Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 15

የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን ፕሮጀክት ጽ/ቤት

ADDIS ABABA CITY PLANNING PROJECT OFFICE

የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መመሪያ

Local Streets Guideline

3/9/2017
ማውጫ

1. መግቢያ..........................................................................................................................................................................................................3
2. መመሪያው የተዘጋጀበት ዓላማ....................................................................................................................................................................3
3. ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ .................................................................................................................................................................................... 4
4. መርሆች እና ደረጃዎች .................................................................................................................................................................................7
5. የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ማሳያ ፕላኖች.................................................................................................................................................7

2|Page
መግቢያ

መንገድ የከተማ መዋቅር አካል እና ከተማን ቅርፅ የሚሰጥ ነው፡፡ የአንድ ከተማ የመንገድ ጥራት ደግሞ የነዋሪዎቸን የኑሮ ደረጃ
የማሻሻያ አንዱ መሳሪያ ነው፡፡መንገድ የተለያየ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ይህም ለሰዎች፣ መጓጓዣዎች እና የቁሳቁስ መዘዋወሪያነት
የሚያገለግል ቦታ ነው፡፡ በተጨማሪም መንገድ የመገበያያ ቦታዎች፣ በመንገድ ያሉ ፓርኮች መገኛ፣ መኖሪያ ቤት ጋር ያሉ
መግቢያዎች፣ የተለያዩ ፕሮግራሞች መሰብሰቢያ ቦታ፣ የመጫዎቻ ቦታ … የመሳሰሉት የሚከናወኑበት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ለሰዎች እና
ለቁሳቁስ መዘዋወሪያነት ከመንገዱ አካል ምጣኔ ሃብታዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስነምህዳራዊ፣ እንዲሁን ፍልስፍናዊ እንደምታ ያለው
ላይ ድርሻ ከመስጠት በተጨማሪ ያሉ ናቸው፡፡ የከተማ መንደሮች መንገድ ትልቅ አካል መሆኑን እና የከተማ መዋቅር አካል መሆኑን
መነሻ ያደርጋል፡፡ ይህም ለአንድ ከተማ ከስር የተጠቀሱት ሃቦች ከማሟላት አንፃር ነው፡፡

 የእግረኞችን ምቾት እና መጓጓዣዎች ፍጥነት የሚያመጣጥን የመንገድ ንድፍ እና የአጠቃቀም ስርዓት አቀናጅቶ ማዘጋጀት፡፡
 ተመጋጋቢ ሆነ የመንገድ መረብ መፍጠር ይህም እግረኞችን እና ሳይክል ተጠቃሚዎችን ሊያስተናግድ በሚችል የመሬት
አቀማመጥ ላይ ማቀድ፡፡
 ለእግረኞች ምቹ የሆነ እና እግረኞችን ሊስብ የሚችል መንገድ ንድፍ ማዘጋጀት ይህም ከመዘዋወር ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን
በመሬት ላይ የሚከሰተውን ሙቀት መጨመር ከመከላከል አንፃር ነው፡፡
 የመንገዶችን አገልግሎት አቅም ማሻሻል ይህም የመንገድ መዘጋጋትን ቀንሶ ሰዎችን እና ቁሳቁስን በተሻለ ፍጥነት ለማንቀሳቀስ ነው፡

