Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 42

መሬት የማን ነው?

ከአቤ ጉበኛ

አዱስ አበባ
፲፱፻፷፯ ዓ/ም

የዯራሲው መብት በሕግ


የተጠበቀ ነው።
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ማውጫ
መነሻ። ............................................................................................................................................................ 1

ክፍል ፩ ....................................................................................................................................................... 1

ክፍል ፪........................................................................................................................................................ 3
መግቢያ.......................................................................................................................................................... 6
ኢትዮጵያውያን ዴርሻ። ............................................................................................................................... 10
የጢሰኝኖች ዴርሻ ........................................................................................................................................ 11
የሰሜናዊ ሕዝብ ዴርሻ................................................................................................................................ 12
የችግሩ ምክንያቶች ...................................................................................................................................... 14
፪ኛ የዯቡባዊው ኢትዮጵያ ክፍሌ። .............................................................................................................. 15
፫ኛ ላሊው የዯቡባዊ ክፍሌ አቋም። ............................................................................................................ 17
፪ኛ ክፍሌ ስሇ ሇውጡ። .............................................................................................................................. 17
፩ኛ ክፍሌ። .................................................................................................................................................. 18
ስሇ አሠፋፈሩና ስሇ አሠራሩ ዘዳ............................................................................................................... 20
ስሇ ባሇርስቶች የወዯፊት ዯኅንነት። ............................................................................................................ 21
ስሇ ስሜናዊው ክፍሌ መሻሻሌ። ................................................................................................................. 22
የሕዝቡን አሠፋፈርና የአሠራር ዘዳ .......................................................................................................... 24
ስሇመሇወጥ .................................................................................................................................................. 24
የማስተማሪያው ዋና ዘዳ ............................................................................................................................ 25
የተሇየ ኃሊፊነት ያሇባቸው ክፍልች ............................................................................................................ 26
፪ኛ ቤተ ክርስቲያናችን ................................................................................................................................ 27
ኃሊፊእንት አሇባት........................................................................................................................................ 27
፫ኛ ወጣቶች ታሊቅ ኃሊፊነት አሇባቸው ...................................................................................................... 28
ግባችን .......................................................................................................................................................... 29
ወዯ ግባችን የምንጓዝባቸው መንገድች። ..................................................................................................... 31
መዴረሻ ........................................................................................................................................................ 36

Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss


መነሻ።
በ፲፱፻፶፫ ዓ/ም በጥቅምት ወር ማሇቂያ ሊይ ከታተመው «የሮም አወዲዯቅ» ከሚሇው
መጽሏፌ የተወሰዯ።

ክፍል ፩
ነጋዳ - ዛሬ አንተ ገበሬ በጣም ወስሌተኻሌ ብርቱ ነው ጥፋትህ በህሌ መውቂያ ወራት ሥራን
ሁለ ትተህ

ከተማ መምጣትህ!

ገበረ- እኔ ምን ቸገረኝ በዋሇበት ቢቀር ቢወዴም ቢጠፋ እኔ እዴሇ-ቢሱ ክረምቱን በዝናም


በጋውን

በሏሩር ብማስን ብሇፋ የሮም ባሊባት ሌጅ በሰው ተዯግፋ በሀገራችን ሀብት ዯግሞም በኛ
ዴካም ሥቃይ በሞሊበት ከቤቷ ሳትወጣ እስዋ ሇብቻዋ ዓሇም ዏየችበት።

እኔ ግን ሇፍቼ በጋውን በሏሩር ክረምቱን በጭቃ

እንኳን ሇላሊ ሀብት ሇዕሇት ትዲሬም አሌቻሌሁም ሌበቃ።

ነጋዳ - ምንም ሥቃይ ቢሆን ያው ይሻሊሌ

እንጂ የግብርናው ሥራ

የንግደማ ነገር እንዯ ቀረ ይቅር

ተወው አይወራ!

ገበሬ - አዬ የሰው ነገር! ሇካ የሇም ፍጡር

የፈጠረ አምሊኩን የሚያመሰግን

አሁን ያንተው ጩኸት ዯግሞስ

ማማረሩ ስሇምን ይሆን?

ነጋዳ - ሁለም በያሇበት ይገፋ ይሆናሌ

ምናሌባት አሊውቅም!

ግን አሇ እንዲይመስሌህ በአሁኑ

ዘመን ውስጥ ነግድ መጠቀም!

1
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ባታውቀው ነው እንጂ የዛሬውን

ዘመን የነጋዳ ሥራ

የታክሱ የግብሩ የጽዲቱ ጉቦ ሥቃዩ

መከራ

ዯግሞ ከዚህ በሊይ ገበያው የሞተ

ሁሌ ጊዜ ኪሣራ

በዚህም ተናዯህ ጥቂት ብትናገር

ታፍሰህ ትጓዛሇህ ከተረፈችህ ሀብት

ከጥሪትህ ጋራ!

ገበሬ - መጏዲቱ ባይቀር ግፍም መቀበለ

ሁለም ባሇበቱ

የገበሮች ሞት ግን ከሁለም ሌዩ

ነው ሲኦሌ ነው በውነቱ

ሹሙ አገረ ገዥ ቆሮው ባሊባቱ

ሥራን የማይወዯው እኔ ጌታ - ነኝ

ባይ ወይ ዘር ቇታሪው ጨቋኙ

መብዛቱ!

የሁልችም ሥራ ያው የተሇመዯው

አንዴ ነው ብሌሏቱ

ሲያሊግጡ መኖር ንጹሐን ገበሬ

ሲያሥሩና ሲፈቱ።

ነጋዳ - አንተንስ የሚያዝህ ያገርህ ባሊባት

ወይንም ገዢህ ነው

እኔን የሚያስቸግር የሚያሠቃየኝ


2
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ግን ዯሀ ነው እንዯኔው

ነገር ሥራ ተብል ተቀጥሮ የሚ

ኖር አንደንም ሳያውቀው።

ገበሬ - ቂሌ ነህ ሌበሌህ!

ነጋዳ - እንዳት?

ገበሬ - ከተኵሊና ከጅብ ማናቸው ቢበሊህ ይሻሌኻሌ?

ነጋዳ - ማንኛውም አውሬ እንዱበሊኝ አሌፈሌግም

አውሬ እንዱበሊኝ ከፈሇግሁ ግን

ሁለም በገጠጠ ጥርሱ ነው የሚያነክተኝ!

ታዱያ ሊውሬ ጥርስ የተኵሊ

ሆነ የጅብ ምን ምርጫ አሇው?

ገበሬ - ይኸን ካወቅህስ እኔም ያሌሁህ

ይኸን ነው አንተን ከበዯሇህ ባሊባት

አገረ ገዥ ሹም ተራ ሰው ቢሆን

ምን ሌዩነት አሇው?

ነጋዳ - እውነትህን ነው እኔው ራሴ ተሳስቼ? ነው።

ክፍል ፪
ጢባርዮስ - እናንተ ወንዴሞቼ በዛሬው ቀጠሮ

እዚህ ተሰብስበን እንዴንመካከር ስሌ

የነገርኋችሁ

ማሌኮስ- የባሮች ነፃነት ተወርቶ እንዯሆነ

ሁሊችን ጭጭ ተወርቶ አዴምጡ

እባካችሁ!

አብዴናጏ - እኔም ይመስሇኛሌ የሚነግረን ጉዲይ

3
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ይኸም ሳይሆን አይቀር።

ገበሬ - ቆይኮ ይናገር!

ነጋዳ - ነፃነት ከሆነ መቼ ይሇያለ ጢሰኛና ገባር።

ጢባርዮስ - እስኪ ቆዮኝ!

እስከዚህ ዴረስ ነፃ ሕዝብ በመሆን

ሠርቶ ሇመጠቀም በውነት ካማራችሁ

ነፃነት እዚህ ነው ያሇ ከዯጃችሁ።

ነጋዳ - አዬ! ሇካስ ሞኝ ነህና! ጌታው

ሲኞር ጢባርዮስ ታሊቅ ሰው ነህ

ብዬ ሳምንብህ በውነት።

እስኪ አምሊክ ያሳይህ ባገር መኖር

ብቻ ይባሊሌ ነፃነት?

ብዙ ሀብት ታሽጎ ባገራችን መሬት

ሮማውያን ሁለ ሠርተን በመጠቀም

እንዲንኮራበት

ሰብስቦ በመያዝ አትዴረሱ ሲሇን

አንዲንደ ባሊባት!

ገበሬ - እባክህ ወንዴሜ ጉዲቴን ሌናገር

ሇኔ ምንም የሇኝ ላሊው ሁለ

ቀርቶ ቤት የምሠራበት

ወይም እንኳ ትንሽ ከብት

የማቆምበት።

ነጋዳ - ቆይኮ ታገሠኝ ነገሬን ሌጨርስ።

ገበሬ - እስከ መቼ ዴረስ?


4
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጢባርዮስ - እኔ እንዲሌናገር ያሰብሁትን ነገር

ጊዜውን ጨረሰው የናንተው ክርክር።

፩ኛ ሰው - እባካችሁ ቆዩ! ሲኞር ጢባርይዮስ

እንዯጀመሩሌን ሁለን ይናገሩ።

ሇዴሆቹ ዴጋፍ ሳይሆን እንዯ

ማይቀር ገና ከቅዴሙ ገብቶኛሌ

ምሥጢሩ!

፪ኛ ሰው - እኔንም ገብቶኛሌ!

፫ኛ ሰው - ከሁሊችሁ ይሌቅ እጅግ በጣም

እርጎ ቅዴሙን ታውቆኛሌ።

ጭቆና ይቅርና ዯሀም በሀገሩ በነፃ

ነት ይኵራ ያለ ይመስሇኛሌ!

፩ኛ ሰው - አማሌክት ይባርኩህ ነገሩ ገብቶኻሌ

እኔም እስማማሇሁ!

ይህን አሰባችሁ ተብል ሞት ቢመጣ

በርግጥ እሞታሇሁ።

፫ኛ ሰው - እኔም እሞታሇሁ ስሇዚህ ነገር!

ዯግሞ አትጠራጠር።

ማሌኮስ - እኔስ በጣም ፈራሁ ስሇሁኔታችሁ

ሁሊችሁ ባንዴ ቀን ሙታችሁን

ሙታችሁ

መሬት የት ሉገኝ ነው ሇመቃብራችሁ?

አብዴናጏ - እርግጥ ነው! መሬታችሁ ሁለ የአገራችሁ አፈር

ሇጥቂት ሀበታሞች ጥንት የተሰጠ ነው!


5
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መግቢያ
«መሬት ሇአራሹ» የሚሌ መዝሙር እየዘመሩ ተማሪዎቻችን ብዙ ዓመታት አሌፈዋሌ።
በዯቡባዊ ኢትዮጵያ በብዛት የሚገኙ ጢሰኞችን አሳዛኝ የኑሮ ሁኔታ የተዯረሱ ወጣቶች ይህን
ማዴረጋቸው የሰውነትና የኢትዮጵያዊነት ተግባራቸው ነው።

ይህ ነገር ያስጨነቀው እነሱን ብቻ አሌነበረም። ከነሱ መነሣት በፊትና ከዚያም በኋሊ


ብዙ ሰዎች ሇዚህ ጉዲይ ታግሇዋሌ። በራሴም በኩሌ በየመጽሏፎቼ የመንግሥቱንና የግፈኞች
ባሇሥጣኖኙን መጥፎ ተግባር ሳጋሌጥ የጢሰኞችን ችግርና መከራ ሳሌጠቅስ ቀርቼ አሊውቅም።

ሇምሳላ ከዛሬ አሥር ዓመታት በፊት ጽፌ ባሳተምሁት «ሰይፈ ነበሌባሌ» በተባሇው


መጽሏፌም ስሇከተማና ገጠር መሬቶች ይዞታ የሚከተሇውን ሏሳብ ገሌጬ ነበር።

«ላልች መንግሥታት ያገራቸው መሬት ሲጠብ ሇተቸገረው ሕዝባቸው በቂ ቦታ


ሇማግኘት የላልችን ወሰን እየገፉ ጦርነት እስከ ማንሳት ይዯርሱ ነበር።

እኛ ግን አንዲንዴ ባሇጥቅሞች በስም የያዙትን የሀገራችን መሬት አዯሊዴሇን የመሬት


ዕጦት ሊስቸገራቸው የሀገራችን ሕዝቦች ማከፋፈሌ አቅቶት እንጨነቃሇን።

መሬታችን ሁለ መሥራት ሇሚችለና የሀገሪቱ ተወሊጆች ሇሆኑ ተከፋፍል ተሰጥቶ


በሥራ ሊይ ማዋሌ እንጂ በአንዲንዴ ሰዎች ስም ቦዝኖ መቀመጥ የሇበትም።

የአንዲንዴ ሰዎችን ቍጣ እየፈራን የሀገችንን ጠቅሊሊ ጥቅም የሚጎዲ ነገርን ዝምብሇን


ማየት የሇብንም።

፩ኛ/ ሇርሻ የሚሆኑ መሬቶች ሁለ ሇሀገራችን ገበሬዎች ይዯሇዯሊለ። የጢሰኛና የገባር


ታሪክም በዚህ ያሌቃሌ።

፪ኛ/ በታወቀ ጊዜ በገንዘብ ሳይገዛ በሌዩ ሌዩ የማጭበርበር ምክንያት ብዙ የከተማ ቦታ


የያዘ ከሁሇት ቤቶች በሊይ ያሇው በቦዘን ያስቀመጠው ቦታ ቢገኝ መንግሥት የቤት መሥሪያ
ገንዘብ እያሇው መሬት ሇላሇው ሰው ይሰጣሌ።

፫ኛ/ ማንኛውም ሰው መንግሥት ሳያውቅ ከአንዴ የተቸገረ ሰው መሬት መግዛት


ሻጩም መሸጥ አይፈቀዴሇትም።

፬ኛ/ በተራዴኦ ሇተቋቋመ የርሻ ዴርጅት ካሌሆነ በቀር ሇአንዴ ሰው ቢበዛ ከሁሇት ጋሻ
የበሇጠ መሬት አይፈቀዴሇትም።

፭ኛ/ አንዴ ሰው ሇአካሇ መጠን ባሌዯረሱ ሌጆቹ ወይም የላልች ሌጆች ስም መሬት
መካፈሌ ወይም መግዛት አይችሌም።»

6
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ብዙ ሰዎች የዚህን ጉዲይ አሳሳቢነት በየጊዜው ገሌጸዋሌ። ላሊው ቀርቶ ሇብዙ የመሻሻሌ
እርምጃዎች የቀረቡ ሏሳቦችን ሁለ «ጆሮ ዲባ ሌበስ» ብል ሲበዛሊቸው የኖረው መንግሥት ብዙ
ባያሠራውም የመሬት ይዞታና አስተዲዯር ሚኒስቴርን አቋቁሞ ነበር።

ይሁን እንጂ ሁለም ነገር ሁኖ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ኤክስፐርቶችም አማክረው
ምንም መዴኃኒት ሳያስገኙሇት ቆይተዋሌ።

ሇዚህ ችግር ዋና ጠንቆች ከሆኑት ነገሮች መካከሌም እጅግ ጎሌተው ሇማንም የሚታዩ
ታሊሊቅ ምክንያቶች አለ። እነሱም

፩ኛ/ ራሳቸው ዋናዎቹ የመሬት ዘራፊዎች ከመሆናቸው በሊይ ስሇ ሕዝብ ችግር ምንም
ስሜት ያሌነበራቸው የዴሮ ባሇሥሌጣኖች የሇውጡ ፍጹም ተቃራኒ ስሇነበሩ

፪ኛ/ ራሱ የመሬቱ ሥሪት ዝብርቅር መሆኑ

፫ኛ/ እነዚያው ታሊሊቅ የመሬት ዘራፊዎች የነበሩት ከፍተኛ ባሇሥሌጣኖችና ግብረ -


አበሮቻቸው ሇራሳቸው ወገን ሇማብዛት ሲለ የተወሰነ መሬት ያሊቸውን ሁለ በአንዴ ሊይ
አስበርግገው ሇማስነሣት በመፈሇግ ባሇርስት ሁለ ተነቅል ጢሰኛ ብቻ ባሇ ርስት ይሆናሌ
የሚሌ ወሬ ያስነዙ ስሇ ነበር

፬ኛ/ ጢሰኞች መንግሥት የራሳቸውን ዴርሻ መሬት እንዱሰጣቸው ሇመስፈርና


ሇመቋቋም እንዱረዲቸው በመጠየቅ ፈንታ «እኛ ሰፍረንበት ከተገኘን» አንዴ ጋሻም ሆነ ግማሽ
ጋሻ አንዴ ማሳም ይሁን ያሇውን ላሊ ኢትዮጵያዊ እየቀማችሁ ስጡን የሚሌ ግሌጽ አዴሌዎን
ብቻ ሳይሆን ግሌጽ ሁከትን የሚፈጥር ተግባር እንዱፈጸምሊቸው መፈሇጋቸው

፭ኛ/ የሰሜናዊ ኢትዮጵ ክፍሇ ሀገሮች ሕዝብ ስሇ መሬት ያሇው አስተሳሰብ ከሃይማኖት
ከቤተ ሰብ ጋር የሚመሳሰሌ ሁኖ ሇራሱ ሇሕዝብ ዯኅነት ሲባሌ በሚሞከር የመሬት ጉዲይ ሁለ
ምክንያቱን ሇመረዲት እንኳ ሳይፈሌግ በሏሰተኛ ወሬ ብቻ የሚበረግግ መሆኑ

፮ኛ/ ሕዝቡ ችግሮቹን ተረዴቶ በመግባባት እንዱያስወግዲቸው ታፍኖ መኖሩ ናቸው።


እንግዱህ የመሬት ይዞታ ሥርዓታችንን በስም መሇወጥ ብቻ ሳይሆን በሇውጡ ሇመጠቀም
የምንችሌበት ዕዴሌ ባገኘንበት በአሁኑ ጊዜ ከነዚህ ችግሮች አንዲንድቹ በመጠኑ የዯከሙ
ቢመስለም ገና እንዲለ ማወቅ አሇብን። ከዚህ በሊይ «መሬት ሇአራሹ» ሲባሌ «ጢሰኛው ገበሬ
ራሱ ሇራሱ የሚሠራበት መሬት ኑሮት ከጢሰኝነት ይውጣ» በሚሇው ስሜቱ ሁሊችንም መቶ
በመቶ ከመስማማት ጋር አንዲንዴ የተሳሳቱ ትርጕሞቹን አስተውሇን ማረም ከብዙ ጉዲት
ያዴነናሌ። ከሁለ በፊት መሬት የገበሬዎች ብቻ መጠቀሚያ ወይም የግሌ ርስት አይዯሇችም።
ሰው ብቻ ሳይሆን በመሬት ሊይና ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ፍጡር የመሬት ባሇቤትነት መብት
አሇው። የፋብሪካ ሠራተኞች ሏኪሞች መሏንዱሶች ወታዯሮች መምህራን አርቲስቶች ተማሮች
ካህናት መኃይምናን በጠቅሊሊው የሰው ዘሮች ሁለ በመሬት ሊይ እየኖሩ በመሬት ሊይ
ስሇሚሠሩ ሲሞቱ እንኳ በመሬት ሰሇሚቀበሩ ፍጹም የመሬት ባሇቤቶች ናቸው። ሰዎች ብቻ
ሳይሆኑ እንስሳት አራዊትን አእዋፍና ዕፀትን የመሰለት ፍጥረቶች ሁለ የሚገባቸው የመሬት
7
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ዴርሻ ካሊገኙ ያሊቸው ዕዴሌ ከመሬት ገጽ መጥፋት ስሇሆነ ሰውም ያሇነርሱ ሉኖር ስሇማይችሌ
መሬት «አራሾች» ወይም «የሰፊው ሕዝብ» የግሌ ሀብት ብቻ ሳትሆን በሊይዋ የሚኖሩ
ፍጥረታት ሁለ የጋራ ርስት ናት።

