Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 87

የፈሳሽ ሳሙና አሠራር ሥልጠና

ደብረ ብርሀን
30/02/2013-04/03/2013
ክፍል 1

መሰረታዊ ሳይንስ ፤መንጽህን (Detergent)


በተመለከተ
አሲድና ቤዝ (Acid and Base)
ዓላማ

• የአሲድና የቤዝ ልዩነት ለመረዳት

• ሥለ አሲድና ቤዝ ማወቅ (ማጥናት) ባለው ጠቀሜታ ላይ


ለመወያየት

• አሲድና ቤዝን በተመከተ ሙከራወችን መሥራት


የአሲድና ቤዝ ትርጓሜ
• አሲድ ልይ ቁስ (substance) ሲሆን ከውሃ ጋር ሲቀላቀል የሀይድሮጅንን
አዮን (H+) አዮን ይፈጠራል፡፡ ሀይድሮጅን አዮን ከውሃ ጋር በመጣመር

ሀድሮኒየም አዮንን ያስገኛል፡፡

HCl + H2O H3O+ + Cl-

• ቤዝ ወይም አልካሊ ልክ እንደ አሲድ ልይ ቁስ ሆኖ ከውሃ ጋር በሚቀላቀልበት


ጊዜ የሀድሮ ኦክሳይድ አዮን ይፈጥራል

NaOH + H2O Na+ + OH-


pH (Power of Hydrogen) ምንድን ነው?

• pH አንድ ውህድ፣ሙሙት ወይም ድብልቅ አሲድ ወይም አልካሊ (ቤዝ)


መሆኑን የምናውቅበት ስልት ነው፡፡

• የ pH ዋጋ ከ1 እስከ 14 ሲሆን ይህም የሚወሰነው ቁሱ በውስጡ ባለው


የሀይድሮጅን አዮን መጠን ነው

• ብዙ የሐይድሮጅን ክምችት መኖር የpH ዋጋን ዝቅ እንዲል ያደርገዋል


፡፡ይህም የአሲድ መጠን መጨመርን ያመለክታል፡፡

• የሐድሮጅን አዮን ክምችት ማነስ ማለት የ pH ዋጋን ከፍ ሲያደርግ የቁሱ


የአሲድን መጠን ማነስና የአልካሊ ይዘት መጨመርን ያስገነዝባል
• የአንድን ቁስ pH ለማወቅ የሚከተለውን ቀመር እንጠቀማለን
pH = -log10[H+] ወይም pH = -log[H+]
ምሳሌ 1
Calculate pH
given [H+] = 1.4 x 10-5 M
Answer:
pH = -log10[H+]
pH = -log10(1.4 x 10-5)
pH = 4.85
አሲድና ቤዝን መለየት
የአንድን ውህድ፣ሙሙት ወይም ቅልቅል ማንነት ባላቸው የ
pH ዋጋ ማወቅ ይቻላል

የpH ዋጋ (መጠን) የቁስ ባህርይ


0-7 አሲድ
7 ግሉል (Neutral)
7-14 አልካሊ (ቤዝ)
አሲድ
➢ የpH ዋጋው ከ 0-7 ነው
➢ ከብረት አስተኔ (Metals) ወይም ከቤዝ ጋር ይጸገበራል
➢ ኮምጣጣ ጣዕም አለው
➢ በሰውነት ወይም በልብስና በመሳሰሉ ቁሶች ላይ ቢፈስ ከባድ ጉዳት ያስከትላል
➢ በሙሙት ውስጥ የሀይድሮጅን አዮን ( H+ ) ይፈጥራል

➢ ሰማያዊ ሊትመስ ወረቀትን ወደ ቀይ ቀለምነት ይቀይራል

ምሳሌ
HCl H+ (aq) + Cl(aq)

✓ aq (aqeous) ማለት አሟሚው ውሃ መሆኑን ይገልጻል፡፡


መጸግበር = Reaction
ቤዝ
➢ የpH ዋጋው ከ 7 በላይ እስከ 14 ድረስ ነው
➢ ከብረት አስተኔ (Metals) ጋር አይጸገበርም ነገር ግን ከአሲዶች ጋር በመጸግበር
ጨውና ውሃ ን መፍጠር ይችላል
➢ የመራራነት ጣዕም አለው
➢ በሰውነት ወይም በልብስና በመሳሰሉ ቁሶች ላይ ቢፈስ ከባድ ጉዳት ያስከትላል
➢ በሙሙት ውስጥ የሀይድሮኦክሳይድ አዮን ( OH– ) ይሰጣል (ይፈጥራል)
➢ ቀይ ሊትመስ ወረቀትን ወደ ሰማያዊ ቀለምነት ይቀይራል
➢ ከፍተኛ የሆነ የማንዳለጥ (የማንሸራተት፣ተሙለጭላጭነት) ባህርይ አለው

ምሳሌ
NaOH Na+ (aq) + OH– (aq)
ለማስታወስ ያህል
ጥያቄ 1) የልይ ቁሱ የpH ዋጋ 7 ቢሆን ምንን
ያመለክታል?
መልስ፡
ቁሱ ግሉል እንደሆነ እንረዳለን ምሳሌ ውሃ
ግሉል (Neutral)
• pH=7
• የአሲድነትም ሆነ የአልካሊ ባህርይ የለውም
• ምሳሌ ንጹህ ውሃ
አግልሎት (Neutralization)
✓ አሲድን በቤዝ ወይም ቤዝን በአሲድ ማግለል ይቻላል