የትራንስፖርት እና የመንገድ ጥናት የመዋቅራዊ ፕላን ጥናቶች መካከል አንዱ ክፍል ሲሆን ይህ ጥናት የትራስፖርት እና የመንገድ መረብ
በዝርዝር የተጠናበት እና በመዋቅራዊ ፕላን ላይ የተቀመጠበት ነው ፡፡ በመዋቅራዊ ፕላን ላይ የተካተቱት ጥናቶች የትራንስፖርት
መረብ ዝርዝር ጥናት እና የመንገድ መረብ ተዋረዱን ጠብቆ ሲሆን በመዋቅራዊ ፕላኑ ላይ የተካተቱት የመንገድ መረብ ተዋረዶችም
ዋና መንገድ፣ መለስተኛ ዋና መንገድ እና ሰብሳቢ መንገዶች ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በተሰሩ ፕላኖች ላይ ከሰብሳቢ መንገድ በታች ያሉ
መንገዶች ማለትም የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የሚጠኑት በአካባቢ ልማት ፕላን ውስጥ ሲሆን የአካባቢ ልማት ፕላንም የመሪ ፕላን
ማስፈፀሚያ ስልት ነው፡፡ በአሁኑ የመሪ ፕላን ጥናት ውስጥ የአካባቢ ልማት ፕላን በተወሰኑ ቁልፍ የኢንቨስትመንት አካባቢዎች ላይ
ብቻ የሚጠና ሲሆን ከመሃል ከተማ ውጪ ባሉ አካባቢዎች ላይ መዋቅራዊ ፕላኑ በቀጥታ የሚተገበር ይሆናል፡፡ ለከተማዋ ሁሉም
አካባቢዎች ዝርዝር አካባቢ ልማት ፕላን ስለማይሰራና ስለማይቻልም የመዳረሻ መንገዶች ከፕላን አፈፃፀምና ከመልካም አስተዳደር
አንፃር ከፍተኛ ችግር ሆነው ቆይተዋል፡፡ ይህን መሰረት በማድረግና የአፈፃፀም ችግሮችን ለመፍታት የአካባቢ ልማት ፕላን
በማይሰራላቸው አካባቢዎች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የመዋቅራዊ ፕላኑ የማስፈፀሚያ መሳሪያ እንዲሆኑ ታሳቢ በማድረግ ዝርዝር
የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ማሻሻያ (Local streets) ስራ ተሰርቷል፡፡

መመሪያው የተዘጋጀበት ዓላማ

 የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የመዋቅራዊ ፕላን አንድ ማስፈፀሚያ መሳሪያ ይሆናሉ፡፡


 ተደራሽ፣ ምቹ እና ደረጃውን የጠበቀ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እንዲኖር ማድረግ፡፡

የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ፋይዳ

1. የሥራ እድልን ከመፍጠር አኳያ

2. ተደራሽ (accessibility) ለማሳለጥ

3. የሰፈር የርስ በርስ ግንኙነትን ምቹ ለማድረግ

4. በሰፈር ገፅታ ላይ ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር

3|Page
ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ

አዲስ አበባ ከተማ የተለያየ የመንገድ አይነት ያላት ሲሆን እነዚህም ዋና መንገድ፣ መለስተኛ ዋና መንገድ፣ ሰብሳቢ መንገድ እና የውስጥ
ለወስጥ መንገድ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህ መንገዶች ውስጥ የከተማው መዋቅራዊ ፕላን አካል የሆኑት፡-

ዋና መንገድ (Arterial Street)

ይህ የመንገድ አይነት በዋናነት የሚያገለግለው ለረጅም ርቀት የትራፊክ እንቅስቃሴ ሲሆን ይህም ከጉዞ መነሻ እስከ መዳረሻ፣ ለከተማ
ውስጥ እንቅስቃሴ፣ ለብዙሃን መጓጓዣነት፣ ጥንቃቄ ለሚያስፈልጋቸው ቁሳቁስ መጓጓዣ እና ለክልል ጉዞዎች መስመር ናቸው፡፡በሁለት
ዋና መንገዶች መካከል ያለው አማካኝ ርቀት 2ኪ.ሜ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ያስቀመጠው የዋና መንገድ የስፋት
ወሰን ዝቅተኛው 30ሜትር ነው፡፡ ዋና መንገዶች ከዚህ በተጨማሪ ለሁለት ይከፈላሉ፡፡ ይህም የከተማ ትራንስፖርት መንገድ
(boulevard) እና የፍጥነት መንገድ (expressway) ተብለው ነው፡፡ የዋና መንገድ ንድፍ በዋናነት ጨረራማ (radial) ሲሆን ይህም
ከዋና ማዕከል ወደ ተለያዩ የከተማ መውጫዎች የሚሄዱ ናቸው ሌላኛው ዋና መንገድ ደግሞ የምህዋራዊ (orbital) የመንገድ አይነት
ነው፡፡

