Professional Documents
Culture Documents
Special Issue On Texa: Published By: Internal Communications Section
Special Issue On Texa: Published By: Internal Communications Section
በዚሁም መሰረት ቴ.ል.አ በአሁኑ ጊዜ ስልጠናዎችን በስፋት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም የሰልጣኞች በስልጠና ላይ
ያለመገኘትና ስልጠናን አቋርጦ የመውጣት ችግር አካዳሚው በሚያደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲያሳድር ቆይቷል፡፡
ይህንንም ችግር ለማቃለል ቴ.ል.አ ሰልጣኞችን በስልክ በመጋበዝና በስልጠናው ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ለሰጡ ሰራተኞች
በኢ-ሜይል የስልጠና ተሳትፎ ግብዣ ሲልክ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ይህ አሰራር በቴልአ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ጫና ከማሳደሩም በላይ
ውጤታማነቱም እንደሚጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ በመሆኑም ቴ.ል.አ በዚህ አሰራር ላይ ማሻሻያ በማድረግ ለስልጠና ውጤታማነት
ሁሉም የበኩሉን ሚና በላቀ ሁኔታ ሊወጣ የሚችልበትን የአሰራር ስርአትና የሃላፊነት ድርሻ እንደሚከተለው አስቀምጧል፡፡
ማስታወሻ፣
•ሰልጣኞች ከሰለጠኑ በኋላ ያገኙትን እውቀትና • ሰልጣኞች ከስልጠናው አለበቂ ምክንያት • የሥልጠና ማስተባበሪያ ክፍሉም ከስልጠና
ልምድ ተግባራዊ በማድረግ፣ የተማሩትን ለሌሎች ከቀሩ ወይም ካቋረጡ የሰልጣኞች የቅርብ የቀሩ ወይንም ያቋረጡ ሰራተኞችን ዝርዝር
በማካፈል እንዲሁም ራሳቸውን በቀጣይነት አለቆች ከቴ.ል.አ. ሥልጠና ማስተባበሪያ በመያዝ በቀጣይ ለሚወሰዱ እርምጃዎች ዝግጁ
በማብቃት (ባዘጋጁት ቀጣይ የራስ ማብቂያ ክፍል በሚደርሳቸው ሪፖርት መሰረት በስራ ማድረግ እና ለስራ ክፍሉ በወቅቱ ማሳወቅ
መርሃ-ግብር እና ከዚህም ባለፈ) ለግልና ለጋራ ምዘና ውጤትም ሆነ ሌሎች ወደፊት በሚወጡ
ልማት መስራት እንዲሁም አስተዳደራዊ መመሪያዎች መሰረት ተገቢውን • የስልጠና ውጤታማነትንና ተግባራዊነትን
ዕርምጃ መውሰድና ማሳወቅ እንዲሁም ለመለካት የሚያስችል መጠይቅ አዘጋጅቶ
•የስልጠናውን ውጤታማነትና ተግባራዊነት ለሰልጣኞችና ለሰልጣኞች የቅርብ አለቆች
ለመለካት ለሚላኩ መጠይቆች ወቅታዊና ተገቢ • ሰልጣኞች ከሰለጠኑ በኋላ የተማሩትን በመላክ ዳሰሳ ማከናወን፣ የዳሰሳውን ውጤት
ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተግባር እንዲያውሉ፣ ለሌሎች እንዲያካፍሉና ማሳወቅ እንዲሁም የማሻሻያ ስራዎችን ማከናወን
በቀጣይነት፣ ራሳቸውን እንዲያበቁ ሁኔታዎችን ይጠበቅበታል፡፡
ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል፡፡
• በቴልአ ‘የለርኒንግ እና ዴቨሎፕመንት ፖሊሲ ፕሮሲጀር’ መሰረት አንድ ሰልጣኝ ቢያንስ የስልጠናውን ጊዜ ዘጠና በመቶ (90%) በስልጠናው ላይ
ካልተገኘ ስልጠናውን እንዳልተካፈለ ተቆጥሮ የወሰደው ስልጠና በግል ማህደሩ ውስጥ እንዳይመዘገብ ይደረጋል፡፡
• አንድ ሰልጣኝ ከስልጠና ያለፈቃድ የሚቀር ወይንም አቋርጦ የሚወጣ ከሆነ ከስልጠና በመቅረቱ ከስራ እንደቀረና የስነ-ምግባር ጉድለት እንደፈፀመ
ተቆጥሮ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ይደረጋል::
ቴ.ል.አ ሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች ተቋሙን ስኬታማ ለማድረግ ፅኑ ፍላጎትና ተነሳሽነት እንዳላቸው ያምናል፡፡ በመሆኑም
ሁሉም ሰራተኞች በተጠሩበት ስልጠና ላይ መገኘታቸውና ስልጠናውን መተግበራቸው ለራሳቸውና ለተቋሙ የሚያስገኘውን ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን ጥቅሞች ከግንዛቤ በማስገባት የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ ያቀርባል፡፡
• ሠራተኞች ከሥልጠናው የሚገኘውን እውቀትና ልምድ መቅሰማቸው ለውስጥም ሆነ ለውጭ ደንበኞች ብልጫ ያለው አገልግሎት
እንዲሰጡ በማገዝ የደንበኞችን እርካታ የላቀ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
• በአሰራር ጉድለት ምክንያት የሚመጡ ብክነቶችን በመቀነስና ውጤታማነትን በማሻሻል የተቋሙ ገቢ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
• የሠራተኞችን የግል ምርታማነት በመጨመር ሠራተኞች በስራቸው እንዲደሰቱና የተሻለ የስራ ውጤት እንዲያገኙ ያግዛል፡፡
• በስልጠና የተያዘው እቅድ በአግባቡ እንዲከናወን በማገዝ፣ ቴ.ል.አ የተቀረፁ ፕሮራሞችን በፍጥነት የሚሰጥበትንና አዳዲስ የስልጠና
ፕሮግራሞችን የሚያመርትበትን ፍጥነት እንዲጨምር ያግዛል፡፡
• ለስልጠና የተመደበው የሰው ሃይል፣ ጊዜ እና ጉልበት፤ የስልጠና ክፍል/ላቦራቶሪ እንዲሁም መሳሪያና ቁሳቁሶች እንዳይባክኑ
ያደርጋል፡፡
ስለሆነም ከጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ሰልጣኝ (ሠራተኛ፣ የሥራ ኃላፊ) የስልጠና ጥሪ የሚደርሰው በኢ-ሜይል
አማካኝነት ብቻ እንደሆነ ተገንዝቦ የበኩሉን ሃላፊነት በመወጣት የተለመደውን አጋርነቱን እንዲያሳይ በትህትና እንጠይቃለን፡፡