ምሳሌ፡
NaOH+HCl→NaCl+H2O
ጥያቄወች
1. የአሲድ pH ከስንት እስከ ስንት ነው?
2. የቤዝ ተለዋጭ ሥም ምን ይባላል? የpH ዋጋውስ
ከሥንት እስከ ሥንት ነው ?
መልስ
1. ከ0- 7
2. ቤዝ፣ ከ7-14
pH ን እንዴት መለካት ይቻላል

❑የአንድ ቁሥ የpH ዋጋ በያዘው የሐድሮጅን አዮን ( H+ )


መጠን እንደሚወሰን ቀደም ሲል አይተናል፡፡ ይህንን መጠን
ሊለኩ የሚችሉ የተለያዩ ምርቶችና መሳሪያወች አሉ፡፡

ምሳሌ፡ ሊትመስ ወረቀት፣pH ሜትር ወዘተ


የሊትመስ ወረቀት ሥዕላዊ መግለጫ
ሊትመስ ወረቀት
pH ሜትር
መለኪያወች pH ሜትር ሊትመስ ወረቀት

ትክክለኛነት የpH ዋጋን በትክክል ያሳያል የቀለም ማመሳሰል ሥለሆነ


(Accuracy ትክክለኛውን ዋጋ አያሳይም

የአጠቃቀም ወደ ሙሙቱ ለማስገባት ቀላል ነው ወደ ሙሙቱ ስናስገባ


ምቹነት ኬሚካሉ እጃችንን ሊነካ
ይችላል
ቆይታ ለረጀም ጊዜ ያገለግላል አንዴ ጥቅም ላይ የዋለ
ሊተመስ ወረቀት ዳግም
አያገለግልም

የመግዣ ዋጋ ውድ ርካሽ

ተሰባሪነት በቀላሉ ይሰበራል፣በልቡን በጥንቃቄ አይሰበርም


መያዝ ይጠይቃል ና ለራሱ ተብሎ
በተዘጋጀ ቁስ ውስጥ ተነክሮ መቀመጥ
አለበት
ሥለ አሲድና ቤዝ ማወቅ ለምን አስፈለገ?

1. የደብረ ብርሀን ውሃ pH ምን ያህል ይሆናል ብላችሁ


ትገምታላችሁ?

2. በመንጽህ (detergent ) የማምረት ሂደት የእየ ወቅቱ ምርት


(Each Batch) pH መለካት ለምን ያስፈልጋል?

3. የሳሙናን ለማምረት ጥቅም ላይ የሚውል ውሀ pH ግሉል


እንዲሆን የሚመረጠው ለምን ይመስላችኋል?
የተለመዱ ፈሳሾችን pH መለካት

1. የቧንቧ ውሃ
2. የሚሪንዳ
3. የፔፕሲ 2.53
4. የታሸገ ውሃ pH አሲድ፣ግሉል ወይም አልካሊ መሆኑን
ሊትመስ ወረቀት በመጠቀም ተናገሩ
ክፍል ሁለት

ሳሙና ና መንጽህ

Soap and Detergents


ይዘት
✓መንጽህ ምንድን ነው ?
✓የማጽዳት ኬሚስትሪ ?
✓የፈሳሽ ሳሙና ጥሬ ዕቃወች
✓የፈሳሽ ሳሙና የጥራት መለኪያ መስፈርቶች
መንጽህ
መንጽህ ምንድን ነው ?

መንጽህ ማለት ገጸ አግባሪ (surfactant) ወይም የገጸ


አግባሪወች ቅልቅል ሲሆን በውሃ ወይም በሌላ አሟሚ
በቀጠነ/በተበረዘ ሙሙት ቆሻሻን የማስወገድ ሀይል ያለው ቁስ
ነው

❖መንጽህ የሶዲየም ወይም የፖታሲየም ቤንዚን ሰልፎኒክ አሲድ


ጨው ናቸው

Linear alkylbenzene sulfonic acid (LABSA)


የማጽዳት ኬሚስትሪ

• በማጽዳት ሂደት ውሥጥ የጽዳት ይዘቶች፣ ኬሚካዊ ቀመርና


ድርጊታቸወን የምንገልጽበት የተለያዩ ቴክኒካል ቃላቶች አሉ

• አብዛኛወቹ መንጽሆች በውስጣቸው በርካታ


ምንዝሮችን/ጥንቅሮችን (Components) የያዙ ናቸው
መንፅህ ለማምረት ና የማምረቻ ቀመር ለማውጣት
የምንጠቀምባቸው የተለያዩ ቁሶች ስብስብ
1. ገፀ አግባሪ (SURFACTANTS)-የሚታጠበውን ቁስ ገፅ
የሚያረጥቡ፡፡“Surface Active Agent”. የሳሙናው ዋና ክፍል