መለስተኛ ዋና መንገድ (Sub Arterial Street)


የመለስተኛ ዋና መንገድ ዋና ጠቀሜታ ደግሞ የተለያዩ አካባቢዎችን ከዋና መንገድ ጋር ማገናኘት ነው፡፡ ይህም መንገድ በዋና መንገዶች
መካካል ያለ፣ ብዙሃን መጓጓዣዎች መስመር እና የክልል መጓጓዣ መስመር ነው፡፡ በሁለት መለስተኛ ዋና መንገዶች መካከል ያለው
አማካኝ ርቀት 1 ኪ.ሜ ነው፡፡ እንዲሁም የመለስተኛ መንገድ አማካኝ የስፋት ወሰን በመዋቅራዊው ፕላን መሰረት ዝቅተኛው 25ሜትር
ነው፡፡ የመለስተኛ መንገድ ንድፍ(design) በአብዛኛው ቀጥተኛ ተላላፊ መስመር(grid iron) ይህም መለስተኛ መንገዶችን ከዋና
መንገድ ጋር የሚገናኝበት ነው፡፡

ሰብሳቢ መንገድ (Collector Street)

የሰብሳቢ መንገድ የጉዞ መጨረሻ ላይ ያለን የትራፊክ ፍሰት ተሸክሞ ከተለያዩ አገልግሎቶች መገኛ አካባቢ እና ከመኖሪያ አካባቢ ጋር
የሚያገናኝ ነው፡፡ ይህም በአብዛኛው በብዙሀን ትራንስፖርት፣ በእግረኛ እንቅስቃሴ እና በሳይክል ነው፡፡ በሁለት ሰብሳቢ መንገዶች
መካከል ያለው የርቀት ወሰን 500ሜትር ነው፡፡ በመዋቅራዊው ፕላን መሰረት የሰብሳቢ መንገድ የወሰን ስፋት ደግሞ 20 ሜትር ሲሆን
ዝቅተኛው የሰብሳቢ መንገድ ስፋት 15ሜትር፡፡ሰብሳቢ መንገድን እንደ መለስተኛ መንገድ ያለው የመንገድ ንድፍ(design) በአብዛኛው
ቀጥተኛ ተላላፊ (grid iron) ሲሆን ይህም ሰብሳቢ መንገድን ከመለስተኛ መንገድ ጋር የሚገናኝበት ነው፡፡

የውስጥ ለውስጥ መንገድ (Local Street)

ይህ መንገድ ከሰብሳቢ መንገድ በታች ያለ እና ተጓዦችን ከመኖሪያና ከአነስተኛ አገልግሎቶች ወደ ሰብሳቢ መንገድ የሚያገናኝ የመንገድ
ዓይነት ነው፡፡ በውስጥ ለውስጥ መንገዶች መካከል ያለው ርቀት ደረጃዎች ከ50 እስከ 100ሜ ሲሆን ስፋቱ ደግሞ 10ሜትር ነው፡፡

የተለያዩ አለም አቀፍ ከተሞች የውስጥ ለውስጥ መንገዶቻቸውን ካላቸው የመሬት አጠቃቀም ጋር የተለያየ ክፍል ይሰጡታል፡፡ ይህም
በመኖሪያ አካባቢ ያለ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ኢንዱስትቦታ ላይ ያለ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና የንግድ ቦታዎች ያለ የውስጥ
ለውስጥ መንገድ ናቸው፡፡ እያንዳንዳቸው የተለያየ የመንገድ አካል ያላቸው ሲሆን የመኖሪያ አካባቢ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች
ባመዛኙ የእግረኛና የብስክሌት ሆነው ለአውቶሞቢል እና አነስተኛ መኪናዎች ጭምር የሚገለግሉ ናቸው፡፡ የንግድ ቦታዎች ላይ ያሉ
የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ሲታቀዱ እግረኛን እና አነስተኛ መጓጓዣዎችን ከግምት ውስጥ በሚያስገባ መልኩ ሲሆን በአብዛኛው
ለሞተር ተሸከርካሪዎች በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ዝግ ይሆናሉ፡፡ የኢንዱስትሪ ቦታ ዎች ላይ ያሉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግን
ሲታቀዱ የጭነት መኪናዎች እና የእግረኞችን መዘዋወሪያ ቦታ ከግምት ውስጥ በሚያስገባ መልኩ በመሆኑ ስፋታቸው ከ15 ሜትር
አያንስም፡፡

