Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

እመቤታችን ስለምን ለዮሴፍ ታጨች?

ድንግል ማርያም ለዮሴፍ የታጨችው በባልና በሚስት ግብር ለመገናኘት አይደለም፡፡ታዲያ ለምን በእጮኛ ስም ተሰጠች
ቢባል ሰል ብዙ ምክንያት ነው፡፡

1 ኛ.ከድንግል የሚወለደው ክርስቶስ ከይሁዳ ከዳዊት ወገን እንደሆነ ትንቢት ተነግሯል፡፡ ነገር ግን ከእናት ብቻ ተወለደ
እነጂ አባት ስለሌለው ዮሴፍ ከዳዊት ዘር ነውና ክርስቶስ በእናቱ እጮኛ በዮሴፍ የዳዊት ልጅ ተብሎ እነዲቆጠር ነው፡፡
ለምን በእናቱ የዳዊት ልጅ ተብሎ አይቆጠርም ቢባል በአይሁድ ሴትን ከትውልድ ቁጥር አግብተው አይቆጥሩም እና
የእናቱን ከትውልድ መቆጠር ስለማይቀበሉ ነው፡፡ ለዚህም ነው ወንጌላውያን የክርስቶስን ትውልድ ሲቆጥሩ በዮሴፍ
የቆጠሩት፡፡

" ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።"

(የማቴዎስ ወንጌል 1:16) እና

" ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት
ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።"

(የሉቃስ ወንጌል 2:4-5)

እኛ የተዋህዶ ልጆች ክርስቶስን የዳዊት ልጅ የምንለው በዮሴፍ በኩል ሳይሆን ከዳዊት ወገን በተወለደችው በእውነተኛዋ
እናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡ ሌላው ዮሴፍ እና እመቤታችን ዝምድና ስላላቸው ነው፡፡ እስቲ ዝምድናቸውን
ቀጥሎ እንመልከት፡-

አልአዛር

ማታን ቅስራ

ያዕቆብ ኢያቄም

ዮሴፍ ድንግል ማርያም

ከላይ እንደተገለፀው ወንጌላውያን የአልአዛርን ልጆች ማታንና ቅስራ ሲሆኑና ትክክለኛው የክርስቶስን ትውልድ ለመግለፅ
በቅስራ በኩል አልፈው እመቤታችን ላይ አርፈው ጌታ ከእስዋ እንደተወለደ መጻፍ ሲኖርባቸው በማታን በኩል የቆጠሩት
ዕብራዊን ከላይ እንደተጠቀሰው ሁሉ ሴትን ከትውልድ አግብተው ስለማይቆጥሩ ወንጌላዊያንም አይሁዶች ምክንያት
አግኝተው ወንጌልን ከመቀበል ወደ ኋላ አንዳይሉና ከመዳን መንገድ እንዳያዘነብሉ ሲሉ ነው፡፡ወንጌላዊያኑም በዘዴ
የዬሴፍንና የእመቤታችንን ዝምድና ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በዮሴፍ ቆጥረዋል፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ከድንግል ማርያም
የተወለደው ያለ ወነድ ዘር መሆኑን መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ስለዚህም ከላይ በተገለፀው ምክንያት መስረት እናታችን
የዮሴፍ እጮኛ ተብላለች፡፡

2 ኛ.እናታችን ሴት ናትና ጠባቂ ያስፈልጋታልና በእጮኛ ስም እንዲጠብቃት ነው፡፡

3 ኛ.ክርስቶስ ያለወንድ ዘር መወለዱን አይተው እናቱ ማርያምን ከሰማይ የመጣች ሃይል ናት እነጂ የአዳም ዘር ሰው
አይደለችም ክርስቶስም ከመልአክ የተገኘ መልአክ ነው የሚሉ መናፍቃን በኋላ እንደሚነሱ ስለሚያውቅ ከሰማይ
የመጣች ኃይል ብትሆንማ ለዮሴፍ ትታጭ ነበርን? ብሎ ነገራቸውን ለማፍረስ እንዲመች ለምእመናን እውነተኛ የአዳም
ዘር እንደሆነች ለማስረዳት በእጮኛ ስም ለዮሴፍ እንድትሰጥ ተደረገ፡፡