2. አሲድ፣ አልካሊና ነጣጣዮች (ACIDS & ALKALIS


SEQUESTRANTS)- በጥኑ ውሃ ውስጥ ያሉ አዮኖችን
ማስወገድና የገፀ አግባሪወን ሥራ ማገዝ

3. አሟሚወች (SOLVENTS)- ዘይትና ግሪሶችን በማሟሟት ገፀ


አግባሪው ሥራውን በትክክል እዲሰራ ማድረግ
የገጸ አግባሪወች ተግባራት
✓ማርጠብ (Wetting)

✓ማጓሸት / ማደባለቅ (Emulsification)

✓እንደ ሁኔታው አረፋ እንዲፈጥር ወይም እንዳይፈጥር ማድረግ


(Foaming / Defoaming )

✓ማሟሟት (Solubilization)

✓መበታተን (Dispersion)
ጤዛው ለምን ወደ ሳሩ ውስጥ ዘልቆ አልገባም ?
የገጸ አግባሪወች መዋቅራዊ ሥሪት
• ገጸ አግባሪወች ሁለት ዋና ዋና መዋቅራዊ ክፍሎች አሏቸው
1. ቅባታማ (ዘይት) ወዳድ ጭራ (oil-loving “tail”)- ወደ
ዘይታማው ገጽ / ወደ አየር ይሳባል
2. ውሃ ወዳድ ራስ water-loving “head”-ወደ ውሃው ገጽ
ይወሰዳል
✓ በተነፃፃሪ የእንቁራሪት እጭ (እንቁሪት) ቅርጽ አላቸው

እንቁሪት
Sodium 4-decylbenzene sulfonate
Sodium pentadecyl sulfonate
የገጸ አግባሪ አይነቶች
በመንጽህ ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ገጸ አግባሪወች
1. አሉታዊ ሙል ያላቸው Anionic (negatively
charged) 90% Detergents
2. አወንታዊ ሙል ያላቸው Cationic (positively
charged) 10% Polishes/Finishes
3. ሙል አልቫ የሆኑ Non-ionic
➢ የተለያየ ሙል ያላቸው ገጸ አግባሪወች ከመኖራቸው የተነሳ
የሳሙና ማመረቻ ቀመር ለማዘጋጀት ገደብ የመፍጠር አቅም
አላቸው
• አሉታዊ ና አወንታዊ ሙል ያላቸውን ገጸ አግባሪወችን ቀላቅለን
ሳሙና ብናመርት ምርቱ በማጽዳት ሂደት ውስጥ ውጤት አልባ
ይሆናል

• ምክንያቱም አሉታዊና አወንታዊ ሙሉ እርስ በርሳቸው በመሳሳብ


ሙል አልባ በመሆን የምናጸዳውን ቁስ ገጽ የሚያነሳሳ ሙል
ስለማይኖር ነው

• በመሆኑም ሳሙና በማምረት ሂደት ዋጋውና የሳሙናው የማጽዳት


ብቃት ተመጣጥነው መቀመር አለባቸው

• ትልቅ ዋጋ ነገር ግን ደካማ የማጽዳት አቅም ያላቸው በርካታ


ምርቶች ገበያ ላይ ይታያሉ
የገጸ አግባሪወች የፅዳት ድርጊት/ተፅዕኖ

በማርጠብ ወቅት
• የውሃ ገፀ ውጥረት ነፍሳቶች በውሃ ላይ እንዲራመዱና በቅባታማ ገጾች
ላይ የውሃ ጠብታወች እንዲፈጠሩ የሚያደርግ ሽፋን ነው፡፡

• የገጸ አግባሪው ዘይት (ቅባት) ወዳድ ጭራ ከውሃው ገጽ ሲሸሽ


የውሃውን ገጻዊ ውጥረት (Surface tension) ይሰብረዋል፡፡

• ገጸ አግባሪወች የውሃን ገጻዊ ውጥረት በመቀነስ የውሃ ጠብታወች


እንዲበተኑና የቅባታማውን ቁስ ገጽ እንዲረጥብ /እንዲርስ
ያደርጉታል፡፡በዚህ ድርጊታቸውም “ የአርጣቢወች ወኪል “ የሚል
ቅጽል አሰጥቷቸዋል፡፡
ማ ጓሸት/ማደባለቅ- Emulsification
• የቅባታማ እንክብሎች በውሃው ላይ በሚበተኑበት ወቅት በላይኛው ገጽ ላይ
ተከታታይነት ያለው ቅባታማ ስሶ /Oil film/ ይፈጥራሉ