4|Page
በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የሚገኙበት ሁኔታ

የትስስር ችግር ያለባቸው፡- አብዛኛዎች በከተማዋ ውስጥ የሚገኙት ውስጥ ለውስጥ መንገዶች የትስስር ችግር ያለባቸው እና የሚቋረጡ
ናቸው፡፡

ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ያልሆኑ፡- በከተማዋ ውስጥ ካሉ ጥቂት አካባቢዎች ውጪ አብዛኛዎች የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ
መንገዶች ምቹ ስላልሆኑ እና በአግባቡ ያልተሸፈኑ ስለሆኑ ለሁሉም ተጠቃሚዎች ምቹ አይደሉም (በተለይ ለአዛውንቶች፣ ለህፃናት እና
ለአካል ጉዳተኞች)፡፡

መንገዶቹ ጠባብ ስለሆኑ የእግረኛ እና የመኪና እንቅስቃሴን ያውካሉ፡- በከተማ ውስጥ ሌላ የሚስተዋለው ችግር ተገቢ የሆነ የመንገድ
ወሰን ስፋት አለመኖር ነው፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተለያየ የመንገድ ወሰን ስፋት ከመኖሩም በተጨማሪ መንገድ በሚጠብባቸው
አካባቢዎች ላይ የሚኖረው የመንገድ ወሰን ስፋት የሞተር እና ሞተር አልባ መጓጓዣዎችን ለማስተናገድ አያስችልም፡፡ በዚህም ምክንያት
አንቡላንስ፣ እሳት አደጋና ሌሎች አስቸኳይ ችግሮችን የከፋ ያደርጉታል፡፡

የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ማከናወኛ መሆን፡- የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በአብዛኛው በከተማው አሰፋፈር እና ከከተማው
የአኗኗር ባህል ምክንያት የተለያዩ አገልግሎቶች ማስተናገጃዎች (የልጆች መጫወቻ፣ ብቅል እና እህል ማስጫ፣ ምግብ ማብሰያ፣ ልብስ
ማጠቢያ፣ እቃ ማስቀመጫ፣…ወዘተ) ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት የሰዎችም ሆነ የመኪናዎች እንቅስቃሴ እንዲታወክ ያደርጋል፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች እና ቆሻሻ መጣያ ቦታዎች አለመኖር፡- የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በቂ የሆነ የፍሳሽ ማስገጃ መስመር
የላቸውም፡፡ በተጨማሪም በከተማ ውስጥ ባለው ትክክለኛ ያልሆነ የቀሻሻ አጣጣል ባህል ምክንያት አብዛኛዎች የውስጥ ለውስጥ
መንገዶች በፍሳሽ እና በደረቅ ቆሻሻ የተሞሉ ናቸው፡፡

ቀጣይነት የሌላቸው መንገዶች መኖር፡- በአንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በማህል ከተማ ውስጥ የሚገኙ መንገዶች የሚቆራረጡ
ስለሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማገናኘት አይችሉም፡፡ ይህም በከተማዋ ውስጥ ያለው አሰፋፈር በአብዛኛው ጥግግት ያለበት እና
የቤቶቹ አይነት ደግሞ ፕላንን የጠበቁ ስላልሆኑ ነው፡፡

ተዋረዱን ያልጠበቀ የመንገድ ስርዓት፡- በከተማ ውስጥ ያሉ መንገዶች ተዋረዳቸውን ያለመጠበቅ ችግር በሁሉም የመንገድ አይነቶች
ላይ የሚስተዋል ነው፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችም ከሰብሳቢ መንገድ ጋር መመጋገብ ሲኖርባቸው ከመለስተኛ እና ከዋና መንገዶች
ጋር የሚገጥሙበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህ ደግሞ ያልተሳለጠ ጉዞ ፍሰትን የሚፈጥር ሲሆን በመንገዶች ላይ የሚኖረውንም የጉዞ ፍሰት
በከፍተኛ ደረጃ ያውካል፡፡

