II

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

I. አጠቃላይ መግለጫ
የመሥሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
ጤና ጥበቃ ሚ/ር የጤና አገልግሎት ጥራት ማጠናከር የጤና አገልግሎት ጥራት
ባለሙያ II
የቅርብ ኃላፊ የሥራ በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር/ቢሮ ብቻ የሚሞላ
መደብ /ተጠሪነት
የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ
ለቡድን መሪ

መሥሪያ ቤቱ የሚገኝበት
ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 ሥራው ለስልጠና ማኑዋል ዝግጅት አስፈላጊ መረጃዎችን በማደራጀት፣ ጥናታዊ መረጃዎችን
በመተንተን ፣የአድቮኬሲ ተግባራትን በማከናወን፣ ጥራት ያለው የሜዲካል
አገልግለትእንዲሰጥ ማድረግ፤

ውጤት 1፡ የስልጠና ማንዋልና የተለያዩ ሰነዶች ዝግጅት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማደራጀት፣ መለስተኛ
ትንተና ማካሄድ፤
 የሚዘጋጁ ማሰልጠኛ ሰነዶች ለማዘጋጀት የሚያግዙ መረጃዎችን ያደራጃል፣
 ለሚደረጉ ጥናቶች አስፈላጊ መረጃዎችን ያደራጃል፣ መለስተኛ ትንተና ያካሂዳል፣
 መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች ጋር ለሚሠሩ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ
አጋሮችን ለመለየት መረጃ ያሰባስባል፣ያደራጃል፣
 የስራ ክፍሉን አሠራር ሊያሻሻል የሚችል አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፣
 በሚዘጋጁ ሥልጠናዎች ላይ ተሳታፊዎችን በመለየት ለስልጠና የሚያስፈልጉ ግብአቶች
እንዲሟሉ ያደርጋል፣
 እቅድና የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያዘጋጃል፣
ውጤት 2፡ በእናቶችና ህፃናት ጤና ዙሪያ የሚሰጡ ስለጠናዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች
ማስተባበር እና ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
 በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፍ የጤና አጠባበቅ ትምህርቶችን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣
 በየግንዛቤደረጃውለሕብረሰቡየአድቮኬሲ፣ የግንዛቤማስጨበጫናየማሕበረሰብንቅናቄስራይሰራል፡፡
 የሚዘጋጁ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችንና የስልጠና ማንዋሎች በተደራሲያን ቅድመ ሙከራ እንዲካሄድ
ያደርጋል፣ የታተሙ ማንዋሎችና ጋይድ ላይኖች ላይ ስልጠና ይሰጣል፣
 የሚሰጡ ስለጠናዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች እንዲሟሉ
ይከታተላል፤
 የሚዘጋጁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዶች እና ማንዋሎች ህትመትና ስርጭት ይከታተላል፤
 በሃገርም ሆነ በውጭ ሃገር የተሳተፈባቸው የልምድ ልውውጥናና ኮንፍራንስ ሪፖርት
አዘጋጅቶ ያገኘውን እውቀትና ክህሎት ያስተላፋል፤
 በየደረጃው ላሉ የጤና ተቋማት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
 ወቅታዊ የስራ እቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፣
III. የሥራው ባህርይ መግለጫዎች
3.1. የሥራ ውስብስብነት
 ስራው ለሚደረጉ ጥናቶችና ለእቅድና ለመመሪያ ዝግጅት የሚውሉ መረጃዎችን የማደራጀትና
የዳሰሳ ጥናት ማድረግ፣ ማንዋሎችና ጋይድ ላይኖች ላይ ስልጠና መስጠት የአድቮኬሲና የግንዛቤ
ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወን ሲሆን
 እነዚህን ተግባራት ሲያከናውን የሚያጋጥሙ ችግሮች ለትንተና የተሰበሰቡና የተደራጅ መረጃወች
የጥራት ደረጃውን ያልጠበቀ መሆን፣የህብረተሰቡ የግንዛቤ ችግር፣ መመሪያዎችና ማንዋሎችን
ተግባራዊ አለማድረግ ናቸው፡፡
 እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተሻለ የመረጃ ማሰባሰቢያ ስልቶችን በመቀየስ፣ ተከታታይ
የአድቮኬሲ ወይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት በማከናወን፣በማማከር፣በውይይትና ከአሁን
ቀደም ይጠቀሙበት የነበረውን የስራ ቅደም ተከተል በመከተል ችግር መፍታትን ይጠይቃል ፡፡
3.2. ራስንችሎመሥራት
3.2.1. ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው ከቅርብ ኃላፊ በሚሰጥ የአፈፃፀም መመሪያና የሜዲካል አገልግሎትንለማስፈፀም የወጡ
መመሪያና ደንቦችን መሠረት በማድረግ የሚከናወን ነው፡፡