የመሬት ይዞታ ሥርዓት ይሇወጥ ስንሌም ይህን ሁለ ጨምረን ማሰብና ሊሌተረደት


ማስረዲት አሇብን።

የአንዴን አገር ሕዝብ መሠረታውያን ጥቅሞች ሇመጎሌመስ ጥረት በሚዯረግበት ጊዜ


አንደን ወገን ያሇ በቂ ምክንያትና ያሇወግ ጎዴቶ ላሊውን ወገን ያሇወግና ያሇ ምክንያት
ሇመጥቀም ወይም ማንንም ሳይጠቅሙ ሁለንም ሇመጉዲት መታገሌ ከጤነኞች ጠቅሙ
ሁለንም ሇመጉዲት መታገሌ ከጤነኞች ሰዎች የሚጠበቅ አይዯሇም።

በራሴ በኩሌ ይህቺን ትንሽ መጽሏፍ (ፓምፍላት) ስጽፍ በአንዴ የመሬት ይዞት ወይም
በጠቅሊሊው በአንዴ ሀብት አፈራርና ይዞታ ትምህርት የሠሇጠንሁ ኤክስፐርት ነኝ በማሇት
አይዯሇም። ይሁን እንጂ አንዴ ኢትዮጵያዊ ስሇ ሀገሩ ችግር ከተመራመረ ከአንዴ የውጭ
ኤክስፐርት የተሻሇ ሏሳብ ሉያቀርብ ይችሊሌ ብዬ አምናሇሁ።

በተሇይ የአንዴን አገር ሕዝብ ባህሌ ማኅበራዊ ኑሮና ፖሇቲካ ስሇሚመሇከት ጉዲይ
የተጨበጠ ሏሳብ ሇማቅረብ በክፍሌ የሚሰጥ ትምህርት ብቻ ሳይሆን የባሇጉዲይ ሀገር ተወሊጅ
ጉዲይን በቅርብ ማስተዋሌና በጥንቃቄ ማጥናት አስፈሊጊ ነው።

ስሇዚህ የሀገራችንን ችግሮች ሇማስተዋሌ ብዙ ምክንያቶች ያጋጠሙኝ እንዯመሆኑ


መጠን ሇጀመርነው ሇውጣችን የመጀመሪያ ተግባር ሁኖ ስሇሚገኘው የመሬት ይዞታ መሇወጥ
ይረዲሌ ብዬ ያመንሁበትን ሏሳብ ሇመግሇጽ ፈሇግሁ።

ምንም ውጣ ውረዴ ሳይኖር «መሬትን በጠቅሊሊው መንግሥት በቍጥጥሩ ሥር ማዋሌ


አሇበት» የሚለ ሰዎች አለ።

ይህ ነገር እንዱህ እንዯ አነጋገሩ በቀሊለ ሉፈጽም የሚችሌ ቢሆን ኑሮ እኔም ይኸን ዘዬ
(ስልጋን) ባስተጋባሁ ነበር። ነገር ግን ይህ ንግግር በአሁኑ ጊዜ በቀጥታ በሥራ ሊይ ይዋሌ
ማሇት ኢትዮጵያንና ሕዝቧን እንዱሁም ያሇባትን ችግር ባሇመገንዘብ ወይም በግዳሇሽነት
የሚነገር ነው።

በተሇይም አሁን በሀገራችን የተጀመረው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ፍጹም ሰሊማዊነቱና


አስዯናቂ ውጤቱ በአንዴ ሊይ ሲታዩ ታሊቅ ተአምር ያሇበት ስሇሆነ መዴኃኒት የላሇው ከባዴ
ችግር ካሊጋጠመን በቀር ይህን ሰሊማዊ ሇውጥ ወዯ ላሊ አቅጣጫ ሇመምራት የሚችለ
ስኅተቶች እንዲይፈጸሙ በጣም መጠንቀቅ አሇብን።

ኢትዮጵያ በተባበሩ ሌጆችዋ ጥረት ሇማንኛውም አገር ጠቃሚ ሁኖ ከተገኘ የሥሌጣኔ


ዯረጃ የማትዯርስበት ምክንያት ከቶ አይኖርም።

8
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ይህን ከተፈሇገ ግብ ያዯርሰናሌ ብሇን የምናምንበትን አንዴነት ሇማግኘትም አስቀዴሞ
ሕዝቡን ማሳመን እጅግ አስፈሊጊ ነው።

የሀገራችን ሕዝብ አስተዋይና ንቁ መሆኑ ያሇጥርጥር የተረጋገጠ ነው። ይሁን እንጂ


ካሇፈው የኑሮ ሥርዓቱ ጋር በመጠኑም ቢሆን ሉጋጩ የሚችለ አዲዱስ ሏሳቦችን በግዴ
ተቀበሌ ከሚለት በቅን መፈስ ቢያረጋግጡሇት ይበሌጥ ከሌብ ሉቀበሇው ይችሊሌ።

አንዴ ኢትዮጵያዊ የግለ በሆነች ትንሽ ርስቱ ይኮራ ይሆናሌ። ግን ጉዲዩን ከመንዯሩ
ራቅ አዴርጎ በሚመሇከተው ጊዜ ዋናዋና ሰፊዋ ርስቱ ኢትዮጵያ ራሷ እንጂ ያቺ ባንዱት ቀበላ
ያሇች ቁራሽ መሬት አሇመሆኗን መገንዘብ አይሳነውም። አንዴ ኢትዮጵያዊ በጣም ወዯ ራቁ
ሀገሮች ቀርቶ ቅርብ ጎረቤቶቻችን ወዯ ሆኑት ወዯ ሱዲን ወዯ ኬንያ ወዯ ሱማሉያ ቢሔዴ
የሚታወቀው በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በአንዴ ቀበላ ባሇቺው ትንሽ ርስቱ አይዯሇም።

ስሇዚህ አንዴ ሰው ሇሀገሩ ጠቅሊሊ ዯኅንነት ራሱ ሳይነካ የሚቀርብሇትን ጠቃሚና


አዲዱስ ሏሳብ ሁለ የሌማዴ ሰንሰሇቱን በጣጥሶ እየጣሇ ሉቀበሌ ይገባዋሌ።

አዱሷ ኢትዮጵያ የምትራመዴበት ቅን ጏዲና በጣት የሚቇጠሩ ሰዎችን የሀብት


ሥሌጣን በጠቅሊሊው የሁለ ነገር ጌቶች አዴርጎ አብዛኛውን ሕዝቧን የውርዯትና የችግር ሁለ
ተሸካሚ የሚያዯርግ ሳይሆን ሀገሪቱ ሇሚኖራት ሇማንኛውም ነገር ጠቅሊሊው ሕዝብ ሙለ
ተሳታፊነት እንዱኖረው የሚያዯርግ መሆኑ የተረጋገጠ ነው።

ስሇዚህ እያንዲንደ ኢትዮጵያዊ ሀገሩ ሇምትጠቀምበትም ሆነ ሇምትጎዲበት ነገር ሙለ


ኃሊፊነት ያሇበት መሆኑን አምኖ ሇግሌ ቤቱ መሟሊት የሚያዯርገውን ሌባዊ ጥረት ሇናት ሀገሩ
ዯኅንነትም ማዴረግ ብሔራዊ ተግባሩ ነው። በአሁኑ ጊዜ የመሬት ይዞታ ይሇወጥ ሲባሌም
እያንዲንደን ሰው ከርስቱ ነቅል ሇተወሰኑ ሰዎች ጢሰኛና ገባር ሇማዴረግ ሳይሆን ኢትዮጵያ
በሙለ ሇኢትዮጵያውያን ሁለ የጋራ ርስት ሁና በኅብረትና በአዱስ ዘዳ ሠርተን ሰብአዊ
ክብራችንን ሳይቀር አዋርድት ከሚገኘው የመከራ ኑሯችን ሇመሊቀቅ ነው።

ስሇዚህ ይህን ሇውጥ ማንኛችንም ወገኖች በጥርጣሬ ሳናይ ሌንተባበርበት ይገባሌ።

ሇሇውጡ መግባባት እንጂ ኃይሌ ብቻ አይጠቅምም።

ኢትዮጵያ ሕዝብና ወታዯር ተባብሮና ተፋቅሮ ከተራመዯ እጅግ አስፈሊጊና ተቀዲሚ


ስሇሆነው የመሬት ይዞታ ሇውጥም በሰሊም ሉፈጽመው የማይችሌ ተግባር እንዯማያጋጥመው
ባሇፉት ጥቂት ወራት የተፈጸሙት ተአምራቶች አረጋግጠውናሌ። ኃይሊችንና ሌባችን ተከፋፍል
ቢሆን ኑሮ እነዚያ እንዯዘበት ከአናታችን ወርዯው የተንኮታኮቱ ኃይልቹ ስንት ጉዴ ሉሠሩብን
ይችለ እንዯነበረ መዘንጋት የሇብንም።

አሁንም ኅብረታችንና ሰሊማችን ይበሌጥ አስፈሊጊዎቻችን ናቸው ስሌ ካሁን በፊትም


በጋዜጣ ዯጋግሜ ያቀረብኳቸውን ምክንያቶች ሊቀርብ ነው።

9
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
፩ኛ/ ኢትዮጵያ ውስጥ ወታዯራዊው ክፍሌ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ በሥሌጣኔ ወዯ ኋሊ
የቀሩ የሚባለት ቀርቶ ራሳቸው የተራቀቁ የጦር መሣሪያዎች የሚጠሩ ሕዝቦች እንኳ
ያዯርጉታሌ ተብል በማይጠረጠር መጠን በጦር መሣሪያ የዯረጀ የወታዯርነት ወኔ የተጫነው
በመሆኑ ሇኛ ሀገር የርስ በርስ ጦርነት ማሇት በሚሉዮን በሚቇጠሩ ነፍሶች ሊይ የአረመኔ
የሞት ፍርዴ ያሇ ምክንያት ማስተሊሇፍ ነው።

፪ኛ/ ማንኛውንም የሕዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በጦር ኃይሊችን ጉሌበት ብቻ ፀጥ


እናዴርግ ብንሌ

ሀ/ የሀገሪቱን አንዴነትና ወሰኖቿን በማስከበር ግዳታው ሊይ የሚገኝ የጦር ኃይሊችንን


ወዯ ማያስፈሌግ ከወገን ጋር የመፋጀት ግዳታ አስገብቶ ሀገራችንን ከፍጹም ጥፋት ሊይ መጣሌ

ሇ/ የወዯቀው መንግሥት ርዝራዦች በምክንያት እንዱያንሠራሩ ማዴረግ ይሆናሌ።

፫ኛ/ እንዯ ኢትዮጵያ ባሇ ሀገር የርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ማሇት የውጭ ኃያሊንን
«ኑ ግቡና ቀሌደብን» ብል በቀጥታ መጋበዝ ነው።

፬ኛ/ በግሌ ስሜታችን ኃይሌ በመገዯዴ የመጣውን ይምጣ ብሇን አንዲንዴ ሀገራቸውን
በሚገባ የሚያውቁት ሰዎች እንዯሚለት በኃይሌ ብቻ ይሠራ ብንሌ

ሀ/ የሚባክነው ገንዘብና የሰው ጉሌበት በሀገሪቱ የዯከመ ኢኮኖሚ ሊይ የሚያስከትሇው


ውዴቀት

ሇ/ ሇረጂም ጊዜ ሉዯርስ የሚችሇው የሰሊምና ፀጥታ መታጣት

ሏ/ በመካከሊችን ሉፈጠርና የረጂም ዘመን የኑሮ ጠንቅ ሆኖ ሉቆይ የሚችሇው ጥሊቻና


አሇመተማመን ይህን ተአምራዊ ሇውጣችንን ወዲሌተጠበቀ የስኅተት ፍጻሜ ሉመራው ይችሊሌ።

እንግዱህ ከዚህ ሊይ ነው «ያገሩን ስርድ ባገሩ በሬ» የሚባሇውን የምሳላ አነጋገር


ሌንጠቀም የሚገባው። በዯቡብ ኢትዮጵያ ከወሰን አሇፍ ያሇ መሬት የያዙ ግን ላሊ ጉዴሇት
የላሇባቸው

ኢትዮጵያውያን ዴርሻ።
ታሊሊቅ መሬት ዘራፊዎች ከመሊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በቍጥር ሲነጻጸሩ ጥቂቶች
ከመሆናቸው በሊይ እንዯ ወዯቁት መሪዎች ሁለ የኢትዮጵያ ሕዝብና አፈሩ የከዲቸው
በመሆናቸው ቢወደም ቢጠለ መሬታቸው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወዯ መንግሥት ተዛውሮ
መንግሥት ሇላሊ ብሔራዊ ተግባር የሚያውሇው በመንግሥት እጅ ሲቀር የቀረው መሬት
ሇላሊቸው ገበሬዎች እንዯየ አስፈሊጊነቱ መሰጠቱ እንዯማይቀር ይጠራጠራለ ተብል
የማይታሰብ ነገር ነው።

10
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ነገር ግን እንዯዚያም ባይበዛ ከሚያስፈሌጋቸሁ በሊይ መሬት የያዛችሁ ሁለ ችግሩ
በጊዜውና በተራው ወዯናንተም ዓይኑን አፍጥጦ እስከ ሚመጣ መጠበቅ እይሇባችሁም።

በአሁኑ ጊዜ የታወቁት በቃኝ - አይላዎቻችን ሁለ «እኔን ያየህ ተቀጣ» እያለ ወዯፊት


ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገባቸው በሊይ እየዘረፉ ወገኖቻቸውን መዴረሻ ሇሚያሳጡ ሰዎች ቦታ
እንዯማይኖራቸው መማሪያ ሁነዋሌ። ከቀዲማዊ ኃይሇ ሥሊሴና ከቅርብ ባሇሟልቻቸው በሊይ
በሥሌጣኑ በሀብቱ በትውሌደና በጉሌበቱ የተመካ ማንም ይዯፍረናሌ ብልም ያሌተጠራጠረ
ኢትዮጵያዊ አሌነበረም።

ነገር ግን የአብዛኛውን ሕዝብ ምኞትና ፍሊጎት በንቀት አሌፎ ጥቅሙን ዘርፎ መብቱን
ገፍፎ ከጥጉ ባለ ጥቂት የጥቅም መሰልቹ ብቻ ተማምኖ የሚኖር ወገን ሁለ ያ የተናቀ ብዙ
ሕዝብ በኅበረት በተነሣ ጊዜ መውጫ ቀዲዲ ስሇሚገኝ የኛም ናቂዎች በሚገባቸው ጉዴ ሊይ
ወዯቁ።

በነሱ የማይማሩ ዯግሞ ምናሌባት ከዚህ በከፋ ጉዴ ሊይ ሉወዴቁ ይችሊለ።

አባቶቻችን ሆይ!

ከአሁም ቢሆን የራሳችሁ ሌጆች ሳይቀሩ ተነሥተውባችኋሌ። «መሬት ሇአራሹ» እያለ


ከሚዘምሩት አብዛኛዎቹ የተሻሇ የመማር ዕዴሌ ያገኙት የናንተው ዓቅም ያሊችሁ ሰዎች ሌጆች
ናቸው። የምስኪኑ ጢሰኛችሁ ሌጅማ የተማረና ባሇብዙ ርስት ሇሚሆነው ሌጃችሁ እሱም
በተራው ጢሰኛ ሇመሆን ከተወሇዯበት መንዯር ሳይወጣና ፊዯሌ የመቍጠር ዕዴሌ ሳያገኝ
ቆይቷሌ።

በጊዜው የሚመጣ ኃይሌን ጊዜው ባሇፈበት ዴርቅና መቋቋም አይቻሌም። በብዙ ሀገሮች
የመሬትን ይዞታ ሥርዓት አናስሇውጥም ብሇው በተቃወሙ ሰዎች ሊይ የተፈጸመ አሳዛኝ ነገር
ሞሌቷሌ። እኛ ግን ሇውጣችን የመጣሌን በሰሊምና በመግባባት ስሇሆነ በዚህ በኩሌ
የሚፈሌገውን ሇውጥም በሰሊም እንዯምናከናውነው አይጠረጠርም። ይህንንም ስናዯርግ ማንም
የመኖር መብቱን ሳያጣ ጠቅሊሊው ሕዝብና ተተኪ ትውሌድቻችን የሚጠቅሙበትን መንገዴ
በሰሊም ሇመክፈት እንችሊሇን።

ስሇዚህ ቀሊለ ነገር ከባዴ መስሎችሁ ቀዴሞ ሇመገኘት ስትቸገሩ የማይቀር ከባዴ ችግር
ዯርሶ እንዲይዛችሁ ሇሰሊማዊ ሇውጣችሁ ፍጹም ተባባሪ ብትሆኑ ከፍተኛ የሀገር ፍቅር
የሥሌጣኔ የጨዋነት የብሌህነትና የሰሊም መንፈስ ከሀገራችን ሳይጠፋ ሀገራችሁ እንዴትሇወጥ
አዯረጋችሁ ማሇት ነው።