በቂ የሆነ የመብራት አቅርቦት አለመኖር፡- የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በአብዛኛው የብርሃን አቅርቦት የሚያገኙት ከግለሰብ መኖሪያ እና
ድርጅት ስለሆነ ቀጣይነት ያለውና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የመብራት አገልግሎት ባለመኖሩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለምሽት ጉዞ
አመቺ አይደሉም፡፡ ይህም ለሰዎች ደህንነት የሚሰያጋ እና ምቹ ያልሆነ ነው፡፡

የመልክዓ ምድር አቀማመት፡- ምእራባዊው እና ሰሜናዊው የከተማዋ ክፍል በዓብዛኛው ጠመዝማዛ እና ዳገትነት ያለው ስለሆነ በነዚህ
አካባቢዎች ያለ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በዓብዛኛው ምቹ ባልሆነ የመሬት አቀማመጥ ላይ ያሉ ሲሆን እነዚህም መንገዶች ለሁሉም
መጓጓዣዎች ምቹ ያልሆኑ ናቸው፡፡ በዓብዛኛው ጊዜም የጎርፍ ማወገጃ መስመር ይመስላሉ፡፡

በወንዞች አካባቢ አሰፋፈር መኖር፡- በአንዳንድ ወንዞች አካባቢ ላይ ሰዎች ሰፍረው ይኖራሉ፡፡ ወንዞች አካባቢ ያሉ መንገዶች ደግሞ
ለሰዎች እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆኑና ወንዞችን የማያቋርጡ ስለሆኑ መንገዶች ደግሞ የመንገድ ተደራሽነት ችግር በወንዞች አካባቢም
ይስተዋላል፡፡

5|Page
የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለማቀድ የተቀመጡ ምክንያቶች

1. ከአካባቢ ልማት ፕላን በሌለባቸው አካባዎች መሪ ፕላኑን ለማስተግበር አንዲቻል፡፡


2. የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሌለባቸውን አካባቢዎችና አገልግሎቶች በመንገድ ተደራሽ ለማድረግ፡፡
3. ተገቢና ደረጃውን (standard) የጠበቀ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ወሰን መፍጠር፡፡
4. በውስጥ ለውስጥ መንገዶች መካከል ተገቢውን ርቀትን (span) እንዲኖር ለማድረግ
5. ለነዋሪዎች እና ለአገልግሎት ምቹ መንገድን ለመፍጠር በተገቢ ንጣፍ የተሸፈኑ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች አንዲኖሩ
ለማድረግ፡፡
6. ከመንገድ መጨናነቅና መዘጋጋት ነፃ የሆነ መንገድ መፍጠር

ጥናቱን ለማጥናት የተጠቀምናቸው መረጃዎች

የውሰጥ ለውስጥ መንገዶች ማስፋፊያ እና ማሻሻያ ጥናት የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን የተጠቀመ ሲሆን እነዚህም የመረጃ ምንጮች
በዋናነት ከ2003 የመስመር ካርታ (line map) የተወሰደ ሲሆን ሌሎች ማመሳከሪያ መረጃዎች የተሰበሰቡት ደግሞ ከጂኦ አንፎርሜሽን
ሲስተም(GIS)፣ በሊዝ ከተሰጡ ቦታዎች የተሰበሰቡ ካርታዎች፣ ከጉግል ኧርዝ ፣ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት፣ ከአካባቢ ልማት ፕላን፣
ከአዲሱ መዋቅራ ፕላን እንዲሁም በወረዳዎች ላይ ደግሞ ከመስክ በተሰበሰበ መረጃ ነው፡፡

6|Page
መርሆች እና ደረጃዎች (Principles and Standards)
ቀጥሎ የተጠቀሱት ደረጃዎች እና መርሆች የተቀመጡት አለም አቀፍ እና ሃገር አቀፍ ልምዶችን፣ ከተማ ውስጥ ያለውን አማካኝ የይዞታ
ስፋት፣ በከተማ ውስጥ ያለውን የህንፃዎች ስብጥር እና የከተማውን የአሰፋፈር ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡

ርቀት፡- ከአንድ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እስከ ሌላኛው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ያለው ርቀት ከ50 እስከ 100ሜትር ድረስ መሆን
አለበት፡፡ ትልልቅ ግንባታዎች ባሉበት ቦታ የተቀመጠውን ደረጃ ማሟላት በማይቻልባቸው ቦታዎች ደግሞ ከ150 ሜትር መብለጥ
የለበትም፡፡

ስፋት፡- ለመኖሪያ ቦታዎች እና ለኢንዱስት ቦታዎች የተቀመጠው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ስፋት የተለያየ ነው፡፡

 የመኖሪያ ቦታዎች - በመኖሪያ ቦታዎች ያለው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ስፋት 10ሜትር መሆን ያለበት ሲሆን በአንዳንድ
ትልልቅ ግንባታ በተፈፀመባቸው፣ በታሪካዊ እና መጠበቅ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች መንገዱ ቀድሞ የነበረውን
የመንገድ ስፋት ጠብቆ እንዲሄድ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ከ6ሜትር ስፋ ማነስ የለበትም፡፡
 የኢንዱስትሪ ቦታዎች - በኢንዱስትሪ ቦታዎች ላይ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች እንደተጠበቁ ሆነው የውስጥ ለውስጥ
መንገዶች ከ15 ሜትር በታች መሆን የለባቸውም፡፡

ወንዞች - የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ወንዞችን ማቋረጥ የማይኖርባቸው ሲሆን በአማካኝ በ500 ሜትር ርቀት ወንዞችን ማቋረጫ
የሌላቸው አካባቢዎች ሲኖሩ ይህንን ለማሟላት በተመረጡ ቦታዎች ብቻ ሰብሳቢ መንገድ እንዲኖር ይደረጋል፡፡

አረንጓዴ ጥብቅ ቦታዎች፡ - የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ጥብቅ የአረንጓዴ ቦታዎችን አያቋርጡም፡፡ በፕላን በጥብቅ ለአረንጓዴነት
ብቻ የተያዙ ቦታዎችን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች አቋርጠው መግባት አይኖርባቸውም ነገር ግን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ጥብቅ
የአረንጓዴ ቦታዎቹ በሌላ አገልግሎት እንዳይጣሱ እና ለእግረኛ እንቅስቃሴ እንዲያመቹ ጥብቅ የአረንጓዴ ቦታዎችን ይከባሉ፡፡

የመንገድ ተዋረድ (Street Hierarchy) - የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ወደ ሰብሳቢ መንገዶች ይመገባሉ እንጂ አልፈው ወደ ዋና እና
መለስተኛ መንገድ መግባት የለባቸውም፡፡ በ 500 ሜትር ስፋት ውስጥ ሰብሳቢ መንገድ ካልኖረ እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ወደ
ዋና መንገድ የሚገቡበት አንዳንድ ሁኔታ ሲኖር የአካባቢው ሁኔታ ታይቶ የተመረጡ ውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ወደ ሰብሳቢ
መንገድ መቀየር ይቻላል፡፡

መጋጠሚያ ቦታዎች (junctions) - በመጋጠሚያዎች ላይ የሚከሰቱ ግጭቶችን እና ተመሳሳይ የትራፊክ ችግሮችን ለማስወገድ
በአማካኝ የ3ሜትር መታጠፊያ በመጋጠሚያዎች ላይ በእቅድ መያዝ አለበት፡፡ ትላልቅ ይዞታዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች
የመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ መታጠፊያዎች ይወገዳሉ፡፡