• የገጸ አግባሪወች ቅባት ወዳድ /ውሃ ጠል/ ጭራ ከቅባታማው እንክብል ገጽ ላይ


ሲለከክ ውሃ ወዳዱ ራስ ደግሞ ከውሃው ጋር ይያያዛል፡፡

• ይህም የቅባታማው ገጽ (ቆሻሻው) ውሃ የሚስብ ስስ ሽፋን እንዲፈጥር በማድረግ


እንክብሎቹ በውሃው ላይ ተሰራጭተው እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል፡፡

• የቅባታማ እንክብሎች በውሃው ውስጥ በተረጋጋ ሁኔታ መሰራጨታቸው ሂደቱን


ማጓሸት/ማደባለቅ ሲያሰኘው ድብልቁ ደግሞ የውሃ ቅባታማ ጉሸት ይሆናል፡፡
“oil in water” emulsion.
የማ ጓሸት/ማደባለቅ- Emulsification ሥዕላዊ መግለጫ
ሥሞና (Saponification)
• የእንስሳት/የዕፅዋት ስብ ወይም ዘይቶች ከጠንካራ ኮስቲክ ሶዳ
/NaOH/ ጋር በሚደባለቁበት ወቅት አልካሊው የቅባታማውን አሲድ
ክፍል ገንጥሎ ግሉል በማደረግ ሳሙና / የስብ አሲድ ጨው- Fatty
Acid Salt / እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ማሰሰቢያ
• የእንስሳት/የዕፅዋት ስብ ወይም ዘይቶች የአንድ ኬሚካዊ ቤተሰብ
ክፍሎች ሲሆኑ ልዩነታቸው ከ20-23 ዲ.ሴ ሙቀት ላይ ስብ
ጠጣር መሆኑና ዘይት ደግሞ ፈሳሽ መሆናቸው ብቻ ነው
ስሞና
LABSA
ሰው ሰራሽ መንጽኅ

A) CH3 (CH2)10-CH2-O3SOH + NaOH


Alkyl Sulfuric acid
CH3 (CH2)10-CH2-O3SONa +H2O
Sodium dodecayl sulfate

B) CH3 (CH2)11-C6H4-O2SOH + NaOH


LABSA
CH3 (CH2)11-C6H4-O2SONa +H2O
Sodium dodecayl benzene sulfate
የሳሙና ፒ ኤች- pH of soap
• የ pH ዋጋ በአንድ ቁጥር ማነስ ማለት የሀይድሮጅን አዮን በአስር እጥፍ
መጨመር ማለት ነው፡፡በሁለት ቁጥር ካነሰ ደግሞ በመቶ እጥፍ
ይጨምራል፡፡

• የ pH ዋጋ በአንድ ቁጥር መጨመር ደግሞ የሀይድሮጅን አዮን በአስር


እጥፍ ሲያንስ በተቃራኒው የሀይድሮ ኦክሳይድ ክምችት በአስር እጥፍ
መጨመርን ያመለክታል

ሲጠቃለል
የሚመረቱ ማጽጃወች / ሳሙና pH ግሎል ወይም ደካማ አልካሊ መሆን
አለበት
• በአብዛኛው ቆሻሻወች የአሲድ ባህርይ አላቸው፡፡ሳሙና ደግሞ የግሉል
ወይም የአልካሊ pH ስላለው በማፅዳት ሂደት ቆቀሻሻውን ግሉል
በማድረግ ወደ ሟሚ ጨውነት ይቀይራቸዋል

ሳሙና የአልካሊ ባህርይ በመያዙ

• በስብና ቅባታማ ቆሻሻወች ላይ ስሞና እንካሄድ ያደርጋል


• ፕሮቲኖች እንዲሰባበሩና እንዲሟሙ ያግዛል
• የቆሻሻውን የአሲድ ባህርይ ወደ ግሉልነት ይለውጣል
• የብረት አስተኔ ኦክሳይዶችን ከቁስ ገፅ ላይ ያስወግዳል
• የሚፀዳውን ቁስ ገጽ ያረጥባል፡፡ ጠጣር ቆሻሻወችም እንዲንሳፈፉና
እንዲበተኑ በማድረግ ያሥወግዳል
አሲድ በባህርይው
• በርካታ ብረት አስተኔወችን፣የመሰረታዊ የብረት አስተኔ
ኦክሳይዶችን (ምሳሌ ዝገት)፣የብረት አስተኔ ጨውን (ምሳሌ-
የካልሲየምና የማግኒዠየም ካርቦኔት-water scale)
፣ብረቶችን፣ኮንክሪት፣ሞርታር ወዘተ ያጠቃል/ያሟሟል
• የአሲዱ አይነትና መጠን፣የብረት ዝገትን የሚከላከሉ መካቾች
(Corrosion Inhibitors) ና ሌሎች ተደማሪ ቁሶች
(Additives) የአሲዱን የማጥቃት ኃይል ደረጃ ይወስናሉ
ገንቢወችና ነጣጣዮች-Builders/Sequestrants
• ገንቢወች (አጋዦች) ና ነጣጣይ ኬሚካሎች በሳሙና ማመረት ቅመራ ላይ
ተሰልተው የሚገቡ ቁሶች ናቸው
• በሚጸዳው ቁስ ላይ ቅርፊት መሳይ የብረት አስተኔ ኦክሳይዶች
እንዳይፈጠሩ ያግዛሉ
• ሌሎች አጽጂ ኬሚካሎች እርስ በርሳቸው እንዳይጸገበሩና ተግባራቸው
እንዳይሰተጓጎል ያደርጋሉ
• በውሃ ውስጥ የሚገኙ የብረት አስተኔ አዮኖች የውሀን የማጽዳት ሐይል
ይፈታተናሉ በመሆኑም ነጣጣዮች ከእነዚህ አዮኖች ጋር በመጸግበር የውሃ
ጥራትን አሻሽለው የማፅዳት ኃይሉን ያሳድጋሉ
• በውሃ ውስጥ የሚገኙ የብረት አስተኔ አዮኖች ከካልሲየም፣
ማግኒዥየም፣ብረት፣ማንጋኒዝና መዳብ የሚፈጠሩ ናቸው ናቸው
የገንቢወችና ነጣጣዮች-Builders/Sequestrants ተጨማሪ
አስተዋጾወች