3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 ሥራው በተሰጠው መመሪያ መሰረት በአግባቡ ስለመከናወኑ በኃላፊው ክትትልና ድጋፍ
ይደረግበታል፡፡
3.3. ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /
 ስራው ለሚደረጉ ጥናቶችና ለእቅድና ለመመሪያ ዝግጅት የሚውሉ መረጃዎችን የማደራጀትና
የዳሰሳ ጥናት ማድረግ፣ ማንዋሎችና ጋይድ ላይኖች ላይ ስልጠና መስጠት፣ የአድቮኬሲና የግንዛቤ
ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወን ሲሆን እነዚህን ተግባራት በአግባቡ ባያከናውን የስራ ክፍሉ የስራ
አፈፃጸም ያስተጓጉላል፣ የህብረተሰቡ የአመለካከት ለውጥ አይመጣም ፣ የሚጠበቀው የሜዲካል
አገልግሎትላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
3.3.2. ተጠያቂነት ለምስጢራዊ መረጃ
 ስራው የሚሰበሰቡ መረጃዎች የሚመለከተው አካል በይፋ መግለጫ ከመሰጠቱ በፊት በሚስጢር
የመያዝ ሃላፊነት አለበት፡፡ በሚስጢር መያዝ ያለበት መረጃ ለማይመለከታቸው አካላት ቢደርስ
በውስጥ ሰራተኞች መካከል ያለመግባባት ያሳድራል፣ ሕብረተሰቡም በመስሪያ ቤቱ ላይ እምነት
እንዲያጣ ያደርጋል፡፡
3.4. ፈጠራ
 በስራላይያሉማንዋሎችናየመረጃማሰባሰቢያቅፃቅፆችያለባቸውንችግሮችበመለየት ማሻሻልን፣ የተለያዩ
መረጃዎችን ለማደራጀትና ለመተንተን የሚያስችሉ የተሻለ የአሰራር ዘዴዎችና ሃሳቦችን
ማመንጨት ይጠይቃል፤
3.5. የሥራ ግንኙነት
3.5.1. የግንኙነቱ ደረጃ
 ሥራውበመ/ቤትውስጥከሥራክፍሉና ከሌሎች የሥራ ክፍል ባለሙያዎችና ኃላፊዎች፣ ከውጭ ጤና
ተቋማትና መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ባለሙያዎች ጋር
ግንኙነት ማድረግ ይጠይቃል፡፡
3.5.2. የግንኙነቱ ዓላማ/አስፈላጊነት
 የሥራ ትዕዛዝ ለመቀበል፤ ዕቅድና ሪፓርት ለማዘጋጀት፣ ሙያዊ ድጋፍ ለማግኘት፣ መረጃ
ለመስጠትና ለመቀበል ፣ በቅንጅት ለመስራት ግንኙነት ያደርጋል፡፡
3.5.3. የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ከመደበኛሥራው 40 የሥራ ግንኙነት ያደረጋል፡፡
3.6. ኃላፊነት
3.6.1. ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1. በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለበትም፡፡
3.6.1.2 .የኃላፊነት ዓይነትና ደረጃ
 የለበትም፡፡
3.6.2. ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም፡፡
3.6.3. ኃላፊነት ለንብረት
 ለቢሮ ሥራ የሚጠቀምበት ግምታቸው እስከ 40000 ብር የሚደርሱ እንደ ኮምፒውተር፣
ወንበሮች፣ ጠረጴዛ እና ኘሪንተር በጥንቃቄ የመያዝና የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ለእቅድ ለምርጥ ተሞክሮ፣ሰነድ ዝግጅት የሚውል መረጃ ለማሰባሰብና ለማደራጀት፣ የትምህርት
መርጃ መሣሪያዎች ዝግጅት በተመለከተ የቅድመ ሙከራ ለማድረግ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስልጠናዎች ለመስጠት እና የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ 40% የአዕምሮ ጥረት ይጠይቃል፡፡
3.7.2. ስነልቦናዊ ጥረት/Emotional effort/
 ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች መረጃ በማሰባሰብ ሂደት ከባለሙያዎች ትብብር ማነስና፣ መረጃው
በወቅቱና በተሟላ መልኩ ካለመገኘቱ ጋር በተያያዘ ሊፈጠሩ የሚችሉ ጭቅጭቆችና
አለመግባባቶችን ተቋቁሞ በትግሥትና በመረጋጋት መስራትን ይጠይቃል፣
3.7.3. የዕይታ ጥረት
 ሥራው መረጃዎች በኮምፒውተር ማደራጀትና መተንተን፣ የስልጠና እና የግንዛቤ ማስጨበጫ
መርሃ ግብሮች፣ እቅድና ሪፖርት ማዘጋጀትን የሚጠይቅ ሲሆን ከስራ ጊዜውም እስከ 25% የእይታ
ጥረት ይጠይቃል፡፡
3.7.4. የአካል ጥረት
 ሥራው 80% በመቀመጥ፣ 20% በመንቀሳቀስ ይከናወናል፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 የለውም

3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ


 ሥራው በምቹ የስራ አካባቢው የሚከወን ነው፡፡
3.9. እውቀትና ክህሎት፣
3.9.1. የትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
የመጀመሪያ/ሁለተና ዲግሪ ወይም በጤና
ሁለተኛ
3.9.2 ዲግሪ ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ
ሥራውን
የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
2/0 ዓመት
የሥራ ዝርዝሩን ያዘጋጀው ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን


የኃላፊው ሥም

You might also like