ምጣኔ ሃብታዊ (Economic) ፋይዳቸው ከፍተኛ የሆኑ ቦታዎች - የውሰጥ ለውስጥ መንገዶች የማሻሻያ ጥናት ሲከናወን ከግምት
ውስጥ ማስገባት ያለበት የተለያዩ ጉዳዮች ያሉ ሲሆን እነዚህም በአንድ አካባቢ ላይ ያለውን የህንፃ ከፍታ፣ የመሬት ሊዝ፣ የግንባታ
ዓይነት እና የመሬት ይዞታን ያካትታል፡፡ይህንን መሰረት በማድረግ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ
የሆኑ ቦታዎች መነካት አይኖርባቸውም፡፡

የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ማሻሻያ ሃሳብ

የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለማሻሻል የተለያዩ ደረጃዎችን ጥናቱ የተጠቀመ ሲሆን ይህም ያሉትን የመንገድ አይነቶች በመመሪያው
መሰረት የማስተካከል ስራ ነው፡፡ በአብዛኛው የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የሰዎች ቀደምት አሰፋፈር ላይ መሰረት ያረጉ ስለሆነ
መንገዶች በፕላን ያልተመሩ (organic) ናቸው፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ ጥናቱ ደረጃቸውን የጠበቁ እና በፕላን የተሰሩ መንገዶች
እንዲኖሩ በእቅድ ይዟል፡፡ አብዛኛዎች መንገዶች የተቀመጠውን የርቀት ወሰን (ለመኖሪያ አካባቢ 10ሜትር፣ ለኢንዱስትሪ አካባቢ
15ሜትር) የጠበቁ እንዲሆኑ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ርቀቱን መጠበቅ የማይችሉበት አጋጣሚ ሲኖር ደግሞ
ለተቀመጡት መርሆች እና ደረጃዎች የተጠጋ የርቀት ወሰን ተቀምጧል፡፡

የመንገድ ተዋረዳቸውን ያልጠበቁ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በሰብሳቢ መንገድ እንዲጠቃለሉና ወደሚቀጥለው ዋና መንገድ እንዲገቡ
የተደረገ ሲሆን ሰብሳቢ መንገድን ማቀድ በማይቻልበት የመንገድ ሁኔታ ላይ ያሉ እና በቀጥታ ወደ ዋና መንገድ የሚገቡበት ሁኔታ ወደ

7|Page
ዋና መንገድ መገናኛ የሌላቸው መንገዶች (dead end) እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በቀጥታ ወደ ዋና መንገድ የሚገቡ የውስጥ ለውስጥ
መንገዶች ለሞተር ትራንስፖርት የማይፈቀዱ ሲሆን ለእግረኛ እንቅስቃሴ ግን አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡

ከዚህ በፊት በ6ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በፕላን የተሰሩ አካባቢዎች የሚኖራውን ምጣኔ ሃብታዊ ተፅህኖ መሰረት የአንድ
አቅጣጫ የመኪና መንገድ በማድረግ በ6ሜትር እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ትልቅ ግንባታዎች ያረፈባቸውን ቦታዎችም
እደዚሁ የሚኖራቸውን የመንገድ ስፋት ይዘው ይቀጥላሉ፡፡

መመሪያው ካስቀመጠው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ስፋት በላይ ያላቸው የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ከተቀመጠው የ10 ሜትር ደረጃ
በላይ ያለው የመንገዱ ስፋት ለአካባቢው ማስዋቢያ ለአረንጓዴ ሽፋን የሚውል ይሆናል፡፡

የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንደ መዋቅራዊ ፕላን መንገዶች በአዋጅ የፀደቁ አለመሆናቸውን እና የአካባቢ ልማት ፕላን ሲሰራ ሊሻሻሉ
የሚችሉ ናቸው፡፡ ሊሻሻሉ የሚችሉባቸውም ሁኔታዎች ቀጥሉ የተተቀሱት ሁኔታዎ መሟላት ሳይችሉ ሲቀሩ ነው፡፡

