Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 5

ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል'ዑሰይሚን

- ረሂመሁሏህ - በሸዋል ፆም ዙሪያ


የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ፡-
ከሸዋል ወር የስድስት ቀናት ጾምን አስመልክቶ በላጩ የቱ ነው?
መልስ፡-የሸዋልን ወር የስድስት ቀናት ጾምን በተመለከተ
በሚከተሉት ምክንያቶች ከዒድ በኋላ አከታትሎና ወዲያውኑ
መጾሙ በላጭ እንደሆነ የእውቀት ባለቤቶች ግልጽ አድርገዋል፡፡
- “ሱምመ አትበዓ” ከዚያም ያስከተለ የሚለውን የሐዲስ መልክት
ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡
- እነዚህን ጾሞች በተግባር ያዋለ ሰው የተወደሰና ለዚህ መልካም
ተግባር የሚያነሳሱ መረጃዎችን ተግባራዊ ያደረገ ተሸቀዳዳሚ
መሆኑን ያሳያል፡፡
- በአምልኮ ላይ ያለውን ቁርጠኝነትና ሙሉነትን ይጠቁማል፡፡
ስለዚህ ባሪያው ለቀጣይ ጊዜ ምን እንደሚገጥመው ስለማያውቅ
እነዚህን ቀናቶች ፈጥኖ መጾም ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ በጾም ብቻ
ሳይሆን በማንኛውም ዒባዳ ላይ ልንከተለው የሚገባ ጎዳና ነው፡፡
٩٨٣\‫مجموع فتاوى ورسائل اجملدل السابع عرش‬
http://t.me/alateriqilhaq
ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል'ዑሰይሚን
- ረሂመሁሏህ - በሸዋል ፆም ዙሪያ
የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ፡-
አንድ ሰው ከሸዋል ወር መርጦ የፈለገውን መጾም ይችላል? ወይስ የታወቁ
ቀናቶች ናቸው? አንድ ሙስሊም እነዚህን ቀናቶች አንዴ ከጾመ ከዚያ በኋላ
በየአመቱ የመጾም ግዴታ አለበት?
መልስ፡- ከረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለው ሐዲስ ተላልፏል፡-
‫من صام رمضان ثم أتبعه ستا من شوال كان كصيام الدهر‬
“ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ ልክ አመቱን በሙሉ
እንደጾመ (ይቆጠራል)፡፡” ሙስሊም፡
እነዚህ ስድስት ቀናቶች የታወቁና የተገደቡ አይደሉም፡፡ ከወሩ በአጠቃላይ
ከሚገኙ ቀናቶች የፈለገውን መርጦ ይጹም፡፡ ከፈለገ ከወሩ መጀመሪያ ወይም
ከወሩ መካከል ወይም ከወሩ መጨረሻ ከሚገኙ ቀናቶች መርጦ መጾም
ይችላል፡፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው ጉዳዩ ሰፊ እንጅ በጣም የሚያጨናንቅ
አይደለም፡፡ ከመልካም እሽቅድድም አኳያ ከዒድ በኋላ አከታትሎ መጾሙ
አማራጭ የለውም፡፡ ከፈለገ ያከታትል ከፈለገ ነጣጥሎ መጾም ይችላል፡፡
የሸዋል ጾም ፈርድ ሳይሆን ሱና በመሆኑ የተወሰነውን አመት ጹሞ ሌላውን
አመት ቢተው ችግር የለውም፡፡