የጢሰኝኖች ዴርሻ
ጢሰኝኖች ሁነው የኖሩ ኢትዮጵያውያን ሇወገኖቻቸው ዏውቀው ባዲ መሆን እንዯ
ላሇባቸው ሉያስተውለ ይገባሌ። በአሁኑ ጊዜ ሇነሱ መሬት ሇመስጠትና እነሱን ብቻ ሇመርዲት
ሲባሌ ባሇርስት ነኝ የሚሇውን ሁለ ወሰን ሳይሇዩ ትነቀሊሇህ ቢለት ምን ዓይነት ችግር
11
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዯሚፈጠርና በዚህም ሳቢያ የነሱም ሰሊም በቂ ዋስትና እንዯማይኖረው ማወቅ
አይሳናቸውም። ኢትዮጵያ ሇሁከተኛ ሇውጥ የምትመች አገር አይዯሇችም። ምክንቱም ሁከት
ብንፈጥር ተመሌሶ የሚያጠፋና ራሳችንን ነው። የጦር ኃይሊችን በንቃትና በጥንቃቄ
ሉያስወግዲቸው የተጠመዯባቸው የመሬት ይዞታና ሥርዓት ከመሇወጥ ጀምሮ ብዙ የሀገር
ውስጥና የወሰን ችግሮች ስሊለበት ተጨማሪ ችግሮች መፍጠር ሀገርን በቀጥታ መበዯሌ ነው።

ስሇዚህ አስፈሊጊ በሆነበት ጊዜና አካባቢ ሁለ መንግሥት ተስማሚ ቦታ እያዘጋጀ በተሻሇ


ዘዳ ሉያሰፍራችሁና ሉረዲችሁ ሲፈሌግ መሬት ከነእገላ ቀምታችሁ ካሌሰጣችሁን ብል
ማስቸገር የሇውጡን እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን የራሳችሁን ነጻነት ጭምር መቃወም ይሆናሌ።

በአካባቢያችሁ ታውቋቸው ከነበሩ ጎረቤቶቻችሁ ጋር ካንዴ የራሳችሁ ካሌነበረና የሰው


በታች ሁናችሁ ከቆያችሁበት ቦታ ተነሥታችሁ በዘመናዊ መሌክ እየሠራችሁ ወዯ ምትኖሩበት
የራሳችሁ ቦታ ስትዛወሩ የእምትጎደበት እናንተ አይዯሊችሁም። እናንተ ከነበራችሁበት ቦታ
በመነሣታችሁ የሚጎደት ሰዎች የምትሇቋቸው መሬቶች ባሇቤቶች የነበሩት ናቸው።

ምክንያቱም

፩ኛ/ እናንተ ስትሇቁት ባድ መሬታቸው ምንም ጥቅም ሉሰጣቸው ስሇማይችሌ የባሇ


መሬትነት ትርፋቸው ዴካም ብቻ ይሆናሌ።

፪ኛ/ የማይጠቀሙበትን መሬት ሇስም ብቻ ይዘው ከባዴ ግብር መገፍገፍ ስሊማይፈሌጉ


ሇችግር ያቦዘኑትን መሬት በፈቃዲቸው ሇመንግሥት ያስረክባለ።

ይህ በሚሆንበት ጊዜ የናንተ ተባባሪነት ሇራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ሇጠቅሊሊው ሕዝብ


ሰሊማዊ ርምጃ ከፍተኛ ዴርሻ አበረከተ ማሇት ነው።

የሀገራችንን ርምጃ እንቅፋቶች በያሇንበት በያቅጣጫው በየችልታችን በአንዴነት


ሇመዋጋት እንሰሇፍ። ኢትዮጵያ በማያዋጣ የተሳሳተ መንገዴ እየተመሩ ሁከትን ሇማስፋፋት
ከሚቀባጥሩ ሰዎች ይሌቅ ባሊቸው ችልታ በያለበት በጎ ፈቃዴና ኅብረትን የሚዯግፉ ሌጆችዋን
ትፈሌጋሇችና እንተባበር።

የሰሜናዊ ሕዝብ ዴርሻ


ባሕሌና ወግን ማክበር ሃይማኖትን ማፅናት ሀገርን መውዯዴ ከፍተኛ ሰብአዊ ተግባሮች
ናቸው። ነገር ግን አእምሮን አጥብቦ ሀገር በተወሇደበት መንዯር መከሇሌ እግዚአብሔር
ያሊዘዘንን አንዲንዴ መጥፎ ሌማድች በሃይማኖት ስም እያስጠጉ ራስን መበዯሌና ሇሀገር ዕዴገት
ዕንቅፋት መሆን እጅግ አሳፋሪ ነገሮች ናቸው።

በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ክፍልች ከዓመት ዓመት የሰው ቍጥር እየጨመረ መሬት ከኖረበት
ሁኔታ ምንም ስሊሌጨመረ ሇኗሪዎች እየጠበበ ሲሔዴ ካንዴ አገር ከፍተኛ የሀብት ምንጮች
አንደ የሆነው ዴነ ቀርቶ ሇማገድ የሚሆን ቁጥቋጦ እየጠፋ ሲሔዴ በየዓመቱ አፈሩ እየታጠበና
12
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ምዴሩ እየሳሳ ሲሔዴ የግጦሽ ቦታዎች እየጠበቡና እየተራቆቱ የከብቶች ቍጥርና ባሇውም
ቍጥር የሚሰጡት ጥቅም እየቅነሰ ሲሔዴ ላሊም ይህን የመሰሇ ችግር ተዯራርቦ ሲመጣበት
እያየ ራሱንና ሀገሩን ሇማዲን እግዜር ካወረዯሇት ኃይሌ ጋር የማይተባበር ሰው ከጥፋት ወሀ
በፊት ኖኅ መርከብ ሲሠራ እየተዘባበቱ ቆይተው እስኪ ጠፉ ዴረስ «አስረሽ ምቺው» አለ
ከሚባለት የጥንት ሰዎች ጋር ሉመሳሰሌ የሚገባው ነው።

መቼም ዋና ዋናውን የሀገሪቱን ችግር ሁለም በየቤቱ ሁኖ እንዲይመሇከተው የየግሌ


ችግሩ ክብዯት ጋርድት ነው እንጂ ኢትዮጵያ አሁን ያሇቺው ታሊቅ መሥዋዕትነት
በምትጠይቅበት ጊዜ ሊይ ነው።

ተርባሇች እናብሊት።

ተጠምታሇች እናጠጣት።

ታርዛሇች እናሌብሳት።

ታሥራሇች እንፍታት።

ታማሇች እናስታማት።

በገዛ ቤቷ ዕንግዲ ሁናሇች እናስተናግዲት።

፪ኛ/ የማይጠቀሙበትን መሬት ሇስም ብቻ ይዘው ከባዴ ግብር መገፍገፍ ስሇማይፈሌጉ


ሇችግር ያቦዘኑትን መሬት በፈቃዲቸው ሇመንግሥት ያስረክባለ።

ይህም ማሇት የኛ የኑሮ ሁኔታ ከእነዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የበሇጡ ከባዴ
ችግሮች አዴርጎ የገሇጻቸው ችግሮች ሁለ የሰፈኑበት ስሇሆነ ራሳችን ሇራሳችን በዯኅንነት
እንሥራ ማሇት ነው።

በእውነት ከተሔዯ ከኛ ይበሌጥ የሚያሳዝኑ የተሠቃዩ የሰው ዘሮች የት ይገኛለ?


ምናሌባት በጥቂት አገሮች ይገኙ ይሆናሌ። አንዯኛ በመከራው የሚኮራ ሕዝብ ግን በየትም
ዓሇም እንዯላሇ አያጠራጥርም።

ኧረ እባካችሁ እንንቃ! አባቶቻችን ከውጭ ወራሪዎች ጠብቀው ያቆይዋትን ሀገር ከነዚያ


ጠሊቶች ከሚከፉ ጠሊቶች ሇማዲን እንሰሇፍ!

አሁን ወዯ ታሊቅ ጦርነት ገብተናሌ። በችግር በበሽታ በዴንቁርና በጭቆና ተከበን


መኖራችን አንገፍግፎን በነዚህ ጠሊቶቻችን ሊይ ዴሌ ሇማግኘት ቆርጠን ተነሥተናሌ። ስሇዚህ
ሇኢትዮጵያ ዯኅንነት የሚመጣውን እውነተኛ ሇውጥ ባጉሌ ግትርነት ሇማበሊሸት መሞከር
አገርን ማጥፋት መሆኑን አንዘንጋ።

አቤ ጉበኛ።

13
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የችግሩ ምክንያቶች
የአንዴ አገር ሕዝብ ጠቅሊሊ የኑሮ አቋም ሇመሇወጥ በሚፈሌግበት ጊዜ የሀገሩን
ችግሮችና ችግሮቹን ሇማስወገዴ የሚቻሌባቸውን ዘዳዎች ግሌጽ በሆነ መንገዴ ሇመመሌከት
መቻሌ የመጀመሪያ ተግባር ነው። ከዚያ ቀጥል የሚያስፈሌገው ነገር ዯግሞ ሇሇውጡ
የሚጠቅሙ ተግባሮችን ቅዯም ተከተሌ ተረዴቶ በኅብረትና በፅኑዕ በጎ ፈቃዴ ሇሥራ መራመዴ
ነው።

ስሇ ሀገራችን ፈጣን የኢኮኖሚ ሇውጥ በምናስብበት ጊዜም የመሬት ይዞታችን አቋም


በተቀዲሚነት በአእምሮአችን የሚዯቀን ከፍተኛ ችግራችን ሁኖ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ብዙ ንግግር
ሲዯረግበት ቆይቷሌ። ይህ የሆነበት ምክንያትም የመሬት ይዞታችን ሥርዓት ዝብርቅርቅነት
ብቻ ሳይሆን ሀገራችን በሌማት በኋሊ መቅረቷና የተፈጥሮ ጸጋዋም ሇርሻ ሥራ ተቀዲሚነት
እንዴንሰጥ ስሇሚያስገዴደን ነው።

በሀገራችን የመሬት ይዞታ ሥርዓት ውስጥ ብዙ ጥቃቅን ሌዩነቶች በየክፍሇ ሀገሩ ሉኖሩ
ይችሊለ። እነዚህ ጥቃቅን ሌዩነቶች ብዙ የጎለ ስሊይዯለ ብዙ ሊያስቡ ይችሊለ።

ነገር ግን በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ክፍልችና በዯቡባዊ ኢትዮጵያ ክፍልች ያለት የመሬት


ሥሪቶች እጅግ የተሇያዩ ናቸው።

በአሁኑ ጊዜ አጠራራችንና እኔም እሱን ተከትዬ እንዯጠራሁት ሰሜናዊ ኢትዮጵያ


የሚባሇው አማርኛና ተናጋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ርስት አዴርገው እስከ ዛሬ የኖሩበት ክፍሇ
- ኢትዮጵያ ነው።

በዚህ ክፍሌ በሚገኙ የተሇያዩ አውራጃዎች የመሬት ሥሪት ውስጥ እጅግ ጥቃቅን
የሆኑ ሌዩነቶች ሉኖሩ ይችሊለ። ግን የመሬቱን ይዞታ በፍጹም አንዴ የሚያዯርጉት ሁሇት
ታሊሊቅ ምክንያቶች አለ። እነሱም፦

በዚህ ክፍሌ በሚገኙ የተሇያዩ አውራጃዎች የመሬት ሥሪት ውስጥ እጅግ ጥቃቅን
የሆኑ ሌዩነቶች ሉኖሩ ይችሊለ። ግን የመሬቱን ይዞታ በፍጹም አንዴ የሚያዯጉት ሁሇት
ታሊሊቅ ምክንያቶች አለ። እነሱም፦

፩ኛ/ በነዚያ አውራጃዎች መሬት ማሇት የማይሸጥ የማይሇወጥ የማይቀማ የተወሊጆቹ


የጋራ ርስትና ሀብት ነው።

፪ኛ/ አንዴ ሰው የነዚያ አውራጃዎች ተወሊጅ ከሆነ ከተወሊጆቹ ጋር የሚካፈሇው የጋራ


የሆነ የትውሌዴ ርስት አሇው። ስሇዚህ ሇያንዲንደ ሰው ያሇው ዕዴሌ አሳርሶ ከመብሊት ይሌቅ
አርሶ መብሊት ሲሆን ከትውሌዴ ቦታው ካሌወጣ በቀር ማንም ጢሰኛና ገባር ሉያዯርገው
አይችሌም። የዕሇት ራት የሚያሳጡት ችግሮች ቢኖሩበት

ሀ/ እንዯ በረዴ ዴርቅ ጎርፍ አንበጣና እነሱን የመሰለ የተፈጥሮ አዯጋዎች

14
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሇ/ የአሠራሩ ዘዳዎች ዯካማነት ማሇት የርሻውና የእርባታው ዘዳ ጨርሶ ያሌተሻአሇና
ትርፉ ከዴካሙ ጋር በምንም የማይመጣጠን መሆኑ

ሏ/ የአስተዲዯር የፍርዴና የፀጥታ አሇመሟሊትና የሙግት ብዛት

መ/ የበዓሊት ብዛት

ሠ/ ሥራን መናቅና ስንፍና ናቸው።

ከነዚህ ነገሮች በአንደ ያሌተጎዲ ከሰሜናዊ ኢትዮጵያ ክፍልች አንደ የዘር የትውሌዴ
ቦታው

የሆነ ኢትዮጵያዊ ይነስም ይብዛ ሠርቶ የሚኖርበት የግላ የሚሇው የትውሌዴ መሬት አሇው።

ይህም በመሆኑ የሰሜናዊ ኢትዮጵያ መሬት ያው ቋሚ የሆነ የጠቅሊሊው ተወሊጅ የጋራ


ርስት ሁኖ ኑሯሌ ሇማሇት ተችሎሌ። ይሁን እንጂ በነዚያ ክፍልች በቍጥራቸው በጣም
አነስተኛ በሆኑት የጅ ባሇሙያዎችና በላልች በቍጥር አነስተኛ በሆኑ የተሇያዩ ሃይማኖቶች
ተከታዮች ሊይ የቆየውን ክፉ ሌማዴ በመከተሌ ባሇርስት የሚባሇውን ስም የመከሌከሌ ሌማዴ
ስሊሇ በትምህርትና በመግባባት ማስወገዴ እጅግ ያስፈሌጋሌ።

፪ኛ የዯቡባዊው ኢትዮጵያ ክፍሌ።


በሌማዲዊው አነጋገራችን ዯቡባዊው የኢትዮጵያ የምንሇው ሌዩ ሌዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ
በሕዝብ ብዛት ታሊሊቅና ታናናሽ የሆኑ ሌዩ ሌዩ ነገድች ያሎቸው ኢትዮጵያውያን በበዛት
የሚኖሩባቸውን የኢትዮጵያ ክፍልች ነው። የዚህ ክፍልች መሬት ባሇፈው የኑሮ ሥርዓት
እንዯታየው የተወሊጆችም ሆነ ከላልች ክፍልች የመጡ ተራ ኢትዮጵያውያን ቋሚ ርስት
አሌነበረም።

ይህም በመሆኑ ቀዯም ብል ከተባሇውና ከተራቆተው አብዛኛው የሰሜናዊ ኢትዮጵያ


መሬት ይሌቅ ሇምና ዴንግሌ የሆነው የኢትዮጵያ ክፍሌ በብዛት የሚከተለት ወገኖች
ተቀራምተዉት ብዙው ዯሀ ተወሊጅ ከገባርነት በማይሻሌ ጢሰኝነት ሲቆራመዴበት በበረኃውም
ክፍሌ በዘሊንነት ሲንከራተትበት ኑሯሌ።

፩ኛ/ ባስፈሇገበት ጊዜ ሁለ ሇንጉሥና ሇንግሥት ሇሌዐሊን ሌዕሌታት ሇክቡራን


መኳንንትና ወይዛዝርት ሇታሊሊቅ የጦር አሇቆችና ሇተወዯደ ዯጀጠኝዎች ሇመታዯሌ እንዱመች
የመንግሥትነት ጠባይ ሳይኖረው መንግሥት በመባሌ ተቋቁሞ በኖረው የቅሚያና የሥርዓት
ዴርጅት ስም ተይዞ የቆየ ብዙ መሬት አሇ።

፪ኛ/ ንጉሡ ሇራሳቸው ሇባሇቤታቸው ሇሌጆቻቸው ሇሌጅ ሌጆቻቸው እንዱሁም


በቅርባቸው ሁነው በዝርፊያ ሇተባበሯቸው መሰልቻቸው ሁለ ዓይናቸው በቻሇ ቃሊቸው
በተናገረ መጠን እየመረጠ ያከፋፈለት ብዙ መሬት አሇ።

15
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
፫ኛ/ ዲግማዊ አፄ ምኒሌክ አብሯቸው ሇዯከመ ወታዯራቸው ሁለ በዯመወዝ መሌክ
ይሰጡት የነበረው ሀብት ርስት ስሇነበር ሇራሶችና ሇዯጃዝማቾች ከነተከታዮቻቸው የስጡትን
የጋራ ርስት ጮላዎች መሳፍንትና መኳንንት ሇየራሳቸው እየጠቀሇለ ወስዯውት ዛሬ
በሌጆቻቸው ወይም በሌጅ ሌጆቻቸው ስም የሚገኝ ብዙ መሬት አሇ።

፬ኛ/ ባሇፈው መንግሥት በከፍተኛም ይሁን በዝቅተኛ ሥሌጣን እየተሾሙ ወዯ ነዚያ


ክፍልች ሑዯው በሥሌጣን በተዯገፉ ሌዩ ሌዩ ተንኮልች ባሇርስቶችን እየቀሙ የያዙት መሬት
አሇ።

፭ኛ/ ፍጹም ሕገ ወጥ በሆነ መንገዴ አራጣ እያበዯሩና ዯሀውን ገበሬ በዘዳ አሳስተው
በኋሊ እያስጨነቁ መሬት ሲዘርፉ የኖሩ አራጣ አበዲሪዎች የያዙት መሬት አሇ።

፮ኛ/ ተወሊጅነታቸው በዚያው ክፍሌ ሁኖ እንዯባሊባትነት ባለ ከሌጅ ወዯ ሌጅ


በሚተሊሇፉ የዘር ሹመቶችና የተሇዩ ተከባሪነቶች ስም በአንዲንዴ ሰዎች በብዛት የተያዘ መሬት
አሇ።

የዯቡባዊ ኢትዮጵያ መሬት የሚሸጥና የሚሇውጥ ብቻ ሳይሆን በቀጥታ የሚቀማ ሁኖ


ኖረ ሇማሇት ይቻሊሌ። ከዚህም በሊይ እንዯ ሰሜናዊ ክፍሌ የግብርና ሥራ ሁለ ምንም
ባሌተሻሻሇና ውጤት ከዴካሙ ጋር ፈጽሞ በማይመጣጠን ዯካማ የርሻ ዘዳ የሚተዲዯረው
አብዛኛው የዯቡባዊ ኢትዮጵያ ገበሬ ያቺውን ያፈራትን ትንሽ የሊብ ፍሬ ታሊሊቅ የመንግሥት
ሥራና ሥሌጣን ከነ ከፍተኛ ዯምወዙ ሇያዙ ከፍተኛ የኪራይ ገቢ ያሊቸው የከተማ ቤቶችና
ሰፋፊ ርስት የተዯበቀ የሽርክና ንግዴ ሕግ ጣሌቃ ሉገባበት ያሌቻሇ ጉቦ ከዚህም በሊይ
የጠገበውን ሆዴ ጨርሶ በቁንጣን ሇመተርተር በንጉሠ ነገሥቱ ሌዩ ትእዛዝ ከመንግሥት ግምጃ
ቤት የሚሰጥ ሰፊ ጉርሻ ሊናጠጣቸው ባሇጊዜዎችና ያን የዝርፊያ ዘመን እንዯ ከፍተኛ ዕዴሌ
በመቍጠር ዯሀውን ሕዝብ ሲዘርፉ ሇኖሩ ግብረ አበሮቻቸው ሲገብር ቆይቷሌ።

