እንጨት ነክ ያልሆኑት እጣንና ሙጫ፤ ለመድሃኒት

አገልግሎት የሚውሉ ዛፎችን የሚገልፅ ፕሮፖዛል ማቅረብ እና የደን ልማቱ የአካባቢውን


ሥርዓተ-ምህዳር መሠረት ያደረገ መሆኑን፤
ለ) ደን ለማልማት ከሚመለከተው አካል ለደን ልማት ስራ አገልግሎት የሚውል መሬት
ስለመኖሩ ወይም የሚገኝበት ሁኔታ እና የመሬቱ ስፋትና የሚገኝበት አካባቢማስረጃ
ማቅረብ፣
ሐ) የደን ማኔጅመንት የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የልማት ዕቅድ እንዲሁም የደን
በሽታና እሳት መከላከያ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑየሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ፣
መ) የደን ልማት ስራው በአካባቢው ኅብረተሰብ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ
እንዲሁም በአከባቢው ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተዕፅኖ በማያስከትል መልኩ ለማከናወን ያለው
ዝግጅት ማረጋገጫ እና፣
ሠ) አግባብነት ያለውን ስልጠናየወሰዱ ባለሙያዎች ቀጥሮ ለማሰራት ያለው ዝግጅት
የሚያሰይ መግለጫ ፤

በረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 9 ስር ከፊደል ተራ (ሀ) እስከ ከፊደል ተራ (ሠ) የተደነገጉትን


እንደቅደም ተከተላቸው ከንዑስ አንቀፅ (1) እስከ ንዑስ አንቀፅ(5) ተደርገው እንዲስተካካሉ
ይደረግ

10. ብርኬት ለማምረት የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶች ብርኬት ለማምረት ስራ የብቃት ማረጋገጫ
ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1) በዚህ መመሪያ አንቀዕ 6 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም በብርኬት ማምረት


ስራ ላይ መሰማራት የሚፈልግ ሰው የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል
የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ለአረጋጋጭ አካል ማቅረብ አለበት በሚል ይስተካከል

ሀ) ከመኖሪያ ቤት፣ ከጤና እና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ድርጅት 500 ሜትር


ባላነሰ ርቀት የተለየ የማምረቻ ቦታ ወይም ለኢንዱስትሪ ዞን በተከለለ አካባቢ
ማግኛት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ ፤
ለ) ለሰራተኞች የመፀዳጃ፣ የልብስ መቀየርያ እና የንፁህ ዉሃ አገልግሎት የመሳሰሉትን
ያሟላ ስለመሆኑ ማረጋገጫ፣
ሐ) የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ስለመኖሩ ማረጋገጫ፣
መ) የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ስለመኖሩ ማረጋገጫ፣
ሠ) የእሳት ማጥፍያ ማሟላት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ፣
ረ) የዝርያ ዓይነት የሚገልፅ ዝርዝር ፕሮፖዛል ማቅረብ፤
ሰ) የአካባቢና ማህበረሰብ አያያዝ እቅድ ለማሟላት ማረጋገጫ ማቅረብ፣ ግልፅነት
ይጎድለዋል በተለይም ማህበረሰብ አያያዝ እቅድ ለማሟላት ማረጋገጫ በግልፅ ይቀመጥ
ሸ) የምርት ክፍልን ጨምሮ ክፍት የማምረቻ ቦታ መደርደሪያ ለማሟላት የሚችል

ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቀረብ እና፣


ቀ) ማድረቅያ፣ ለጥሬ ዕቃዎች አስተማማኝ ማከማቻ ቦታ ለማሟላት የሚችል

ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቀረብ አለበት፡፡

በረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 10 ስር ከፊደል ተራ (ሀ) እስከ ከፊደል ተራ (ቀ) የተደነገጉትን