• የማጽጃ ውሃው የአልካሊ ወሰኑን (pH) መጠኑን ጠብቆ እንዲቆይ


ያግዛሉ

• ልብስ ላይ የነበሩ ቆሻሻወች በሳሙና ከተወገዱ በኋላ


ተመልሰው እንዳይከማቹ ያደርጋሉ
• ነጣጣዮች በጽዳት ጊዜ በውሃ ውስጥ ያሉ የአዮን መጠን ይቀንሳሉ
• ለመንጽሁ/ለሳሙናው የማርጠብ እገዛ ያደርጋሉ
ምሳሌ፡- ሶዲየም ሲሊኬት-NaSiO3፣ሶዲየም ካርቦኔት-
Na2CO3፣ሶዲየም ትራይ ፖሊ ፎስፌት Na5P3O10
• ከጥጥ የተሰሩ አልባሳት ገጻቸው አሉታዊ ሙል አለው፡፡ውሃ ወዳድ
ናቸው፡፡
• ከሳሙናው ገጸ አግባሪ የሚመጣው አሉታዊ ሙል በላዩ ላይ በመለከክ
መጠኑን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡የሙሙቱ ፒ ኤች ሲጨምር አሉታዊ
ክምችት አብሮ ይጨምራል፡፡ቆሻሻም አሉታዊ ሙል ስላለው
በመገፋፋት ሂደት ከልብሱ ላይ ይወገዳል፡፡ይህ ጠቀሜታ ከገንቢወች
ይገኛል፡፡
• በእርግጥ ይህ መገፋፋት ብቻውን ቆሻሻሸን ከልብሱ ላይ
አያስወግደውም፡፡
• በዚህ አይነት እጥበት ተመራጭ ፒ ኤች ከ9-10.5 ነው፡፡
• የሰው ሰራሽ ፋይበር ሙል ግሉል ነው
• ይህ ጠቀሜታ ከገንቢወች ይገኛል፡፡
የአጋዦች ና ነጣጣዮች ጠቀሜታ ሲጠቃለል

1. ማለስለስ (softening)-ጥኑ ውሃን ወደ ጥኑ ያልሆነ ውሃ


መለወጥ፡፡ የብረት አስተኔ አዮኖችነ በሙሙቱ ውሰጥ ነጥሎ በመያዝ
(Sequestration) ና የብረት አስተኔ አዮኖችን ወደ ኢሟሚነት
በመለወጥ ማዝቀጥ (Precipitation)

2. የሙሙቱ pH ባለበት እንዲቆይ ማገዝ (buffering)


3. ማ ጓሸት (emulsifying).
የውሃ ጥኑነት-Water Hardness
• የውሀ ጥኑነት ባለባቸው አካባቢወች የሚዘጋጀው የሳሙና ማምረቻ ቀመር
በተነጻጻሪ(የውሃ ጥኑነት ከሌለባቸው) መጠኑ ከፍ ያለ ገንቢወች/ነጣጣዮች
ያሥፈልጉታል

• የመጠናቸው መብዛት ውሃ ውስጥ ያሉትን የካልሴየምና ማግኒዥየም ውህዶችን


መጠን ያስተካክላል (ተፅዕኗቸውን ያስቀራል)

• የአልካሊኒቲ መጠን ሲጨምር በጥኑ ውሃ ውስጥ ያሉ ውህዶች የመሟሟት


እድላቸው ይቀንሳል የተለዩ ነጣጣዮችን ክልተጠቀመን በስተቀር የ ፒ ኤች መጠን
7.6 ሲድረስ በመሟሟ ፋንታ መዝቀጥ ይጀምራሉ፡፡
አሟሚወች-Solvents
• ብዙ ጊዜ አሟሚ የሚለውን ቃል ስንሰማ ወደ አዕምሮአችን
የሚመጣው ላምባ (paraffin)፣የቀለም ማቅጠኛ (White spirit)፣
ክሎሪን ያለባቸው የተለያዩ ውህዶች (methylene chloride and
trichloroethylene) ናቸው፡፡

• ነገር ግን ማንኛውም ሌላ ቁስን ሟሟት የሚችል ፈሳሽ ሁሉ አሟሚ


ይባላል

• በጽዳት ወቅት የምንጠቀመው የተለመደና ዋናው አሟሚ ውሃ ነው


ሌሎች አሟሚወች
• ሀይድሮ ካርቦኖች
• የተፈጥሮ ዘይቶችና አልኮሎች
• ኬቶን, ኢስተርስ, ኢተርስ, ግላይኮልና ና ግላይኮል ኢተርስ
የመንጽህ ተደማሪወች-Detergent Fillers
• ተደማሪወች በምርት ሂደት ወቅት የመንጽህን ፊዚካዊ/አካላዊ ባህርያት
ለመቀየርና ሊመረት የታቀደውን ሳሙና የፈሳሽ ወይም የዱቄት መልክ
እንዲይዝ የሚጨመሩ ኬሚካሎች ናቸው፡፡