ይህም በመሆኑ የዯቡባዊ ኢትዮጵያ የመሬት ሥሪት የአብዛኛውን ሕዝብና


የመንግሥቱን ጥቅም ምን ያህሌ እንዯጎዲው እንመሌከት።

፩ኛ/ ሇፍቶ ሇፍቶ ከሌፋትም ሌፋት ባሌተሻሻሇ የሥራ ዘዳ ዯክሞ የፈራውን የግብርና
ውጤት ሇጠገበ ባሊተኛ የማስረከብ ግዳታ ስሇተጫነበት የያንዲንደ ጢሰኛ ገበሬ የሥራ ፍሊጎት
ከዓመት ዓመት እየዯከመ በመሔደ የብዙዎች የነዚያ ክፍሇ ሀገሮች የርሻ ሥራ ውጤት
ከሇምሇምነታቸውና ከዴንግሌነታቸው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ሁኖ ይታያሌ። ባንዲንዴ
ክፍሌ ቡና በላልችም ብዙ ከብት ባይኖርማ እነዚያ ክፍልች የረኅብ ክፍልች በመባሌ በታወቁ
ነበር።

፪ኛ/ ሰፋፊውንና በይበሌጥ ፍሬያማ ሉሆን የሚችሇውን መሬት በየክፍለ የያዙት መሬት
ዘራፊዎች

ሀ/ ብዙውን በስማቸው ተከብሮ በጠፍነት እንዱኖር በማዴረግ

16
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሇ/ በሇሙም በጠፉም ሇመንግሥት የሚገባውን ግብር ባሇመክፈሌ ሀገሪቱን
አዯህይተዋሌ።

፫ኛ ላሊው የዯቡባዊ ክፍሌ አቋም።


ምንም እንኳ የዯቡባዊው ኢትዮጵያ ክፍሌ መሬት ከፍ ብዬ እንዯገሇጽሁት ሲሸጥ
ሲሇወጥና ሲቀማ የኖረ ቢሆን በተሇያዩ ምክንያቶች በአንዲንዴ ሰዎች እጅ በግሌ ርስትነት
የተያዘ መሬት ይገኛሌ። ይኸውም እንዯሚከተሇው ነው።

፩ኛ/ የዘር ርስታቸው ሳይሸጥ ሳይሇወጥ ወይም ሳይቀማ የተሊሇፈሊቸው አንዲንዴ


የክፍለ ተወሊጆች የያዙት መሬት

፪ኛ/ አያቶቻቸው ወይም ቅዴመ አያቶቻቸው ከማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍሌ መጥተው


በወታዯርነት ሊበረከቱት አገሌግልት በጊዜው እንዯ ዯመወዝ ሁኖ የተሰጣቸውን ርስት
ወርሰው የሚገኙ ነፍጠኞች ወይም የነፍጠኞች ሌጆች የያዙት መሬት (ከዚያ አሌፈው
ከዘራፊዎች ጋር በመተባበር የያዙም አሌፎ አሌፎ ይኖሩ ይሆናሌ።)

፫ኛ/ ከሰሜናዊ ኢትዮጵያ ክፍልች

ሀ/ በአንዲንድቹ መሬት ጨርሶ ተበሌቶ ዯኑ ተራቁቶ አፈሩ ታጥቦ ዝናሙ

ተቀንሶ ወይም ጭራሽ ጠፍቶ ሇግብርና ሥራ ፈስሞ ባሇመመቸቱ

ሇ/ በላልች ክፍልች ሕዝቡ እየበዛ መሬት እየጠበበ በመሔደ ወይም በላሊ ችግር

ተገዯው ከሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍሌ ወዯ ዯቡባዊ እየሔደ በገንዘብ በመግዛት የያዙት


መሬት አሇ።

፪ኛ ክፍሌ ስሇ ሇውጡ።
በዓይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁትን መረጃ ዴጋፍ በማዴረግ እስካሁን የቆየ የመሬት
ሥሪታችንን የተሇያየ አቋም ከሞሊ ጎዯሌ የገሇጽሁ ይመሇኛሌ።

የሚቀጥሇው ጥያቄ መንግሥት የመሬት ይዞታን አቋም በፍጹም ሇውጦ በሙለ


ተመሳሳይ የሆነ ዘመናዊ መንገዴ ሇማስያዝ ምን ማዴረግ ይገባዋሌ? የሚሌ ይሆናሌ።

በመግቢያው እንዯገሇጽሁት ኢትዮጵያንና ሕዝቧን በሚገባ የሚያውቁ አሁን በመካሔዴ


ሊይ ያሇው ከፍተኛ የሇውጥ እንቅስቃሴ ፍጹም ሰሊማዊና ውጤቶቹ ያማሩ የሆነበትን
ምሥጢርም ያሌተረደ ዯመፍልች ባጭሩ ሉሰጡት የሚችለ አንዴ መሌስ አሇ። እሱም
መንግሥት አንዴ አዋጅ አርቅቆ «ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮጵያን መሬት በሙለ መንግሥት
ወርሶታሌ። መንግሥት እንዲስፈሊጊነቱ እያየ ሇዕሇት ሠርቶ ማዯሪያ ከሚሰጠው በስተቀር
ባሇርስት የሚባሌ ሰው አይኖርም» ይበሌ የሚሌ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ
17
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ውስጥ እንዱህ ያሇ አዋጅ ይነገር ማሇት በመሊው የሀገሪቱ ክፍልች የርስ በርስ ጦርነት አውጆ
የተጀመረውን ሰሊማዊ የሇውጥ እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱ ን ሕሌውና እንዯማጥፋት
የሚቇጠር ነው።

ይህንንም ስሌ ከሀገራችን ጠቅሊሊ ሁኔታና ከአካባቢያችን ሳይጋጭ ሰሊማዊ የሇውጥ


እንቅስቃሴያችንን ዓሊማም ሳያበሊሽ ከሚፈሌገው ግብ የሚያዯርሰን ቀሊሌና ሰሊማዊ መንገዴ
ሌንመርጥ ይገባናሌ ሇማሇት እንጂ የመሬት ይዞታችን ሉሇወጥ አይችሌም ሇማሇት አሇመሆኑን
ከዚህ ሊይ እምግሇጽ ሰዎችን የኔ ሏሳብ አይገባችሁም ብዬ እንዯሰዯብሁ እቇጥረዋሇሁ።
ምክንያቱም የምጽፈው እጅግ አስፈሊጊና ተቀዲሚ ስሇሆነው የመሬት ይዞታ ሇውጥ ነውና!

በመጀመሪያ ዯረጃ።

፩ኛ ክፍሌ።
፩ኛ/ በመሊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባሇፉት ረጂም ዘመናት ስሇመንግሥት የነበረው
አስተሳሰብ ፈጽሞ መሇወጥ አሇበት።

ሀ/ የወዯፊቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ከመሊው የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከሌ ወጥተው


በሕዝቡ የወሇከለ የሕዝብ አገሌጋዮች የሚያቋቁሙት ሇመሊው ሕዝብ ሰሊምና ብሌጽግና
የሚሠራ ሕዝባዊ ማኅበር መሆኑን መሊው ሕዝብ እንዱረዲው ማዴረግ

ሇ/ ዘራችን ከዘራችን ዯማችን ከዯማችሁ ይበሌጣሌ ብሇው የሚያምኑ ጥቂት ግብዞች


ሇግሌ ጥቅማቸው አቋቁመው ሕዝቡን ረግጠውና አዯንቁረው ይገዙበት ሀብቱን
ይበዘብዙበት የነበረው ስመ - መንግሥት በወንጀሌ ማኅበር እንጂ እውነተኛ መንግሥት
ያሌነበረ መሆኑን ማስረዲት

ሏ/ በአዱሱ ሥርዓት «መንግሥት» ቢለ «ሕዝብ» ቢለ «መንግሥት» እንጂ የተሇያዩ


አካልች አሇመሆናቸውን ሕዝብ ዏውቆ የሕዝቡንና የመንግሥቱን አንዴ አካሌነት
የሚያረጋግጡ ተግባሮችን ማቀሊጠፍ ማሇት በምንም ዓይነት የመንግሥት ሥራ
ተሌከው አሮጌውን ሌማዴና አስተሳሰብ እስካሁን ሳይሇቁ በሕዝቡ መካከሌ የሚገኙትን
ሹማምንት በሙለ ከያለበት በቅዴሚያ አንሥቶ ሕዝቡ አዱስ ሥርዓትና አዱስ ዓሇም
መጀመሩን በተግባር የሚያረጋግጡሇት ቅኖች ትጉሆችና ንቁዎች ኃሊፊዎችን መሊክ
እጅግ ይጠቅመናሌ።

፪ኛ/ በሰሜናዊ ኢትዮጵያና በዯቡባዊ ኢትዮጵያ መካከሌ ብቻ ሳይሆን በዚያው በዯቡባዊ


ክፍሌ እጅግ የተራራቁ የመሬት ይዞታ ሌዩነቶች መኖራቸውን የዚያው ክፍሌ ሕዝብ
በሚገባ እንዱረዲና ሇውጡን በቅን መንፈስ እንዱመሇከት ማስቻሌ እጅግ ያስፈሌጋሌ።

ሀ/ የታሊሊቅ መሬት ዘራፊዎች ዘሮች ወገን ሇማብዛትና ቢቻሌ ብጥብጥ ፈጥሮ


የወዯቀው የቅሚያ ሥርዓታቸው ተመሌሶ እንዱያንሠራራ ሇማዴረግ ርስት ያሇው ሰው

18
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሁለ ተነቅል መሬት ሇሰፈረበት ጢሰኛ ብቻ ሉሰጥ ነው እያለ የሚነዙትን ወሬ
መውረሱ የሚመሇከት እነሱን ዘራፊዎችን ብቻ መሆኑን ገሌጦ ማጋሇጥ

ሇ/ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሩ የራሱን ዴርሻ መሬት የማግኘትና በዚያው ሊይ


ዓቅሙ እስከቻሇ የመሥራት መብት ስሊሇው በውርስም ሆነ በግዢ የተወሰነ መሬት
ያሊቸው ኢትዮጵያውያን ሁለ በታሊሊቅ መሬት ዘራፊዎች ሊይ ሉፈጸም የሚችሇው
ውርስ በአሁኑ ጊዜ ፈጽሞ የማይመሇከታቸው መሆኑን ዏውቀው በሇውጡ ሊይ ጥርጣሬ
እንዲይኖራቸው ማስረዲት

፫ኛ አሁን በጢሰኝነት የሚገኙት ገበሬዎች ሁለ ሉዯረግሊቸው የታቀዯውን ነገር


በትክክሌ እንዱረደት ማዴረግ ያስፈሌጋሌ።

ሀ/ መንግሥት የሚሰፍሩበት የራሳቸው መሬት እንዯሚያዘጋጅሊቸውና ሇመቋቋም


በሚገባ እንዯሚረዲቸው ተገንዝበው አስተሳሰባቸውን ብቻ ሳይሆን የቆዩበትን ቦታ
መሇወጥ እንዲያስቸግራቸው ማሳመን

ሇ/ መንግሥት የሚወርሰው ታሊሊቅ ዘራፊዎች ያሇወግና ያሇሌክ የዘረፉትን መሬት


እንጂ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከሌክ ሳያሌፍ የያዘውን መጠነኛ መሬት ሁለ ስሊሌሆነ
ሰፍሬበት ከቆየሁ የማንንም መሬት እየቀማችሁ ስጡኝ የሚሌ አዯገኛ ስሜት
እንዲያዴርባቸው እወነቱን ገሌጾ ማስረዲት እጅግ ያስፈሌጋሌ።

፬ኛ/ የሰሜናዊው ኢትዮጵያ ክፍልች መሬት በመሠረቱ የዚያው ሕዝብ ርስት ስሇሆነ
በዚያ ክፍሌ የሚኖረው ሕዝብ ሇራሱ ሇአካባቢው ሕዝብና ሇጠቅሊሊው የሀገር ሌማት
ሉፈሌጉ

ከሚችለ አንዲንዴ ቦታዎች በቀር ርስቴን የሚነካብኝ ይኖራሌ ብል የሚሠጋበት ምክንያት የላሇ
መሆኑን በሚገባ እንዱያውቅ ማዴረግ ይጠቅማሌ።

ከዚህ በኋሊ ወዯ ዋናው ጉዲይ እንግባ። ይኸም ጉዲይ የራሳቸው መሬት የላሊቸው
ገበሬዎች በሰሊም መሬት የሚያገኙበት መንገዴ ነው። ይህም ሲዯረግ መንግሥት የሕዝቡን
ሰሊም አዯፍራሽ ሳይሆን በሰሊማዊ መንገዴ መሬቱን ወዯጁ ሉያዛውርባቸው ይችሊሌ ብዬ
ያመንሁባቸውን ዘዳዎች እንመሌከት።

፩ኛ/ በመንግሥት ስም የቆዩትን መሬቶች ሇርሻና ሇግጦሽ የሚሆኑትን ሇዯን ሇማዕዴንና


ሇላሊም ይህን ሇመሰሇ ነገር ከሚከሇለት እየሇየ ጢሰኞች ገበሬዎች በጓዴ በጓዴ እየሰፈሩ
ሉያሇሟቸው እንዱችለ ማዴረግ

፪ኛ/ ከንጉሡ ጀምሮ እስከ ታች ዴረስ በገንዘብ በመግዛት ወይም በሕግ በመውረስ
ሳይሆን በጉሌባትና በሥሌጣን በመመካት ወይም ይኸን በመሰሇ ተንኮሌ የዘረፉ ሰዎች
የያዙዋቸውን መሬቶች በሙለ ወዯ መንግሥት እጅ በቀጥታ ማዛወር።

19
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
፫ኛ/ በምንም መንገዴ ይሁን ሉያሇማ ከሚችሇው በሊይ መሬት የያዘ ማንኛውም ሰው
ሇም ሇም ከጠፍ ጠፍ የሚባሇው የግብር አመዲዯብ ዯረጃ ጋሻ ሁኖ ሳይጠብቀው ከባዴ አዲጊ
ግብር እንዱከፍሌ ማዴረግ (ይህ ዓይነቱ የግብር አከፋፈሌ ሇአንዴ ዴርጅት የቀን ሙያተኞችም
ሆነ ቋሚ ሠራተኞች ከሥራቸውና ከዴካማቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ በቂ ዯመወዝ ከማስከፈሌ
ጋር የሰዎችን ኑሮ ሇማቀራረብ ዋና መዴኃኒት ሁኖ ስሇተገኘ ሇሕዝቡ የሚሠራ እውነተኛ
መንግሥት ባሇበት አገር ሁለ ይሠራበታሌ። ስሙ በእንግሉዝኛ ሔቪ ፕሮግሬሲቭ ታክሴሽን
ሲባሌ ዋና ሏሳቡም አንደ ሰው ገቢው ከፍ ባሇ መጠን ወይም የያዘው ማንኛውም ዓይነት
ሀብት ሰፊ በሆነ መጠን ከመቶ የሚፈሇግበት ግብር ወዯ ሊይ እያዯገበት ይሔዲሌ ማሇት ነው።
ሇምሳላ አንዴ ሰው በርሻ በንግዴ ወይም በላሊ ሥራ በዓመት ሏያ አምስት ሺህ ብር አግኝቶ
በመቶ አሥራ አምስት ግብር እንዱከፍሌ ቢዯረግ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሏምሳ ብር
ሇመንግሥት ግብር ከፍል ሏያ አንዴ ሺህ ሁሇት መቶ ሏምሳ ብር ይቀርሇታሌ ማሇት ነው።
ነገር ግን የዚህ ሰው ገቢ በዓመት መቶ ሺህ ብር ቢሆን ግብሩ ዯረጃ በዯረጃ እያዯገ ሰሇሚሔዴ
የሚከፍሇው በመቶ ሏምሳ ሁኖ ሏምሳ ሺሁን ሇመንግሥት ግብር ከፍል ሇራሱ ሏምሳ ሺህ
ብር ያስቀራሌ ማሇት ነው። በዚህ መንገዴ የግብር ክፍያ መጠን እያዯገ አንዴ ከፍተኛ ገቢ
ያሇው ሰው ከገቢው በመቶ ሰማኒያ እስከ ዘጠናውን ዴረስ ግብር ሉከፍሇው ይችሊሌ። ይኸም
ሕዝብ መንግሥት መንግሥት ሕዝብ በሆኑባቸው አገሮች ሁለ እየተሠራበት ያንደ ኑሮ ወዯ
ሰማይ ሲጉን የላሊው ኑሮ ወዯ እንጦርጦስ የሚወርዴበትን ሥርዓት ሉገታውና ሰብአዊ መሌክ
ሉያስይዘው ችሎሌ። በሀገራችንም በግዴም ሆነ በውዴ መሇመዴ ያሇበት ነገር ሲሆን ራሳቸው
ሠርተው የማይጠቀሙበትን መሬት የመሰብሰብ ሌማዴ ያሊቸውን ሰዎች ከዚህ ክፉ ሌማዴ
ሇማገዴና በማይገባ የያዙትንም ሇማስሇቀቅ ይበጃሌ።)

፬ኛ/ ከአሁን ጀምሮ መንግሥት ሳያውቅ በየቀበላው የሚያዯርገውን የመሬት ግዥና


ሽያጭ በቀጥታ ማገዴ ያስፈሌጋሌ።

ስሇ አሠፋፈሩና ስሇ አሠራሩ ዘዳ
መንግሥት በኃይሌ ብቻ ሁለን ሇማስተካከሌ ቢፈሌግ ከላሊው ብዙ ከባዴ ችግር ጋር
መንገዴ ዴሌዴይ መሥራቱ ወታዯር ማመሊሇሱ ስንቅና ትጥቅ መጫኑ ብቻ በገንዘብ በኩሌ
ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቅ መሆኑ አያጠራጥርም። ወጭ ካሌቀረም ወጪው ሇሰሊማችንና
ሇሌማታችን ቢውሌ በብዙ መንገዴ ይጠቅማሌ። ይኸም ማሇት ባሇመሬት ከሆኑ ሰዎች ጋር
መሬታችሁን ሇጢሰኝኖቻችሁ ሌቀቁ ብል ሇመጣሊት ገንዘብ ከማባከንና ቂሙ በቀሊለ የማይሽር
ሁከት ከመፍጠር እጅግ በሚቀሌና በሚጠቅም መንገዴ ጢሰኞችን በአካቢያቸው ከኖሩና
ከሚያውቋቸው መሰልቻቸው ሳይሇዩ በጓዴ በጓዴ እያዯረጉ በአዱስና ዘመናዊ በሆነ ዘዳ ሰፋፊና
ጤነኛ የሆኑ መንዯሮች እየቆረቆሩ ማስፈር ያስፈሌጋሌ ማሇት ነው። ሇዚህም የሚያስፈሌገው፦

