Professional Documents
Culture Documents
የቀን ገቢ ግምት ግብር ስሌት
የቀን ገቢ ግምት ግብር ስሌት
የቀን ገቢ ግምት ግብር ስሌት
በአዲስ አበባ ከተማ የ 2009 ዓ.ም. አማካይ የቀን ገቢ ግምት መሰራቱን ተከትሎ የግምቱ ውጤት ለግብር ከፋዮች መገለፅ
ተጀምሯል፡፡ የግብር ከፋዮች የቀን ገቢ ግምት እና ዓመታዊ የሽያጭ መጠናቸው እንዲሁም ዓመታዊ ሽያጫቸውን መሰረት
አድርጎ የግብር ከፋዮች ደረጃ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የተገለፀውን መረጃ ማለትም የቀን ገቢ ግምቱንና ዓመታዊ የሽያጭ
መጠኑን በማየት ብቻ ያን ያህል ግብር ክፈሉ እንደተባሉ ቆጥረው የመደናገጥና የማማረር ሁኔታዎች መስተዋላቸውን ተከትሎ
የግብር ከፋዮች ዓመታዊ የቀን ገቢ ግምቱንና ዓመታዊ ሽያጩን መሰረት አድርጎ ገቢ ግብር እንዴት እንደሚሰላ ከዚህ ቀጥሎ
በምሳሌ እናቀርባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከምሳሌው እንደምንረዳው ግብር ከፋዮች የቀን ገቢ ግምቱን ተከትሎ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ዓመታዊ ግብር
እንደሚባለው በአብዛኛዎቹ ላይ የተጋነነ አይደለም፡፡ የተመደበላቸው ግብር አንድ ተቀጣሪ ከደመወዙ ላይ ከሚከፍለው
ግብር አነስተኛ ነው፡፡ ከላይ የተገለጹት ምሰሰሌዎች ለደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- የ 10 ሺ ብር ደመወዝተኛ በወር 2 ሺ 45 ብር፤ በዓመት ከሚከፈለው 120 ሺ ብር ደግሞ 24 ሺ 540 ብር ግብር
ይከፍላል፡፡ 120 ሺ ብር ዓመታዊ ገቢ ያለው ነጋዴ ግን የትርፍ መተመኛ መቶኛው 10 በመቶ ላይ ካረፈ ግብር የሚጠየቅበት
ገቢው 10 በመቶ ወይም 12 ሺ ብር ይሆናል፡፡ ቀሪው 90 በመቶ ወይም 108 ሺ ብር እንደ ወጪ ይታይለትና ከግብር ውጪ
ይሆናል፡፡ 12 ሺውን ደግሞ በግብር ማስከፈያ መጣኔ ሲሰላለት 10 በመቶ ላይ ያርፍና 1 ሺ 200 ብር ብቻ ዓመታዊ ግብር
ይጠየቃል፡፡ ስለዚህ የነጋዴውን 1 ሺ 200 ብር ከደመወዝተኛው 24 ሺ 540 ጋር ማነጻጸር በቂ ነው፡፡