• የምርት መጠኑን ከፍ በማድረግ የሳሙናውን ዋጋ ለማስተካከል ያግዛሉ

• በሳሙናው ውስጥ ያሉ ሌሎች ድብልቆችን ተረጋግተው እንዲቀመጡ


ይረዳሉ

• አረፋ እንዳይፈጠር (በተለይም በማምረት ሂደት ላይ) ይገድባሉ


✓ በሳሙና ማምረት ሂደት ውስጥ የሳሙናውን ሽታ
በምንፈለገው መልኩ ለመቀየር ሽቶ መጨመር ና
ማንጫወችንም ማካተት ይቻላል

የተደማሪ ምሳሌወች
▪ sodium silicate Na2SiO3
▪ borax Na₂[B₄O₅(OH)₄]·8H₂O and
▪ sodium carbonate Na2CO3
የቆሻሻ አይነቶች- Soil Types

• የሚጸዳውን ቆሻሻ ባህርይ ማወቅ የምናመረትውን ሳሙና ቀመር


ለማዘጋጀተና ለማጠቢያ የምንጠቀምበትን መንጽኅ ለመወሰን ከፍተኛ
እገዛ አለው

• በርካታ ቆሻሻወች የተለያዩ ቁሶች ጥርቅም ናቸው፡፡ሥለሆነም


ሳሙና ከማምረታችን በፊት የማምረቻ ቀመሩን በተስማሚ ሁኔታ
ለመቀመር የቆሻሻውን የክምችት መጠን፣የሚጸዳው ቁስ የገጽ ባህርይ
ና የማጽጃ ዘዴ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት የግድ ነው
ሳሙና ቆሻሻን የሚያጸዳበት ዘዴ
MICELLES
Soap Molecule
የፈሳሽ ሳሙና የጥራት መለኪያ ነጥቦች

የሳሙና ጥራት ሲመዘን መታየት ያለባቸው መሥፈሪያወች


1. ቀለም
2. ሽታ
3. ፒ ኤች
4. ውፍረት
5. የማጽዳት አቅም / Active matter performance /
ሳሙና ማምረትና የጥራት ቁጥጥር

በምርት ሂደት ወቅት 3 ዋና ዋና ተግባራት ይከናወናሉ


1. ጥሬ ዕቃ ማሰባሰብ
2. በጥራት ማምረት
3. ገበያ ማፈላለግ ናቸው
በሳሙና ማመረት ሂደት የሚያስፈልጉ ዝርዘር ሂደቶች

• ግባቶችን ለሥራ ዝግጁ ማድረግ


• ማቀላቀል/ ቁሶች እንዲጸገበሩ ማመቻቸት
• ፒ ኤችና ውፍረትን መለካትና መከታተል
• እንደ ሽቶና ማቀለሚያ ያሉ የሳሙናው አሳማሪወችን መመጠን
• ማሸግ (ጀሪካን፣መጠቅለያ ፕላስቲኮች;
• ምርት ማከማቸት
• ምርት ማሰራጨት
ግባቶችን ወደ ሥራ ስናስገባ የመንከተላቸው ቅደም ተከተሎቸ
1. በቀመሩ መሰረት በተለካ ውሃ ውስጥ የተለካ ጨው ጨምሮ ማ ሟሟት
2. አሲድን ውሃ ላይ መጨመር አጽግብሮቱን ለማቀዝቀዝ/ለማረጋጋትና
አደጋን ለማሰወገድ ወሳኝነት አለው፡፡ ውሀን አሲድ ላይ መጨመር
ክልክል ነው፡፡አሲድን ውሃ ላይ መጨመር ግን ይቻላል፡፡
✓ LABSA ን ውሃ ላይ ማስገባት/ መቀላቀል
3. SLES ማዋሀድ
4. ፒ ኤች ከተለካ በኋላ ሲሊኬት መጨመር
5. ፒ ኤች በተፈለገው መጠን (ግሉል ወይም አልካሊ) ካልመጣ ቀደም ብሎ
የተዘጋጀውን የሶዲየም ሀይድሮኦክሳይድ ውህድ በትንሹ እየጨመሩ ፒ
ኤቹ ን በመለካት ማስተካከል
Check pH at critical stages (before adding caustic soda)
• የፈሳሽ ሳሙና ማምረት ሂደት ላይ ጥሬ ዕቃወችን በምናቀላቅልበት
ወቅት መጣደፍ የማመረት ሂደቱን ስለሚያበላሽ መረጋጋት ግዴታ
ነው

• ኬሚካሎችን የምናደባልቀው ረጋ ብለን በንጹህ እንጨት በማማሰል


ነው

• ለማዋሀድ/ለማማሰል ተብለው የተዘጋጁ በሞተር የሚሰሩ መሳሪያወች


ያሉ ቢሆንም በዚህ ኢነትርፕራይዝ ደረጃ አንጠቀምባቸውም
ልኬታ-Measurement
በሳሙና ማምረት ሂደት ሁለት አይነት ልኬታወች መጠቀም እንችላለን
1. አይነታዊ(QUALITATIVE)፡-የውህዱን ቀለምና አካላዊ ሁነታ
በማየት ብቻ መመዘን/መለካት