፩ኛ/ የመሬት ይዞታና አስተዲዯር ሚኒስቴር አሁን ከሚሠራው በሊይ በጦሩ ኃይሌ
በቅርብና በቀጥታ እየተረዲ ሇግብርና ሥራ የሚውለትን መሬቶችን እየሇየ ሇግብርና ሥራ

20
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሚውለትን መሬቶች እየሇየ ሕዝብ የማስፈሩን የማቋቋሙንና ሥራውን የመቇጣጠሩን
ኃሊፊነት ይዞ እንዱመራ ማዴረግ

፪ኛ/ ከዚህ የሚቀዴም ችግር ስሇላሇ የሀገሪቱ ዓቅም የሚፈቅዴ ከሆነ መንግሥት ሇዚሁ
አንዴ ቋሚ በጀት መመዯብና ሀገሪቱ ዓቅም ካነሳት እርዲአታና ብርዴ በሰጡ ቍጥር አንዲንዴ
ግዳታ ከሚጠይቁ ኃያሊን ሳይሆን እንዯ እስካንዱኔቪያን አገሮችና እንዯ ዓሇም ባንክ ካለት
ዴርጅቶች ብዴር ጠይቆ ሇዚህ ሥራ መመዯብ።

፫ኛ/ በቀና አስተሳሰብና በዘመናዊ ዘዳ እየመሩና እየተቆጣጠሩ ካሠሩት የርሻ ሥራ


በዓመትና በሁሇት ዓመት እንኳ ጥቅም ሉያስገኝ ስሇሚችሌ

ሀ/ እንዯ እህሌ የቅባት እህሌ ጥጥና እነሱን የመሳሰለትን የርሻ ውጤቶች


በሚመረቱባቸው ቀበላዎች የሚሰፍሩ ገበሬዎች ከሰፈሩ ከሁሇት ዓመት በኋሊ ጀምረው
መንግሥት ያወጣሊቸውን ገንዘብ መክፈሌ እንዱጀምሩ ማዴረግ።

ሇ/ እንዯ ቡና እንዯ ፍራፍሬ ዛፎች ያለ ተክልችን የሚያሇሙና ከብት የሚያረቡ


ገበሬዎች ፍሬዎቹና ከብቶቹ ሇገበያ ከሚዯርሱሊቸው ጊዜ ጀምሮ የመንግሥቱን ገንዘብ
መክፈሌ እንዱጀምሩ ማዴረግ በጢሰኝነት የሚገኙ ገበሬዎችን ከጢሰኝነት ቀንበር ነፃ
አውጥቶ በአዱስ ዘዳ የተሻሇ ኑሮ እንዱኖሩና የሀገራቸውን ኢኮኖሚ በሰፊው እንዱዯግፉ
የሚከናወነውን ተግባር በጣም ሉያፋጥነውና ሉያጠናቅቀው ይችሊሌ። ከዚህም በሊይ
በርሻ በሚሇሙት ቀበላዎች ሁለ የየቀበላው የርሻ ውጤቶች በተሇይም ሇውጭ ገበያ
የሚቀርቡት እንዯየአስፈሊጊነታቸው በእንደስትሪ እየተዘጋጁ የሚቀርብባቸው ቀሊሌ
እንደስትሪዎችን ሇማቋቋም ያስችሊሌ።

፬ኛ/ አሁን በመንግሥት ስም በሚገኝና ከታሊሊቅ ዘራፊዎች በቀጥታ የሚወረስ ቦታ ሊይ


ሰፍረው የሚገኙ ጢሰኞች የአሠፋፈራቸውና የአሠራራቸው ዘዳ ዘመናዊነት እንዱኖረው
በአዱስ መሌክ አዯራጅቶ በያለበት እንዱቆዩ ማዴረግ ካንዴ ቦታ አንሥቶ ወዯ ላሊ
አዛውሮ ሇማስፈር የሚያስፈሌገውን ዴካምና የገንዘብ ወጭ ሉያስቀር ይችሊሌ።

፭ኛ/ በዘሊንነት የሚኖረው ሕዝብ በአንዴ አካባቢ ሰፍሮ ቋሚ ቤት ሠርቶ በዚያው


አርሶና ከብት አርብቶ የተሻሇ ኑሮ መኖር መቻለን ማስተማር ያስፈሌጋሌ።

ስሇ ባሇርስቶች የወዯፊት ዯኅንነት።


በየከተማው ሁነው ብዙ ጥቅም እያገኙ በተጨማሪ የርሻን ውጤት ከዯሀ ጢሰኛ አፍ
ሲነጥቁ የኖሩት ብዙ ባያሳስቡም ላልች ሉያሳስቡ የሚችለ ወገኖች አለ። እንዯ ዘራፊዎች
ተቇጥረው መሬታቸው በቀጥታ የማይወሰዴባቸው ሰዎችም ጢሰኞቻቸው ሰሇሚወሰደባቸውና
በመሬታቸው የሚከፍለት ተራና አዲጊ ግብር ስሇማይቀርሊቸው ሇጊዜው ቅር ሉሊቸው ይችሌ
ይሆናሌ። ነገር ግን በሇውጡ አምነውበትና አስተሳሰባቸውን ሇውጠው ሀገራቸውን በሰሊም
ሇመሇወጥ ከተባበሩ በአዱስ ዘዳ ከሇመደት የተሻሇ ኑሮ ሉኖሩ ይችሊለ።
21
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
፩ኛ/ አንዴ ሰው በስሙ ብቻ የሚኮራበት አሥር ጋሻ መሬት ይዞ አንዲንደን በጠፍነት
አቦዝኖ ከሚያስቀምጥ እንዱሁም በከሱ ጢሰኞችና ገበሬዎች ጉሌበት ብቻ ተማምኖ ከሚኖር
የተወሰነ መሬት ኑሮት ከጎረቤቶቹ ወይም ከወዲጆቹ ጋር ተባብሮ በብዴር ከቻሇም በራሱ ገንዘብ
ዘመናውያን የርሻ መኪናዎች ገዝቶ በተቃሇሇና በተቀሊጠፈ ዘዳ በማኅበር ወይም በወንፈሌ
ቢሠራ የበሇጠ ጥቅምና የማይወቀስ ስም ሉኖረው ይችሊሌ።

፪ኛ/ እነዚህ ሰዎች ሇሇውጡ ተባባሪ ሁነው ሲገኙ ጢሰኞችን ሇማስፈርና ሇማቋቋም
የሚዯክመው መንግሥት የነዚህ ወገኖች ኑሮ አቋም እንዲይናጋም አስፈሊጊ በሆነው ሁለ
መዯገፍና መርዲት ይገባዋሌ።

ሀ/ አስፈሊጊ በሆነበት ጊዜና ቦታ ሁለ ሇአዱሱ የአሠራር ዘዳ የሚያስፈሌጋቸውን


ምክርና ትምህርት በመስጠት

ሇ/ ሥራቸውን ሇማሻሻሌና ሇማስፋፋት የሚያስፈሌጋቸውን ብዴር በመስጠት አስዯሳችና


ጤነኛ የሚሆን አዱስ ሕይወታቸውን እንዱጀምሩ ሉረዲቸው ያስፈሌጋሌ።

ስሇ ስሜናዊው ክፍሌ መሻሻሌ።


በብዙ አገሮ እንዯሚታየው የአንዴ አገር መሬት ዓየር የባሕር ክሌሌ እንዱሁም በመሬቱ
ሊይ በባሕሩ በምዴሩ ውስጥ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብት ሁለ መንግሥት በቀጥታ የሚያዝበት
ነው። ይህም ማሇት እንዲሇፉት የኛ አገር ዘራፊ- መሪዎች ያቋቋሙት የቅሚያ ዴርጅት ያሇ
መንግሥት እያዘዘበት አብዛኛው ሕዝብ በሚያሠቅቅ የችግር የበሽታና የዴንቁርና መከራ
ሲማቅቅ ጥቂት ላቦች ያሇሌክና ያሇ ገዯብ ይፈነጩበታሌ ማሇት አይዯሇም።

በነዚያ አገሮች አስተሳሰብ አንዴ ነገር የመንግሥት ነው ሲባሌ ከአንዴ አገር ሕዝብ
ውስጥ ጥቂቶቹ ብቻ እንዯፈሇጋቸው የማያዙበት የጠቅሊሊው ሕዝብ ቋሚና ከትውሌዴ ወዯ
ትውሌዴ የሚተሊሇፉ ሀብት ነው ማሇት ነው።

እንግዱህ የሰሜናዊ ኢትዮጵያ ክፍሇ - ሀገሮች መሬት ቀዯም ሲሌ ዯጋግሜ


እንዯገሇጽሁት የማይሸጥ የማይሇወጥ የኗሪው ሕዝብ ቋሚ ርስት ስሇሆነ በመሠረቱ
የመንግሥት መሬት ነው ሇማሇት ይቻሊሌ። ምክንያቱም መንግሥት ማሇት ሕዝብ ሕዝብ
ማሇት መንግሥት ነው።

ሁኖም ሇሕዝቡ ጥቅምና ሇዘመናዊ አሠራር ሲባሌ በስምምነት ሉዯረጉ የሚገቡ አንዲንዴ
ሇውጦች መዯረግ አሇባቸው።

፩ኛ/ በየትም ቢሆን የአንዴ አገር የምዴር ውስጥና ከምዴር በሊይ ያለ ሰፊ ሀብቶች
ማሇት ዯን የደር አራዊት ወንዞች ተራሮችና የማዕዴን ሀብት የመንግሥት ናቸው። (ማሇት
ሀብቱ የተገኘበት ቀበላ ተወሊጆች ብቻ ሳይሆን የመሊው የሀገሩ ተወሊጆች ሀብት ነው።) ይህ
ከሚሆንባቸው ምክንያቶች ዋና ዋናዎቹም

22
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሀ/ በአንዴ አካባቢ የሚገኝ የአንዴ አገር የማዕዴን ሀብት በካፒታሉስ አገሮች (ማሇት
የግሌ ሀብትን ሇማዲበር ነጻ ውዴዴር እንዱሁም ማጭበርበርና በሚቻሌ መጠን ሠራተኛን
ተጭኖ ራስን ማክበር የፈሇጉትን ሥራ መርጦም የመጀመር ሇያንዲንደ ግሊዊ ሰው ዕዴሌ
ባሊቸው አገሮች) አብዛኛውን ጊዜ በአንዴ የብዙ ሀብታሞች የንግዴና የእንደስቲ ማኅበር ወይም
በአንዴ ታሊቅ ከበርቴ በሆነ ቤተ ሰብ በሚመራ ዴርጅት እንዱያዝ ሲዯረግ አሌፎ አሌፎ
በመንግሥትም ሉያዝ ይችሊሌ።

ሇ በሶሽያሉስ አገሮች (ማሇት «ኮሚኒስት ፓርቲ» የሚባሌ አንዴ ማኅበር ብቻ


የሚመራው መንግሥት ሁለንም ነገር በቀጥታ በሚቇጣጠርባቸው እያንዲንደ ሰው ወይም
አንዴ ጓዴ በግለ የሚካሔዴባቸው የሥራ ዴርጅቶች እንዱቋቋሙ በማይቻሌባቸው አገሮች)
እንዯማንኛውም ነገር ሁለ በመንግሥት የተያዘ ነው።

እንዱሁም ዯኖችና የደር አራዊት በሚገባ ተጠብቀው ሀገሩን በብዙ መንገዴ


እንዱጠቅሙ አስፈሊጊ የሆነውን ጥንቃቄና ቁጥጥር ማዴረግ በየትም ዓሇም ቢሆን የመንግሥት
ተግባር ነው። ወንዞች አስፈሊጊ ሁኖ በተገኘበት ቦታ ሁለ እየተገዯቡ ሇአካባቢው ሕዝብ የመስኖ
ሌማት የኤላክትሪክ ኃይሌና ብርሃን እንዱጠቅሙ ማዴረግና በጠቅሊሊው የአንዴ አገር መሬት
በጎርፍ በመታጠብ በዛፎች ያሇ አግባብ በመጨፍጨፍና ይህን በመሳሰለ ባሇማወቅ ወይም
በግዳሇሽነት በሚዯርሱ ጉዲቶች ሀገር እንዲትራቆት መቆጣጠርም የመንግሥት ኃሊፊነት ነው።
ይህ እንዱሆን ያስፈሇገበት ምክንያት እነዚህን የመሳሰለ ታሊሊቅ ብሔራዎ ተግባሮች የተሇየ
የሀብት ይዞታ በላሊቸው ግሊውያን ሰዎች ዓቅም ብቻ ሉፈጸሙ ስሇማይችለ ነው።

እንግዱህ ሕዝብ ይኸን ተገንዝቦ በሕዝብ የተቋቋመ መንግሥት የሚጠይቃቸውን ተገቢ


ጥያቄዎች ሁለ ያሇማመንታት ማሟሊት አሇበት ማሇት ነው።

፩ኛ/ የአካባቢውን ሕዝብ ወይም የሀገሪቱን ሕዝብ በጠቅሊሊው ሉጠቅም የሚችሌ


ብሔራዊ ሀብት ያሇበት ቦታ ሁለ የመሊዋ ኢትዮጵያ ሀብት ስሇሆነ የትም ቢሆን መንግሥት
ሉያዝበት ይገባዋሌ።

፪ኛ/ መንግሥት የአካብቢውን ሕዝብ ኑሮ ሇማሻሻሌ የርሻና የርቢ ሥራዎችን ሠርቶ


ማሳያ ጣቢያዎች ሇማቋቋም በሚፈሌግበት ጊዜ በየትኛውም ቀበላ አስፈሊጊ የሆነውን መሬት
የማግነት መብቱ በማንም ዘንዴ ሉታወቅሇት ያስፈሌጋሌ።

፫ኛ/ የአካባቢውን ሕዝብ ኑሮ ሇማሻሻሌና የተሟሊ ሇማዴረግ ሇሚከፈቱ ሕዝባዊ


መገሌገያዎች ማሇት ሇመንገዴ ሇትምህርት ቤት ሇክሉኒክ ሇሆስፒታሌ ሇገበያ ሇመናፈሻና
እነሱን ሇመሰለ ሁለ የሚፈሌገውን መሬት በቀጥታ የመውሰዴ መብት አሇው።

፬ኛ/ በአንዲንዴ ሰፋፊና የተሇየ ሁኔታ ባሊቸው ክፍልች ሇምሳላ በሰሜንና በጌምዴር
ክፍሇ ሀገር እንዯነ መተማና ሰቲት ሁመራ በጎጃም እንዯነ መተከሌ ባለት ቦታዎች ሇከፍተኛ
መንግሥታዊ የሌማት ዴርጅት የሚፈሌገውን መሬት የማግኘት መብት አሇው።

23
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሕዝቡን አሠፋፈርና የአሠራር ዘዳ

ስሇመሇወጥ
በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ክፍልች የሚኖረው ሕዝብ ከዯቡቡ ክፍሌ በመጠኑ ሇየት ባሇ
ሁኔታ በየቀቤውና በየሰበካው ተፈነጣጥረው በሚገኙ መንዯሮች ተበታትኖ ይገኛሌ። የያንዲንደ
ገበሬ ማሳዎችም በአንዴ ሊይ ተጋጥመው የሚገኙ ሳይሆኑ በየጎጡ የሚገኙ የመሬት ትሌታዮች
ናቸው። ይህ ዓይነቱ የአኗኗር ሌማዴ እስከ ዛሬ እንዯነገሩ ሁኖ ሇኖረው እናት አባቱ አያት
ቅዴመ አያቱ ተወሌዯው በኖሩበት ቦታ ተወሌድ ኑሮ ከዚያው ሳይወጣ መሞቱንና መቀበሩን
እንዯ ከፍተኛ ክብር ሇሚቇጥረው ሕዝብ ስሜቱን የሚያረካ ጠባይ ኑሮት ቢቆይም ገጠሬውና
ሇፍቶ አዲሪው ኢትዮጵያዊ የከተማ ኗሪዎች ከሚያገኟቸው ዕዴልች ምኑም ሳይጎዴሌበት
በዕዴገት እንዱራመዴ አዱሷ ኢትዮጵያ ሇምታዯርገው የወዯፊት ሰፊ ጥረት እጅግ አስቸጋሪ
በመሆኑ ሕዝቡ ሇራሱ ዕዴገትና ዯኅንነት ሲሌ የአኗኗርና የአሠራር ዘዳውን በፍጹም መሇወጥ
አሇበት።

፩ኛ/ ቢያንስ ቢያንስ የአንዴ ሰበካ (አጥቢያ) ሕዝብ ሇመንዯር አሠራር ምቹ መሆኑ
በተጠና አንዴ አካባቢ በዘመናዊ ዘዳ መሇስተኛ ከተማ የሚሆን መንዯሩን ሠርቶ መስፈር እጅግ
ይጠቅመዋሌ ይህም ማሇት በመጀመሪያው አነስተኛ የመሻሻሌ ዯረጃ

ሀ/ በራሱና በመንግሥቱ መረዲዲት በአካባቢው ሇሚሠራ መንገዴ አቅራቢያ በመሆን


በግብርና ሙያ ያፈራውን የርሻ ውጤት በቀሊለ ሇገበያ ማቅረብና ጥቅሙን ማሻሻሌ
ይችሊሌ።

ሇ/ የታመሙ ሰዎች ወይም በምጥ የተያዙ ሴቶች ብዙ መንገሊታት ሳይዯርስባቸው


በቅርቡ መኪና አግኝተው ወዯ ሕክምና ቤት ሉዯርሱ ይችሊለ።

ሏ/ ሇሰው ወይም ሇከብት ክትባትና ሕክምና ሇላሊም ይህን ሇመሰሇ እርዲታ መንግሥት
የሚሌክሇት ነገር ሁለ በቀሊለ ሉዯርስሇት ይችሊሌ።

