Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

እማማ ኢትዮጵያ ግርማዋ ተገፎ የልጆቿ ሬሳ ሜዳ ላይ ረግፎ፣

አድኑኝ እያለች አሻግራ ወደኛ ምን አንጀት ያለው ነው አርፎ የሚተኛ

ብዙ አይን የሚያርፍባት ውብ ሀገር እያለን፣

እንዴት ፍቅር አጥተን ለማኝ እንሆናለን

እንዴት በሀገራችን ተስፋ እንዲህ ይመክናል፣

ከልጅ እስከ አዋቂ ሁሉም ለማኝ ሆኗል፡፡

ስለ ኢትዮጵያ ቁጭ ብለን አናውራ፣

ወይ ተነሱ እንርዳት ወይ ስሟን አንጥራ

ነበርሽ አስታራቂ ተከባሪ እንዳልሆንሽ

ለኮሪያ ለኮንጎ ጦር እንዳላሰለፍሽ

አባይን ደፍገሽ ስንቱን እንዳልመገብሽ

እንዴት አንዱን አጥተው ይራቡ ልጆችሽ

ለውጭ ወራሪ ሀይል አንድም ሳንደለል፣

በራሳችን ጥፋት ለችግር ተጋለጥን

መጠፋፋት ባይኖር ፍቅር ቢጠነክር

እርሀብና ችግር መች ይደፍሩን ነበር፡፡

You might also like