2. መጠናዊ(QUANTITATIVE)፡-ሳይንሳዊ መለኪያወችን በመጠቀም


በአሀዝ መለካት
ምሳሌ
✓ 200ሜ -ርዝመት
✓ 15 ሚሊ-ይዘት
✓ 13.98 ግ- ክብደት/መጠነ ቁስ
➢ ሳሙና በምናመርትበት ወቅት ጥሬ ዕቃወችን የምንለካው በክብደት
ሲሆን ለዚህ መለኪያ የሚያገለግለል ሚዛን እንጠቀማለን
የሳሙና ማምረቻ ቀመር ማዘጋጀት
• የፈሳሽ ሳሙና ማመረት ከመጀመር በፊት ጥሬ እቃወች የሚደባለቁበት
መጠን ቀመር ማዘጋጀት ና በቀመሩ መሰረት ክብደታቸውን ያለ ምንም
ስሀተት በመለካት ማቀላቀል የምርቱና ጥራት በጣም ከፍ ያደርገዋል

• የማምረቻ ቀመር ለማዘጋጀት ግንዛቤ ውስጥ የሚገቡ ወሳኝ መሥፈርቶች


1. ሊመረት የታቀደው ሳሙና የማጽዳት ብቃት/ጥራት
2. የሳሙናው ተስማሚነት
3. ዋጋ
4. ቴክኒካዊ ምቹነት
5. የደንበኞች ፍላጎት
የሳሙና ጥሬ ዕቃወች የቅልቀል መጠን ምሳሌ
❑የማምረቻ ዋጋ በወሳኝነት በሽያጭ ወቅት በሚገኘው ትርፍና
በደንበኞች የመግዛት አቅም ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል

❑ሥለሆነም የማምረቻ ቀመሩ የሳሙናውን ጥራት አስጠብቆ


የገበያ ተወዳዳሪነትንና ትርፋማነትን ሊያረጋግጥ የሚችል
እንዲሆን ተደርጎ መቀመር አለበት
Formulation – 1: Medium cost
Description Unit Value Percentage

LABSA Kg 1.1 4%
SLES Kg 0.15 0.5%
Silicate Kg 1.2 4.4%
NaOH Kg 0.05 0.2%
Salt Kg 0.12 0.4%
CMC Kg 0.7 2.6%
Water Kg 24 87.8%
Total 27.32 100%
የፈሳሽ ሳሙና አሰራር ቅደም ተከተል-ቀመር 1
በመጀመሪያ የተለያዩ የፕላስቲክ ባልዲወችን ማዘጋጀት
1. በመጀመሪያው ባልዲ ውሃ መጨመር ና ጨውን ማሟሟት
2. በቀመሩ ላይ የተመለከተውን LABSA ለክቶ በዝግታ እያማሰሉ የጨው
ሙሙቱ ጋር መቀላቀል
3. SLES ለክቶ እያማሰሉ መጨመር
4. ፒ ኤች መለካት
5. ሲሊኬት መጨመር
6. ፒ ኤች ደግሞ መለካት የግሉል ወይማ የአልካሊ ፒ ኤች ካሳየ ሶዲየም
ሀይድሮ ኦክሳይድ አለመጨመር ይቻላል
7. የ ፒ ኤች መጠን አሁንም አሲድ መሆኑን የሚያሳይ ከሆነ ሶዲየም
ሀይድሮ ኦክሳይድ በትንሹ እየጨመሩ ፒ ኤች እየለኩ የሚፈለገው ፒ
ኤች እስኪመጣ ማቀላቀል
• CMC በውሃ ቶሎ ስለማይሟሟ አንድ ቀን ቀደም ብለን በቀመሩ
ከተመለከተው የውሃ መጠን ቀንስን ማዋሀድ ያስፈልጋል፡፡ በደንብ
ከተዋሃደ ወጥ የሆነ ሊጥ መሳይ ስሪት ይታያል

• በሚቀጥለው ቀን ከላይ የተሰራው ውህድ ጋር ቀስ ብሎ እያማሰሉ መጨር


ነው

• ቅደም ተከተሉ ከተጠበቀ፣ የተዋጣለት ማዋሀድ ና ትክክለኛ ልኬታ ጥቅም


ላይ ከዋለ የሳሙናው ጥራት አስተማማኝ ነው

• የምንቀላቅልበት ውሀ ፒ ኤች ግሉል ና ጥኑነት የሌለው ከሆነ በሳሙናው


ጥራት ምንም ተፅዕኖ አይኖረውም
• CMC በቀላሉ ሥለ ማይሟሟ በቀመሩ ውስጥ እንዲጨመር ከተፈለገው ውሃ
40% በተቀነሰው ውሃ CMC ማዋሀድ
• ቀሪወቹ ኬሚካሎች ተቀንሶ በቀረው ውሀ ውስጥ በመጨመር
ማዋሀድ፡፡ለማዋሃድ ቀስ እያሉ ማማሰል ግዴታ ነው፡፡ (በነጋታው ይጨመሩ)