፪ኛ/ ከጎረቤቶች ጋር ተባብሮ ሇመሥራት

ሀ/ በማኅበር ሇማረስ ከብት ድሮ ንብን ላሊም እንስሳት ሇማርባት

ሇ/ ከበር ሊይ ትምህርት ቤት ክሉኒክ እንዱሁም የፈሇጉትን ነገር ሁለ የሚገዙባቸው


ሱቆች ሇማግኘት

ሏ/ ወሀና መብራትን የመሳሰለ ነገሮችን ሇማስገባት።

መ/ በምክክርና በኅብረት ሇርሻና ሇግጦሽ የሚሆኑትን መሬቶች በመሇየት የርሻና የርቢ


ሥራዎችን ዘመናውያን ሇማዴረግ

ሠ/ በኅብረት የአካባቢን ጽዲትና የግሌ ንጽሕናን ሇመጠበቅ


24
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ረ/ በኅብረት የአካቢን ሰሊምና ፀጥታ እየጠበቁ ሥርቆትን ግዲያንና እነሱን የመሰለ
ወንጀልችን ከሀገር ጨርሶ ሇማጥፋት ጠቅሊሊው ማኅበራችን ሇሚያዯርገው ትግሌ
የራስን ዴርሻ ሇማበርከት

ሰ/ ወንዞችና ምንጮች ወይም የተፈጥሮ ሏይቆች በማይገኙባቸው አካባቢዎች በመንዯሩ


ኗሪዎችና በመንግሥት ተራዴኦ ሇሰውና ሇከብት እንዱሁም ሇአትክሌት ሥራ የሚውሌ
በቂ ወሀ ሉሰጡ የሚችለ የወሀ ጉዴጓድችን ሇማስቆፈር እንዱሁም ሇሰውና ሇከብት
መጠጥ ዓሣዎችን ሇማርባት የሚጠቅሙ ሰው - ሰራሽ ሏይቆችና ጉዴጓድች ሇመቆፈር
ላልችንም ይህን የመሰለ አንዴን ሕዝብ በአካሌም በአእምሮም የሚያዯረጁ ተግባሮችን
በተባበረ ጉሌበት ሇማከናወን ፍቱን መዴኃኒት የሚሆንና በብዙ አገሮች እየተሠራበት
የሚገኝ ነው። በዯቡብ ክፍሌ የሚገኘውን ጢሰኛ ገበሬ በመንግሥት እቅዴ መሠረት
በዘመናዊ መሌክ ማስፈር ስሇሚቻሌ ይኸ ሁለ ነገር ብዙ አስቸጋሪ አይሆንም።

የማስተማሪያው ዋና ዘዳ
የሥሌጣኔ ፋና ርቆት የኖረ አንዴ ሕዝብ በተሇይም እንዯ ኢትዮጵያ ሕዝብ መብትንና
ጥቅሙን በትክክሌ እንዲያውቅ ተዯርጎ በዯንቆሮነትና በጭካኔ በዯነዙ ሹማምንት ሲሠቃይ የኖረ
ሕዝብ በርግጥ ከመንግሥት ጎን ነገር ይመጣሌኛሌ ብል ሇማመን እንኳ ይጠራጠር ይሆናሌ።
አይፈረዴበትም። አስተዲዯር ፍትሕና ርትዕ ማጣት ብቻ ሳይሆን ሇሌዩ ሌዩ የሌማት ሥራዎች
እየተባሇ በየጊዜው ከወጣው ገንዘብ አብዛኛው ተበሌቶበታሌ። ጉሌበቱ በከንቱ ባክኖ ቀርቷሌ።
ከመንግሥት በኩሌ ስሇሚመጣ ምንም ዓይነት እርዲታ በመንፈሱ ቀርጾት የነበረውን ቅን
አስተሳሰብ ተስፋ ከመቁረጥ ጋር ሇውጧሌ። ነገር ግን አሁን ወዯ ላሊ የታሪክ ዘመን
መሸጋገራችንንና ንጉሠ ነገሥቱ ከነዘረፋ ማኅበራቸው የተወገደትም ባሇፈ ክፉ ሥራቸው
በመጠሊታቸው ብቻ ሳይሆን ሇወዯፊቱ ሕዝቡ አጥቶት የኖረውን ብዙ መሌካም ዕዴሌ በአፋጣኝ
መንገዴ እንዱያገኝ ሇማዴረግ መሆኑን ሉገነዘብ ይገባሌ።

ይኸም ሁኖ ሕዝቡን ይህን ሥራ እያለ በመንገር ከመወሰንና ሇማስገዯዴም ከመሞከር


ይሌቅ ላሊ ዘዳ መፈሇጉ የበሇጠ ውጤት ሉያስገኝ ይችሊሌ።

ሇምሳላ መንግሥት የአንዴን ወረዲ አስተዲዯር ሕዝብ ኑሮ ሇመሇወጥ በብዙ መንገዴ


ከሚዯክም በዚያ ወረዲ ውስጥ አማካይነትና ሇሥራው ምቹነት ያሇው አንዴ ሰበካ (አጥቢያ)
መርጦ። ከሕዝቡ ጋር በተቻሇ መጠን በመግባባት በሚፈሇገው መንገዴ በአንዴ አካባቢ
ሠፍረውና ከመንግሥት ከሚዯርስባቸው እርዲታ ጋር ኑሯቸውን ሇውጠው እንዱገኙ ቢዯረግ
እነሱን በማየት ብቻ የዚያ ወረዲ ሕዝብ በሙለ ከምንም የበሇጠ ትምህርትና በመንግሥት ቅን
ፕሮግራም የማመን ዕዴሌ በቀሊሌ ሉያገኝ ይችሊሌ።

ከዚያ በኋሊ የሚፈጠውን «የኔ እበሌጥ እኔ እበሌጥ» የመንፈሳዊ ቅናት ውዴዴር


መገመት አያዲግትም።

25
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ይህም ማሇት ሕዝቡ በአካቢው የራሱን ኑሮ እጅግ ወዯ ተሻሇ ሁኔታ የሚሇውጥ ዘዳ
በሥራ ሊይ ውል ካየ ያሇ አንዲች ማመንታት ወዯ ጋራ ትግለ ይገባሌ ማሇት ነው።

የተሇየ ኃሊፊነት ያሇባቸው ክፍልች


ጠቅሊሊው ሕዝብ ጉዲዩን በትክክሌ ከተረዲው ምን ጊዜም ቢሆን የራሱ ተቃዋሚና የገዛ
ዕዴለ ተቀናቃኝ ስሊይዯሇ ፍጹም ተባባሪነቱን እንዯሚያሳይና ተባብሮም እንዯሚሠራ ሳይታሇም
የተፈታ ነው።

ነገር ግን የሇውጡን ዓሊማ ሇማስረዲት መሞከር ብቻ ሳይሆን በሏሰተኛ ወሬ ሕዝቡን


ሇማወናበዴ የሚፈሌጉ አንዲንዴ ወስሊቶችን የተንኮሌ ወሬ ሇመከሊከሌ እንዱሁም አስናፊና ወዯ
ኋሊ ጎታች የሆኑ ባሕልችን የማጥፋት ኃሊፊነት ያሇባቸው ክፍልች አለ።

፩ኛ/ መንግሥት የሇውጡ መሪ ስሇሆነ ከፍተኛ ኃሊፊነት አሇበት

ሀ/ እጅግ የተመረጡ አስተዲዲሪዎችን የፖሉስ አዛዦችን ዲኞችንና ላልችንም የሕዝቡን


መብት ፀጥታና ሰሊም ሇመጠበቅ የሌማቱን ሥራና አንዴነቱን ሇማጠንከር ከሌብ
የሚሠሩ ሰዎችን ሇየቀበላው መሊክ

ሇ/ እንዯ አጥቢያ ፍ/ቤት ም/ወረዲ አስተዲዯር ያለትን የሥራ ማስፈቻ መሥሪያ ቤቶች
በቀጥታ መዝጋት

፪ኛ/ ከሀገሪቱ በጀት ከፍተኛውን ሇሌማት ሥራ በተሇይ ሇርሻ ሥራ ዕዴገትና መስፋፋት


መመዯብ ይገባዋሌ።

ሀ/ ከፍተኛም ሆነ መጠነኛ የርሻ ሥራ ዕውቀት ያሊቸውን ሰዎች በሙለ የሚገባቸውን


ዯመወዝ እየከፈሇ የሀገሪቱን የተፈጥሮና የአካባቢ ሁኔታ ተከትል የርሻን ሥራ
ሇማሻሻሌ ሇሚዯረጉ ምርምሮች በተቋቋሙና በሚቋቋሙ ኢንስቲቱቶችና በየቀበላው
ተሰራጭተው የተሻሻሇ የግብርና ዘዳን እንዱያስገኙና ሇሕዝቡ እንዱያስተምሩ ያለን
የርሻ ትምህርት ቤቶቻችንም እንዱስፋፉ ማዴረግ

ሇ/ አስፈሊጊ በሆነበት ቦታ ሁለ የርሻና የርቢ ሙከራ ጣቢያዎችን ማስፋፋት

፫ኛ/ ሇገበሬዎች ሰፊ የገበያ ዕዴሌ ሇማስገኘት መጣጣርና ያገር ውስጥ ችግራቸውን


ማስወገዴ

ሀ/ በርሻ ሥራ በሇሙ ቀበላዎች ሁለ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር ቢያንስ ቢያንስ የበጋ


መንገድች ባስቸኳይ እንዱሠሩ ተቀዲሚነት መስጠት

ሇ/ ሇሀገር ውስጥ ገበያ በሚውለ የርሻ ውጤቶች ሊይ ሁለ እንዯየ አካባቢው የመገናኛ


ሁኔታና የሠራተኞች የዴካም መጠን እንዱሁም እንዯ ሸማቹ ዓቅም ታይቶ
በሚተመነው መሠረት ጥብቅና ፍጹም የሆነ የዋጋ ቁጥጥር ማዴረግ
26
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሏ/ በውጭ ገበያዎች በሚያጠራጥር ሁኔታ ተፈሊጊ የሆኑ የርሻ ውጤቶች በብዛትም
ሆነ በጥራት በየዓመቱ በሰፊው እንዱጨመሩ ገበሬዎችን መምከር ማበረታታት
መርዲትና በአንዲንዴ ጮላ አስመጭና ሊኪ ነጋዳዎች እንዲይበሇጡ በጥብቅ መቆጣጠር።

መ/ ሇሰራተኞቻቸው ተገቢውን ዯመወዝ እንዱከፍለ የአካብቢውን አነስተኛ ገበሬም


እንዲይጫኑ እየተቆጣጠሩ ሰፋፊ የግሌ እርሻ ያሊቸው ኢትዮጵያውያንም የግሌ
ሥራቸውን ሇማስፋፋት ላልችም ይህን መሳዩን ሥራ ሇመወጠን የሚያዯርጉትን ጥረት
አሇማዯናቀፍ ያስፈሌጋሌ።

፪ኛ ቤተ ክርስቲያናችን

ኃሊፊእንት አሇባት
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ክርስቲያን መሆን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱ በሙለ ተቆራኝቶ
የኖረው ከቤተ ክርስቲያኗ ጋር ነው። ይህ በመሆኑ በቤተ ክርቲያን ስም የመጣ
ማንኛውም ነገር ክፉነቱና ዯግነቱ ሌማቱና ጥፋቱ እውነትነቱና ሏሰትነቱ ሳይመረመር
ሙለ ተቀባይነት እያገኘ ሕዝቡን ሲበዴሌ የኖረ ብዙ ከንቱ ሌማዴ በሀገራችን
ተንሠራፍቶ ይገኛሌ። ስሇዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የራሷን አቋምና የሌጆችዋን ኑሮ
ከሏያኛው መቶ ዓመት አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ከራሱ ከቤተ ክርስቲያን መሥራች
ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ውጭ አዴርገዉት የሚገኙ ተረቶችን በቅደስ
ሲኖድስ እየወሰነች ማስወገዴ አሇባት።

ሀ/ የበዓሊትን ብዛት ባስቸኳይ ቀንሳ ሇመሊው ተከታዮቿ ማወጅ

ሇ/ በየከተማውና በየገጠሩ በሚገኙ አዴባራት እየተዘዋወሩ ከክርስቶስ ትእዛዝና


ትምህርት እንዱሁም ከተዋሕድ ሃይማኖት ቋሚ ሥርዓቶች ውጭ በሆነ የውሸት
ትምህርት ሕዝበ - ክርስቲያኑን ሲያዯናግሩት ሥራውን እንዲይሠራ ሲገዝቱ የሚውለ
አጭበርባሪ ሰመ - ባሕታውያንን ከኦርቶድክስ ክርስቲያን አባሌነታቸው ሊይታ በየዯብሩ
እንዱታወጅባቸው ማዴረግ

ሏ/ በዯቡባዊ ኢትዮጵያ ክፍሌ ስሙ ሇቤተ ክርስቲያን ሁኖ አብዛኛውን ጊዜ መሳፍንት


መኳንንትና ወይዛዝር ወይም ላልች ገፋፊዎች የቅስና የዱቁና የዴብትርና የግብዝና
የዚህ የዚያ እያለ ይዘው ሲጠቀሙበት የኖሩትን ሇስሟ ማጥፊያ ብቻ የተቀመጠ መሬት
በቀጥታ ሇመንግሥት ማስተሊሇፍ

መ/ ሳታስተምር በክህነት ባሕር ያጥሇቀሇቃቸውን ማኃይምናን ካህናቶቿንና ሕዝቡን


ሇሌማትና ሇአዱስ አስተሳሰብ እንዱነቁ በሚዯረግሊቸው ዴካም ተቀዲሚ አርአያ መሆን

ሠ/ ከሌክ በሊይ በመጾምና እርሱን በመሰለ እውነተኛው የክርስቶስ ትእዛዝ


በማይፈሌግብን አዴካሚ መከራ የሚንገሊቱ ብዙ መኃይምናን ክርስቲያኖችን ዴካም
27
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሚያቃሌሌ መንገዴ መፈሇግና ይህን የመሳሰለ ጉዴሇቶችን ማረም በዘመናችን
ሇሚፈሇገው ፈጣን የሇውጥ እርምጃ ከፍተኛ አገሌግልት ከማበርከቷ በሊይ የሀገሪቱን
ነጻነት በሌጆቿ አማካይነት በመከሊከሌ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አገሮች በሙለ የማይገኝ
የራሷ ፊዯሌ ከባዕዴ ተፅዕኖ ፍጹም ነጻ የሆነ ከፍተኛ የዜማ የቅኔና የሥነ - ጽሐፍ
ቅርስ እንዱሁም ታሊሊቅ ታሪካውያን ቦታዎች አስዯናቂ የሕንጻ የስዕሌ የመጻሕፍት
ሀብቶች እጅግ ከፍተኛ የሆኑ የሥነ - ምግባርና የማኅበራዊ ኑሮ ግዳታዎች የመፈጸም
ኃሊፊነቶች ከብዙ እኒህን ከመሰለ ተግባሮች ጋር እንዱኖሯት ኃሊፊነቱን ሁለ ተሸክማ
አቆይታ ሇማስረከቧ የሚከፈሊትን የግፍ ዋጋ መሰዯብን - መወቀስን ባንዲንዴ ምኑንም
ስያውቁ ሇጉራና ሇአሇ - ይበለኝ ብቻ የሚቃጁ አጭበርባሪዎችን ቅርሻት ሁለ መቀበሌን
በዴፍረት ሇማስወገዴ ያስችሊሌ።

፫ኛ ወጣቶች ታሊቅ ኃሊፊነት አሇባቸው


ሀ/ ሇሁከት ሇውጭ አይዱኦልጂ ማስፋፊያና ሇግሌ ፍሊጎታቸው ማሟያ መሣሪያ
ሉያዯርጓቸው በሚፈሌጉ አንዲንዴ ሰዎች የሏሰተኛ ተስፋ ስብከት (ዳማጎጂ) ወጥመዴ
ሳይወዴቅ ሀገራቸው በራሷ መንገዴ ከሚፈሇገው ፍጹም ሇውጥ ሇምትዯርስበት ዓሊማ
ቢሠሩ ከፍተኛ ዴርሻ ያበረክታለ።

ሇ/ ነገ ሀገሪቱን ዯኅና ብትሆን ከነዯኅነቷ በችግር ሊይ ብትሆን ከነችግሯ በሙለ


ኃሊፊነት የሚረከቧት ራሳቸው መሆናቸውን አምነው ሇሀገራቸው ዯኅንነት በሙለ ሌብና
ቆራጥነት ሉሠሩሊት ይገባቸዋሌ፡

ሏ/ አንዴ አፍሪቃዊ መሪ እንዲለት ሁለ በምዕራብም ሆነ በምሥራቅ የባዕዴ


አይዱኦልጂ ተጠምድ መያዝ የሀገሩን ስረ - ወጥ የተፈትሮ አስተዋይነት ከመዯምሰሱ
በሊይ በአንደ አገር የተሠራውን በላሊው በቀጥታ ሇመገሌበጥ ሲሞክር የሚያስከትሇውን
አዯገኛ ውጤት ተረዴተው የሀገሪቱን ችግሮች በተሇይም የመሬት ይዞታን በዘዳና
በሰሊም ሇመሇወጥ ያሇውን ችግር ሇማስወገዴ «መሬት ሇአራሹ» የሚሌ ዘዬን (ስልጋን)
በመዘመር ብቻ ሳይሆን በሚያዋጣው መንገዴ ተባብረው ሉሠሩ ይገባሌ።

፬ኛ እያንዲንደ ያገር ቤት ኗሪ

ከፍተኛ ኃሊፊነት አሇበት

ሀ/ በሆነ ባሌሆነው ምክንያት ሙግት እየፈጠሩ ሇሥራ የሚውሌ ጉሌበትና


ጊዜያቸውን ወዯ ፖሉስ ጣቢያዎችና ፍርዴ ቤቶች በመመሊሇስ ዯክመው
ያፈሯትን መጠነኛ ሀብት በጉቦ ስሇሚያባክኑ ዏዋቂዎች ሥሌጡኖችና ብርቱዎች
የሆኑ የሚመስሊቸው ሰዎች ሁለ ጊዜ ያሇፈባቸው በአዱሷ ኢትዮጵያ ምንም
ግምት የማይሰጣቸው የዋሆች መሆናቸውን መረዲት አሇባቸው።

28
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሇ/ የጅ ባሇሙያዎች በየትም ዓሇም እጅግ ተከብረው ሙያቸውንና የሥራ
ዘዳያቸውን እያሻሻለ የየሀገራቸውንና በጠቅሊሊውም የዓሇምን ሕዝብ ኑሮ
በፍጹም ሇመሇወጥ ዕዴሌ ሲያገኙ በኛ ሀገር ርስትን የጋብቻ ግንኙነትን ከዚህም
አሌፎ በሙለ ሰውነት መታየትን እየተከሇከለ ኢትዮጵያ የሰነፍ ዘር ቇጣሪዎችዋ
መቀሇጃ የሠርቶ አዲሪዎችዋ መቆራመጃ ሁና የቆየችበትን ርኩስ ወግ በኅብረት
መዯምሰስ ያስፈሌጋሌ።