٩٣\‫مجموع فتاوى ورسائل اجملدل السابع عرش‬


http://t.me/alateriqilhaq
ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል'ዑሰይሚን
- ረሂመሁሏህ - በሸዋል ፆም ዙሪያ
የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ፡-
አንዲት ሴት የረመዷን ቀዷ ቢኖርባት ከቀዷው በፊት የሸዋልን
ስድስት ቀናት ጾም ታስቀድም ወይስ የረመዷንን ቀዷ ታስቀድም?
መልስ፡- አንዲት ሴት የረመዷን ቀዷ ካለባት ከቀዷው በፊት
የሸዋልን ስድስት ቀናቶች ማስቀደም የለባትም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ
‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"‫"من صام رمضان ثم أتبعه ستا من شوال‬
“የረመዷንን ጾም የጾመ ከዚያም ከሸዋል ስድስትን ያስከተለ” ሙስሊም፡ 1164
ቀዷ ያለባት ሴት የሸዋልን ስድስት ቀናት ምንዳ ሊሟላ
የሚችለው ቀዷውን ስታጠናቅቅ ነው፡፡ ለምሳሌ አንዲት የወሊድ ደም
የምታይ ሴት የሸዋልን ወር ጨርሳ ዙል ቃእዳ ወር ከገባ በኋላ
የወሊድ ደም ቢያቆም ስድስቱን ቀናት በዙል ቃእዳ ወር መጾም
ትችላለች፡፡ ይህ ጾሟ ልክ በሸዋል ወር እንደጾመች ተደርጎ
ይቆጠርላታል፡፡ ምክንያቱም የዘገየችው በአንገብጋቢ ምክንያት
በመሆኑ ነው፡፡
٦٨٣\‫مجموع فتاوى ورسائل اجملدل السابع عرش‬
http://t.me/alateriqilhaq
ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል'ዑሰይሚን
- ረሂመሁሏህ - በሸዋል ፆም ዙሪያ
የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ፡-
ቀዷ እያለበት የሸዋልን ስድስት ቀናት በሚጾም ሰው ላይ የሚሰጡን
አስተያየት ካለ?
መልስ፡- ለዚህ መልስ የሚሆነው የሚከተለው የረሡል ‫ ﷺ‬ሐዲስ
ነው፡-
‫من صام رمضان ثم أتبعه ستا من شوال كان كصيام الدهر‬
“ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ ልክ
አመቱን በሙሉ እንደጾመ (ይቆጠርለታል)፡፡” ሙስሊም፡
ቀዷ እያለበት የሸዋልን ስድስት ቀናት የሚጾም ሰው “ረመዷንን
የጾመ ከዚያም ከሸዋል ስድስቱን ያስከተለ ይባላል? አይባልም?
ለዚህ የምንሰጠው መልስ ይህ ሰው ረመዷን የተባለውን ወር
አሟልቶ አልጾመም፡፡ የረመዷንን ወር ጾመ የሚባለው ረመዷንን
አሟልቶ ሲጾም ነው፡፡ በዚህ መሰረት የረመዷንን ቀዷ ያወጣ እንጅ
የረመዷን ቀዷ እያለበት ከሸዋል ስድስት ቀናትን የጾመ አጅሩ
አይረጋገጥለትም፡፡
٧٨٣\‫مجموع فتاوى ورسائل اجملدل السابع عرش‬
http://t.me/alateriqilhaq
ሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል'ዑሰይሚን
- ረሂመሁሏህ - በሸዋል ፆም ዙሪያ
የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ፡-

የሸዋል ስድስት ቀን መጾም ያለበት ከዒዱ ቀጥሎ


በተከታታይ መሆን አለበት ፣ ይህ ካልሆነ ጥቅም
የለውም የሚሉ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡

መልስ፡- ከሸዋል ስድስቱ ቀናቶች ከዒዱ ቀጥሎ


ወይም ከወሩ መጨረሻ ላይ ቢጾሙ ችግር
የለውም፡፡ ማከታተልም ለያይቶ መጾምም
ይቻላል፡፡ ዋናው ነገር የረመዷን ጾም ካበቃ በኋላ
መሆኑ ነው፡፡ ቀዷ ያለበት ሰው ቀዷውን
ከስድስቱ የሸዋል ሱናዎች ያስቀድመው፡፡

٨٨٣\‫مجموع فتاوى ورسائل اجملدل السابع عرش‬


http://t.me/alateriqilhaq

You might also like