Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ጅማ፣ነሀሴ 28/2013(ኢዜአ)በቡኖ በደሌ ዞን በቦረቻ ወረዳ የለውዝ የጤፍና የቦቆሎ ሰብል በክላስተር ማልማት የተሻለ

የአመራረት ዘዴ መሆኑን የወረዳው አርሶ አደሮች ተናገሩ።

አርሶ አደሮቹ እንዳሉት የሚዘሩትን ሰብል በመነጋገር በተያያዘ መሬት ላይ መዝራታቸው ለጥበቃና ለእንክብካቤ አመቺ
ሆኖላቸዋል።

አርሶ አደር መሀመድ ሁሴን እንዳሉት የለውዝ ሰብልን አስርና ከዚያ በላይ ሆነን ስናለማ ተባዩ ይቀንሳል ለባለሞያ ቁጥጥር
ይመቻልና ጥሩ አመራረት ነው ብለዋል።

አርሶ አደሩ አክለውም ለውዝን በሄክታር ከሃያ አምስት እስከ ሰላሳ ኩምታል እንደሚያመርቱ ተናገረው የመንገድ ችግር
ስላለ በተገቢው ዋጋ መሸጥ አልቻልንም ብለዋል።

ሌላው አርሶአደር ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው በቆሎም ለውዝም በኩታ ገጠም እያለሙ በመሆኑ ከዚህ በፊት ከነበረው
ምርት የተሻለ እንደሚያመርቱ ተናገረዋል።

ጤፍን በመስመርና በኩታገጠም በማልማት ላይ የሚገኙት አርሶ አደር ጀበሉ ከድር በበኩላቸው በተያያዘ መሬት ላይ
ጤፍን መዝራት ለስራ ሞራል የሚሰጥና አሰደሳች ነው ብለዋል።

ከግብርና ባለሞያዎች ጋር በመተባበርና ምክር ተቀብሎ በመተግበር ማሳቸውን ውጤታማ ሊሆን በሚችል የጤፍ ሰብል
መሸፈናቸውን ነው የተናገሩት።

የወረዳው የግብርና ሰብል ልማት ባለሞያው ወርቁ ተስፋዬ አንዳሉት ሰብሎች በኩታ ገጠም ሲለሙ ተባብሮ ለመስራትና
ለመማማር እንዲሁም ሰብሉን ለመጠበቅ ትልቅ ሚና አለው።

የቦቆሎ የለውዝና የጤፍ ሰብሎችን በኩታ ገጠም የሚያመርቱት አርሶአደሮች ምርታቸውን በተሻለ ዋጋ መሸጥ ይችሉ
ዘንድ የመንገድ ችግሩ መቀረፍ አለበት ነው ያሉት ባለሞያው።

ሌላዋ የግብርና ባለሞያ ወይዘሪት አሚና ሀሰን በበኩላቸው የጤፍ የስንዴና የቦቆሎ ሰብልን በክላስተር የማልማት ፍላጎት
መኖሩን ገልጸው የዘር አቅርቦት እጥረትና እንዲሁም በጊዜው ያለመድረስ ችግር መኖሩን ገልጸዋል።

የቦረቻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሱልጣን ሲራጅ አንደ ገለጹት በወረዳው ከ 19 ሺ አራት መቶ ሄክታር ዘላይ መሬት በሰብል
ተሸፍኗል።

አስተዳዳሪው አክለውም ለኩታ ገጠም የሰብል እርሻ አመቺ በሆኑ መሬቶች ላይ ከሶስት ሺህ አራት በላይ የቦቆሎ
ክላስተር፣ 2 መቶ ዘጠና የጤፍ ክላስተርችና አርባ አንድ የለውዝ ክላስተሮች በወረዳው አርሶአደሮች እየለሙ መሆኑን
ተናግረዋል።

በተጨማሪም የስንዴ የአተር የባቄላና የማሽላ ሰብሎች እየለሙ እንደሆነ የገለጹት አቶ ሱልጣን አየለማ ካለው አጠቃላይ
ሰብል ከ 617 ሺ ኩምታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ይጠበቃል ብለዋል።

"የአካባቢያችንን ሰላም እየጠበቅንና ለሀገራዊ ጥሪዎች ምላሽ እየሰጠን ጎን ለጎን የግብርና ልማታችንን አንሰራለን"
ብለዋል አስተዳዳሪው።

የቡኖ በደሌ ዞን የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳዊት ጅፋር በበኩላቸው ከ 8 ሺ ስምንት መቶ በላይ
ክላስተሮች የጤፍ የለውዝና የቦቆሎን ጨምሮ በሰባት የሰብል አይነቶች መሸፈኑን ገልጸዋል።

እንደ አቶ ዳዊት ገለጻ በዞኑ ባጠቃላይ ከ 174 ሺ 4 መቶ በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን ገልጸው ከዚህም 5
ነጥብ ስምንት ኩንታል ምርት ይጠበቃል።
የቡኖ በደሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሻፊ ሁሴን በበኩላቸው የዞኑን ግብርና ለማዘመን የግብአት አቅርቦት ችግሮችን
በመፍታት በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆ ለኢዜአ ተናግረዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም በዞኑ ለግብርና የሚሆኑ ለም መሬቶች በሙሉ በሰብል እንዲሸፈኑ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን
ገልጸዋል።

You might also like