ሏ/ እያንዲንደ ኢትዮጵያዊ ሇሀገሩ ችግርም ሆነ ዯኅንነት የየራሱ ዴርሻ ያሇበት


መሆኑን አምኖበት ራሳችን ራሳችንን የምንፈራበት የሹክሹክታ ወሬና ሏሜት
በገዛ ራሳችን ሊይ እየፈጠርን የራሳችንን ጥሊ በማየት እየዯነበርን እኛ
የማናመጣው ችግርና ጥፋት ከመሬት እንዯ እንጉዲይ የሚበቅሌብን ከሰማይ
እንዯ መብረቅ የሚወርዴብን ይመስሌ ስሇራሳችን ጥፋት ራሳችን የምንፈጥረውን
ሌብ ወሇዴ ታሪክ ማሾክሾኩን ትተን መሊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአንዴ እናት
እንዯ ተወሇዯ ቤተ ሰብ አዴርገን በማየት ያሇብንን ችግር ሁለ በወንዴማማችነት
እየተወያየንበትና በኅብረት እያስወገዴን መሥራት ያስፈሌገናሌ።

ግባችን
የተነሣሁበት ዋና ርእስ የመሬት ይዞታን ሥርዓት ሇመሇወጥ ይረዲሌ ብዬ በራሴ በኩሌ
ያመንሁበትን አስተያየት መግሇጽ ቢሆንም ከዚሁ ጋር ግንኙነት ያሊቸው ብቻ ሳይሆኑ
ሇጠቅሊሊው ሇውጣችን ሉጠቅሙ የሚችለ አንዲንዴ አስተያየቶችን ጨማምሬያሇሁ።

ከዚህም ሊይ ስሇጠቅሊሊው የሇውጣችን ዓሊማ ጥቂት ሌገሌጽ እፈሌጋሇሁ። ሕሌማችን


የዓሇም ቅን ሕዝብ ሁለ ሕሌም ነው።

የኛ ብቻ ሳይሆን የመሊው ዓሇም ሕሌም የሆነ ታሊቅ ግብ አሇ። ይህም ግብ ምዴራዊ


ገንት ፈጥሮ የሰው ሌጆች ከችግር ከበሽታ ከዴንቁርና ነፃ ወጥተው ወንጀሌ እሥራት ጭቆና
ግፍ የኑሮ ጭንቀት ተረስተው የሰው ሌጆች በፍቅርና በዯስታ እንዱኖሩ ሇማዴረግ መጣጣርና
ሲሆን ብዙ ሀገሮች ከዚያ ገነት በመጠኑ ቀረብ ብሇው አሁንም እርምጃቸውን እያፋጠኑ
ወዯዚያው ጨርሶ ሇመግባት በመገስገስ ሊይ ናቸው።

እኛ ግን ከገነቱ ቀርቶ ከመካነ - ንስሏው ሳንዯር ገና በሲኦሌ ውስጥ ሁነን ስንሠቃይ


እንገኛሇን።

በሥሌጣኔ ወዯፊት ከገፉት አገሮች ጥቂቶችንም ሆነ ብዙዎችን የምዕራቦችንም ሆነ


የምሥራቆችን ያየ አንዴ ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዯ ሰው ነው የሚኖረው ብል
ማመን እጅግ ያስቸግረዋሌ። እኛ የምንኖረው በቁም መቃብር ውስጥ ነው። የመጀመሪያ
ተግባራችንም መግነዛችንን ቀዲዯንና በጣጥሰን የተጫነብንን የመቃብር ዴንጋይና አፈር
ፈነቃቅሇን ወዯ ብርሃን ዓሇም መውጣት ሲሆን ሇዚህም የተባበረ ክንዴና ኃይሌ ያሻሌና።

29
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከዚያም በተባበረ ኃይሊችን የራሳችንን ገነት ሇመፍጠር «ሀ» ብሇን እንጀምራሇን።
በቆራጥነት እንራመዲሇን። በምንፈጥረው ገንት እኛ አሁን ያሇነዎች ሰዎች ገብተን ሌንንቧችበት
መጓጓት የሇብንም። ሇዚህ ብንታዯሌ ኑሮ አባቶቻችን እኛ ያገኘነውን ዕዴሌና ዴሌ ያገኙሌን
ነበር። እኛ ሇዚህ አሌተመዯብንም አምሊክ እኛም የመዯበን «እኔ ከሞትሁ ሰርድ አይብቀሌ»
ያሇቺውን የአሕዮች ፈሊስፋ ትምህርትና «ከራስ በሊይ ነፋስ» የሚሇውን የበሰበሰ ምሳላ አነጋገር
ከወዯቀው የኑሮ ሥርዓታችን ጋር ዯምስሰን «እያንዲንደ ትውሌዴ ዓሇምን እሱ በተረከበት ጊዜ
ከነበረችበት ሁኔታ እጅግ የተሻሇች አዴርጎ ሇተተኪው ትውሌዴ የማስረከብ ኃሊፊነት አሇበት።»
የሚሇውንና ብዙ ፈሊስፎች የተስማሙበትን ቁም ነገር ፈጽመን አንዴ የተሻሻሇች አገር
ሇትውሌዲችን ሇማስረከብ ነው።

ከዚህ ሊይ በታሊቅ ምሳላነቱ የማንኛውም አገር ሰው የሚጠቅሰውን የአንዴ የዓረብ


ሽማግላ ታሪክ ሌጠቅሰው እፈሌጋሇሁ። ታሪኩም የሚከተሇው ነው።

ዘጠና ዓመት ዕዴሜ የነበረው አንዴ ዓረባዊ ሽማግላ በጓሮው የተምር ዛፍ ችግኞች
በትጋት ይተክሊሌ። አንዴ መንገዯኛ ይህን ሥራ ሲያይ በነገሩ ይዯነቅና መንገደን አቋርጦ ወዯ
ሠራተኛው ሽማግላ ሔድ «በዚህ የርጅና ዘመንህ በማረፍ ፈንታ እነዚህን የተምር ችግኞች
በመትከሌ የምትዯክመው መቼ ዯርሰውሌህ ሌትጠቀምባቸው ነው?» ይሇዋሌ።

ሽማግላውም በመንገዯኛው ሰውዬ ሞኝነት ስቆ «እኔ ስበሊው የኖርሁት ተምር እኔ


ሳሌሆን አያት ቅዴም አያቶቼ የተከለትን ነው። ከነሱ የወሰዴኩትን ዕዲም ሇሌጅ ሌጆቼ
መክፈሌ ስሊሇብኝ ሇነርሱ እተክሌሊቸዋሇሁ» ሲሌ መሇሰ ይባሊሌ።

ሽማግላው እንዲሇው ሁለ የሰው ጠቅሊሊ ሕይወት በማያቋርጥ ረጂም ገመዴ


የተቀጣጠሇ በመሆኑ አንዴ ትውሌዴ ሊሇፉት ትውሌድች ባሇ ዕዲ እንዯመሆኑ መጠን
ሇሚተካው ትውሌዴ አሳሳቢ የሆነ የውሇታ ዕዲ ትቶ የማሇፍ ግዳታ አሇበት። በተሇይም
እንዯኛ ቅዴመ አያቶች በሀገሩ ያገኘው ጥቅም ሇሀገሩ ካፈሰሰው ሊብና ዯም በምንም
የማይመጣጠን የሆነ ብዙ ሕዝብ ስሇላሇ ያባቶቻችን ባሇዕዲዎች ነን።

በዚህ ካሊመንና «እኔ ዕሇተ - ምፅዓት እኔ የምሞትበት ዕሇት ነው» አሇ በሚባሇው


ራሱን ብቻ ወዲጅ ሰው እምነት ከተጓዝን ምስኪን ኢትዮጵያ የዴኩማን የሇማኞች የረኃብተኞች
የዯንቆሮዎች በላሊም በኩሌ የጨቋኞች የዘራፊዎች የቀማኞች የወንጀሇኞች አገር እንዯሆነች
ትቆያሇች። እንዯዚያው ሁነው እንዱኖሩ የምንፈርዴባቸውም ከራሳችን በሊይ እንወዲቸዋሇን
የምንሊቸው የያንዲንዲችን ሌጆችና የሌጅ ሌጆች ይሆናለ። ሇየራሳችን ሌጆች ዯኅንነት ብቻ
እንጥራሇን ብሇን ራሳችንን ብናሞኝ ዯግሞ የአንዴ አገር ሕዝብ በአንዴ ሊይ እንዱሻሻሌ
ካሌተዯረገ በሏያኛው መቶ ክፍሇ ዘመን ብዙዎቹን በአዘቅት ውስጥ ጥሇው ራሳቸው ብቻ
በምቾት መፈንጨት ሇሚፈሌጉ ጥቂት ጮላዎች ምንም ቦታ የላሊቸው መሆኑን መዘንጋት
ይሆንብናሌ። ሇዚህም ምሳላ፦ ወዯሩቅ ቦታ ወዯ ሩቅ ዘመን ሳንሔዴ በዓይናችን ያየናቸው
ሇሠሊሣ ሶስት ዓመታት ሀገራቸውን በጉዴ አዘቅት ውስጥ ጥሇው ኑረው በመጨረሻው
በራሳቸው ሥራ በጉዴ አዘቅት ውስጥ የወዯቁት የኛን የዴሮ ገዥዎች ማስታወስ ይበቃሌ።

30
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንግዱህ የነገሩ ሁለ ውጤት እንዱህ መሆኑ ከታወቀ ዘንዴ የየግሌ ምኞታችንንና
ፍሊጎታችንን ከሀገራችን ጠቅሊሊና ዘሊቂ ጥቅም ሳናስቀዴም መሥራት ብቻ ሰሊም ብሌጽግና
ፍቅርና የኑሮ ዋስትና የሚሰጠን ኃይሌ ነው ማሇት ነው።

ወዯ ግባችን የምንጓዝባቸው መንገድች።


ወዯ ምንፈሌገው ግብ ሇመዴረስ የሚረደን ብዙ የሥራ ዘርፎች አለ። ሁኖም በቅዴሚያ
የሚያስፈሌጉን ስሊለ የቀሩትንም ዯረጃ በዯረጃ የሚመጡ ስሇሆኑ በሥራ ቅዯም ተከተሌ በኩሌ
ብርቱ ጥንቃቄ ሌናዯግ ይገባሌ።

በዚህ ሁኔታ የአገራችንን የኢኮኖሚ ዕዴገት ሇማፋጠን የቱን የሥራ ዘርፍ


ሌናተኩርበትና የሚበሌጠውን ገንዘብ ሌናውሌበት ይገባሌ? ብሇን ስንጠይቅ ቀዯም ብዬ
እንዯገሇጽሁትና ብዙ ሰዎችም እንዯተናገሩት እርሻ ያሇጥርጥር ተቀዲሚውን ቦታ ይዞ ይገኛሌ።

ይህ ይሆነባቸው ምክንያቶችም የሚከተለት ናቸ።

፩ኛ/ ሀገራችን ሇርሻና ሇርቢ ሥራ ምቹ የሆነ በጣም ብዙ ቦታ አሊት።

፪ኛ/ በተሇያዩ የዓሇም ክፍልች ከሚገኙ የእህሌና የየዕሇቱ ምግብ እጅግ አስፈሊጊ ከሆኑት
የእህሌና የአትክሌት ዓይነቶች ብዙዎቹ በተሇያዩ የሀገራችን ክፍልች ሉበቅለና ሉዲብሩ
ይችሊለ።

፫ኛ/ በወጉ ይዘን ከሠራንበት የከብት እርባታ ሥራችን በዓሇም ውስጥ በሥጋና በወተት
ከታወቁት ጥቂት አገሮች ኢትዮጵያ አንዶ እንዴትሆን ሉያዯርጋት ይችሊሌ።

፬ኛ/ የንብ እርባታ በየትኛውም የሀገራችን ክፍሌ ሉስፋፋ የሚችሌ ሥራ ነው።

ከዚህ በኋሊ እነዚህን ሥራዎች በዘመናዊ መሌክ አዯራጅተን ብናራምዲቸው ምን ያህሌ


ተፈሊጊነት እንዯሚኖራቸው ይህ የሚሆንባቸውን ምክንያቶች እንመሌከት።

፩ኛ/ የዓሇም ሕዝብ ቍጥር በየቀኑ እየጨመረ ሲሔዴ የዓሇም የርሻ ውጤት እኩሌ
እየጨመረ ባሇመሔደ የምግብ እጥረት የአህኑንና የወዯፊቱን የዓሇም ሕዝብ እጅግ
ከሚያሠጉት ታሊሊቅ ችግሮች አንደ መሆኑ በየጊዜው ተነግሯሌ።

፪ኛ/ በብዙ አገሮች ሆዴን ሇመሙሊት ያህሌ የሚበቃ ምግብ ቢገኝም ሇሰው የተሟሊ
ጤንነት በየቀኑ የሚያስፈሌጉ የተሇያዩ የምግብ ዓይነቶችን ማግኘት ችግር እየሆነ በመሔዴ ሊይ
ነው።

፫ኛ/ የገሇሌተኛነታችንን አቋም በማያጠራጥር መንገዴ በሥራ ሊይ አውሇን ብሔራዊ


መብታችንን በማይነካ ወዲጅነት ከተቀራረብን ብዙ የርሻ ሥራ ውጤታችንን ጉረቤቶቻችን ሇሆኑ
የመካከሇኛው ምሥራቅ አገሮች ሌናቅርብ እንችሊሇን።

31
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
፬ኛ/ ከዚህ ሁለ በሊይ ዯግሞ ራሳችንን እየዯጋገመ ካጠቃንና ከመጀመሪያው ክፉ ጠሊት
ከረኅብ ነፃ በመውጣት የመጀመሪያውን ብሔራዊ የኢኮኖሚ ዴሌ እንቀዲጃሇን።

፭ኛ/ የግብርና ሥራ እጅግ አስፈሊጊ የሆኑ የራሱ ሉቃውንት ቢኖሩትም አብዛኛው ክፍለ
ፊዯሌ ባሌቇጠሩ ሰዎች ሉከናወን ስሇሚችሌ ላሊው ጤነኛ ሥራ ፈት ቀርቶ የዯከሙ አካሇ
ስንኩሊንና በዕዴሜያቸው የገፉ አረጋውያንና አረጋውያት ሉካፈለበት ይችሊለ።

፮ኛ/ የርሻ ሥራ በዓመት ብቻ ሳይሆን በወራት ውስጥ ውጤቱን ስሇሚያበረክት


ከማንኛውም ሥራ ይሌቅ ፈጥኖ ዯራሽ ነው።

እንግዱህ ሀገራችን የርሻ ውጤቷን

ሀ/ በብዛት

ሇ/ በጥራት

ሏ/ በዓይነት አሻሽሊ ብታቀርብ በሀገሯ ረኅብን በማጥፍት ሳትወሰን ከፍተኛ የሆነ


የውጭ ገንዘብ ሌታገኝበት መቻሎ አያጠራጥርም ማሇት ነው።

እርግጥ ነው እንዯማንኛውም የገበያ ሁኔታ ሁለ አንዲንዴ ዓይነት የርሻ ውጤቶች


ገበያም

በየጊዜው የሚሇዋወጥ ነው። ስሇዚህ ጉዲዩ የሚመሇከታቸው የመንግሥት ዴርጅቶችና


የነጋዳዎች ምክር ቤት የዓሇምን የገበያ ሁኔታ እያጠኑ በየጊዜው ሇገበሬዎች ምክርና መግሇጫ
በመስጠት የሀገራችን የግብርና ሥራ እንዯ ጊዜ ሁኔታ እየተራመዯ በዓሇም ገበያ የተሟሊ
ተወዲዲሪነት እንዱኖረው ሇማስዯረግ መጣጣር ያስፈሌጋቸዋሌ።

በዚህ መንገዴ ሕዝብና መንግሥት ሇርሻ ተቀዲሚነት ሰጥተው ከተራመደ ሀገሪቱ በርሻ
ሥራ ውጤት ብቻ ገቢ ሌታገኝ ትችሊሇች ማሇት ነው። ገንዘብ ከተገኘ ዯግሞ ብዙ ነገር
ማግኘት ይቻሊሌ።

ሀ/ ትምህርት ቤቶችን ክሉኒኮችን ሆስፒታልችን መንገድችን ዴሌዴዮችን በሰፊው


እንሠራሇን።

ሇ/ ሌጆቻችንን በሙለ ወዯ ትምህርት ቤቶች ሇመሊክ እንችሊሇን።

ሏ/ ወንዞቻችንን እየገዯብን ይህ በማይቻሌበት አካባቢዎች ጉዴጓድችን እየቆፈርን ሰው


ሰራሽ ሏይቆችን እየሠራን ሇሚፈሇጉበት ጥቅም ሁለ እናውሊቸዋሇን።

መ/ በምዴራችን ውስጥ ተቀብረው የኖሩ የማዕዴን ሀብቶችን ህለ በሀብታችንና


በዕውቀታችን ከምዴር በሊይ እያዋሌን ሌጠንቀምባቸው እንችሊሇን።

ሠ/ ቀሊሌና ከባዴ እንደስትሪዎችን እናስፋፋሇን።


32
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እነዚህ ተግባሮች መፈጸም በኋሊ ኢትዮጵያ ሠሇጥኑ ከሚባለት አገሮች ጎን ትሠሇፍና
የወዯፊት

ሩጫዋን ትቀጥሊሇች። የሕዝቧ አኗኗር መሌክ በፍጹም ይሇወጣሌ። ጥሩ ቤት ጥሩ መኪና


ሌጅን ወዯ ሚያስፈሌገው ትምህርት ቤት መሊክ ቢታመሙ ወዯ ጥሩ ሆስፒታሌ ገብቶ
መታከም በቤት ውስት ወሀ መብራት ማስገባት የሬዱዮ የቴላቪዢን የሇስሊሳ የአሌጋና ወንበር
የማቀዝቀዣ የስሌክ አሇፍም ሲሌ የግሌ መኪና ባሇቤት መሆን በዘርና በሥሌጣን ሇተመረጡ
ወይም ሇከተማ ኗሪዎች ብቻ የተሇዩ ጸጋዎች መሆናቸው በፍጹም ይረሳሌ። በገጠር ይኑሩ
በከተማ ሹም ይሁኑ መንገዴ ጠራጊ በትጋትና በቅንነት የሚሠሩ ሰዎች የሊባቸውን ዋጋ እያገኙ
የተቀራረበና የተመጣጠነ ኑሮ ይኖራለ።