1. በአምስት አመት የአካባቢ ልማት ፕላን በሚሰራላቸው ቦታዎች ላይ ጥናቱ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ማሻሻያ ያላጠና ሲሆን
እነዚህም ቦታዎች በቀጣይ የአካባቢ ልማት ፕላን የሚጠናላቸው ስለሆኑና በቀጣዩ ጥናት ውስጥ በዝርዝር መንገዶቹን ጨምሮ
ይጠናሉ፡፡ ሆኖም በነዚህ አካባቢዎች ላይ የሚታቀዱ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በዚህ መመሪያ ላይ ያለውን መርዎች እና
ደረጃዎች በቀጥታ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በአስር ዓመት በሚለሙ ቦታዎች እና በሌሎች የአካባቢ ልማት ፕላን በሚሰራላቸው አካባቢዎች ደግሞ ላይ አካባቢዎቹ መልሶ
ማልማት (renewal) የሚከናወንባቸው ከሆነ የዚህን መመሪያ መርዎች እና ደረጃዎች ቀጥታ መወሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ የማሻሻያ
ጥናት (upgrading) የሚሰራላቸው አካባቢዎች ግን ይህ ጥናት የተጠናበት አካሄድ ተጠብቆ ይጠናል ይህም ትልቅ ግንባዎች
ያረፉባቸውን ቦታዎች፣ ታሪካዊ ቦታዎች፣ ትልልቅ ተቋማትን … ሳይነኩ የአካባቢውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይጠናል፡፡

በተጨማሪም የአካባቢ ልማት ፕላኖች ሲጠኑ በዚህ ጥናት ውስጥ የተካተቱትን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መጠበቅ ካልተቻለ
ማለትም ጥናቱ የሚፈጠረው የመሬት አጠቃቀም እና መንገዶቹ ካልተጣጣሙ መንገዶቹን ከመሬት አጠቃቀም ጋር አጣጥሞ
ማጥናት የሚቻል ይሆናል፡፡

8|Page
የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ማሳያ ፕላን

የመኖሪያ አካባቢ ያሉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች

ምንጭ (የOregon ከተማ የአካባቢ መንገድ ንድፍ መመሪያ)

9|Page
የመንገድ ወሰን ስፋት 10 ሜትር
 የተጨመረ የመንገድ ስፋት
 በአንድ አቅጣጫ
ከአንድ የመንገድ ጠርዝ እስከ ቀጣይ የመንገድ ጠርዝ ያለው 8ሜትር
ስፋት
 የተጨመረ ስፋት
 በአንድ አቅጣጫ
ከፍተኛ ልዩነት(grade) 15%
ትልቁ የመዞሪያ ራዲየስ 30ሜ
የመሬት አጠቃቀም ዝቅተኛ ጥግግት ያለበት የመኖሪያ ቦታ፣ የክፍት ቦታ እና መናፈሻ
የመሬት አጠቃቀም ትምህርት ቤት፣ የማምለኪያ ቦታ እና ህንፃዎች

የኢንዱስት ቦታዎች ላይ ያሉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች

የመንገድ ወሰን ስፋት (19.2ሜ) – (22.2ሜ)


የፍጥነት ንድፍ (40ኪሜ በሰዓት)
ከአንድ የመንገድ ጠርዝ እስከ ሌላኛው የመንገድ ጠርዝ ያለው ስፋት (13.2ሜ)
ከፍተኛ ልዩነት(grade) 8%
ትልቁ የመዞሪያ ራዲየስ 85ሜ
የመሬት አጠቃቀም የኢንዱስትሪ

ምንጭ (የ Oregon ከተማ የአካባቢ መንገድ ንድፍ መመሪያ)

10 | P a g e
ምንጭ (የOregon ከተማ የአካባቢ መንገድ ንድፍ መመሪያ)

11 | P a g e
የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ(Street Cross - section) ማሳያ

የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ ማሳያ በ4 ሜትር መንገድ

የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ ማሳያ በ6ሜትር መንገድ

12 | P a g e
የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ ማሳያ በ8 ሜትር መንገድ

የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ ማሳያ በ9 ሜትር መንገድ

13 | P a g e
የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ ማሳያ በ10 ሜትር መንገድ

የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ ማሳያ በ10 ሜትር መንገድ

14 | P a g e
የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ ማሳያ በ15 ሜትር መንገድ

የመንገድ የጎንዮሽ ዕይታ ማሳያ በ25 ሜትር መንገድ

15 | P a g e

You might also like