• የ CMC መጠኑ ከሚቀላቀልበት ውሀ ጋር ተደምሮ 7% ይደረግ


• NaOH የሚዘጋጀው ሶዲየም ፍሌክስ (በጠጣር መልክ የሚገኝ) ከው ጋር
በመቀላቀል ነው
• ለመቀላቀል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያሻዋል ለ228ኪ.ግ ፈሳሽ ሳሙና 1ኪ.ግ NaOH
ሶሊዩሽን በቂ ነው
• የቅለቅል ይዘቱም 40 በመቶ (0.4ኪ.ግ) ሶዲየም ፍሌክስን 60 በመቶ (0.6 ኪ.ግ)
ውሀ ላይ ቅስ እያሉ በመጨመር ነው
ከፍተኛ ዋጋ ቀመር – 2
Description Unit Value Percentage
LABSA Kg 25 11
SLES Kg 5 2.2
Silicate Kg 15 6.6
NaOH Kg 1 0.4
Salt KG 2 0.9
Water Kg 180 78.9
Total 228 100
የአጨማመር ቅደም ተከተል
1. ሁሉም ጥሬ ዕቃወች የሚቀላቀሉበት በቂ ይዘት (ሥፋት) ያለው ዕቃ
ማዘጋጀት
2. በቀመሩ መሰረት የታየውን የውሃ መጠን ማዘጋጀት
3. በቀመሩ የተመለከተውን የጨው መጠን ውሃ ውስጥ ጨምሮ
ማሟሟት
4. በቀመሩ ላይ የተቀመጠውን LABSA ና SLES ለክቶ በቅደም ተከተል
በዝግታ እያማሰሉ ወደ ውሃው መጨመር
5. ፒ ኤች መለካት
6. ሲሊኬት መጨመር
7. ፒ ኤቹ የተፈለገው ላይ ካልመጣ ሶዲየም ሀይድሮኦክሳይድ ቀስ እያሉ
ፒ ኤች እየለኩ መጨመረና ተፈላጊው ፒ ኤች ላይ ሲደረስ ሥራው
ማጠናቀቅ
የመንጽህ ኢንደስተሪ ምርት፣ ገበያና የወጋ ትመና ስሌት

የምርት ዑደት (Product Life Cycle)


• የምርት ዑደት በመግዛትና መሸጥ ሂደት (Marketing) ላይ አስፈላጊ
የሆነ ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ምርቱን ለማምረት በሀሳብ ከተወጠነበት
ጀምሮ ከገበያ እስኪወገድ ድረስ ያለውን ሂደት ይመለከታል/ይገልጻል
• ሁሉም ምርቶች ይህን ሂደት አያልፉም፡፡አንዳንድ ምርቶ በተከታታይ
እድገት ሲያሳዩ ሌሎች ደግሞ እድገት ከታየባቸው በኋላ ተመልሰው
ከገበያ ይጠፋሉ
የምርት ዕድገት ወሳኝ ደረጃ የሚባሉት

1. መግቢያ (Introduction)፡-ምርቱን ወደ ገበያ ማውጣት

2. ዕድገት (Growth)፡-የምርት ሽያጭ ጭማሬ ፈጣን ምጣኔ ላይ መገኘት

3. ጉምረት (Maturity)፡-ሽያጩ የመጨረሻ ከፍተኛ ደረጃውን ሲቃረብ


ነገር ግን በገበያው መጥገብ ወይም ሌሎች ተወዳዳሪወች
በመምጣታቸው የዕድገት መቀነስ ደረጃ

4. ማሽቆልቆል (Decline)፡-የሽያጭ መቀነስ ና የዑደቱ የመጨረሻ ደረጃ


የምርት የህይወት ዑደት
በቢዝነስ የህይወት ዑደት ውስጥ መለያን እንደገና ማጠናከር
የምርት የህይወት ዑደትን መስቀጠል/ማራዘም

• ውጤታማ የሆነ ምርት የቢዝነስ ዑደቱን ለማስቀጠል


የዕድገትና የመጎምረት ደረጃወች ዘመናት ማራዘም
ይጠበቅበታል

• አንድን ቢዝነስ በውጤታማነት ለማስቀጠል ምን ማድረግ


ይገባል?
የቢዝነስ ማስቀጠያ ዘዴወች

1. ማስታወቂያ መሥራት፡- አዳዲስ ደንበኞችን ለመሳብና ነባሮችን


ለማስታወስ/ለመጎትጎት

2. ዋጋ መቀነስ፡-ደንበኞችን የበለጠ ይስባል

3. እሴት መጨመር፡- የምርቱን ገጽታ በማሻሻል

4. አዲስ ገበያ ማፈላለግ፡-አዳዲስ የገበያ መዳረሻወችን መፈለግ ና መጠቀም


ወይም አዲስ ሥሪት በመፍጠር ለተመረጡ ተጠቃሚወች መሸጥ

5. አዲስ አስተሻሸግ፡- ሳቢና ማራኪ የሆነ የማሸግ ሥራ መጀመር


የዋጋ ስሌት (Cost Analysis)

አንድ ካምፓኒ የዋጋ ስሌት የሚሰራባቸው ምክንያቶች


1. ገንዘቡ ምን ላይ መዋል እንደለበት ለመወሰን/ የት እንደሄደ ለማወቅ
2. አላስፈላጊ ወጭወችን ለመቀነስ
3. ትርፍን ለማወቅና ለማሳደግ እንዲያስችል
4. ተወዳዳሪ ለመሆን ናቸው
የዋጋ ስሌት መስራት ያልቻለ ድርጅት መደረሻውን አያውቅም

You might also like