4 ኛ.ሌላው እጮኛ የተባለችበት ምክንያት አገልጋይዋ ተላኪዋ እንዲሆን ነው፡፡ሄሮድስ ልጇን ሊያስገድለው በአስፈለገው
ጊዜ ስትሰደድ ዮሴፍ ተከታይ ሆኖ እንዲረዳት እግዚአብሔር ለዮሴፍ እንድትታጭ አዘዘ።
" እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ። ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥
ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።"

(የማቴዎስ ወንጌል 2:13)

5 ኛ.እናታችንን ከመደብደብ ሊያድናት፤በኦሪት ዘኁልቅ 5፡19

" ካህኑም ያምላታል፥ ሴቲቱንም እንዲህ ይላታል። ሌላ ወንድ አልተኛሽ፥ ባልሽንም አልተውሽ፥ ራስሽንም አላረከስሽ
እንደ ሆነ፥ እርግማንን ከሚያመጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤"

(ኦሪት ዘኍልቍ 5:19)

በተጠቀሰው ምክንያት አንዲት ሴት ከባልዋ ውጪ ፀንሳ ብትገኝ ማየ ዘለፋ ያጠጧት ነብር፡፡እንዲሁም አንዲት ሴት ባል
ሳታገባ ብትጸንስ በሙሴ ህግ መሰረት ደብድበው ይገድሏት ነበር፡፡ስለዚህም እናታችን ለዮሴፍ ሳትታጭ ቀርታ ጸንሳ
ቢሆን አይሁድ ለድብደባ ባበቋት ነበር፡፡እናታችን ለዮሴፍ መታጨቷ ስለዚህና ይህን ስለመሰለ ምክንያት ነው እንጂ
ለሚስትነት አይደለም፡፡ እነጂ ቢሆንማ ኖሮ ለዮሴፍ ትታጭ ሲል ተዓምራት ባላሳይ ነበር በትር ባላለመለመ ነበር፡፡

ለማጠቃለል ያህል እጮኛ ማለት፦

1.አጋዥ ጠባቂ ማለት ነው

2.ባል ወይም ሚስት ለመሆን የተዘጋጀ ማለት ነው

3. መሾም ማለት ነው

በመሆኑም እጮኛ ማለት ባል ወይም ሚስት ማለት ብቻ ቢሆን ኖሮ በ 2 ኛ ቆሮ 11፡2

" በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ
አጭቻችኋለሁና፤"

(2 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:2)

የተጠቀሰው ጥቅስ ላይ አጭቻችኋለሁና የሚል ቃል አለ ታዲያ አጋብቻችኋለው ማለት ነው?

በሌላ በኩል እናታችን ለዮሴፍ እጮኛ የተባለችው እስክትወልድ ድረስ ብቻ ነው ለምን ቢሉ 3 ቱ ሰባ ሰገሎች ከሃገራቸው
ወደ ቤተልሔም እስኪመጡ ድረስ 2 ዓመት ፈጅቶባቸው ነበር ይህም ማለት ክርስቶስ የ 2 ዓመት ህፃን ልጅ ነበር፡፡ታዲያ
ዮሴፍ ለምን ህን ያክል ጊዜ ጠበቀ ለምን አላገባትም ይህም እንዴት ሊሆን ይችላል ቢሉ ሄሮድስ 2 ዓመት የሆናቸውን
ህፃናት ሲያስገድል መልዓኩ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡-

" እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ። ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥
ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።"

(የማቴዎስ ወንጌል 2:13) እና

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 2)

19፤ ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ።

20፤ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።
ታድያ እናታችን ሚስቱ ሆና ቢሆን ኖሮ ሚሰትህን እና ህፃኑን አላለም ነብር?

ስለዚህ ዮሴፍ ለማርያም እጮኛ የተባለችው እንዲያግዛት እንዲረዳት እንጂ ለሚስትነት አደለም፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር ይሁን አሜን!!!!!

You might also like