እንደቅደም ተከተላቸው ከንዑስ አንቀፅ (1) እስከ ንዑስ አንቀፅ(9) ተደርገው እንዲስተካካሉ
ይደረግ

11. የጣውላ፣ ኮምፖንሳቶ እና ሌሎች ተዛማች አገልግሎቶችን ለማምረት የብቃት ማረጋገጫ


መስፈርቶች የጣውላ፣ ኮምፖንሳቶ እና ሌሎች ተዛማች ምርቶችን ለማምረት የብቃት ማረጋገጫ
ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ተብሎ ቢስተካከል
1) በዚህ መመሪያ አንቀዕ 6 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የጣውላ፣ ኮምፔንሳቶ እና
ሌሎች ተዛማች አገልግሎቶች ማምረት ማምረት ስራ ላይ መሰማራት የሚፈልግ ሰው የሚከተሉትን
መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡-
የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ለአረጋጋጭ አካል ማቅረብ አለበት በሚል ይስተካከል

ሀ) ለስራዉ የሚያስፈልግ በቂ የሰዉ ሀይል ማሟላት ለማሟላት የሚችል መሆኑን የሚገልፅ


ማረጋገጫ፤
ለ) ከመኖሪያ ቤት፣ ከጤና እና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ድርጅት 300 ሜትር ባላነሰ ርቀት
ላይ የሚገኝ ስለመሆኑ፣
ሐ) ለሰራተኞች የመፀዳጃ፣ የልብስ መቀየርያ እና የንፁህ ዉሃ አገልግሎት የመሳሰሉትን ያሟላ
ወይም ለማሟላት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፤
መ) የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ለማሟላት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ፤
ሠ) የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ለማሟላት የሚችል ስለመሆኑ
ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፤
ረ) የእሳት ማጥፍያለማሟላት የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ፤
ሰ) የጣውላ እና ኮምፖንሳቶ እና ሌሎች ተዛማች ምርቶች ለማደራጀትና ለማከማቸት
የሚያስችል ቦታ ማግኘት የሚችልበት ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጫ ማቅረብ፣
ሸ) የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማሟለት ያለውን ዝግጁነት የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ
ቀ) የዝርያ ዓይነት የሚገልፅ ዝርዝር ፕሮፖዛል ማቅረብ እና
በ) ስራው በአካባቢ ዘላቂነት፤ በማህበራዊ ደህንነትና ኢኮኖሚያዊ ልማት እንቅስቃሴ ላይ
አሉታዊ ተዕፅኖ እንደማያስከትል የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡

በረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 11 ስር ከፊደል ተራ (ሀ) እስከ ከፊደል ተራ (በ) የተደነገጉትን


