Professional Documents
Culture Documents
የካህሊል ጂብራን መሳጭ ንግግሮች
የካህሊል ጂብራን መሳጭ ንግግሮች
📖📖📖
📜 ጭንቅላቱ የሰው ፣ ሰውነቱ የአንበሳ የሆነው የግብፅ ሐውልት (ስፊንከስ) አንድ ጊዜ ብቻ ተናግሯል ። እንዲህም አለ ፦
" ደቃቅ አሸዋ በረሀ ነው ፣ በረሀም ደቃቅ አሸዋ ነው ። አሁን ሁላችንም እንደገና ዝም እንበል ። "
📜 እግዚአብሔር እኔን እንደጠጠር ወደዚህ አስገራሚ ሀይቅ ሲወረውረኝ የረጋውን የላይኛውን ክፍሉን በበርካታ የክብ
ሞገዶች አደፈረስኩት ። ነገር ግን በጥልቁ ቦታ ስደርስ ያለምንም እንቅስቃሴ ተቀመጥኩ ።
፨ እኔ ደግሞ ለቤቴ እና ለጎዳናው " እኔ ያለፈም ሆነ የወደፊት ህይወት የለኝም ። እዚህ ከቆየሁኝ በመቆየቴ ውስጥ መሄዴ
አለ ፣ ከሄድኩኝም በመሄዴ ውስጥ እዚህ መቆየቴ አለ ። ሁሉንም ነገሮች መለወጥ የሚችሉት ፍቅር እና ሞት ብቻ ናቸው
" አልኳቸው
📖📖📖
✍ ንባብ ለሕይወት
@books4all32
📜 የካህሊል ጂብራንን ንግግርና ፍልስፍናዎች በርከት አርጋችሁ ብታስነብቡን ብላችሁን ነበር በጥያቄአችሁ መሰረት እነሆ
ተጋበዙልን
📜📜📖📜📜
📖 " እምነት ማለት ልብ ውስጥ የሚገኝ ውሀ ያለበት የበረሀ ቦታ ሆኖ በፍጹም ጉዞ ሊደረስበት የማይቻል ነው ። "
💫💫💫
💫💫💫
📖 " በልባችን ያሉትን ሚስጥራት ማየት የሚችሉት ፣ በልባቸው ሚስጥሮችን የያዙ ብቻ ናቸው ። "
💫💫💫
📖 " ደግነት መስጠት ከምትችለው በላይ መስጠት ሲሆን ፣ ኩራት ደግሞ ከምትፈልገው ያነሰ መውሰድ ነው ። "
💫💫💫
💫💫💫
💫💫💫
📖 " በጥልቀት የማሰብ ችሎታ የሌለው ሳይንቲስት ፣ የደነዘ ቢላዋ እና የተበላሸ ሚዛን እንዳለው ስጋ ነጋዴ ነው ። "
💫💫💫
💫💫💫
📖 " ህልምና ምኞት በሌላቸው ሰዎች መሃል ታላቅ ከመሆን ይልቅ ፣ ህልም እና ምኞት ባላቸው ሰዎች መሃል ደካማ
መሆንን እመርጣለሁ ። "
💫💫💫
📖 " ሁላችንም እስረኞች ብንሆንም ልዩነታችን አንዳንዶቻችን የታሰርንባቸው ክፍሎች ፣ መስኮቶች ሲኖራቸው
የአንዳንዶቻችን ግን የላቸውም ። "
💫💫💫
📖 " የሌላ ሰውን ድክመቶች ከማወቅ የበለጠ ምንም አይነት ድክመት የለም ። "
💫💫💫
💫💫💫
📖 " ዓይኖቹ ውስጥ ያለውን ጥላቻ በከንፈሮቹ ፈገግታ ለመሸፈን የሚሞክር ሰው የማይረባ ነው ። "
💫💫💫
📖 " <<አልተገነዘብኩህም>> ማለትህ ለኔ ከሚገባኝ በላይ ሙገሳ ሲሆን ለአንተ ደግሞ የማይገባህ ስድብ ነው ። "
💫💫💫
📖 " ህይወት ልክ እንደ ሰልፍ ናት ። ቀስ እያለ ለሚራመደው ሰልፉ ስለሚፈጥንበት ከሰልፉ ይወጣል ፤ ለፈጣኑ ደግሞ
በጣም ስለሚዘገይበት እሱም ከሰልፉ ይወጣል ። "🗒🗒🗒
✍ ካህሊል ጂብራን
@filsfina
@books4all32