ሥራ የተባሇ ሁለ በየመሌኩ ታሊቅ ክብር ይኖረዋሌ። የርሻ ሥራ አሁን ካሇው መሌክ


በፍጹም ይሇወጣሌ።

፩ኛ/ አንዴ ሰው የርሻን ሥራ ዓይነቶች በሙለ ራሱ ብቻ ሌሥራ ማሇቱን የሚረሳበት


ቀን ይመጣሌ።

ሀ/ አንዴ ገበሬ ራሱ እህሌ አብቃይ ከብት በግ ፍየሌ ድሮና ንብ አርቢ መሆኑ ይቀርና
አንደን ዓይነት ሥራ በሚገባ ያስፋፋሌ። ላሊው ቀርቶ በከብት ርቢ ሥራ ውስጥ
የወተት ከብቶችንና የሥጋ ከብቶችን የሚያረቡ ገበሬዎች የተሇያዩ ይሆናለ።

ሇ/ እንዯ ማንኛውም የሠሇጠነ ሕዝብ ሁለ በየመንገደ ጥግ በቂ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ


መዯብሮች ስሇሚኖሩና እያንዲንደ ሰው የሚፈሌገውን ወተት ቅቤ ሥጋና ላሊም የምግብ
ዓይነት ስሇሚያገኝ ሁለን ከቤተ ሊግኝ ብል ጉሇብቱንና ሏሳቡን በተሇያየ አቅጣጫ
ያበክን የነበረበትን ሌማዴ ትቶ አንደን ዓይነት ሥራ በዘመናዊ መሌክ እያሻሻሇ
ይሠራሌ።

ይኸም ሲሇመዴ አንዴ ገበሬ አባት ራሱ ወዯ እርሻ ሥራ ሲሔዴ ሌጆቹ - ሴቶች


ሕፃናት ሳይቀሩ

ሕፃናት ሳይቀሩ ጥቂት ወይም አያላ የከሱ እንስሳትን እየተከተለ ሲዞሩ መዋሊቸው ቀርቶ ወዯ
ትምህርት ቤቶች ይሔዲለ።

መ/ እያንዲንደ ገበሬ ሥራውን ሇይቶ ይዞ በዘመናዊ ዘዳ ሲሠራ የዴካሙ ፍሬ የእጥፍ


እጥፍ እየሆነ ይሔዲሌ። ሇምሳላ በዯንብ ያሌተጠበቁና ያሌተሻሻለ አንዴ መንጋ ከብቶች
እያንጋጋ ሉገኝ ከሚችሇው የወተትና የሥጋ ውጤቶች ይሌቅ በሚገባ ተመርጠውና
ተዲቅሇው በሚገባ ተጠብቀው ከሚገኙ ጥቂት ከብቶች እጅግ የበዛ ጥቅም ሉገኝ
ይችሊሌ።

፪ኛ/ ሰዎች «ሇሇት ጉርሳቸው ሇዓመት ሌብሳቸው» ጭረው በተወሇደበት መንዯር


መኖርን እንዯታሊቅ ነገር ማየታቸው ይረሳሌ።
33
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሀ/ ሰዎች ሁለ በተሇያየ ሙያ እየሠሇጠኑ በመሊው የሀገራቸው ክፍልች በመዘዋወር
ስሇሚሠሩ ያንዴ አባት ውሇታ በዴንበር ግፊያ በትውሌዴ መካካዴ በግዥ ሥነ ሥርዓት
አሇመሟሊት በግብረ ጠሌነትና እነዚህን በመሳሰለ ምክንያቶች ከከፍተኛ የሙግት የዯጀ -
ጠኝነት በሽታዎች ጋር የተያያዘ ትንሽ የመሬት ቁራሽ ማውረስ መሆኑ ይቅርና ሰፊዋን
ርስቱን ኢትዮጵያን የተሻሇች አገር አዴርጎ ማስረከብ ይሆናሌ።

ሇ/ በየአቅጣችዎቹ ታሊሊቅ አውራ ጏዲናዎች ሲከፈቱ የመመሇሻ ዴርጅቶች በጣም


ሲሻሻለና ሲስፋፉ አሁን የተራራቁ መስሇው የሚታዩት ክፍሇ ሀገሮች እጅግ
ይቀራረባለ። በየክፍለ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ጨርሰው መተዋወቅ ብቻ ሳይሆን
ፈጽመው ተቀሊቅሇው የጎሳ ስሜትን የክፍሇ ሀገር ሌዩነትን ይረሳለ። ከዚያ በኋሊ
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዯ ማንኛውም የሠሇጠነ ሕዝብ ሁለ ምኞቱና ዓሊማው ከገዯብ
በሊይ ይሆናሌ። የተፈጥሮ ኃይልችን ምሥጢር በዴፍረት እየተጋፋ አካባቢውን የሰው
ሌጆችን ኑሮ ያሇማቋረጥ ሇማሻሻሌ ይታገሊሌ።

ሇዕዴገታችን የሚዯረገው ትግሌ ከሚጀምርበት ጊዜ አንሥቶ የአካቢ ዓየር ወንዞች


ምንጮችና

ሏይቆች በቁሻሻና በጢስ በላሊም ነገሮች እንዲይበከለ የተራቆቱ ክፍሇ ሀገሮች ወዯ ሇምሇምነት
እንዱመሇሱ ተገቢ ትግሌ ይዯረጋሌ።

የተፈጥሮ ኃይልችን ጨርሶ መቆጣጠር ባይቻሌም በጣም በሠሇጠኑ ነገሮች ላሊ ቀርቶ


በረድ ወርድ በሰብሌ ሊይ ጥፋት ከማዴረሱ በፊት በዓየር ሊይ ሟሙቶ እንዱቀር በዴርቅ ጊዜ
ዯመና ተሰብስቦ ዝናም እንዱቀጥሌ ሇማዴረግ በዘመናዊ የሳይንስ ምርምር የተዯገፈ ብዙ ጥረት
እየተከናወነ ጠቃሚ ውጤት በመስጠት ሊይ ነው።

በአሁኑ ጊዜ የሰው ሌጅ እጅግ ተራቋሌ። በዚያው ሌክ ኑሮው እጅግ ተሻሽሎሌ። እኛን


ኑሮ በጣም ከሠሇጠኑት ሕዝቦች ኑሮ ጋር ስናስተያየው በመጠኑ ተመቸው የምንሇው መካከሇኛ
ኢትዮጵያዊ የኑሮ ምቾት ያነሰ ሁኖ ሰሇሚገኝ ሇጥረታችን ሇኅብረታችንና ሇምኞታችን ገዯብ
ሌንሰጠው አይገባም።

ምንም የሕይወት መሻሻሌ እንዲይኖረን እጅ እግራችንን አሥረው የኖሩትን ዯካማ


ሌማድች ሁለ ጨርሰን መዯምሰስ አሇብን።

ከእንግዱህ ግባችን ባጭሩ ሲገሇጽ ይህ ከሆነ ዘንዴ ስሇየግሌ ቁራሽ ርስታችን የነበረንን -
ሙግት - የጭቅጭቅ የሏሳብ - የጠባብነት የዴኅነት ሥራን ያሇማሻሻሌ ሌማዴም በፍጹም
መሇወጥ አሇብን።

ይህንንም ስናዯርግ በቅርብ ጊዜ ኑሯችንን ማሻሻሌ ብቻ ሳይሆን ሇውጣችን ፍጹም


ሰሊማዊ ይሆናሌ። መንግሥት ማሇት ሕዝብ መሬት ማሇትም የማይሸጥ የማይሇወጥ የአንዴ
አገር ሕዝብ መንግሥት ሇመሊው ሕዝብ ዯኅንነት በሚያውሌበት መንገዴ ሁለ በቀጥታ

34
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የሚያዝበትና የሚጠብቀው እስከ ኅሌፈተ ዓሇም በመከታተሌ የሚመጡ ትውሌድች ቋሚ ሀብት
መሆኑን ማንም ይረዲዋሌ።

ቀዯም ሲሌ እንዯገሇጽሁትም መንግሥት ከአሁን ጀምሮ ስሇ መሬት ይዞታ ወዯ


ምንፈሌገው ግብ በሰሊማዊ መንገዴ የሚዯርሱንን ዋና ዋና ተግባሮች በቀጥታ በሥራ ሊይ
ማዋሌ አሇበት።

፩ኛ/ በዯቡባዊ ኢትዮጵያ ታሊሊቅ መሬት ዘራፊዎች በሥሌጣን በጉሌበት እየተመኩ


በላሊም ዘዳ እያጭበረበሩ የያዙትን ሰፋፊ መሬት በቀጥታ ወርሶ በመንግሥት እጅ ካሇው ጋር
ማቀሊቀሌ

፪ኛ/ በግሌ ባሇ መሬቶች ሊይ ሰፍረው የሚገኙ ጢሰኞችን እያስነሡ በመንግሥቱ መሬት


ሊይ ማስፈር

፫ኛ/ ስሇ መሬት ግብር የነበርው ሇምሇም - ከጠፍ የሚባሌ ነገር ሳይኖር አንዴ ሰው
የመሬት ይዞታው ከፍ ባሇ መጠን እያዯገ የሚሔዴ ከባዴ ግብር እንዱከፍሌና ሉጠቀምበት
አሇመቻለን እየተረዲ በፈቃደ እንዱሇቅ ማዴረግ

፬ኛ/ መንግሥት መሬትን ሇገበሬዎች መሥራት በሚችለት መጠን የሚሰጠው በግሌ


ርስትነት ሳይሆን በኮንትራት ሁኖ የግሌ ባሇ መሬቶችም እንዲይሸጡ እንዲይሇወጡ በአዋጅ
ማገዴ

፭ኛ/ በሰሜናዊው ክፍሌ መንግሥት ሇጠቅሊሊው ሕዝብ ዕዴገት የሚፈሌገው ማንኛውም


መሬት በሊዩና በውስጡ ካሇው ነገር ሁለ ጋር መንግሥት በቀጥታ የሚያዝበት መሆኑን
እንዱያውቅ ማዴረግ

፮ኛ/ በማንኛውም ከተማ የሚገኝ ቦዘን መሬት ሁለ የችርቻሮ ዕቃ መሆኑ ቀርቶ


በየማዘጋጃ ቤቶች ቁጥጥር ሥር ሁኖ ሇሚያስፈሌጉ የሕዝብና የመንግሥት አገሌግልቶች
እንዱውሌ ማዴረግ እጅግ አስፈሊጊ ነው።

ጉዲዩ የሚመሇከተው ሕዝብም ሇውጡ የራሱ ሇውጥ በውጤቱ የሚገኘው ጥቅምም


ጥቅም መሆኑን ተገንዝቦ በሙለ ሌቡ እንዯ ሚተባበር ሙለ እምነት አሇኝ።]

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ሇግለ የዕሇት ትንሽ ጥቅም ሲሌ ራሱ ጨምሮ


የሚጠቅምበትን ከፍተኛ ብሔራዊ ጥቅም ይቃወማሌ ብዬ አሌጠራጠርም።

ሀገራችን እጅግ የምታሳዝን ምስኪን እናታችን ናት። ሁሊችንም በያሇንበት እሷን ሇማዲን
እንሰሇፍ። ያሇዚያ ሁሊችንም የምናሳዝን የሙት ሌጆች እንዯሆንን እንኖራሇን። ሇሌጆቻችን
የምናወርሳቸው ሀብትም የሚያኮራ ርስት ሳይሆን ችግር በሽታ ዴንቁርና ውርዯትና ኃፍረት
ብቻ ይሆናሌ። ሇሁሊችን ዯኅንነት የመጣሌንን ሇውጥ እንዯ ጠሊት ዏይተን የዓሇም ሕዝብ
መዘባበቻ እንዲንሆን ችግራችንን ዴሌ ሇማዴረግ እንተባበር።

35
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መዴረሻ
በ፷፭ ዓ/ም ከታተመው «ሬትና ማር» ከሚሇው የግጥም መጽሏፌ የወሰዴሁት።

ምንም ሕሌም አይዯሇም።

ዴንገት ጋዯም ስሌ በዯከምው ጏኔ

ሲዞር ይታየኛሌ ታሊቅ ነበር ባይኔ።

ያ አጉሌ ዘር ከፋፋይ ጉረኛው ፈሊስፋ

በወንዴሞች መሏሌ መርዝ እንዲያስፋፋ

ታርሞ ተነቅል ከሀገር ሲጠፋ

ያገር ዕዴገት ጠሊት የዕዴሌ አሳዲጅ

ጥቅምን ሁለ ሉያንቅ እንዱያ ሲጏመጅ

በግራ በቅኙ እየዘረጋ እጅ

ላሊውን ሁለ ገዴል ሇራሱ እሚያበጅ

የጥቅሙ ተካፋይ ሳይሆን አማሊጅ

በወንጀሌ ተከቦ ፈርድበት ፈራጅ

ሲማቅቅ ሲከርም ሲማቅቅ ሲባጅ

ሲባሌ የሕብ ጠሊት የሰይጣን ወሊጅ

በላሊ እንኳ ሳይሆን በሥሌጣን ሰበብ

የሣንቲሟን ግማሽ የቀማ ከሕዝብ

እንዯ ሠረቀ ሰው የመንግሥት ገንዘብ

በሰንሰሇት ታሥሮ ታጅቦ በዘብ

ቅጣቱን ሉቀበሌ ፍርዴ ቤት ሲቀርብ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሌብ ተቀራርቦ

ባንዴ ቃሌ ተናግሮ ባንዴ ሌብ አስቦ

የጠሊቶቹን አፍ ዘግቶና ሸብቦ

36
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አብሮ የዘራውን ባንዴ አብሮ ሰብስቦ

ሳይኖር ራብተኛ ሁለም እህሌ ጠግቦ

በኢትዮጵያ ወገብ እንዯመቀነት

የተጠመጠመው ሇምሇሙ መሬት

ከወባ ተሊቆ ህዝቡ ሰፍሮእብት

ባሇም ታይቶ እማያውቅ የሰሉጥ ብዛት

የጫኝ ያሇህ የሚሌ ጉዴ የጥጥ ጭነት

የጤፍ የበቆልው የስንዳውም ምርት

ተትረፍርፎ ሲቀር ካመት እስካመት

እንዯ ተነበዩት ቀዴመው ሉቃውንት

አገራችን ሁና የዲቦ ቅርጫት

ሇሩቅ ወዲጅና ሇቅርብ ጏረቤት

እስከቻሇን ዴረስ ሁለም ሰው ተምሮ

ማብራሪያ ተሰጥቶት በዏዋቆች ተመክሮ

ራሱም አስቦ ሁለን ተመራምሮ

ሙግት ጭቅጭቅን ወዱያ ጥል አንቅሮ

እግዜር እንዲዘዘው አንደ አንደን አፍቅሮ

ራሱም እንዲየው በሇመዯው ኑሮ

ባንዴ አብሮ እርሻን አርሶ ባንዴ አብሮ መንጥሮ

ባንዴ አብሮ አጨዲ አጭድ ባንዴ አብሮ ከምሮ

አንደ ሲዲር አንደ ዘፍኖ አንደ ሲሞት ቀብሮ

ስኖር በዯስታ ከብሮ ተከባብሮ

ሁለም ወገናችን ምሥጢሩ ገብቶት

ሇመዯሩ አሠራር ቅጥ መጠን ሰጥቶት


37
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የጋራ መሬቱን ያባቱን ርስት

ዯረቁን ሇመንዴር ሜዲውን ሇከብት

ሇምሇሙን ሇእህለ ጓሮውን ሊትክሌት

ከፋፍል መዴቦ ሠርቶ ባንዴነት

የመንግሥት እርዲታ በቀሊሌ ዯርሶት

ታማሚው መዴኃኒት ሕፃኑ ትምህርት

ሳይወጣ ሳይወርዴ ሲያገኝ በወቅት

ተምሮም ሲሠራ ሠርቶ ሲያገኝ ሀብት

ሲረሣ ግሙ ዕዴሌ መሆን ሥራ - ፈት

በዏራቱ ማዕዘን በሇምሇሙ ሜዲ

የወዲዯሇ ከብት ብዙው ቀንድ - ጏዲ

ግማሹ ሇወተት ላሊው ሇፍሪዲ

ከዚህ ሊይ ፍየሎ ከዚያ በጓ ወሌዲ

የታከመው መንጋ ጤናው ያሌተጎዲ

ጠግቦ እየፈነጨ ወዯቤት ሲንነዲ

የንደስትሪውና የርሻው ውጤት አብሮ

በከባዴ መኪና በባቡር ተሳፍሮ

በዓሇም ሁሉ ሉናኝ ሲጫን በመርከብ

ብዙ ሇውጥ ሉያመጣ ወይንም ገንዘብ

ታሊሊቁ ወንዞች ዓባይ አዋሽ ባሮ

ተከዜ ነዋ ዋቢ? ምኑስ ምን ተቇጥሮ!

ሇሏበሾች ጥቅም ኃይለ ተወስኖ

ግማሹ ሇጉሌበት ግማሹ ሇመብራት ላሊውም ሇመስኖ

ይውሌና ሁለ በየመሌኩ ሁኖ
38
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ብርሃን ብቻ ሁኖ ገጠሩ ከተማው

በሁለም ቀን ሲሆን ተገፎ ጨሇማው

በጭራሽ ሲረሳ ኩራዙና ሻምው

ናፍጣ ችርቻሮ ሥራ መሆን ሲቀር

በከተማ ኪዎስክ እንዱሁም በመንዯር

በዚያም በዚህም በኩሌ ሲያንጏራራ ፋብሪካ

መሬትን ሉያስወሌዴ ቆፋሪው መኪና ዘቅዝቆ ሲያሽካካ

ጏበዙ ሠሪ ሕዝብ ባገሩ በሥራው በኑሮው የረካ

«ወዮሇት! ጠሊት እርሷን ሇሚነካ!

ታሊቋ ኢትዮጵያ ሇዘሇዓሇም ትኑር!» እያሇ ሲያወካ

ይኸ ብቻ አይዯሇም ከዚህ የሚበዛ ይኸን የመሰሇ

ዞትር እየመጣ ባኔ ሊይ ተሳሇ።

ይህ አጉሌ ሕሌም ይሆን የምኞት ቅጀት

ዓሇም እስከምታሌፍ የማንዯርስበት?

ወይስ የሚቻሌ ነው የፈጠጠ እውነት?

የሚያዯክም ምክር የባዕዲን ትንቢት

ሳይኖረን ሳይገባን ሏኬት

አብረን በማስወገ ያሇብንን ችግር

ሁሊችን ከሠራን ባንዴ ሌብ ሊንዴ አገር

ምኑም ሕሌም አይሆንም ከዚህ ሁለ ነገር።

የምዕራብም ሰዎች ይኸነን ከሠሩ

የምሥራቅም ሰዎች ይኸነን ከሠሩ

በኛስ አገር ቢሆን ምንዴን ነው ችግሩ

ሕዝቡ ተባባሪ ባሇጸጋ ምዴሩ።


39
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ኢትዮጵያ ትቅዯም

በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ታተመ።

40
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss

You might also like