እንደቅደም ተከተላቸው ከንዑስ አንቀፅ (1) እስከ ንዑስ አንቀፅ (10) ተደርገው
እንዲስተካካሉ ይደረግ

12. የንግድ አድራሻ ለውጥ ስለማድረግ


ማንኛውም በደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች፤ በጣውላ ኮምፖንሳቶና ብርኬት ማምረት
ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ከአረጋጋጭ አካል ፍቃድ ሳያገኝ የአድራሻ ለውጥ ማድረግ አይችልም፡፡
13. ምትክ የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት ስለመስጠት
1) የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተበላሸበት ወይም የጠፋበት ሰው ምትክ ሊያገኝ
የሚችለው ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ነው ፡-
የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የጠፋበት፣ የተቀደደበት ወይም በማንኛውም ሁኔታ
የተበላሸበት ሰው ምትክ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሊያገኝ የሚችለው፡-
1. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ የተቀደደ ወይም የተበላሸ ሲሆን የተቀደደውን ወይም
የተበላሸውን የምስክር ወረቀት ሲመልስና ምትክ እንዲሰጠው ሲጠይቅ፤ ወይም
2. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ የጠፋ ከሆነ ስለመጥፋቱ የሚያሳይ ማመልከቻ በቃላ-
መሃላ አስደግፎ ሲያቀርብ፤ ነው ተብሎ ቢደነገግ
ሀ) አመልካቹ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተበላሸበት ከሆነ የተበላሸውን የምስክር
ወረቀቱን ሲመልስና ምትክ እንዲሰጠው ሲጠይቅ፣
ለ) የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ የጠፋ ከሆነ ስለመጥፋቱ የሚገልፅ ማመልከቻ
ለአረጋጋጭ አካል ሲያቀርብና ምትክ እንዲሰጠው ሲጠይቅ፣
14. የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት እድሳት
1) ማንኛውም ሰው የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሊታደስለት የሚችለው ከዚህ በታች
የተዘረዘሩት ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው፡-
ሀ) በወቅቱ ይዞት የሚገኘው የብቃት ማረጋገጫየታገደ ወይም የተሰርዞ ካልሆነ ወይም በራሱ
ፈቃድ ስራውን ካላቋረጠ፣
ለ) አረጋጋጭ አካል ለዚሁ ሥራ ዘርፍ ያወጣቸው መመዘኛዎች የተጠበቁ ስለ መሆናቸው
ሲረጋገጥ እና፣
ሐ) ለዕድሳት አገልግሎት አሰጣጥ አስፈላጊውን የአገልግሎት ክፍያ መክፈሉ ሲረጋገጥ፡፡
2) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የምስክር ወረቀቱ በተለያየ
ምክንያት ካልታደሰ በመጀመርያው የጥቅምት ወር 25 በመቶ፣ በህዳር ወር 50 በመቶ፣ በታህሳስ
ወር እና ተከታታይ የበጀት አመቱ ወራት 75 በመቶ ከመደበኛው ክፍያ በተጨማሪ የገንዘብ
መቀጮ በመክፈል ማሳደስ ይቻላል፡፡ ድንጋጌው ግልጽ አይደለም
3) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 እና 4 መሠረት ሳይታደስ የቀረ እንደሆነ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር
ወረቀቱ እንደተሰረዘ ይቆጠራል፣ ስለእድሳት ጊዜ የሚደነግግ ስላልሆነ ድንጋጌው የአገላለፅ ችግር
የሚታይበት ስለሆነ በሚገባ ታይቶ ይስተካከል
4) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 5 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጅቱ በንግድ ስራው መቀጠል
ከፈለገ የተቀመጡት መመዘኛዎች ስለማሟላቱ አረጋጋጭ አካል ባለሙያዎች ሲረጋገጥ አዲስ
የብቃት ማረጋገጫ ምሰክር ወረቀት ማውጣት ይችላል፡፡
15. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እገዳ
1) ማንኛውም በዚህ መመሪያ መሰረት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያገኘ ሰው ከዚህ በታች
በተዘረዘሩት ምክንያቶች በአረጋጋጭ አካል የምስክር ወረቀቱ ሊታገድበት ይችላል፡-
ሀ) የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትና የንግድ ፈቃድ ከሌለው ሰው የጣውላ ኮምፖንሳቶና
ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች፣ብርኬት ማምረትና መላክ፣ደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች
ንግድ ድርጅት ምርቶች ከገዛ ወይም በማንኛውም መንገድ ከተቀበለ ወይም የስራና የንግድ
ፈቃድ ለሌለው ድርጅት ሸጦ ከተገኘ፣
ለ) ለአረጋጋጭ አካል ሳያሳውቅ የአድራሻ ለውጥ ካደረገ፣
ሐ) በስራ ላይ የዋሉ የጥራት ደረጃዎች የማያሟላ ምርት ለገበያ አቅርቦ ሲገኝ፣
መ) አረጋጋጭ አካል ወቅታዊ የክትትል ስራዎችን እንዳያከናውን እክል የፈጠረ እንደሆነ፣
ጥልቅና ግልጽነት የጎደለው ድንጋጌ በመሆኑ ዘረዘር ተደርጎ ቢደነገግ
ሠ) በኮሚሽን መስርያ ቤቱ ወይም አግባብ ያለው የክልል ባለሥልጣን ከሁለት ጊዜ በላይ
ማስጠንቀቅያ ተሰጥቶት ድርጅቱ የማያስተካክል ከሆነ ወይም የህብረተሰቡና የአካባቢው
ደህንነት በማይጎዳ ሁኔታ እንዲመረት መመሪያው ባስቀመጠው መሠረት የምርት ሂደቱን
ካልፈፀመ ወይም፤
ረ) በዚህ መመሪያ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ተላልፎ ሲገኝ፣
በረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 15 ስር ከፊደል ተራ (ሀ) እስከ ከፊደል ተራ (ረ) የተደነገጉትን
እንደቅደም ተከተላቸው ከንዑስ አንቀፅ (1) እስከ ንዑስ አንቀፅ (6) ተደርገው እንዲስተካካሉ
ይደረግ

16. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለመሰረዝ


ማንኛውም የጣውላ ኮምፖንሳቶና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች፣ብርኬት ማምረትና መላክ፣ደን
ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች ንግድ ድርጅት ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ጥፋተኛ ሆኖ
ከተገኘ ኮሚሽን መስርያ ቤቱ ወይም አግባብ ያለው የክልል ባለሥልጣን የብቃት ማረጋገጫ ምስክር
ወረቀቱን ሊሰርዝበት ይችላል፡-
ሀ) የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ ከመመሪያው አሰራር ውጪ በሆነ መንገድ የተገኘ መሆኑን
ከተረጋገጠ፣
ለ) የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ በማናቸው መንገድ ለሌላ ወገን አስተላልፎ ከተገኘ፣
ሐ) ድርጅቱ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ካወጣበት የንግድ ስራ ዘርፍ ውጭ ሲያመርት፣
ወደ ውጭ ሲልክ ወይንም ሲያከፋፍል ከተገኘ፣
መ) በዚህ መመሪያ አንቀጽ 11 መሰረት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱን በወቅቱን ካላሳደሰ፣
በዚህ መመሪያ በአንቀጽ 14 መሰረት.. ተብሎ ይስተካከል
ሠ) የጣውላ ኮምፖንሳቶና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች፣ብርኬት ማምረትና መላክ፣ ደን ማልማትና
ተዛማጅ አገልግሎቶች የንግድ ድርጅቱ በኮሚሽን መስሪያ ቤቱ በተጣለበት እገዳ በመተላለፍ
ስራውን ሲያከናውን ከተገኘ ወይም፣
ረ) የጣውላ ኮምፖንሳቶና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች፣ብርኬት ማምረትና መላክ፣ደን ማልማትና
ተዛማጅ አገልግሎቶች የንግድ ድርጅቱ ስለብቃት ማረጋገጫ እገዳ በአንቀጽ 31 ላይ
የተቀመጡትን መስፈርቶች በመተላለፍ ተመሳሰይ ጥፋቶች በሦስት አመት ጊዜ ውስጥ ከሁለት
ጊዜ በላይ ፈፅሞ ከተገኘ፡፡ ስለብቃት ማረጋገጫ እገዳ በአንቀፅ 15 ላይ የተቀመጡትን… ተብሎ
ይስተካከል
በረቂቅ መመሪያው አንቀጽ 16 ስር ከፊደል ተራ (ሀ) እስከ ከፊደል ተራ (ረ) የተደነገጉትን
እንደቅደም ተከተላቸው ከንዑስ አንቀፅ (1) እስከ ንዑስ አንቀፅ (6) ተደርገው እንዲስተካካሉ
ይደረግ

17. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለመመለስ

1. ማንኛውም የጣውላ ኮምፖንሳቶና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች፣ብርኬት ማምረትና መላክ፣ደን


ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች የንግድ ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
ከተሰጠበት ዓይነትና የቦታ ለውጥ ሲያደርግና አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
ለማግኘት ጠይቆ ተቀባይነት ሲያገኝ ነባሩን ፈቃድ ለኮሚሽን መስርያ ቤቱ ወይም አግባብ ላለው
የክልል ባለሥልጣን መመለስ አለበት፡፡
2. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከተሰረዘ፣ ከታገደ፣ከተቀመጠው የእድሳት ጊዜ ገደብ
ሳይታደስ ከቀረ ወይም በራሱ ፈቃድ የንግድ ስራውን ካቋረጠ ድርጅቱን ነባሩ ፈቃድ በአስር የስራ
ቀናት ውስጥ ለኮሚሽን መስርያ ቤቱ ወይም አግባብ ላለው የክልል ባለሥልጣን መመለስ አለበት፡፡
….ድርጅቱ ነባሩን ፈቃድ… በሚል ይስተካከል

18. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እገዳ ስለማንሳትና የተሰረዘውን ስለመተካት

1. ማንኛውም የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የታገደበት ማንኛውም የጣውላ ኮምፖንሳቶና


ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች፣ብርኬት ማምረትና መላክ፣ደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች
ንግድ ድርጅት የተጣለበት እገዳ ሊነሳለት የሚችለው በዘህ መመሪያ መሰረት ቅሬታ አቅርቦ
ቅሬታውን ተቀባይነት ሲያገኝ ወይም ድርጅቱ ለእገዳ ያበቃውን ጥፋት ካረመ ወይም ካስተካከለ
እገዳው ሊነሳለት ይችላል፡፡
ማንኛውም የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የታገደበት.. በሚል ይስተካከል

2. ማንኛውም የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰረዘበት የጣውላ ኮምፖንሳቶና ሌሎች


ተዛማጅ ምርቶች፣ብርኬት ማምረትና መላክ፣ደን ማልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች ንግድ
ድርጅት የተሰረዘ ፈቃድ ሊተካለት የሚችለው በዚህ መመሪያ መሰረት ቅሬታ አቅርቦ ቅሬታው
ተቀባይነት ሲያገኝና ድርጅቱ ለስረዛ ያበቃውን ጥፋት ሙሉ በሙሉ በማረምና አዲስ የብቃት
ማረጋገጫ እንዲሰጠው ጥያቄ ሲያቀርብ የተደረገው የተሟላ ማስተካከያ በባለሙያዎች
ተረጋግጦ በተሰረዘው የምስክር ወረቀት ፋንታ አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ሊሰጠው ይችላል፡፡

መስሪያቤቱ በሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ላይ የቅሬታ አቀራረብ ሂደት


1. በሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ላይ ቅሬታ የሚቀርበው በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የአስተዳደራዊ እርምጃ
አወሳሰድና ቅሬታ አቀራረ መመሪያ መሰረት ይሆናል
2. ማንኛውም የግንድላ፣ አጣና፣ የጣውላ ኮምፐንሴቶና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች ንግድ ድርጅት
ስለብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ፣እድሳት፣ እገዳ እና ስረዛ ወይም ሌሎች
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በሚወስዳቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች ላይ ቅሬታ የተሰማው አካል
አቤቱታውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተቋቋመው ቅሬታ ሰሚ አካል
ማቅረብ ይችላል
3. የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ቅሬታ ሰሚ አካልም የቀረበለትን ቅሬታ በማጣራት በሰላሳ ቀናት ውስጥ
አግባብነት ያለው ምላሽ ለአመልካቹ መስጠት ይኖርበታል፡፡
4. ቅሬታ ቅራቢው በተሰጠው ግዜ ውሰጥ ምላሽ ባያገኝ ወይም የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ ሆኖ
ሳያገኘው ቢቀር ቅሬታውን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት መውሰድ ይችላል፡፡
19. አገልግሎት ክፍያ

ማንኛውም የጣውላ ኮምፖንሳቶና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች፣ብርኬት ማምረትና መላክ፣ ደን


ማልማትና ሌሎች ተዛማጅ ንግድ ድርጅት በኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ወይም አግባብ ባለው የክልል
ባለሥልጣን በሚሰጠው አገልግሎት አግባብነት ባለው አካል በሚወስነው የክፍያ ተመን መሠረት
ክፍያውን በቅድሚያ መፈፀም ይኖርበታል፡፡
ማንኛውም በደን ማልማት፣ በጣውላ ኮምፖንሳቶ፣ ብርኬትና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎችን
የተሰማራ ሰው

1. ተፈፃሚነት የማይኖራቸው መመርያዎች


ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ፣ ሰርኩላር ደብዳቤ፣ የአሰራር ልምድ በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ
ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት ይሆናል፡፡
20. መመርያው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ………../2013 ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ………….................ቀን 2011 ዓ.ም

ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ

የአከባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር

You might also like